Sunday, October 25, 2015

ቅዱስ ሲኖዶስ በ“ተሐድሶ ኑፋቄ” እና በሙስና ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል




በቤተ ክርስቲያኒቷ ስም በብዙኃን መገናኛ ስለሚተላለፉ ትምህርቶች ይወስናል

 (
አዲስ አድማስ ጥቅምት 13 2008 ዓ.ም)፡-  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ የቤተ ክርስቲያኒቷን ቀጣይ ህልውና እየተፈታተኑና የምእመናኗን ፍልሰት እያባባሱ ናቸው በተባሉ፤ ተሐድሶ ኑፋቄእና የመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ በጥልቀት በመምከር ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ተገለጸ፡፡የቅዱስ ሲኖዶሱ የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ፣ ከትላንት በስቲያ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በመክፈቻ ጸሎት ሥነ ሥርዐት የተጀመረ ሲሆን በምልአተ ጉባኤ የተሠየመው አጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴ በቀረፃቸውና በምልአተ ጉባኤው በጸደቁ የመነጋገርያ ነጥቦች ለቀናት እንደሚመክር ታውቋል፡፡


የቅዱስ ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ ያካተተውና ሰባት ሊቃነ ጳጳሳትን የያዘው አርቃቂ ኮሚቴ፣ ለምልአተ ጉባኤው ካቀረባቸው 15 ያላነሱ አጀንዳዎች መካከል፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር ሰርገው በመግባት  አስተምህሮዋን፣ ሥርዐቷንና ትውፊቷን ውስጥ ለውስጥ በመበረዝ ጉዳት አስከትለዋል የተባሉ  “የተሐድሶ ኑፋቄአራማጆች ጉዳይ አንዱ ሲሆን የእንቅስቃሴውን ችግር የተመለከቱ ጥናቶችና መረጃዎች በጥልቀት ይፈተሹበታል፤ ተብሏል፡ከቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ ቀደም ብሎ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ደረጃ 34 ጊዜ የተካሔደው የሰበካ አስተዳደር አጠቃላይ ጉባኤ ባወጣው መግለጫ፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተወገዘውንየተሐድሶ ኑፋቄ ተጽዕኖ ለመቋቋምና የምእመናንን ፍልሰት ለመግታት በቂና መጠነ ሰፊ በሆነ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ምእመናንን በእምነታቸው ለማጽናት የጋራ አቋም ይዟል፤ ለተፈጻሚነቱም በልዩ ልዩ ብሔረሰቦችና ቋንቋዎች የሚያስተምሩ መምህራንን በጥራትና በቁጥር ማሳደግ እንዲሁም አገልግሎቱን ዘመኑ በሚፈቅዳቸው ሚዲያዎች በመታገዝ ለመላው ዓለም ማዳረስ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል፡፡
ሚዲያዎቹ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ የራስዋን ድምፅ የምታሰማባቸውና ማዕከላዊነታቸውን የጠበቁ መሆን እንደሚገባቸው በመግለጫው የተጠቀሰ ሲሆን ቅዱስ ሲኖዶሱም በቤተ ክርስቲያኒቷ ስም በልዩ ልዩ ሚዲያዎች በመተላለፍ ላይ ስለሚገኙ ትምህርቶች ከምእመናን ሲቀርቡ የቆዩ አቤቱታዎችን በአጀንዳው በማካተት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ተጠቁሟል፡፡የተሐድሶ ኑፋቄአራማጆች፣ አስተምህሮዋን ከመፃረር ባሻገር በአንዳንድ የሀገር ውስጥና የውጭ አካባቢዎች፣ ማዕከላዊውን አስተዳደሯን የሚፈታተንገለልተኛ አስተዳደርበመፍጠር ምእመናኗን እያደናገሩ እንደሚገኙ ተመልክቷል፡፡ የመልካም አስተዳደር ዕጦትና ሙስና ለችግሩ አስተዋፅኦ እንዳለው በጋራ አቋሙ የገለጸው አጠቃላይ ጉባኤው፣ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የወደፊት ህልውና ከፍተኛ ስጋት በመሆኑ ቅዱስ ሲኖዶሱ መዋቅሯን የሚያጠናከርና የሕግን የበላይነት የሚያረጋግጥ አስቸኳይ መፍትሔ ሊፈለግለት ይገባል ተብሏል፡፡ለሙስናና ብክነት የተጋለጡ አሠራሮችን በወሳኝ መልኩ በመቅረፍ አደረጃጀቷና አሠራሯ ዘመኑን በሚዋጅ የግልጽነት፣ የተጠያቂነትና የአሳታፊነት መርሕ ላይ ለመመሥረት ያስችላሉ የተባሉ ዐበይት ውሳኔዎች በቅዱስ ሲኖዶሱ ሲተላለፉ ቢቆዩም ተግባራዊነታቸው የሚጠበቀውን ያህል እንዳልሆነ ተነግሯል፡፡ ያልተተገበሩ ውሳኔዎቹን በዝርዝር ይገመግማል የተባለው ምልአተ ጉባኤው፣ ተፈጻሚነታቸውን በመከታተል መዋቅራዊ ለውጡን የሚያረጋግጥ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሊያቋቋም እንደሚችልና በቀጣይነትም ከኹሉም አካላት የተውጣጣ የቤተ ክርስቲያኗን ችግር የሚያጠና ኮሚቴ እንደሚሠይም ተጠቁሟል፡፡ በተጨማሪም፤ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጾች የተመለከቱ ደንቦችን በተጣጣመ መልኩ የሚያወጣ አካል እንደሚሠየም የተጠቀሰ ሲሆን የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት የሆነው የአዲስ አበባ ልዩ መተዳደርያ ደንብና ከባድ ቀውስ ፈጥረዋል የተባሉት የአስተዳደር ችግሮቹ በአጀንዳነት አብሮ እንደሚታይ ተገልጧል፡፡

5 comments:

  1. እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ይህንን ፍንጭ እራሱ መመልከት ትልቅ ነገር ነው፡፡ አፈጻጸሙንም ደግሞ እግዚአብሔር እንዲሰራ እባካችሁ ጸሎታችንና ጾማችንን በዚሁ መልክ እንቀጥል፡፡ የዘንድሮ የጽጌ ፆም ስለቤተክርስቲያን አንድነት መሆን አለበት፡፡ ከጅምሩ እግዚአብሔር ይህንን አሰምቶናልና የተዋህዶ ልጆች ስለቤተክርስቲያን አንድነትና ችግር እንጸልይ፣ እንጹም ፣እንቀበል፣የአምልኮት ስግደት እናቅርብ ፡፡ እግዚአብሔር ሁሉን ለመስራት ቅርብ ነው፡፡ በርቱ፣

    ReplyDelete
    Replies
    1. አሜን እውነት ብለሀል ሁላችንም ከልብ አልቅሰን ከጸለይን እግዚአብሔር ሁሉን ይመልሰዋል እንደድሮው

      Delete
  2. It is good.It must be continuous.

    ReplyDelete
  3. ማወገዙ መፍትሄ የለውም ማስተማሩ እንጅ ፍልስቱን ያባብሰዋል

    ReplyDelete
  4. ሰበር ዜና – ፈቃድ የሌላቸው የኢ.ቢ.ኤስ ፕሮግራሞች በቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀሙ ተወሰነ፤ የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት ይጀመራል
    • የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ፈቃድ እና ዕውቅና የሌላቸው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞቹ፣ “ታዖሎጎስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” በምልአተ ጉባኤው ውሳኔ በስም ተለይተው ተጠቅሰዋል
    • በምልአተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት፣ በቋሚ ሲኖዶስ የተቋቋመው የብዙኃን መገናኛ ቦርድ ሥራውን ለመጀመር እየተንቀሳቀሰ ነው
    • በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ላይ የቀረቡ ማስረጃዎች የበለጠ ተጠናክረው አጀንዳው በልዩ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ እንዲታይ ተወስኗል

    የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ከማእከል የተሰጠ ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖራቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም፣ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ(EBS) የቴሌቭዥን ጣቢያ፣ “ሃይማኖታዊ ትምህርት” የሚያስተላልፉ ፕሮግራሞች፣ የቤተ ክርስቲያንን ስም እንዳይጠቀሙ ወሰነ፡፡
    ምልአተ ጉባኤው በዛሬ፣ ጥቅምት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. ስድስተኛ ቀን የቀትር በፊት ውሎው ያሳለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ እንዲኾን፤ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና ለኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቭዥን በደብዳቤ እንዲያውቁት ይደረግ ዘንድ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡
    ምልአተ ጉባኤው ከዚሁ ጋር በማያያዝ፤ በሊቃውንት ጉባኤ ሳይመረመሩ እና በማእከል ሳይፈቀዱ በግለሰቦች እየተዘጋጁ የቤተ ክርስቲያንን ስም ይዘው ስለሚወጡ የስብከት፣ የመዝሙር እና የመጻሕፍት ኅትመቶች እንዲኹም የአዳራሽ ጉባኤያት እና ስብሰባዎች ከተወያየ በኋላ ቀደም ሲል ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች በማጽናት ተመሳሳይ ትእዛዝ መስጠቱ ታውቋል፡፡
    ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ “ስብከተ ወንጌል እና ሚዲያን በተመለከተ” በተራ ቁጥር ሦስት በያዘው አጀንዳ፤ ቤተ ክርስቲያን ማእከላዊነቱን ጠብቆ የራስዋን ድምፅ ለዓለም የምታሰማበት እና ስብከተ ወንጌልን የምታስፋፋበት የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት እንዲጀመርም ወስኗል፡፡
    ለቤተ ክርስቲያን የብዙኃን መገናኛ ስርጭት የሚያስፈልገውና በስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ አስተባባሪነት ተጠንቶ የቀረበው በጀት ባለፈው ዓመት ግንቦት በምልአተ ጉባኤው የጸደቀ ሲኾን በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር እንደተመለከተው፤ በዚኽ ዓመት በጀቱ በአፋጣኝ ሥራ ላይ እንዲውል የቀረበውን ጥያቄ በመቀበል የፋይናንስ ምንጮቹን ወስኖ ለነገ የሚያቀርብ ሦስት አባላት ያሉት የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት(ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እና ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ) ኮሚቴ በምልአተ ጉባኤ ተሠይሟል፡፡

    ReplyDelete