Saturday, October 3, 2015

ታዖሎጊስና ቃለአዋዲ የተሰኙት መርሓ ግብሮች ከቤተ ክርስቲያኗ ህጋዊ ፈቃድ እስካልተሰጣቸው ድረስ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንን ስም መጠቀም አይችሉም



To EBS :- እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ጥያቄዎቻችንን ከዚህ በታች አቅርበናል::

1. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ራሱን የቻለ ሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ መዋቅር አላት:: ማንኛውም የቤተክርስትያኒቱን ስም ይዞ የሚወጣ የአየር ፕሮግራም የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕጋዊ ፈቃድ ወይም ይሁንታ ማግኘት አለበት:: ወይም የቤተክርስትያኒቱ ህጋዊ መዋቅር ውስጥ ያለ አካል መሆን ይኖርበታል:: ቤተ ክርስትያኒቱ ያላከችው ማንም አካል ግን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ስም ይዞ መንቀሳቀስ አይችልም:: 

በዚህም መሰረት ታዖሎጊስና ቃለአዋዲ የተሰኙት መርሓ ግብሮች ከቤተ ክርስቲያኗ ህጋዊ ፈቃድ እስካልተሰጣቸው ድረስ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንን ስም መጠቀም አይችሉም:: ስለዚህም ከቤተ ክርስትያኒቱ አስተዳደር ህጋዊ የሆነ ማስረጃ ካላመጡ በስተቀረ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስም መጠቀም እንዲያቆሙ ቴሌቪዝን ጣብያው አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስድልን እንጠይቃለን::

2. በነዚሁ የቴሌቪዝን መርሓ ግብሮች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ስም የቤተክርስቲያኒቱን ቀኖና በሚጥስ መልኩ የሚተላለፉ መልክቶችና ድርጊቶች እየተበራከቱ መጥተዋል:: ይህም የአንድን ሃይማኖት ክብርና ልዕልና የሚነካ ነው::ለምሳሌ ለመጥቀስ - በየትኛውም ኦርቶዶክሳዊ መስፈርት የእመቤታችን ስዕል ከአትራኖስ ስር አትቀመጥም:: እንዲህ አይነት በኦርቶዶክስ ስም የሚከናወኑ - ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ ስብከቶችና ድርጊቶች የሃይማኖቱ ተከታዮች ላይ የሞራልና የስነ ልቦና ጫና እያስከተለ ነው:: ሕዝቡ ወደ ሕጋዊ ጥያቄ ከመሄዱ በፊት የኢቢኤስ አስተዳደር አስፈላጊውን እርምት እንዲሰጥልን እንጠይቃለን:: 

3. በነዚሁ ሰባክያን በነዚሁ ቴሌቪዝን መርሃ ግብሮች ላይ ባደባባይ " መንደርተኛ " በሚል የተዘለፈው የቤተ ክርስትያኒቱ ዘማሪ ይልማ በይፋ ይቅርታ እንዲጠየቅና ድጋሚም በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮም ሆነ መምህራን ላይ ተመሳሳይ ዘለፋ እንዳይከናወን አስፈላጊውን መመርያ እንዲሰጥልን የኢቢኤስን አስተዳደር በኢትዮጵያዊና ክርስትያናዊ ትህትና እንጠይቃለን::

4. በመጨረሻም እነዚሁ ስብስቦች ለቲቪ ፕሮግራሞቻቸው ማስፈጸሚያ ይሆኑ ዘንድ በኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ስም የሚያደርጓቸው የስፓንሰር ጥያቄዎችና ልመናዎች በአስቸኳይ እንዲታገዱ እንጠይቃለን:: 

በዚሁ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን አስተዳደርም፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም ስለሚተላለፉት መርሓ ግብሮች ግልጽ መግለጫ እንዲሰጥ እንጠይቃለን::ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን ታሪክ ዶግማና ቀኖና ከመጠበቅ እና ከማስጠበቅ አንጻር በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፊው ምዕመን ዘርፈ -ሰፊ እንቅስቃሴ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡

4 comments:

  1. ewnet new haymanot liela midia liela.............

    ReplyDelete
  2. እባካችሁ ሁሉም ሰው አውርተን አንለፈው ተግተን እንስራ ቤተክህነት እንደሆን ምን እየሰራ እንደሆነ ግልጽ ባይሆንልንም እኛ የራሳችንን የምንችለውን በመስራት ቤተክርስቲያንን እናግዝ፡፡

    ReplyDelete
  3. እባካችሁ ሁሉም ሰው አውርተን አንለፈው ተግተን እንስራ ቤተክህነት እንደሆን ምን እየሰራ እንደሆነ ግልጽ ባይሆንልንም እኛ የራሳችንን የምንችለውን በመስራት ቤተክርስቲያንን እናግዝ፡፡ የመፍትሄ ሀሳቦች ይነሱ ለምእመኑ ኢንተርኔት ውጪ ተኩላው በሚንቀሳቀስበት መንገድ ሁሉ እኛ እንዳንሄድ የሚያግደን ምንም መንገድ የለም፡፡ እኛም ገንዘባችንን ለዚህ አገልግሎት በግላችን እየተንቀሳቀስን ስራ ላይ እናውለው፡፡

    ReplyDelete