Tuesday, February 11, 2020

ለአንዱ ቦታ እያመቻቹ ሌላውን በራሱም ቦታ ማንገላታት

(በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ)
(አንድ አድርገን 02/6 2012 ዓ.ም):-  መምህር ምሕረተ አብን ለማስደንገጥም ይሁን ጉባኤዎችን ለመረበሽ ትላንት ማታ እንደተደረገ የሰማሁት ነገር ብዙ ነገር የሚጠቁም ነው። ሰሞኑን ወንድሞቻችን ሰማዕትነት የተቀበሉበትና አዲስ ቤተ ክርስቲያን የፈረሰበት 24 ቀበሌው ቦታ ያን ሁሉ መዓት ያመጣው ፓስተር ዮናታን ቦታውን እርሱ እመራዋለሁ ለሚለው የመልካም ወጣት ፕሮጄክት በጠየቀው መሠረት ለማስረከብ በጥድፊያ ላይ ስለነበሩ ነው።


ለረጅም ዘመናት የግለሰቦች የይዞታ ቦታ የነበረውንና ከተማው ለፓርክ ወስኘበታለሁ ብሎ ለግለሰቦቹ ምትክ ሊሰጥ ወስኖበት የነበረውን ቦታ ፓስተር ሲጠይቁ ቦታውን ከፓርክነት ለውጦ ለመስጠት ያን ሁሉ ጥድፊያ ከማድረጉም በላይ ጥፋት እንኳ ቢኖር በቤተ ክህነቱ በኩል መፍታት እየተቻለ በሌሊት ሄዶ ጦርነት ከፍቶ ገድሎና አቁስሎ አስሮ እንዲሁም አፍርሶ እልበቃው ብሎ ነው መሰል በነባር ቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ላይ ተገኝቶ ረብሻ ለመፍጠር መሞከሩ በእጅጉ ያስተዛዝባል። ይህን ሁሉ ጥፋት ለመሸፋፈን ነው መሰል ደግሞ አሁንም የታሠሩት የቤተ ክርስቲያኒቱ ሰዎች ናቸው። ከዚህም አልፎ ወደ ጉባኤ ብጥበጣ መገባቱ ያስገርማል።

እንዲያውም ለሰዎች መማር የምታስቡ ከሆነ ሰፋ ያለ ተጨማሪ ቦታ የሚገባው ምሕረተ አብ ነበረ። ቢያንስ ተጨበርብረናል ብለው ጠቅላይ ሚንስትር /ቤት ድረስ ሄደው የከሰሱት የሉምና። ሁኔታው ግን የተገላቢጦሽ ነው። ለነገሩ እንጂ ሁኔታውስ ከዚህም ያለፈ ነገር መኖሩን የሚጠቁም ነው። ግድ የለም ይሁን። ሆኖም ወንድሞቻችን በግፍ ሰማዕትነት የተቀበሉበት ቦታ ለማን እንደምትሰጡት ነገ የምናየው ብቻ ሳይሆን ታሪካዊቷ ቤተ ክርስቲያን ከአንድ ፓስተር ፕሮጄክት ጋር እንዴት እንደምትወዳደርና ለማን እንደምትወስኑ ለመስማት በሁሉም ዐይን እንደምትጠበቁ ከወዲሁ ብታውቁ መልካም ነው።

"ከዐው መዓትከ ላዕለ አሕዛብ እለ ኢየአምሩከ፣
ወላዕለ መንግሥት እንተ ኢጸውዐት ስመከ" /፸፰ ፥፮/

No comments:

Post a Comment