ዲያቆን
አባይነህ ካሴ
(አንድ አድርገን ጥር 29 2012 ዓ.ም) ፡- አዲስ አበባ ከተማ ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል አካባቢ ቀበሌ ፳፬ ላይ የነበረው ክፍት ቦታ በመዋቅራዊ ፕላኑ መሠረት ለመናፈሻነት (Green
Area) የተጠበቀ
እንደነበር ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ መንግሥት ሊያለማው ቀርቶ የቆሻሻ መጣያ እና ለኗሪው የደኅንነት ስጋት እስኪኾን ድረስ ወንጀሎች ይፈጸሙበት የነበረ ቦታ መኾኑ ኗሪውን ሲያሳስበው ቆይቷል፡፡ በዚህም የተነሣ መጠነኛ የማልማት ሥራዎች ማኅበረሰቡ በራሱ ተነሣሺነት ሲያደርግበት የነበረ ቦታ ነው፡፡
በዚህ መካከል በቦታው ላይ ለሕዝቡ አገልግሎት ይሰጥ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ለመትከል ምእመናን እንቅስቃሴ ይጀምራሉ፡፡ የሚመለከተው የቤተ ክህነት መዋቅርም ጉዳዩን ዐውቆት አስፈላጊውን ድጋፍ ስላደረገ ጥያቄውን ለመንግሥት አካላት ያቀርባል፡፡ በዚህ መካከል አንድ እሽቅድምድም ይጀመራል፡፡
ከአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲ የደረሰን መረጃ ጉዳዩን ይፋ አውጥቶታል፡፡
ቦታውን ለፓስተር ዮናታን የወጣት ማምከከኛ ፕሮጀክት በአጭር ቀናት ጊዜ ውስጥ ማስተር ፕላኑን አሻሽለው ለማስከበር መሯሯጥ ይጀምራሉ፡፡ በዚህ መካከል መቃኞው በፍጥነት ተሠርቶ ለጸሎተ ቅዳሴ ዝግጁ ኾኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ይህ እርር ድብን ያደረገው ባለሥልጣን በቤተ ክርስቲያን ላይ ሞት ዐወጀ፡፡ ይህ የመንግሥት የተንጋደደ እና ሚዛናዊነቱን የሳተ ወገንተኝነት እጅግ በጣም አደገኛ ነው፡፡
ወጣት እየገደሉ የወጣት ፕሮጀክት በሚል ሕዝብን የማጥፋት ተልእኮ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ብቻ የሚቀዳ መኾኑ ይታወቃል፡፡ የኦርቶዶክስን ወጣት ጥይት ይበላዋል የጠቅላይ ሚንስትሩ የጡት ልጆች ግን ይለማሉ፡፡ ይህ ለእኛ አዲስ አይደለም፡፡ የናቡከደነፆር ልጆች የላመ የጣመ ይበላሉ፤ ሠለስቱ ደቂቅ ግን ጥሬ ይቆረጥማሉ፡፡ በአማን የሚለሙት ግን ሠለስቱ ደቂቅ ሲኾኑ የቤተ መንግሥቱ ልጆች ግን ይኮሰምናሉ፡፡
ሠለስቱ ደቂቅ ሚልዮን፣ ሚካኤልና አብርሃም ሆይ እናንተ እሳቱን ሳትፈሩ ተሸግራችሁታል፡፡ እኛም የፈተናችሁትን እሳት እንዳንሰቀቀው አስተምራችሁናል፡፡ ጅምራችሁ ዳር ሳይደርስ የሚመለስ ኦርቶዶክሳዊ እንዳይኖር አድርጋችሁ አጽንታችሁናልና እናመሰግናችኋለን፡፡ ዕረፍታችሁን የሰማዕታት ያድርግላችሁ!!!
No comments:
Post a Comment