Wednesday, February 12, 2020

ጎጠኞች ቤተ ክርስቲያንን ካቆሰሏት በላይ ያቆስሏት ዘንድ ዕድል አይሰጣቸው!!


የኦሮሚያ ቤተ ክህነት አደራጅ ኮሚቴ ብሎ ራሱን የሾመው አካል በከፍተኛ የመተማመን ወይም የመቅበዝበዝ ስሜት ውስጥ ሆኖ እንደሆነ ግራ በሚገባ መልኩ አስቸኳይ የሲኖዶስ ስብሰባ መጠራቱ ከተነገረበት ጊዜ ጀምሮ እየፎከረ ነው፡፡ ቀሲስ በላይ ከአሜሪካእስኪ ውግዘቷን ይሞክሯትና እንታያያለንሲል ኃይለ ሚካኤል ደግሞ ከሀገር ቤት በተደጋጋሚ የቀጥታ ሥርጭት እየገባ ለሰኞ የተጠራውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤእናንተ ፖለቲከኞች ለፖለቲካችሁ ስትሉ ነው የጠራችሁት፣ ብታርፉ ይሻላል፣ ጉባኤው የጉባኤ ከለባት (የውሾች ጉባኤ) እንዲሆን አንፈልግም፣ ቄሮና ቀሪቲ ለሁሉም ነገር ራሳችሁ አዘጋጁበማለት ከወዲሁ ጉባኤውን ዘልፎ፣ ነቅፎና አውግዞ ይባስም ብሎ ውሳኔውን በአመፃ ለመመለስ የራሱን ሠራዊት አሰልፎ እየጠበቀ ይገኛል፡፡


በኦርቶዶክሳዊነት ለሚያምን አማኝ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ የመጨረሻው የቤተ ክርስቲያን የውሳኔ አካልና ጠባቂ ነው፡፡ ሲኖዶስን መሳደብ መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ነው፣ መንፈስ ቅዱሰን መሳደብ ደግሞ ዕጣ ፈንታው ውግዘት ነው፡፡ ይኽ የተለመደ ሥርዓት እንደሆነ በተለይ ኃይለ ሚካኤል ነገረ መለኮት / ቤት ገብቻለሁ ስለሚል የሚጠፋው አይመስለኝም፡፡ በየትኛውም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ የሲኖዶስን ውሳኔ ኃይል ተጠቅሞ ውሳኔን ለመቀልበስ እንደተሞከረም እናውቃለን፡፡ አባቶች የልዮንና የፖለቲከኞችን ውሳኔ እንድቀቡ ባላቸው ሠራዊትና መንጋ ያስደበደቡት ኬልቄዶናውያን እንጂ ኦርቶዶክሳውያን አይደሉም፡፡ ኃይለ ሚካኤል ግን የራሱ ጥሪና ዝግጅት ኬልቄዶናዊ ሆኖ ሳለ በጩኸቴን ቀሙኝ ፈልጥ ሌላውን ፈርጆ እየጠበቀ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ለሚታዘብ ገራሚ ነገር ነው፡፡

ለሚታዘብ የተዘጋጁበትና የተማመኑበት ነገር ያለ ይመስላል፡፡ ወይም ክህደቱ ሃሊናቸውን እያነዋወፀው ይመስላል፡፡ ፖለቲካውን፣ ዘነረኝነቱን፣ ጥላቻውን፣ -ክርስቲያናዊነቱን የተሸከሙትና ከአሕዛብና ከመናፍቃን ጋር ሆነው የቤተ ክርስቲያኗን አንድነት ፈተና የሆኑት እነሱ ሆነው ሳለ ስድባቸውን ወደሌላው ማዞራቸው ምን ያህል ጋጠ-ወጦች መሆናቸውን ከማሳየት ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡

እነዚህና ከሰሞኑ ሲያደርጓቸው የከረሟቸውን ጉዳዮች ቅዱስ ሲኖዶስ በዝርዝር ተመልክቶ የማይድኑ ከሆኑ ቆርጦ በመጣል፣ ሲንከባለል ለመጣው እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ችግር ግን ዘላቂ መፍትሔ የሚሰጥ ካልሆነ የሚያስገርም ነው የሚሆነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ይመለሱ ዘንድ ተነግሯቸው ራሳቸውን ከሲኖዶስ በላይ ያገዘፉ በኢ-ኦርቶዶክሳውያን አይዞህ ባይነት እዚህ የደረሱ መሆናቸውን እያየን እያነበብን ነው፡፡ ትምክህታቸው በክርስቶስ ሳይሆን በሚነዱት መንጋ ነው፡፡ መንጋውን ለፖለቲካም ለሃይማኖትም እንደ አግባቡ ሲጠቀሙበት ደግሞ እያየን ነው፡፡ ታዲያ ይህንን አደገኛ ኃይል ከቤተ ክርስቲያን በረት ለይቶ እውነቱን መግለጥ ያስፈልጋል፡፡ እነ በጋሻው የፎከሩትን ያህል የተከተላቸው የለም፣ ትዝታውም ሲዝትና ሲበዘብዝ ኖሮ አሁን ቀልቡ ተገፎ ብቻውን ፌስ ቡክ ላይ ሲለፈልፍ ነው የሚውለው፣ የእነዚህም ከዚያ የተለየ አይደለም፡፡ ትልቅ የመሰሉት ትልቅ የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ተጠግተው እንጂ ያለ እርሷ ተራዎች ናቸው፡፡

ታዲያ የቅዱስ ሲኖዶስን ጉባኤ ለመርዳት መረጃዎችን፣ ንግግሮቻቸውን፣ ፉከራቸውን፣ እነማን ምን እያሉና ከጀርባ ሆነው እየዘወሩት እንደሆነ ያሉትን አካላት ማስረጃዎች ለአባቶች አደራጅቶ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡ ስሕተት እንደማንደግምና ከታሪክ እንደምንማር ይጠበቃል፡፡ እነ በጋሻውና እነትዝታው መሄዳቸው ላይቀር ነገር ከዐሥር ዓመታት በላይ እነሱን በማስታመም ቤተ ክርስቲያን መከራ ስታይ ኖረች፣ አሁን ደግሞ ጎጠኞች ቤተ ክርስቲያኗን እስከ አሁን ከቆሰሏት በላይ እንዲያቆስሏት መፍቀድ በህልውናዋ ላይ መቀለድ ይሆናል፡፡ እምነቱን እንደሆነ ጨርሰው የጣሉት ስለመሆኑና አካሄዳቸው ቀኖናዊም፣ ሥርዓታዊም አለመሆኑ ለማንም ታዛቢ ግልጥ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment