Monday, November 3, 2014

በሃይማኖት ስም የነቀዙት ‹‹ሃይማኖተኞች››

አንድ አድርገን ጥቅምት 24 2007 ዓ.ም  
ከታደሰ ወርቁ (ዳግም የቀረበ)
ከዛሬ 17 ዓመት በፊት በጦቢያ መጽሔት ንቅዘትን  አስመልክቶ  በቀረበ መጣጥፍ ውስጥ  በሃይማኖተኝነት ሽፋን «ሃይማኖተኞች» ንቅዘትን እንዴት እንደሚፈጽሙ የምትገልጥ ትንሽ ታሪክ አስፍሯል፡፡ ታሪኩ እንዲህ ነው፡፡  በ፲፱፻፶ዎቹ  መጀመሪያ  ላይ  የየረርና  ከረዩ  አውራጃ ገዢ የነበሩት  ባለሥልጣን  ናዝሬት ላይ የቅድስት ማርያምን  ቤተ ክርስቲያን በምእመኑ መዋጮ አሠሩ፡ ፡ በወቅቱ  የተደነቀውን  ቤተ ክርስቲያን  ጃንሆይ ከጎበኙ በኋላፊት ለፊት የተሠራውን ድንቅ  መኖሪያ ቤትም ተመለከቱና «ይህን ያሠራው ማነው?» ብለው ይጠይቃሉ፡፡ የአውራጃውገዢ ምንም ዐይነት መልስ እንደማይሰጡ የተረዱት አረጋዊው ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ «ጃንሆይ፤ ማርያም ሠራችው» ብለው አግድሞሽ መልስ ሰጡ ይባላል፡፡ ቤተ ክርስቲያን አሠሪ የሆኑ የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ የሆኑት በገዢነታቸው ሳይሆን በሃይማኖተኝነታቸው ነው፡፡ ምእመኑም ገንዘቡን አውጥቶ በእምነት ሲሰጥ ሃይማኖተኛ ናቸው ብሎ እንጂ ገዢ ናቸው ብሎአይደለም፡፡ የሆነው ግን ሃይማኖተኝነት ያጎናጸፋቸውን መታመን እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም «ማርያም ሠራችው»ዐይነት ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ሠርተው፣ በንቅዘት የራሳቸውንም ጎጆ ቀልሰዋል፡፡

ይህ ትናንት ነው፤ ዛሬ አይደለም፡፡ ትርፋማ ንቅዘት ልንለው እንችላለን፡፡ ቢያንስ ሕንፃ ቤተ  ክርስቲያኑ  ተሠርቷል፡፡  ባይሆንዋናው  ጉዳይ  ለምልክት  እንኳን ታይቷል፡፡ እንደዛሬው የአመጽ አቀጣጣች «በጠልፎ ኪሴዎች» እጅ ሙሉ በሙሉአልወደቀም፡፡ በእርግጥ በሃይማኖት የንቅዘት ትንሽና ትልቅ ኖሮ ሳይሆን አሁን ካለው ነቀርሳዊ ንቅዘት /Malignant Corruption/ አኳያ የተሻለ ነው ለማለት ነው፡፡ ምክንያቱም እንደ ዘመነኞቹ ሃይማኖተኞች ምኑንም ሳይዙ ፣ ምኑን ምሳይጀምሩ ለኪስ ማሰብ ብቻ አልታየም፡፡ ከመቶ ዐሥሩን ወስዶ ዘጠናውን ለሥራ የሚያውል ቢገኝ መልካም ነበር፡፡ አሁን እኛ ይህን እንኳን ማግኘት ቸግሮናል፡፡ ካለፉት ሁለት አስርት  ዓመታት  ወዲህ  ቀስ ብሎ በቤታችን ባሕል የሆነው ነቀርሳዊ  ንቅዘት ጫፍ ላይ ከመድረሱ የተነሣ የበሽታው ተጠቂዎች እየበረከቱ ሲመጡ ተመልክተናል፡፡ 

የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱን ትተን ነቀርሳዊ በሆነ ንቅዘት በነቀዞቹ የተሾመው ሹም የወደፊት ሁኔታ ስንመለከት እርሱም ያወጣውን ገንዘብ እያሰላና ያወጣውን እስኪያወራርድ በሃይማኖተኝነት ስም ንቅዘትን እየፈጸመ «ሃይማኖተኛ» መስሎ ይኖራል፡፡ የንቅዘታዊ ሙስና ጥቅም በሹማምንት ደም ሥር ውስጥ እንደ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ይታያል፡፡ ጉቦን፣ ሙዳይ ምጽዋት ማድፋፋትን፣የሹም ዘረፋንና የመሳሰለውን እንደ ባሕል ይዘው የቀጠሉ ይመስላሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ይህን አካሄዳቸውን የሚያረግብ ነገር ፈጽሞ መስማትም ሆነ ማየት አይፈልጉም ፤ በመንገዳቸው ላይ የተገኙትን ሰዎች በአንድም በሌላም መንገድ መጋፈጥ የህልውና ጉዳይ ሆኖባቸው ይታያል፡፡

በንቅዘት የተዘፈቁና ሃይማኖታዊ ብኩርናቸውን ለከበርቴም ሆነ ለመንግሥት ሹም እንዲሁም ለአፅራረ ሃይማኖት ጭምርመሸጥን የያዙ የትናንትም ሆነ የዛሬ /በሃይማኖተኝነት ስም የነቀዙ ሃይማኖተኞችሹሞች እውነትን ለመናገር፣ እውነትን ለመወሰንና ትክክለኛ ዳኝነትን ለመስጠት የሞራል የበላይነት አይኖራቸውም፤ ሊኖራቸውም አይችልም፡፡ አሁንም እንደ ቀድሞ በቅዱስ ፓትርያርኩ ዙሪያ ተሰልፎና  ተጠግቶ አብረዋቸው ከቤተ ክህነቱም  ማዕድ እንደአሻቸው እየጎረሱ ያሉትንሁሉ ማሰብ ይቻላል፡፡ እነዚህን የመሰሉ ሰዎች ናቸው በቤተክርስቲያኒቱ ሊካሄድ የታሰበውን መዋቅራዊ ለውጥን አጥብቀው በመቃወም አንዱን ከሌላው ጋር ለማጋጨት በሆቴሎች የሚሰበሰቡት ፤ አድብተውና አስልተው ጠልፎ መጣያ ያሉትን ገመድ በመጠቀም የማያዋጣ ቁማር በመጫወት መሰረታዊ መናወጥን በቤተክርስቲያኒቱ ሊያመጡ ያሰቡት፡፡

ርካሽ ኬጂቢያዊ ስልት  የእኛዎቹ ሽፍቶች  የሚፈልጉትን ውሳኔ ለማስወሰን ሲጠቀሙበት በተደጋጋሚ ታይተዋል፡፡ በተለይ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሚወሰኑት ውሳኔ ቤተ ክርስቲያኒቱን ጠቅሞ የእነርሱን ምጣኔ ሀብታዊና አስተዳደራዊ ተጠቃሚነታቸውን የሚጎዳ ሆነው ካገኙት ተጽዕኖ ፈጣሪ ወደ ሆኑ አባቶች ስልክ በመደወል ማስፈራራት ይጀምራሉ ፤ ውሳኔዎች ተፈጻሚነት እንዳይኖራቸው በግልም ሆነ በቡድን በመሆን ሰዎችን ያስፈራራሉ ፤ እንደ አሁኑ ጊዜ መዋቅራዊ ለውጥን ሲሰሙ ይህን ያደረገው ማኅበር ይህ ነው በማለት የለመዱት ጥቅሞቻቸው እንዳይቀርባቸው ከመንግሥት ጋር ለማላተምና በሚፈጠረው ቀውስ የታሰቡት ለውጦች እንዲንጓተቱ ብለውም እዲቀሩ የማድረግ ስራ ይሰራሉ፡፡
ነቀርሳዊ ንቅዘት ወይስ «ነጭ ለባሽነት»?
በእርግጠኝነት ግን አንድ ነገር መናገር እንችላለን፡፡ እኚህን የመሰሉ በሃይማኖተኝነት ስም የነቀዙ «ሃይማኖተኛ» ሹማምንትንተጠግተው በንቅዘት መዘፈቃቸውን ብቻ ሳይሆን በቤተ ክህነቱ ውስጥ ለሚታየው ለኦርቶዶክሳዊ ሞራል መላሸቅ አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆናቸውን ፡፡ በእነዚህ ሰዎች ዙሪያ ያሉ ሰዎችን ስንመለከት ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት በአቋም የተነሡ መሆናቸው ይገባል ፤  እናም ሰዎቹ ከምጣኔ ሀብታዊ ተጠቃሚነታቸው ባሻገር በሃይማኖተኝነት ሽፋን ቤተክርስቲያኒቱን የማፍረስ «ነጭ ለባሽነት» ሚና እየተጫወቱ ይገኛል፡፡ ከተዘፈቁበት ነቀርሳዊ ንቅዘት በላይ «ነጭ ለባሽነት» ሚናቸው እስከ ምን ነውየሚለው ጥያቄ መመለስ እንዳለበት ጽኑ እምነታችን ነው፡፡ ሚናቸው ኢኮኖሚያዊ ድልቦችን በማደለብ ብቻየተወሰነ አይመስለንም፡፡ ይሁንና ቤተክርስቲያኒቱ ከተዘፈቀችበት ችግር፣ ከወደቀችበት አዘቅት ሳትወጣና ሳታገግም እነዚህ ሰዎች ለሕዝበ እሥራኤል ከወረደው መና የበለጠ በንቅዘት ከብረው ታይተዋልና፡፡



ጊዜው ሲደርስ በቀድሞው መንገድ መቀጠል አይቻልም
ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት በሃይማኖተኝነት ስም የነቀዙ «ሃይማኖተኞች» በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ጥላቸውን ጥለውባታል፤ አሻራቸውን አሳርፈውባታል ፤ ነጋዴ ነግዶ ከሚያተርፈው በላይ የቤተክርስቲያንን ብር በተለያዩ ባንኮች በስማቸው ዘርፈው አስቀምጠዋል ፤ በአዲስ አበባ በሙዳይ ምጽዋት ብር የተሰሩ ሁለትና ከዚያም በላይ የሆኑ ቪላዎችን ያከራያሉ ፤ ቤተክርስቲያኒቱ የምታከራያቸውን ቤቶች በሞኖፖል ተቆጣጥረው የቤተሰብ እስኪመስል ድረስ በከፍተኛ ብር እያከራዩ ከገቢውም ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ ፤ ይህን ጉዳይ ፓርላማ ድረስ ምዕመኑ አቤቱታውን ቢያደርስም የአፈጉባኤው አማካሪ  ‹‹ፓርላማው ይህን ጉዳይ የማየት ስልጣን አልተሰጠውም ፤ ስለዚህ መልስ ልሰጥበት አንችልም›› በማለት መልስ ሰጥቶበታል፡፡ እነዚህ ሰዎች በትውልድና በታሪክ ፊት ምስክርነት ይቆያቸዋል ፤ ፍርድ ይጠብቃቸዋል፡፡ እምነት አጥተው በሠሩበት ሳይከበሩና ሳይወደዱ በሥልጣን በቆዩበት ዘመን ላደረሱት ግፍና ለፈጠሩት ትርምስ እስካሁን የተፈጠረውን ጥላቻ በአይነት እንደመመለስ ብንወስድ እንኳን ውርደቱ ገና ነው፡፡ የመንግሥት ሹሞችን ምርኩዝ በማድረግ በፈጠራ ድራማ አንጻራዊ ሰላምን ለማደፍረስ  መጣር ከታሪክ ተወቃሽነትና ተጠያቂነት አያድንም ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልዕልና መደፈር አንድ ምልክት ይህ ነው፡፡

ይህ ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱ የምትመራው ሕይወት ረጋ ያለ የሚመስል ዳሩ ግን በእሳተ ገሞራ ላይ የተቀመጠች ከተማሕይወት ነው፡፡ ምክንያቱም በዛሬው ዘመን ያለው መቆርቆዝ፣ በመሪዎቻችን አማካኝነት የቤተክርስቲያኒቱ መዋረድ፣የቤተክርስቲያን ጥቅም የሚባል ነገር ትርጉም ማጣት፣ የቤተ ክርስቲያን ሀብት ወደ ጥቂት ሰዎች ኪስ የመግባቱ ሒደት አለመገታት፣ የቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም ዋስትና ማጣት ይችን ቤተክርስቲያን ለአዲስ ዓይነት መከራ የሚያዘጋጅ ይመስለናል፡፡ ግፍ ሲጠራቀም፣ ጊዜው ሲደርስ በቀድሞው መንገድ መቀጠል አይቻልምና፡፡

………………………………………………..
አሁን ላይ በታሪክ የመጀመሪያዋ ገናናዋ ቤተክርስቲያን ሕልምና ዓላማዎች ያጣች ትመስላለች፡፡ የጀግኖች እናት፣ የሰማዕታት ቤት ቤተክርስቲያን ዛሬ የብዙሃን  ሰብሳቢነትና ተንከባካቢነት አልተሰማትም፡፡ ካህናቱ ፣ ምእመኑና ገዳማቱ ያለባቸው መከራ መጪውን ጊዜ ይጠቁማሉ፡፡ ክርስቶስ «ምልክቱን ከበለስ ፍሬ ታውቁታላችሁ» ነበር ያለው፡፡ የቤተክርስቲያኒተን መጪጊዜ ከወቅቱ ጥላ ለማወቅ ይቻላል፡፡ ያለንበት የፕትርክና ዘመን ካለፈው የሚከብድና የሚያስጨንቅ አለመሆኑን እርግጠኛ ሆነን መናገር አንችልም፡፡ በሃይማኖተኝነት ስም ሙዳይ ምጽዋት ላሽና ጀርባ ነካሽ «ሃይማኖተኛ» እስካሁን አላጣንም፡፡ሰዎቹ አእምሮ ውስጥ ዘወትር ያለውም ላሽነትና ነካሽነት ነው፡፡ ከትምህርት ትምህርት፣ ከልምድ ልምድ፣ ከሃይማኖትሃይማኖት የሌላቸው ግለሰቦች ወንበሮችን ያለአግባብ ሲይዙ ምን ያህል ቤተ ክርስቲያኒቱን ወደ ኋላ እንደሚጎትቱ ፣ ምንያህልም አንድነቷንና የታሪክ ቅሪቷን እንደሚያፈራርሱ ለመረዳት አያዳግትም፡፡

በዚህ ረገድ ሲታይ ቤተክርስቲያኒቱ ሁነኛ አመራር አጥታ ቆይታለች ብቻ አይባልም፡፡አጥፊ አገዛዝ ሥር ወድቃ ነበር ማለት ያስደፍራል፡፡ የአስተዳደራችን አካሔድ መለወጥና ከነቀርሳዊ ንቅዘት ሥርዐት መውጣት አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ ሥልጣንን  የቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና በሚፈቅደው አግባብ አግኝቶ ፣ ራሱን ችሎና ቀና አድርጎ የሕዝብ አገልጋይነት ሓላፊነትን የሚረከብና በገዳማዊ ሕይወቱ የተፈተኑ አባቶች ያሿታል፡፡ ዛሬ ምእመኑ በሙሉ የተሳፈረበትን የአመራር መርከብምእናስብ፡፡ በሃይማኖተኝነት ስም የነቀዙ «ሃይማኖተኞች» ያሰናከሉት መርከብ ነው፡፡በሰፊው ውቅያኖስ ላይ እንደ ልብ ሊንሳፈፍ አይችልም፡፡ አውሎ ነፋሱ፣ ወጀቡና የባሕሩ ቁጣ ጠንካራ መርከብ ይፈልጋል፡፡ ይህ ዘመነ ፕትርክና መርከቢቱን ወዳልሆነ መስመር እንዳያነጉዳት መልሕቁን ጥሎ ቆም ብሎ ማሰብን ይጠይቀዋል፡፡ የምእመኑና የሊቃውንቱ ዕድል፣የቤተክርስቲያን አመራር መጫወቻ ስላልሆነ  ንቅዘት ያላገኛቸው ፣ብቃት ያላቸውና ኦርቶዶክሳዊ ፍቅራቸው የተፈተነ ሰዎችን በማስጠጋት እንዲሞክሩት ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ 

እስከመቼ አስተዳደራችን የነቀዘየላዕላይና የታህታይ መዋቅር ሹማምንቶቻችን እምነት የዱር ሆኖ ይቀጥላልየአመራርአስተሳሰብ በንቅዘት ሲሻክርና ቤተክህነታዊ ሽብር ሲበዛበት ወደ ሕዝባዊ አመፅ፣ ወደ አባታዊ ክብር መንሣት መፍትሔነትና የጉልበት ተግባር ይዛወራልና፡፡ ከዚህ አኳያ በሃይማኖተኝነት ስም የነቀዘው አስተዳደርና አስተዳደሩን የከበቡት ነቀዞች ወይም የንቅዘቱ አጫዋችና አልቢተር ደስተኛ ተመልካች ሆነው ይህን ሁሉ ጨዋታ በድል አድራጊነት መንፈስ ይመለከቱታል፡፡ ምክንያቱም የምንጋራቸውን ግቦች፣ የምናከብራቸውን ኦርቶዶክሳዊ እሴቶች ተገንዝበን ለተፈጻሚነታቸው ፈቃደኞች መሆናችንን እስካሁን አላረጋገጥንም፡፡ ማረጋገጫው መንገድ ደግሞ በጥቃት ጊዜ አብሮ መሰለፍ፣ አብሮመሥራት አብሮ መታገል ሊሆን ይገባዋል፡፡

ኦርቶዶክሳዊ ጥቅምን፣ የቤተ ክርስቲያን አንድነትን፣ የአስተምህሮ ጥበቃን ማዕከል አድርገን ከታገልን በአንድነትና በኅብረት በቤተክህነቱ የተንሰራፋውን የንቅዘት ባርነት ቀንበርን ለመስበርና አማናዊውን ሃይማኖተኝነትን አንዲት በሆነች ቤተክርስቲያናችን ለማስፈን የሚያግደን ኃይል አይኖርም፡፡ ይህን የምለው መልካም ካለሆኑት ሃይማኖተኛ ሹማምንት የኃይል አሰላለፍና ከቤተ ክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ሁኔታዊ ግንዛቤ አንጻር ብቻ ነው፡፡ ስንነጋገርበት እንደ ባጀነው የቤተ ክህነቱ አስተዳደር ሕመምተኛ መሆኑን አውቀናል፡፡ ሕክምናውም «አንተ የንቅዘት ርኩስ መንፈስ ልቀቀው ብዬሃለሁ፡፡ ቤተክህነቱን ለቅቀህ ሒድ» ከሚለው ጸሎት ዘዘወትር ባሻገር ሁሉን አቀፍ ትግል ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ቀናኢ ምእመናንና ልዩ ልዩ ማኅበራት ስልታዊ በሆነ መንገድ አዲሱን አስተዳደራዊና መዋቅራዊ ለውጡን ለማስፈን መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል፡፡ መገፋትን ከመኖር ጋር የመላመድ ባሕሉና እዬዬን አርግዞ መቆዘሙ መቆምአለበት፡፡ ተናግሮ ሳይሆን በነቀዘው አስተዳደር ላይ ክፉ አስበሃል እባላለሁ በሚል መጨነቅ መቆም አለበት፡፡ በአጭሩ ቤተክርስቲያኒቱ የሐቀኛ ልጆችዋ እንድትሆን መታገል ይገባል፡፡ ከዚህ አንጻር ኦርቶዶክሳውያን ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል፡፡

የነቀዙት ‹‹ሃይማኖተኞች››  የጀመሩት ስም ማጥፋት ፤ የማይቀረውን መዋቅራዊ ለውጥ መሸሽና ከጀርባ ጋር መወዳጀት የመጨረሻዋን ጥይት እንደመጠቀም ይቆጠራል፡፡

4 comments:

  1. God Bless You! Ewenetegna yebatekerestian Lejoche nachehu Amlak yeagelegelot gizaachehun yarezemew! Amen!

    ReplyDelete
  2. The problem can be solved only with prayer and fasting and not by making the mistake others made! I doubt you are supporting MK! MK requested everybody to be patient and pray and wait for decision of Holy Synod which is as per christian ethics! hence, you might be some of ex-members who left the association for politics or caught with the disease of the Diaspora whom some official use as scapegoat to accuse MK!

    We shall pray as follows!

    Please our Lord and Saver Jesus Christ Kings of Kings Alpha and Omega, please for give those who are accusing your servants and their brothers who do not know what they are doing , Bring them to their sense so that they can stand worldly pressure political sectarianism , ethnic sectarianism and greed for power and money! Our Lord please bring also the self proclaimed supporter of MK, t bloggers such as Andadrigen, Hara and Adebabaye who promote their emotion, put fuel on the fires fire, use political style for spiritual fight,and do not have patience to wait for your replay to their senses! !Our Lord and Saver please cast out the same evil spirit that is misleading these two groups and keep the unit of EOTC although their methods and sides are different they lead to same result!
    Amen

    ReplyDelete
  3. Hig Akibiru Be Bete Kristiyan Sir huno malet Lenate lemin endekebedachihu bayytawokim ahun benekefa bezelefa nwur brmzrzrer ye bete kristiyan abatochin sedbio le sedabi mestet siraye bilachu keyazachut koye enaten ende sihitet ende maysera amlakawi teqwam be mayet egna bicha enawuqalen aye gud

    ReplyDelete
  4. Enter your comm
    ድሮም ከበሮ በሠው እጅ ያምር ሲይዙት ያደናግር እንዲሉ አባ ማትያስ ልበላቸው መንበሩ ላይ በእግዚአብሔር ፈቃድ ስላልተቀመጡ ሲመረጡም ስህተት ስለነበረበት አይፈረድባቸውም አላማው ምንፍቅናን ማሥፋፋት ስለሆነ አይደንቀኝም የገረመኝ ውጪ ሆነው በቀድሞዎቹ ፓትርያርክ ላይ የጻፉት ነው ሲገቡባት ትብስ ቁጭ እንግዲህ ወልደው የሚያጠቡት ሰይጣን ያበርታችው እላለሁ

    ReplyDelete