እንኳን ለቊስቋም ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሰን ።
አንድ አድርገን ህዳር 6 2007 ዓ.ም
ቁስቋም ማርያም በደርቡሾች ተቃጥሎ እንደነበር - 1930 ዓ.ም. |
የእመቤታችን በትልቅ የምስጋና
አገልግሎት ከሚከበሩ በዓላት መካከል የወርሐ ጽጌ በዓል አንዱና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ልብ ውስጥ ጥልቅ የልቦና ፍቅር ያለው
የማኅሌትና የቅዳሴ በዓል ነው፡፡ወርሐ ጽጌ በመባል በቤተክርስቲያናችን የሚከበረው ይኽው የምስጋና በዓል ከመስከረም 26 ጀምሮ እስከ
ኅዳር 6 ቀን ያለው ጊዜ ሆኖ የእመቤታችንን ስደት የምንዘክርበትና የምናስብበት ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ስለ ደብረ ፀሐይ ቍስቋም ማርያም ትንሽ ካነበብነው ማካፈል ወደድን……
ደብረ ፀሐይ ቍስቋም ማርያም ከጎንደር ከተማ በስተ ስሜን ምዕራብ ወጣ ብሎ በሚገኘው በደብረ ፀሐይ ቁስቋም የተሰራ ቤተክርስቲያን ነው። ደብረ ፀሓይ ቁስቋም በእቴጌ ምንትዋብ፣ ከ1725 ዓ.ም. እስከ በ1738ዓ.ም. ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን በጊዜው 360 መስታዎቶች የነበሩት፣ በቀይና ሰማያዊ ሃር አልባሳት ያሸበረቀ፣ እንደ ደብረ ብርሃን ስላሴ በጥሩ ኪነት የተዘጋጀ፣ ከወርቅና ከብር የተሰሩ የቤተ ክርስቲያን ማገልገያወች የነበሩት፣ በጊዜው የተደነቀ ቤተ ክርስቲያን ነበር። ደብረ ፀሐይ በተመሰረተበት ዘመን የራሱ ጉልት የነበረው ሲሆን ይኼውም በእብናት፣ በለሳ እና አርማጭሆ ተሰባጥሮ ይገኝ ነበር፤ ስለሆነም 260 ቀሳውስትን በስሩ ያስተዳድር ነበር፡፡ ከህንጻ ይዘቱ አንጻር በዚሁ ዘመን በምንትዋብ ከተገነባው ናርጋ ስላሴ ጋር ይመሳስል እንደንበር ግንዛቤ አለ።
የቁስቋም ግቢ ሦስት ጊዜ ጉዳት ደርሶበታል። በመጀመሪያ በ1858፣ ዓፄ ቴዎድሮስ መቅደላ ሊያሰሩት ላሰቡት ቤተ ክርስቲያን ከቤተክርስቲያኑ የተለያዩ ንዋያትን መውሰዳቸው ነበር። ሁለተኛው ጉዳት የደረሰው በ1870ወች፣ ደርቡሾች ግቢውን በእሳት በማጋየት ያደረሱት ዋናው ጉዳት ነበር። በዚህ ቃጠሎ ቁስቋም ማርያም ሊፈርስ ችሏል። ቤተክርስቲያኑ አሁን የያዘውን ቅርጽ ያገኘው በጣሊያኖች ጊዜ ሲሆን ያሁኑ መልኩ ከድሮው እጅግ ይለያል። የእቴጌ ምንትዋብ፣ የልጇ ዳግማዊ እያሱ እና ልጅ ልጇ እዮዋስ አጥንቶች በመስታዎት ሳጥን ሆነው በዚህ ቤተክርስቲያን ይገኛሉ። ከእሳት የተረፉ የእቴጌ ምንትዋብ መገልገያዎች አሁን ድረስ በቤተክርስቲያኑ ይገኛሉ።
Source :- http://am.wikipedia.org/
ደብረ ቍስቋም |
nice to read this
ReplyDelete