Tuesday, September 23, 2014

ለገጠር አገልግሎት ለመመዝገብ ለምትፈልጉ!

አንድ አድርገን መስከረም 13 2007 ዓ.ም

በፈረንጆቹ አቆጣጠር 1950 .. በካይሮ በሚገኝ አንድ ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ አንድ አገልጋይ ቆመና ‹‹ለገጠር አገልግሎት መመዝገብ የምትፈልጉ ....›› የሚል አንድ ማስታወቂያ ተናገረ፡፡ የገጠር ገልግሎት ማለት የከተማ ሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮች ወደ ገጠር መንደሮች እየሔዱ የሚያስተምሩበትና የሚያገለግሉበት የአገልግሎት መስክ ነበር፡፡ ይህ ማስታወቂያ ሲነገር በወቅቱ የሃይስኩል ተማሪ የነበረ አንድ 14 ዓመት ልጅ ተመሥጦ ይሰማል፡፡ ይህ ልጅ የሰንበት ትምህርት ቤት የሕጻናት መምህራን ሆነው ከተመለመሉ ልጆች አንዱ ነበር፡፡ ስለዚህም ወደ ገጠር ሔዶ ለማገልገል ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር ይመዘገባል፡፡


ጊዜው ሲደርስም እንደ ሐዋርያት ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ ገጠር ከሚዞሩት የሰንበት ተማሪዎች አንዱ ሆኖ ማገልገሉን ቀጠለ፡፡ በዚህም ወቅት የጀመረው ሌሎችን የማገልገል ፍላጎት በጣም በመጨመሩ የዩንቨርሲቲ ትምህርቱን አጠናቅቆ በህክምና እስከተመረቀበት ጊዜ ድረስም ይህን አገልግሎቱን አላቋረጠም፡፡ ትምህርቱን ሲጨርስ ግን የህክምና ሙያውን ተጠቅሞ አገልግሎቱን ማስፋት ተመኘ፡፡ ሌሎችን የማዳን ፍላጎቱን ለማርካት ግን የግብፅ ምድር አልበቃችውም፡፡ በአፍሪካ ሀገራትም ለማገልገል ቆርጦ ተነሣ፡፡ የመጀመሪያ ጉዞውንም ወደ ኢትዮጵያ አድርጎ በአሥመራና በደብረ ብርሃንና በአዲስ አበባ እስከ 1966 ድረስ አገለገለ፡፡ ከዚያም ወደ ግብፅ ተመልሶ መነኮሰ፡፡ ከምንኩስናው በኋላም የአገልግሎት ጉዞውን ቀጠለ፡፡ ከአስቄጥስ ገዳም ተነሥቶ ወደ ናይሮቢ ኬንያ ከናይሮቢ ወደ ዛምቢያው ሉሳካ ከሉሳካ ወደ ዚምባብዌው ሐራሬ ከሐራሬ ወደ ዛየር ኪንሻሳ ከኪንሻሳ ወደ ቦትስዋና ከቦትስዋና ወደ ማላዊ ሌሴቶ ከዚያም ወደ ሌሎች ሀገራት.... በአጠቃላይ ወደ 23 የአፍሪካ ሀገራት ተጓዘ፡፡ አብያተ ክርስቲያናትን ገዳማትን መንፈሳዊ ኮሌጆችን አቋቋመ፡፡ በየሀገራቱ ቋንቋዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ መጻሕፍትን ተርጉሞ አስተማረ፡፡ በዐሥራ አራት ዓመቱ በልቡ የተጫረው የመንፈሳዊ አገልግሎት እሳት በብዙ ቋንቋዎች እና ባህሎች ውስጥ እየተቀጣጠለ ብዙ አፍሪካውያንን ወደ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እንዲገቡ አደረገ፡፡ የካይሮ ሰንበት ትምህርት ቤት ትንሹ አገልጋይ በፎቶው ላይ የምትመለከቷቸው የዛሬው የየኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን የአፍሪካ ጉዳዮች ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ አንቶንዮስ ማርቆስ ናቸው፡፡

10 comments:

  1. Edmena Tena yistilin!!!! Ewnetegna abat endih yetarike miskirinet yagegnal.


    Haile silassei the debre berhan

    ReplyDelete
  2. ለሰሙ ከሆነ ሀሳብህ አይከፋም፡፡ወርቁን ስናየው ግን በግብፅ ቤ/ክ….
    _ድጓ የለ፣አቋቋም የለ፣ዝማሬመዋስእት የለ፣14ቱ ቅዳሴያት የሉ፣ቅኔ ከነአገባቡ የለ፡፡ መጽሐፍቅዱስ ብቻ--እሱም እኮ ደግሞ 81 አይደለም፡፡እና በዚህ ሁኔታ አንድ የግብፅ ሰንበት ተማሪ ጳጳስ ቢሆን ምን ይገርማል?? የኛ ጳጳሳት እኮ በልመና ተንከራተው ከላይ ያሉትንና በግብፅ ቤ/ክ የማይሰጡ ጉባኤያትን ቢችሉ ጠንቅቀው ካልቻሉም ቢያንስ በጉባኤው አልፈው ነው የሚጰጵሱት፡፡ማንን ለማስቀናት ነው??
    _ስለዚህ ከቻላችሁ ስለነዚህ ስለራሳቸው መናገር የማይፈቅዱ ብፁዐን አባቶቻችን ንገሩን፡፡የግብጽ ጳጳሳትንማ ራሳችን ከየጎግሉ እየዳሰስን ማየት እንችላለን፡፡አጓጉል የእስክንድርያን ወንበር ናፋቂ እየሆናችሁ ያሳለፍነውን ያሉባልታ ዘመን በመመለስ በታዋቂ ግብጻውያን ጳጳሳት ጀርባ ተቆርቋሪ መስላችሁ አትቆርቁሩን፡፡
    _እኛም አባቶች አሉን፡፡ካልሞቱ በቀር በጎ ጎናቸው የማይነሳ፡፡እንደነ አቡነ ቄርሎስ አይነት ዳገቱን በበቅሎ፣ገደሉን በወሳንሳ እየወጡ የሚሰብኩ--ያውም ምስጢሩን ከድጓና ከወንጌል እየጠቀሱ የሚያበጥሩ!!
    _የጥንተ-አብሶ አማኞቹን፣ የ1600 አመታት ሞግዚቶቻችንን እና የዴር ሱልጣን ተቀናቃኞቻችንን በማወደስ አፋዳሽ አትሁኑብን፡፡ጵጵስና ከፈለጋችሁ አብነት ት/ቤት ገብታችሁ ተማሩ::እንጅ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስም ከሰንበት ት/ቤት በአንድ ወደ ጵጵስና መራመድ አይሆንም፡፡ሥርዓቱ አይፈቀድም፡፡በመማር እንጅ በጥራዝ ነጠቅነት በሚጠቀስ የግእዝ ንባብ ጵጵስናን ሕጋችን አይፈቅድም፡፡
    _የሩቁን ከመናፈቅ የቅርቡን ተማሩ፡፡የኢ/ያ ጵጵስና በአቋራጭ አይገኝም!! ስለ ግብጽ ቤ/ክ ለማወቅ ነጋሪ አያሻንም፡፡ኤቢሲዲ መቁጠር በቂ ነው--እድሜ ለጎግል፡፡ይልቅስ ከበረታችሁ ስለራሳችን አውሩ፡፡አታሳንሱን!!ግእዙን አንብቦ፣ተረድቶ፣ተርጉሞ፣አብራርቶ ማቅረብ ሲያቅታችሁ በግብጽ ኤቤሲዲ ትንጠላጠላላችሁ፡፡20 አመት ለፍፋችሁት ምንም ያላመጣው…እስክንድርያ እናቴ፣ሺኖዳ አባቴ…መዝሙር ቅኝት ቢቀየርልን ደስ ይለናል፡፡ከፋም ለማም ስለራሳችን አባቶችና ስለራሳችን መንበረ-ጵጵስና መነጋገሩ ይሻላል፡፡በቃችሁ!!!

    ReplyDelete
    Replies
    1. Pope Shinoda is the Great leader and the Great Father ..please compare this father with our eotc current fathers...The gap is deep

      Delete
    2. የተሰጠው ሃሳብ አንዳንድ በስሜት የተነገሩ መንፈሳዊነት የጎደላቸው ሻካራ ቃላት ቢኖሩትም ጠጣር ሃሳቦችም ስላሉት ጽሁፉን ስላነበብኩት እኔም ሃሳብ መስጠት ፈለኩኝ::
      1 በግብጽ ቤተ ክርስቲያን አቋቋም ቅኔ ድጓ ቅዳሴ ከነአገባቡ የለም የሚለው ሃሳብ ተገቢና የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን የታደለች መሆን የሚያሳይ ነው:: ወፍ እንደ ሀገሯ ትጮሃለች እንደሚባለው የግብጽ ጳጳሳትን በዚህ መስፈርት ለመገምገም መሞከርም የሚያስኬድ አይደለም:: ከሐዋርያት እስከ early church fathers ፣ ከግሪክ እስከ ሶርያ ያሉ ቅዱሳን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን የምናከብረው በድጓና በአቋቋም መስፈርት አይደለም:: ስለዚህ ከኢትዮጵያ ውጪ ስላሉ ሰዎች ስናወራ ይሄን ጉዳይ መስፈርት ባናደርገው ይሻላል::
      ያስደነቀኝ ሌላ ነገር [መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ] የሚለው አገላለጽ ነው:: አቋቋሙ ድጓው ቅዳሴው የሚያወራው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስን ማወቅ እንዲህ ሲጣጣል መስማት ያሳዝናል:: ቤተ ክርስቲያንን ሳያውቋት ጸረ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነች ለሚለፍፉ መናፍቃንም ዱላ ማቀበል ነው::
      ከዚህ ባሻገር የግብጽ ቤተ ክርስቲያን እንኳን ጵጵስና ንፍቀ ዲያቆን እንኳን ለመሾም የምትወስደው ጊዜና ጥንቃቄ በሚታወቅበት ሁኔታ ይህን መናገር የእኛ ቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ የማመንኮስና የማጰጰስ ሂደት መበላሸት እንድንዘረዝርና እናት ቤተ ክርስቲያናችንንና ቅዱስ ሲኖዶሳችንን እንድንተች የሚገፋፋ ሃሳብ ነው:: ይህን ሃሳብ ይዘን ግን ቀን እስኪወጣ የአሰራር ችግሮች እስኪፈቱ እንጠብቃለን እንጂ የግብጽን ወቅታዊ ሁኔታ ለማሳየት ራሳችንን አንሰድብም:: ሃሳቡን የሰጠውም ሰው ከብስጭት በጸዳ መንፈስ ቢያየው የሚያውቀው እውነታ እንደሆነ ከ አነጋገሩ ብስለት ለመረዳት አያዳግትም::
      በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት እውቀት ብቻ እንኳን ለጵጵስና ለዲቁናም መሾም እጅግ አደገኛና ለቤተ ክርስቲያን ህልውና የሚያሰጋ ነው:: ከላይ ባነበብነው ጽሁፍ ላይም በግብጽ ከሰንበት ትምህርት ቤት ተነስተው ጳጳስ ስለሆኑ ሰው ታሪክ ያወራል እንጂ የኢትዮጵያ በሰ/ት/ቤት እውቀት ብቻ ጳጳሳት ይሾሙ የሚል መልእክት የለውም::
      ማንን ለማስቀናት ነው የሚለው ቃል ደስ ይላል:: ቅዱስ ጳውሎስ [ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ያነሳችሁበት ምክንያት ምንድን ነው] ብሎ ለቆሮንቶስ ምእመናን ይህን ሁሉ ዜማ ፣ ቅኔ ፣ ምስጢር ተሸክመን እንዴት ከሌሎች እናንሳለን ብሎ መቆርቆር ፣ መቅናት ይገባል:: ቤተ ክርስቲያኒቱ ከማንም የማያንስ ይልቁንም የሚበልጥ ሀብት አላት:: ያሳነስናት እኛ ልጆችዋ ነን::
      ከዛ ውጪ ግብጻዊ አባቶች የሰሩትን መናገር ኢትዮጵያውያን ምንም አልሰሩም ማለት አይደለም:: የእኛን አባቶችም እንዘከራለን ፡ ሌሎችንም እናስታውሳለን::
      አዎ ብፁዕ አባታችን ከደዌ ጋር እየታገሉ ፣ በገጠር ተንከራትተው እያገለገሉ ነው:: መጻሕፍትም ጽፈው ለትውልድ አስቀምጠዋል:: ረዥም እድሜ ከሙሉ ጤንነት ጋር ያድላቸው ጻማ ድካማቸው ይደርብን እንጂ ምን ይባላል?
      የሳቸውን ታሪክ መናገር ይገባል፡፡ ይህ ማለት ግን የግብፅ አባቶችን አታንሱ እያልን አይደለም፡፡ Commemorating copts isn't omitting Ethiopians.
      በዚህ ጽሑፍ ላይ የተቀመጠው ሃሳብ ብዙ ሀገራትን እየዞሩ በቋንቋቸው ማስተማር ስለቻሉ አባት ነው፡፡ የእኛ ቤተ ክርስቲያን በቋንቋ ዞሮ በማስተማር ዙሪያ ያለችበት ደረጃ ደግሞ የሚታወቅና ብዙ ምእመናን ወደ መናፍቃን በንጥቂያ እንዲወሰዱ ያደረገ መሆኑን እያየን ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ታሪክ በዚህ ዘርፍ ላለን አገልግሎት እንደማነሳሻ ልናየው የምንችልና እኛም እንዲህ አድርግናል ለማለት የማንደፍርበት ዘርፍ መሆኑ ነው የታየኝ፡፡ ስለዚህ እንኳን ከአኃት አብያተ ክርስቲያናት ከጠላትም አካሔድ ትምህርት ይወሰዳል፡፡
      የጥንተ አብሶ ጉዳይ ላይ ያለን ልዩነት ልክ ነው፡፡ ክብር ይግባትና እመቤታችን ይህ አይነገርባትም፡፡ በአግባቡ ተነጋግረን የኢትዮጵያን ሊቃውንት ከጥንት የተገኘ ትምህርት እንደ ማስረጃ አቅርበን ኢንተር ኦርቶዶክስ ዳያሎግ ላይ ማቅረብና በብዙ ነገር ላይ አንድ ሆነን ሳለ በዚህ ያለን ልዩነት ከጊዜ በኋላ የመጣ እንጂ ከቀደምት አበው ትምህርት ጋር እንደማይሔድ ማስረዳት እንደ ቤተ ክርስቲያን የሚጠብቀን ሥራ ነው፡፡ የዴር ሡልጣን ጉዳይም የሁላችን የእግር እሳት ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ ጽሑፍ ላይ የተነሣው የዞሮ ማስተማር አገልግሎት አርአያነት ያለው ታሪክ ከነዚህ ጉዳዮች ጋር የሚያገነኘው ነገር የለም፡፡ ግብፆች ጨርሶ ስማቸው አይነሣ የምንል ክሆነ ግን ከቅዳሴውና ከስንክሳሩ መጀመር ይኖርብናል፡፡
      ሃያ ዓመት ልፍፋችሁት የሚለው ንግግር ወደ ማኅበረ ቅዱሳን የተቃጣ ይመስላል፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን ‹ሺኖዳ አባቴ እስክንድርያ አባቴ› የሚለው ንግግር ለወጥ ተደረገ እንጂ ‹‹ማርቆስ አባታችን እስክንድርያ እናታችን›› ብለው ሰማዕታት የሆኑ ስንት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት እንዳሉ የነክቡር ጌታው መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬን መጻሕፍት ማገላበጥ በቂ ነው፡፡ ብዙ መጻሕፍትን እና ቅዱሳንን ከግብፅ ናቸው ሳትል በመንፈሳዊ መነፅር ተመልክታ የተቀበለች ቤተ ክርስቲያን ልጆች ሆነን እንዲህ ማለት ያስተሳዝባል፡፡
      እንግዲህ በዚህ ጽሑፍ ላይ ያለችኝ አስተያየት ይቺ ናት፡፡ አልፌ ተናግሬ ካስቀየምኩ ይቅርታ

      Delete
    3. የተሰጠው ሃሳብ አንዳንድ በስሜት የተነገሩ መንፈሳዊነት የጎደላቸው ሻካራ ቃላት ቢኖሩትም ጠጣር ሃሳቦችም ስላሉት ጽሁፉን ስላነበብኩት እኔም ሃሳብ መስጠት ፈለኩኝ:: 1 በግብጽ ቤተ ክርስቲያን አቋቋም ቅኔ ድጓ ቅዳሴ ከነአገባቡ የለም የሚለው ሃሳብ ተገቢና የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን የታደለች መሆን የሚያሳይ ነው:: ወፍ እንደ ሀገሯ ትጮሃለች እንደሚባለው የግብጽ ጳጳሳትን በዚህ መስፈርት ለመገምገም መሞከርም የሚያስኬድ አይደለም:: ከሐዋርያት እስከ early church fathers ፣ ከግሪክ እስከ ሶርያ ያሉ ቅዱሳን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን የምናከብረው በድጓና በአቋቋም መስፈርት አይደለም:: ስለዚህ ከኢትዮጵያ ውጪ ስላሉ ሰዎች ስናወራ ይሄን ጉዳይ መስፈርት ባናደርገው ይሻላል:: ያስደነቀኝ ሌላ ነገር [መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ] የሚለው አገላለጽ ነው:: አቋቋሙ ድጓው ቅዳሴው የሚያወራው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስን ማወቅ እንዲህ ሲጣጣል መስማት ያሳዝናል:: ቤተ ክርስቲያንን ሳያውቋት ጸረ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሆነች ለሚለፍፉ መናፍቃንም ዱላ ማቀበል ነው:
      ከዚህ ባሻገር የግብጽ ቤተ ክርስቲያን እንኳን ጵጵስና ንፍቀ ዲያቆን እንኳን ለመሾም የምትወስደው ጊዜና ጥንቃቄ በሚታወቅበት ሁኔታ ይህን መናገር የእኛ ቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ የማመንኮስና የማጰጰስ ሂደት መበላሸት እንድንዘረዝርና እናት ቤተ ክርስቲያናችንንና ቅዱስ ሲኖዶሳችንን እንድንተች የሚገፋፋ ሃሳብ ነው:: ይህን ሃሳብ ይዘን ግን ቀን እስኪወጣ የአሰራር ችግሮች እስኪፈቱ እንጠብቃለን እንጂ የግብጽን ወቅታዊ ሁኔታ ለማሳየት ራሳችንን አንሰድብም:: ሃሳቡን የሰጠውም ሰው ከብስጭት በጸዳ መንፈስ ቢያየው የሚያውቀው እውነታ እንደሆነ ከ አነጋገሩ ብስለት ለመረዳት አያዳግትም::
      በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት እውቀት ብቻ እንኳን ለጵጵስና ለዲቁናም መሾም እጅግ አደገኛና ለቤተ ክርስቲያን ህልውና የሚያሰጋ ነው:: ከላይ ባነበብነው ጽሁፍ ላይም በግብጽ ከሰንበት ትምህርት ቤት ተነስተው ጳጳስ ስለሆኑ ሰው ታሪክ ያወራል እንጂ የኢትዮጵያ በሰ/ት/ቤት እውቀት ብቻ ጳጳሳት ይሾሙ የሚል መልእክት የለውም:: ማንን ለማስቀናት ነው የሚለው ቃል ደስ ይላል:: ቅዱስ ጳውሎስ [ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ያነሳችሁበት ምክንያት ምንድን ነው] ብሎ ለቆሮንቶስ ምእመናን ይህን ሁሉ ዜማ ፣ ቅኔ ፣ ምስጢር ተሸክመን እንዴት ከሌሎች እናንሳለን ብሎ መቆርቆር ፣ መቅናት ይገባል:: ቤተ ክርስቲያኒቱ ከማንም የማያንስ ይልቁንም የሚበልጥ ሀብት አላት:: ያሳነስናት እኛ ልጆችዋ ነን:: ከዛ ውጪ ግብጻዊ አባቶች የሰሩትን መናገር ኢትዮጵያውያን ምንም አልሰሩም ማለት አይደለም:: የእኛን አባቶችም እንዘከራለን ፡ ሌሎችንም እናስታውሳለን::
      አዎ ብፁዕ አባታችን ከደዌ ጋር እየታገሉ ፣ በገጠር ተንከራትተው እያገለገሉ ነው:: መጻሕፍትም ጽፈው ለትውልድ አስቀምጠዋል:: ረዥም እድሜ ከሙሉ ጤንነት ጋር ያድላቸው ጻማ ድካማቸው ይደርብን እንጂ ምን ይባላልአዎ ብፁዕ አባታችን ከደዌ ጋር እየታገሉ ፣ በገጠር ተንከራትተው እያገለገሉ ነው:: መጻሕፍትም ጽፈው ለትውልድ አስቀምጠዋል:: ረዥም እድሜ ከሙሉ ጤንነት ጋር ያድላቸው ጻማ ድካማቸው ይደርብን እንጂ ምን ይባላል
      የሳቸውን ታሪክ መናገር ይገባል፡፡ ይህ ማለት ግን የግብፅ አባቶችን አታንሱ እያልን አይደለም፡፡ Commemorating copts isn't omitting Ethiopians. በዚህ ጽሑፍ ላይ የተቀመጠው ሃሳብ ብዙ ሀገራትን እየዞሩ በቋንቋቸው ማስተማር ስለቻሉ አባት ነው፡፡ የእኛ ቤተ ክርስቲያን በቋንቋ ዞሮ በማስተማር ዙሪያ ያለችበት ደረጃ ደግሞ የሚታወቅና ብዙ ምእመናን ወደ መናፍቃን በንጥቂያ እንዲወሰዱ ያደረገ መሆኑን እያየን ነው፡፡ ስለዚህ ይህን ታሪክ በዚህ ዘርፍ ላለን አገልግሎት እንደማነሳሻ ልናየው የምንችልና እኛም እንዲህ አድርግናል ለማለት የማንደፍርበት ዘርፍ መሆኑ ነው የታየኝ፡፡ ስለዚህ እንኳን ከአኃት አብያተ ክርስቲያናት ከጠላትም አካሔድ ትምህርት ይወሰዳል፡፡ የጥንተ አብሶ ጉዳይ ላይ ያለን ልዩነት ልክ ነው፡፡ ክብር ይግባትና እመቤታችን ይህ አይነገርባትም፡፡ በአግባቡ ተነጋግረን የኢትዮጵያን ሊቃውንት ከጥንት የተገኘ ትምህርት እንደ ማስረጃ አቅርበን ኢንተር ኦርቶዶክስ ዳያሎግ ላይ ማቅረብና በብዙ ነገር ላይ አንድ ሆነን ሳለ በዚህ ያለን ልዩነት ከጊዜ በኋላ የመጣ እንጂ ከቀደምት አበው ትምህርት ጋር እንደማይሔድ ማስረዳት እንደ ቤተ ክርስቲያን የሚጠብቀን ሥራ ነው፡፡ የዴር ሡልጣን ጉዳይም የሁላችን የእግር እሳት ነው፡፡ ነገር ግን በዚህ ጽሑፍ ላይ የተነሣው የዞሮ ማስተማር አገልግሎት አርአያነት ያለው ታሪክ ከነዚህ ጉዳዮች ጋር የሚያገነኘው ነገር የለም፡፡ ግብፆች ጨርሶ ስማቸው አይነሣ የምንል ክሆነ ግን ከቅዳሴውና ከስንክሳሩ መጀመር ይኖርብናል፡፡
      ሃያ ዓመት ልፍፋችሁት የሚለው ንግግር ወደ ማኅበረ ቅዱሳን የተቃጣ ይመስላል፡፡ ያም ሆነ ይህ ግን ‹ሺኖዳ አባቴ እስክንድርያ አባቴ› የሚለው ንግግር ለወጥ ተደረገ እንጂ ‹‹ማርቆስ አባታችን እስክንድርያ እናታችን›› ብለው ሰማዕታት የሆኑ ስንት ኢትዮጵያውያን ሊቃውንት እንዳሉ የነክቡር ጌታው መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬን መጻሕፍት ማገላበጥ በቂ ነው፡፡ ብዙ መጻሕፍትን እና ቅዱሳንን ከግብፅ ናቸው ሳትል በመንፈሳዊ መነፅር ተመልክታ የተቀበለች ቤተ ክርስቲያን ልጆች ሆነን እንዲህ ማለት ያስተሳዝባል፡፡ እንግዲህ በዚህ ጽሑፍ ላይ ያለችኝ አስተያየት ይቺ ናት፡፡ አልፌ ተናግሬ ካስቀየምኩ ይቅርታ

      Delete
    4. ወንድም AnonymousSeptember 27, 2014 at 2:34 Pm እኔ በቁጭት ስሜት የጻፍኩትን ጽሑፍ በበጎ መንዝረህ ልቤን ስላረጋኸው ምስጋና ይገባሀል፡፡ብዙ ጊዜ ስለ ግብፅ ጳጳሳት የሚጻፉ ጽሑፎች የእኛዎቹን ለማጣጣል ባለመ መልኩ እየሆነ ስለምታዘብ ነው ከላይ ያለውን ሀሳብ የሰነዘርኩት፡፡
      በፊት ለመማማር ይመስለኝ ነበር፡፡ ከጊዜ በኋላ ግን ገደቡን እያለፈና የራሳችንን በየአደባባዩ እያብጠለጠሉ ግብጻውያንን መጥቀስ ጭራሽ ያዋቂነት ማስመሰከሪያ እየሆነ ሄደ፡፡ይሄ ያስከፋኛል፡፡ለዛ ነው ወደ ራሳችን እንመልከት ማለቴ፡፡
      ሀሳቤን 100 % በመረዳትህ ግን ደስ ብሎኛል፡፡ለመናፍቃኑ ዱላ ማቀበል ያልከውንም እቀበላለሁ፡፡ታዲያ የራሳችንን አባቶች በየዓለማዊው ሚዲያ ማጣጣልም ለመናፍቃን በር መክፈት መሆኑን አንዘንጋ፡፡በልክ እንሁን!!
      እንደ አንዳንድ ከራሳቸው ሀሳብ ውጭ የሆነ አስተያየት ባዩ ቁጥር ተናጋሪውን ‘መናፍቅና ተሐድሶ’ በሚሉ ቃላት ለማሸማቀቅ የሚሞክሩ የዋሀን ሳትሆን አስተያየቴን በበጎ ተመልክተህ ለሁላችንም የሚበጀውን በማመላከትህ በድጋሚ ባርኔጣየን አንስቻለሁ፡፡እግዚአብሔር ይስጥልኝ!!አምላከ ቅዱሳን ቅ/ቤ/ክንን ይጠብቅልን!!

      Delete
    5. ውድ anonymous, ስለ ሠጠኸኝ ምላሽ እኔም ባርኔጣዬን አንስቼአለሁ። የብሎግ ላይ እሰጥ አገባ አንዱ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያቃልል እና ችግር ለመፍታት የተፈጠረ ሌላ ችግር መሆኑን ስለማምን እዚህ አዙሪት ውስጥ እንዳልገባ ፈራ ተባ እያልኩ ነበር የጻፍኩልህ። በሠጠኸኝ የጨዋ ሰው ምላሽ ግን እጅግ ተደስቼአለሁ። ቤተ ክርስቲያንን ሰድቦ ለሰዳቢ እየሠጣት ስላለው ዓለማዊ ሚዲያ ስላነሣኸው ነገርም እስማማለሁ። እግዚአብሔር ይሥጥልኝ።
      አሜን ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን!

      Delete
  3. ከሞላ ጎደል በሃሳብህ እስማማለሁኝ.. ግብጻውያኑንን በጅምላ ለማጣጣል ከመሞከርህ ዉጪ… ነገር ግን በአንድ ነገር ላይ ግን መረጃ የጎደለህ ይመስለኛል ወይም የድሮውን ታሪክ ነው የምትነግረን በተለይ.. እንዲህ ያልካት ቦታ..ከሞላ ጎደል በሃሳብህ እስማማለሁኝ.. ግብጻውያኑንን በጅምላ ለማጣጣል ከመሞከርህ ዉጪ… ነገር ግን በአንድ ነገር ላይ ግን መረጃ የጎደለህ ይመስለኛል ወይም የድሮውን ታሪክ ነው የምትነግረን በተለይ.. እንዲህ ያልካት ቦታ..በመማር እንጅ በጥራዝ ነጠቅነት በሚጠቀስ የግእዝ ንባብ ጵጵስናን ሕጋችን አይፈቅድም፡ ይህቺ ትክክል ናት ህጋችን አይፈቅድም ግን .. እየሆነ ያለወስ ምነድነው
    ........የኢ/ያ ጵጵስና በአቋራጭ አይገኝም! ያልከው ግን ህምምም ያሰኛል ያልከው ግን ህምምም ያሰኛል

    ReplyDelete
  4. ከጥሩ ነገር ጥሩ ቁምነገር መማር በሃላችን ነዉ።

    ReplyDelete