Friday, September 12, 2014

ቀኝና ግራቸውን ያለዩ የ21ኛው ክፍለ ዘመን በጎች


 (አንድ አድርገን መስከረም 2 2006 ዓ.ም)፤-
የልዑል እግዚአብሔር ቸርነትና አዳኝነት ከሚገለጥባቸው ምክንያቶች ወይም መንገዶች አንዱ ጠበል ነው፡፡ በገዳማትና አድባራት ቅጽር፣ በቅጽሩ ዙርያና በአካባቢው ሰበካዎች ባሉ የጠበል ቦታዎች በፍጹም እምነት የሚቀርቡ ምእመናን በጠበል እየተጠመቁ ፈውስ ያገኛሉ፤ የእግዚአብሔር ደገኛ ተኣምራት እየተገለጸ ምሕረቱ የተደረገላቸው ሁሉ በየጊዜው ድንቅ ሥራውን እየመሰከሩ ይገኛሉ፡፡
በሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ማጥመቅ የሚችለው የቅስና ሥልጣነ ክህነት ያለው አባት ብቻ ነው፡፡ ቅስና የሌለው ሰው አያጠምቅም፤ አያናዝዝም፤ አይባርክም /ፍት....አን.3 .21/ ቅዱሱን ቅባት መቀባት የሚችለው የክህነት ሥልጣን ያለው ብቻ ነው፡፡ /ያዕ.5÷14/ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ በገንዘብ አይሸጥምና አጥማቂው ካህን መማለጃ መቀበል አይገባውም፡፡ /....አን.7/
‹‹መምህር›› ግርማ ከቅ/ሲኖዶስ ዕውቅና ውጭ በሕንድ በቻይና እና በተለያዩ ሀገራት በፋብሪካ የተመረቱ ለፀጉር ድርቀት መከላከያ የሚሆንን የወይራ ዘይት ‹‹ቅባ ቅዱስ ነው›› በማለት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዐጸድ ውስጥ በማከፋፈልና በመሸጥ ቤተ ክርስቲያንን የንግድ ማእከል አድርጓታል፡፡ ‹‹ርኵስ መንፈስ ያደረባችኹ እገሌ ወይም እገሊት መተት አድርጋባችኹ ነው፤ ›› በማለት እናትን ከልጇ ፤ ዘመድን ከዘመድ ፤ ጎረቤታሞችን እርስ በእርስ በጠላትነት እንዲተያዩ እስከ መጨረሻው እንዳይተማመኑ ፤ የጥርጣሬ መንፈስ በውስጣቸው እንዲያድር በማድረግ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ በአንድ ወቅት ‹‹መምህር›› ግርማ ‹‹እኛ የምንጨነቀው ሰውን ለማዳን እንጂ ለቤተ ክርስቲያን ሥርዐት አይደለም፤›› በማለት በአውደ ምህረት ተናግሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ደሴ አካባቢ በጆንኛ ሞልቶ ያመጣውን መቁጠሪያ ሰዎች እንዳይገዙትና ከስርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ መሆኑን ምዕመኑ በመቃወሙ ‹‹ የዚህ ሀገር ሰውም አጋንንቱም አይታዘዙም›› በማለት በአውደ ምህረት ላይ ተናግሯል፡፡ ሰውየው ለበርካታ ጊዜያት በሕገወጥ መንገድ ሲያጠምቁበት የነበረው የአዲስ አበባው የቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ለአስተዳዳሪው ባለ ሁለት መኝታ የመኖሪያ ኮንዶሚኒየም በአዲስ አበባ ለመግዛት በመስማማት መሆኑን በስተመጨረሻ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህ ሰው እስከ አሁን ምዕመኑ ላይ እያደረሰው ያለው የስነልቦና ጉዳት ይህ ነው የሚባል አይደለም ፤ ቤተክርስቲያኒቱ ላይ እንደ መዥገር በመጣበቅ እያደረሰው ያለው ጉዳትም ቀላል የሚባል አይደለም ፤ ይህን ሰው ስናይ ከ20 ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ፤ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በመገኝት ‹‹አራት ኪሎ ዘንዶ ሊወድቅ ነው ፤ ዘንዶ ሲወድቅ ያየም አይተርፍም ››……ምናምን እያሉ መዓት ሲናገሩ የነበሩት በብዙ ሺህ የሚቆጠር ተከታይ የነበራቸው ፤  በስተመጨረሻ ‹‹እግዚአብሔር አዞኝ ነው›› በማለት ሚስት በማግባት የሦስት ልጆች አባት ለመሆን የበቁት ‹‹ባህታዊ›› ገብረመስቀልን እንድናስታውስ ያደርገናል፡፡  

እጅግ የሚገርመው ‹‹መምህር›› ግርማ እንደሚነዷቸው በሺህ የሚቆጠሩ ግራና ቀኛቸውን ያለዩ የ21ኛው ክፍለ ዘመን በጎች ‹‹ባህታዊ›› ገብረመስቀልንም የሚከተሉ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ለቁጥር የሚያስቸግሩ እጅግ በርካታ ሰዎች ነበሯቸው፡፡ በስተመጨረሻ በ1985 ዓ.ም ግድም ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ ከሁለት ዓመት በኋላ ‹‹ባህታዊው›› ሕዝቡን ወዳልሆነ ጎዳና እየወሰዱ መሆኑን በመገንዘብ አሁን የአፍሪካ ሕብረት የተሰራበት ቦታ የቀድሞ ከልቸሌ ዘብጥያ ወርደዋል፡፡ የእስር ቤቱ ጠባቂዎች ጸጉራቸውን በመላጨት ለተከታዮቻቸው አንዷን ዘለላ በ50ብር ሲሸጡላቸው እንደነበር ይታወቃል፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት ‹‹ባሕታዊ›› ገብረ መስቀል በደብረብርሃን ወይንዬ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን በዓል ለማክበር በሄዱበት ወቅት ከቤተክርስቲያኑ በስተ ደቡብ በኩል ከ20 ዓመት በፊት ቆመው ድርሳን ሲያደርሱ ብርሃን ከሰማይ ግጥም ብሎ በመውረድ ቤቷን ሞልቷት እንደነበር ፤ በማንበብ የጧፍ ብርሃን እንደማያስፈልጋቸው በአንደበታቸው ሲናገሩ ሰምተናል፡፡(እስከ አሁን ‹‹መምህር›› ግርማ ብርሃን ከሰማይ አወረድኩ ሲሉ አልሰማንም ..ወደፊት ግን ላለማለታቸው እርግጠኞች ሆነን መናገር አንችልም ፡፡)

 ይህ ሕገወጥ አካሄድ በዚሁ ከቀጠለ የ‹‹ባህታዊው››ን አንዷን ዘለላ ጸጉር በ50 ብር የገዛው  ሕዝብ አሁን የ‹‹መምህር›› ግርማን በስንት ይገዛው ይሆን…?

ማስተዋሉን ይስጠን
ሰውየው ሕጋዊ መሆናቸውን ለማሳወቅ የበተኑት ከቤተ ክህነት ያልወ ሕገወጥ ደብዳቤ 


የመንበረ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት መልስ 



27 comments:

  1. በመጀመሪያ ደረጃ አንተ ማን ነህ? በድፍረት ዝም ብለህ የምትለቀልቀው ላንተ ደንቆሮ ብለህ ለምትሳደበው ማስተዋሉን ይስጥህ ::በአጋንንት ስም አጋንንት ያወጣል ካሉት ውስጥ ነህ: ስትጽፍ ስምህንና ማንነትህም አሳውቅ አለ በለዚያ ........

    ReplyDelete
    Replies
    1. the guy you have written here is some what the follower or have share... i think so. The blogger wrote based on EOTC norm .......

      Delete
  2. This man girma was in sudan gets medicine there .he is absolutely magician.

    ReplyDelete
  3. yeato girma mekuterya 5 dollar yeshet yele ketsgur yebeza memenanem kemateb yelek mekuterya banget honual

    ReplyDelete
  4. Sema zem beleh seytan yakebelehen atawra bante lay rasu telek metfo menfes ale bemejemeria esun asweged

    ReplyDelete
  5. Thank you guys for sharing this information .I know him well .he is magician he also thought to getachew dony girum and abune yakob of south Africa. Be carful everyone .

    ReplyDelete
  6. Egziabher yestelne Ye swizerland ehzbe yehenen tshufe yemyanbete lela zede yefelge sele Egziabher belachu enzhe yalew hezbe gera gebetotal EGZIABHER MASETWALUN Endestachu Tsleyulachu . Ezhe asetyayet yemtesfu tekmegnch enante eko hayimanote yelachume birr ena zenan new yemtefelgute .

    ReplyDelete
  7. ye egzeabheren sera yemetekawem ante man neh...

    ReplyDelete
  8. የዚህ ሰውዬ የማጭበርበር ሥራ እንደቀጠለ ነው፣ ዛሬም በስዊዘርላንድ ላይ ይሄኛው ስሙ ሰይጣን ነው ይሄኛው አጋንንት ነው፣ ይሄኛው ይሄዳል ይሄኛው አይሄድም፡ እናት ላይ ካለ ልጅም ላይ ይኖራል ኑና ላስወጣላችሁ በዚህ ደግሞ ዣንጥው ተዘቅዝቆ የሚስኪኑ ገንዘብ በፈቃዱ ይበረበራል እንዲህ አይነት የዘመናችን ቀማኛ ዘራፊ እኔ ነኝ ተዓምራትን እየሰራሁ ያለሁት በማለት የእግዚአብሔርን ክብር እንኳን አንዴም የማይናገር የዘመናችን ቀማኛ አጭበርባሪ ስለሆነ ምዕመናን እባካችሁ እራሳሁን ጠብቁ ከእንዲህ ዓይነቱ ዘራፊ
    http://www.soderetube.com/watch.php?vid=95936a4eb

    ReplyDelete
  9. Yegermal eko ye swizerland Betekirestyan ( Memher german yasetengedchu Be Ethiopia Kiduse Sinoduos yemetmra nech gen ??? Le Swizerlad hezbe yemelu Aba Hiyelgeyorges ersachu man nachuna ? Yetgau serate Betkeristyan senurchu new ye Derge wetader ahunme ke jemerchu layeker lezhe Melkuse negn baye besew sende erson debko yemnre tarken Estye Agaltu . Hezbun adenute Egziabher Amelake Yetebtenun hezbe yemesbesb Abat Yametalne .

    ReplyDelete
  10. መላከ ሰላም ዘላለም እሰይ ቃለምልልስ በ አቢሲኒያ ሬድዮ

    http://youtu.be/MX-6v7Y-sMM

    ReplyDelete
  11. Amenzera twelede meleketen yeshale! Thank you ! Andadirgen.

    ReplyDelete
  12. እውነትም አንድ አድርገን...
    በክርስቶስ ሥም መለያየት የለም፤አልነበረም።ነገር ግን ሾኻቸውን የማያሳዩ ተንኮለኞች የሚያውቃቸው እስኪመጣ ድረስ በተንኮል የደም-አበላ እንደተለቃለቁ ይኖራሉ።እነዚህም"አንድ አድርገን" የሚሉ ተኩላዎች፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን መንፈሳዊ ካባ ለብሰው ዛሬ ያላለያዩት የኢትዮጵያ ዖርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሉም።ዛሬ ደግሞ የአባታችንን የመምህር ግርማን መንፈሳዊነት እንደ ባሕታዊ አባ ገብረመስቀል ለማርከስ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፤ሁሌም ግን መጥፊያቸውን እንዳዘጋጁ እየተጋለጡ ይገኛሉ።እነማን በእርኩስ መንፈስ በብዛት ተይዘው እንደሚፈወሱ ያደባባይ ሚሥጥር ሆኖ ሳለ "ከዛሬ-ነገ እንጋለጣለን" ብለው በመስጋት ካህናት ሳይቀሩ እንኳ፣የተወታተበ ረቂቅ ተንኮል ሲሸርቡባቸው በእኛው ዘመን አይተናል።የሚጠብቃቸው መድኃኔዓለም ግን የት ዬዶ?እኛም ለአባታችን መላዕከ መንክራት ግርማ ወንድሙ ዕድሜና ጤና አብዝቶ ይሰጣቸው ዘንድ ምንጊዜም በፀሎት እናስባቸዋለን፤አሜን።

    ReplyDelete
  13. በመጀመሪያ አንተ ማነህ በድፍረት ተናግረህ የምትፈረድ ማነው ፈራጅ ያረገህ?? የሚፈርድ ጌታ እርሱ ክርስቶስ እያለ

    ReplyDelete
  14. ይህን ጠንቋይ ግርማን እነ አንዶዓለም ዳግማዊ ዳላስ ሚካኤል ሊያስመጡት ሂደት ላይ ናቸውና እባካችውን ህዝቡም ካህናቱም ስህተት ውስጥ ገብተዋልና ለህዝቡ እውነቱን ነገሩት

    ReplyDelete
  15. seweyew GErami new..... one of multi millioner in ethiopia

    ReplyDelete
  16. Egziabeher Hagerachenenena Betkersteyanachenin Yetebikelen Amenn!!!
    Minew Hizibu Alastewel Ale Begedam Betsebelu Bota Senet Teamer Eyetaye Ayedel Ende Lik Ende Bahatawi Gebremeskel kihenetachewenem Balawek leblena memher GERMAN Endhi Mektelachew Migermew Atemaki Ye EGZIABEHER sew Yesadebal Ende??? Enzhi Ethiopiawayanoch Shokakoch Belew Beawede Mehert Lay Mesadebachew Lemin Yihon? Besewiz Ayetenal Esachew Yasechohalu Andand Geleseboch Zanetila Zekizikew Misekinun Hezib Genzebun Yelkemalu Ewenetawes Yihe Ayedel Ere Ye Tewahedo Lij lib Letelew Yegebal Hulachen Nekiten Entebik Besime Yemetaluna Yetebalewen Lenastewel Gid Yelenal Migermew Bekirebu Wede GERMEN Kasil Akebabi Endemimetu Be FB post eyetederege New Egziabeher Betleyaye Menged Bezu yastemerenal Yemekrenal Egna gin Libachen Dendenoal EGZIABHER YERDAN amen::

    ReplyDelete
  17. Egziabhere lenante Mastewal Yistachihu.

    ReplyDelete
  18. የሥላሴን ስም ጠርተው፤ የጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርቶስን ስም ጠርተው፤ የቅድስት ድንግል ማርያምን ስም ጠርተው፤ የቅዱስ ሚካኤልን እና የቅዱስ ገብርኤልን ስም ጠርተው አጋንንትን በሲወል እሳት ውስጥ እንዲታሰር አደረጉ እንጁ ምን በደሉ። ይህ ሃይል የስላሴ ነው፤ የመምህር ግርማ አይደለም። እሳቸውም የእኔ ሃይል ነው ብለው አላሉም።
    የኦርቶዶከስ አባቶቸ የሚሉት አይገባኝም፤ ለምን ለመምህር ግርማ ይህ መንፈስ ቅዱስ ሃይል ተሰጣቸው የሚል ቀናት ከሆነ ጥሩ ነው፤ በመንፈስ ቅዱስ ስራ ቅኑና እናንተም ብቁ ሁኑ።
    እስኪ ጌታችን እየሱስ ክርቶስ ያለውን እንመልከት፤ የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 17 14-21 እንዲህ ይላል "ጌታ ሆይ፥ ልጄን ማርልኝ፥ ወደ ደቀ መዛሙርትህም አመጣሁት ሊፈውሱትም አቃታቸው አለው። ኢየሱስም የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ፥ እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደዚህ ወደ እኔ አምጡት አለ። ኢየሱስም ገሠጸው ጋኔኑም ከእርሱ ወጣ፥ ብላቴናውም ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ተፈወሰ። ከዚህ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀረቡና። እኛ ልናወጣው ያልቻልን ስለ ምን ነው? አሉት። ኢየሱስም። ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ። ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም። ይህ ዓይነት ግን ከጸሎትና ከጦም በቀር አይወጣም አላቸው።"
    ተመሳሳይ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ይመልከቱ፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕራፍ 6፡ 10-12 ፤ 1ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ 4፡ 1-11 ።
    ስለዚህ እኔስ ጠላቴ ሰይጣን በሲወል ሲታሰርልኝ ማየት ደስ ይለኛል። እሰየው እልልልልል የጌታየ የፈጣሪየ የሥላሴ ክብር ይሁን፤ የጌታየ የእየሱስ ክርስቶስ ክብር ይሁን፤ የወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያም ክብር ይሁን፤ የቅዱስ ሚካኤል እና የቅዱስ ገብርኤል ክብር ይሁን ። መምህር ግርማን የእድሜ ባለጸጋ ያድርግልን። ዛሬ በፈረንጅ ሃገር አለውን አጋንንት ሲያሰድዱ በኢትጵያ ምድር ያለው ማንሰራራቱ ልቤን ያቃጥለዋል። እባካችሁ ተባብረን ወደ ቤቱ ወደ ሲዖል እናስገባው። መምህር ግርማ እየሰሩት ያለው ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክረሰቲያን በ ዓለም ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። እግዚአብሔር በመረጠው ላይ እየዋለ አለማቸንን ከሰይጣን ስራ ይጠብቅልን። አሜን።

    ReplyDelete
  19. Begoch Tebelu ! Min Yishalal...Hizbu Altemarem. Yih sew bizu sewochen begenzeb Seitanawi tibebun Aseltinoal. Ebakachihu Mereja Sebsibachihu Sefa yale Timihert Situ ! Begetachin Sigana Dem Ayaminim. Yezih ena meselochu ken dersual. Kelay Jemiro Yiteregal !

    ReplyDelete
    Replies
    1. "Begetachin Sigana Dem Ayaminim"? What kind of liar are you? You and your likes including this blog disseminate lies and confuse people. I have, my self, followed memhir's sermons on the importance of the holly Eucharist.

      Delete
  20. ምንድን ነው ዝም ብሎ ማውራት ማንም ምን ቢል እግዚአብሄር ማዳኑን አያቆምም ደግሞም ክፋት የሚያወራ የክርሥቶሥን ድንቅ ሥራውን ማዳኑን የሚቃወም ሠይጣን እና ሠራዊቱ ናቸው እግዚአብሄር ለአባታችን እድሜ እና ጤና እንዲሁም ፀጋውን ያብዛላቸው

    ReplyDelete
  21. https://www.youtube.com/watch?v=iZ7HGuHnecA&list=PL3MhHT8QiVnzBFZiOQBsDmGYI1mAP84Df&index=73

    ReplyDelete
  22. Yememhir Girman Programoch Papasat Barkew sikeftu ayechalehu. Menfesawi bayhonu papasatu endet esachew gar yehedalu. Lemisale Bitsu'e abune Estifanos (Yejimaw yeneberut) Andu nachew. Lejizh melseh mindenew?

    ReplyDelete
  23. "(እስከ አሁን ‹‹መምህር›› ግርማ ብርሃን ከሰማይ አወረድኩ ሲሉ አልሰማንም ..ወደፊት ግን ላለማለታቸው እርግጠኞች ሆነን መናገር አንችልም ፡፡)" For God's sake, do you not have any sense of fairness?... how can you really accuse someone on what he did not say but you expect he might say in the future?

    ReplyDelete