Sunday, September 21, 2014

ከእሳት የተረፉ ቅርሶች

አንድ አድርገን መስከረም 12 2007 ዓ.ም


የመሐል ዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የተተከለው 1292.. ሲሆን በርካታ ጥንታውያን ስዕላት፣የብራና መጻሕፍትና ሌሎች ቅርሶች የሚገኙበት ቤተ ክርስቲያን ነው። ቤተ ክርስቲያኑ 1986-1989.. እድሳት ተደርጎለት 1989 ጀምሮ ሙሉ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።


ቤተ ክርስቲያኑን ሙሉ በሙሉ ያወደመው እሳት ባልታውቀ ምክንያት የተነሳው የካቲት 5 ቀን 2002 .. ነበር።  እሳቱ ቤተ ክርስቲያኑን ሙሉ በሙሉ ያወደመ ሲሆን አብዛኞቹ የቤተ ክርስቲያኑ ጥንታዊያን የብራና መጻሕፍት እና ቅርሶች ያሉበት ዕቃ ቤት ግን ምንም አደጋ አልደረሰበትም። ታቦታቱም ምስጢራዊ በሆነ እሳት በማይደርስበት ቦታ ተቀምጠው ስለነበር ቃጠሎ አልደረሰባቸውም ።ጽላቶቹ ከቤተመቅድሱ ስር ባለ እሳት በማይደርስበት ቦታ ተቀምጠው ስለነበር የካቲት 7 ቀን 2002 .ም ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ተገኝተዋል።  የዚህን ቤተክርስያን ታሪክ ፤ ውስጡ ያሉትን ከእሳት የተረፉ ቅርሶች ፤ ብታውቋቸው ጥሩ ነው ብለን ስላሰብን የቤተክርስያኑ ሰበካ ጉባኤ ያዘጋጀውን ‹‹የገዳም ዘጌ አጭር ታሪክ ለታሪክ አጥኝዎች የተዘጋጀ›› መፅሐፍ በpdf አቅርበንላችዋል፡፡

አቡነ በትረማርያም በህይወት ሳሉ ንጉስ አምደ ፅዮን የሰጣቸው ስዕለ ማርያም 
ሲመለከቷት አይኗ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አብሮ የሚዞር የምትንቀሳቀስ ምትመስል




መቅረዞች፤ የአፄ ዘርአይያቆብ የስጦታ የብር መሶብ ወርቅ ፤
የአፄ ይኩኖ አምላክ የስጦታ ዘውድ(1270-1285እ.ኤ.አ)  
ትልቅ በብራና ላይ የተፃፈ ገድለ ጊዮርጊስ በግዕዝ የተፃፈ ሆኖ 
የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋድሎ ስዕላዊ መግለጫ በመስጠት የሚያሳይ



ይህን መፅሀፍ ፖስት ያደረግንበት ምክንያት

    • የዘጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወበትረማርያም ጥንታዊ እና ታሪካዊ ገዳም የውድና ብርቅዬ ቅርሶች ባለቤት በመሆኑ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር አጥኝዎች  ታሪክና ቅርሶች እውነተኛ መረጃ ለመስጠት
    • በገዳሙ ተጋድሎ ሲያደርጉ በዘጌ ስለነበሩ ቅዱሳን ተግባራ እና እሴቶቻቸውን ለመጭው ትውልድ የማተላለፍ ኃይማኖታዊ ግዴታችንን ለመወጣት
    • የገዳም ዘጌ አባት ስለሆኑት ቅዱስ አባት አቡነ በትረ ማርያም የህይወት ታሪክ ወይም ገድል ፍንጭ ለመስጠት 
    • መተጨማሪ በየደብሮቻችን ያሉትን አባቶቻችን ያቆዩልንን የቤተክርስያንን ቅርሶች ይህ አግዚአብሔር በተአምሩ ከእሳት ያተረፈልንን ቅርሶቻችንን በመመልከት የተለየ ትኩረት እንድንሰጣቸው ለማድረግ
    • በአሁኑ ሰዓት እየተሰራ ላለው ቤተ ክርስያን የበኩልዎን አስተዋፅዎ ያደርጉበታል ብለን የቤተክርስያኑን ታሪክ ወደ pdf ቀይረን አዘጋጅተንዎለታል፡፡




                                 


‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስያንን ይጠብቅ››

2 comments:

  1. አንድ አድርገን እ/ብሔር ይስጣችሁ፡፡ አንብቤዋለሁ፡፡ንባቡ (የግእዙ) ስህተቶች አሉበት፡፡ ልጠቁም…
    -ወእምዝ “አነፀ” የሚለው በገጽ-6 የሚገኝ ንባብ…ወእምዝ ሐነፀ…ተብሎ ቢስተካከል
    -“ኤሊያስ” የሚለው በገጽ-8 የሚገኝ ንባብ…ኤልያስ… ቢባል
    -ገጽ-19 “ንቅድም ዜና ታምራቲሁ” የሚለው…ናቅድም ዜና-ተአምራቲሁ….ቢባል
    -በገጽ-19 “ይሀሉ” የሚለው…የኀሉ….ቢባል
    የቀና ይሆናል፡፡በተረፈ ለዚህ ገዳም እኔም የምችለውን ለማድረግ አላመነታም፡፡

    ReplyDelete
  2. ማንን እንመን እንግዲህ የቲፎዞ አይነት አደረጋችሁት እመቤቴ እውነቱን ታሣውቀን አሜን

    ReplyDelete