Monday, September 30, 2013

‹‹የበደልናትን ቤተክርስቲያንን እንክሳለን ፤ ይዘን የወጣነውን ህዝብ መልሰን እናመጣለን ፤ ላጠፋነው ጥፋትም ቤተክርስቲያኒቱ ይቅርታ ታድርግልን›› ተሀድሶያውያን


ከእንቁ መጽሄት እንዳገኝነው
(አንድ አድርገን መስከረም 20 2006 ዓ.ም)፡- ጉዳያቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ተይዞ በመታየት ላይ የሚገኝው የበጋሻው ደሳለኝ እና የያሬድ አደመን ጉዳይ በእርቅ መንገድ መፍትሄ እንዲፈለግለት በመንቀሳቀስ ላይ የምትገኝው ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ መሆኗን ከቤተክህነት አካባቢ ያገኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡  መረጃው እንደሚያመለክተው በጋሻውና ያሬድ አደመ ‹‹የበደልናትን ቤተክርስቲያንን እንክሳለን ፤ ይዘን የወጣነውን ህዝብ መልሰን እናመጣለን ፤ ላጠፋነው ጥፋትም ቤተክርስቲያኒቱ ይቅርታ ታድርግልን›› ማለታቸውና እርቁን መፈለጋቸው ታውቋል፡፡

ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ የማስታረቁን ተግባር እንደጀመረች እና እነ በጋሻው ደሳለኝን ወደ ብጹእ አቡነ ገብርኤል የሲዳማ ፤ ጌዲኦ ፤ አማሮ፤ ቡርጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዘንድ በማቅረብ እግራቸው ላይ ወድቀው ይቅርታ እንዲጠይቁ አድርጋለች ተብሏል፡፡ ብፁእነታቸውም ‹‹እኔን የሰደባችሁኝ ቢሆንም የተሰደበችው ግን ቤተክርስቲያን ናት ቢሆንም በግሌ ይቅርታችሁን እቀበላለሁ ፤ ጉዳዩ በሲኖዶስ የተያዘ ስለሆነ ግን ውሳኔውን ከወደላይ ጠብቁ›› በማለት መልስ የሰጡ መሆኑም ታውቋል፡፡
ዘማሪት ፋንቱ የማስታረቅ ጥረቷን  በመቀጠል እነ በጋሻው ወደ ብጹዕ አቡነ ሉቃስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ  ያቀረበች ሲሆን ፤ አቡነ ሉቃስም ‹‹ሰው ይቅርታ ሲጠይቅ እምቢ አይባልም ፤ ይቅርታን መግፋት ተገቢ አይደለም ፤ ሆኖም ወደ መድረኩ ስትመጡ ጉዳያችሁ አስቀድሞ በሲኖዶስ የተያዘ በመሆኑ  ትክክለኛውን ምላሽ ከዚያ ያገኛል፡፡›› የሚል ምላሽ ሰጥተዋቸዋል፡፡
በጋሻው በብጹዕ አቡነ ገብርኤል ደብዳቤ ፊርማ ‹‹ሕገ-ወጥ ሰባኪያን ናቸው›› በሚል በእርሳቸው አሕጉረ ስብከት የወንጌል ማስተማር ስራ እንዳይሰሩ ካገዷቸው በኋላ በሀዋሳ ግጭት መከሰቱ የሚታወስ ነው፡፡ ይህንኑ ጉዳይ የሚያውቁና በቅርቡ የማስታረቅ ሂደት መጀመሩን የሰሙ ወገኖች ‹‹ችግሩ በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶ ወደ ሲኖዶስ የተመራ በመሆኑ በእርቅ ሊፈታ የሚችል አይደለም›› በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
በአዋሳ በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት የተደበደቡና ፤ የታሰሩ ስላሉ ጉዳዩ በቀላል መታየት እንደሌለበት የሚያስጠነቅቁ የቤተክርስቲያን ሰዎች አልጠፉም፡፡ በዘማሪት ፋንቱ አማካኝነት እየተመራ ያለው እርቅ የማፈላለግ ተግባር እነ በጋሻውን ከሚቃረኗቸው ሰባኪያንና ዘማሪያን ጋር አቅርቦ ከማነጋገር ደረጃ አልፎ ‹‹ሕዝቡንም ይሁን ቤተክርስቲያኒቱን ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ ነን›› እስከማለት ድረስ የተራመደ ነው፡፡
በሰሞንኛ የእርቅ ማፈላለግ ሂደት ከአዋሳ ከተማ የተገኙ ምዕመናን ጭምር ተሳትፎ ያደረጉበት ሲሆን ፤ ሐሙስ መስከረም 9 ቀን 2006 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ሉቃስ ቢሮ ተይዞ የነበረው ቀጠሮ  በጋሻው ደሳለኝ አለመገኝቱ ምክንያት ለመስከረም 21 2006 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ የተያዘ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
የ‹‹አንድ አድርገን›› ሃሳብ

ተሀድሶያውያን ባገኙት አጋጣሚ የነበራቸውን ቦታ ለማግኝት የማይፈነቅሉት ድንጋይ ፤ የማይወጡት ተራራ ፤ የማይገቡበት ቢሮ ፤የማይከፍሉት ዋጋ አለመኖሩን አስረግጠን መናገር እንችላለን፡፡ ይህ ጉዳይ እርቀ ሰላም የማውረድ እና ያለማውረድ ጉዳይ አይደለም ፤ ቤተክርስቲያን አንድም ሰው እንዲጠፋባት አትፈልግም ፤ ሰዎቹ ቀድሞም ከእኛ ዘንድ አልነበሩም ፤ አይን ባወጣ በክህደት ጎዳና ነጎዱ በአንድም በሌላም  መንገድ የቤተክርስቲያኒቱን አስተምህሮ በማጣመም እና በመበረዝ በርካታ ደጋፊዎችን በማፍራት በርካታ ጉዳቶችን ምዕመኑ ላይ እና ቤተክርስቲያኒቱ ላይ አደረሱ ፤ የምንፍቅና እና የክህደት ትምህርታቸውን በመጽሀፍቶታተቸው ፤ በሲዲዎቻቸው እና በተለያዩ መናፍቅ መናፍቅ ከሚሸቱ ብሎጎቻቸው ማር የተለወሰ መርዛቸውን ሲረጩ ከርመው ካበቁ በኋላ ያሉበት ጎዳና የት እንደሚያደርሳቸው ፤ የቆሙበት ቦታ የት እንደሚወስዳቸው ሲገነዘቡ ፤ ‹‹እርቅ›› ብሎ መምጣት አግባብ መስሎ አይታየንም ፡፡ ቤተክርስቲያን ለመናፍቅ ፤  ለከሃዲ እና ለእናት ጡት ነካሽ ይቅርታ አታደርግም አይደለም ፤ ነገር ግን አካሄዱ ጉዳያቸው በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶ ፤ ስራቸው ተመዝኖና በቅዱስ ሲኖዶስ መክሮበት ከሚሰጠው ውሳኔ በኋላ እንጂ ጉዳያቸው እየታየ ባለበት ሰዓት ‹‹እርቅ›› ብሎ መነሳት በአምስተኛው ፓትርያርክ ሞት የተነሳ የተስተጓጎለውን መዝገብ ዳግም እንዳይነሳ የማድረግ ሃሳብ የማስቀየስ ሥራ መስሎ ይታየናል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግራና ቀኛቸውን ያልተመለከቱ በርካታ ምዕመናን በመያዝ እሁድ ጠዋት ጠዋት ቤተክርስቲያን በማስቀደስ ከሰዓት ከሰዓት አዳራሻቸው እንደ መናፍቃን እያዘለሏቸው በሚገኙበት ሰዓት መሆኑም መዘንጋት የለበትም ፡፡ ‹‹ምንፍቅናን ይቅርታ ይመልሰው ይሆን!››


የአንድ ሰው ሃሳብ

ምናልባትም ሌላኛው አማራጫቸውና ቤተ ክርስቲያኒቱን ዳግም ለማመስ የተዘጋጁበት መንገድ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡ ጥንተ ምንፍቅናን ያስተዋልን እንደሆነ መልኩንና ስልቱን መሰል በሆኑና በተለያዩ መንገዶች በመቀያየር ቅድስት  ቤተክርስቲያንንና ልጆቿን ሲፈታተትንና ሲነጥል ኖሯል፡፡ እነዚህን ወገኖች በሰብአዊነታቸው መቼም አንጠላቸውም፡፡ ድርጊታቸውንና የልብ ክፋታቸውን ግን አጥብቀን እናቃወማለን፡፡ ለይቅርታ መዘጋጀታቸውም እውነት ከልብ ከሆነ ከዚሁ አንጻር መታየት ያለበት ሲሆን ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ግን ይጠብቀናል፡፡ ያም አስቀድሞ ያጠፉትን ጥፋት መመልከት፣ መመዘን፣ መመርመር፣ መወሰን፡፡ ያስተማሩትን ትምህርት፣ የዘመሩትን መዝሙር፣ የጻፉትን መጽሐፍ …. እያንዳንዱን ነጥብ ተመልክቶ ማንነታቸውን ለሕዝበ ክርስቲያኑ ማሳወቅ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል፡፡ ይህ ሲሆን የሚኖራቸው ምላሽና አሁንም ድረስ እየተጓዙበት ያለውን መንገድ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ለማድረግ ያላቸውን ቀና መልስ በማጤን ለአሁኑ ይቅርታቸው ሌላ ውሳኔ ይዘን መጠበቅ ይኖርብናል እንጂ በምንወዳትና በምናከብራት ዘማሪት ፋንቱ ወልዴ በኩል ስለመጡ የሚታለፉበት ሞኝነት ሊኖር አይገባም፡፡ የተሰደቡት  አቡነ ገብርኤል እኮ አይደሉም፡፡ የተሰደቡት እኮ ጧት ማታ ለቤተ ክርስቲያን ደፋ ቀና ያሉ አባቶችና እናቶች፣ ወንድሞችና እህቶች አይደሉም፡፡ እነዚህ ሰዎች በስብከታቸው እግዚአብሔርን ክብሩን አቃለዋል፡፡ በመጽሐፋቸው በዝማሬያቸው ድንግል ማርያምና ቅዱሳንን ተሳድበዋል ፤ ቤተ ክርስቲያን አዋርደዋል፡፡ ይሄ ጉዳይ ሰብአዊነት ላይ ብቻ ትኩረት ተሰጥቶት በይቅርታ እንደዘበት የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም፡፡ ይቅርታም እኮ ቢሆን ዋጋ ሊከፈልበት ይገባል፡፡ ለአዳም ለጥፋቱ ፍርድ ተሰጥቶበታል፤ ለንስሐውም ካሳ ተከፍሎበታልና፡፡ ስለዚህም ስለመጀመሪያው ምንፍቅናቸውና የተሐድሶ ሀሳባቸው የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ አጥብቀን እንሻለን፡፡ የልብ ንስሐቸው በተግባር ሲገለጥ ደግሞ ለይቅርታ እንቀመጣለን፡፡

23 comments:

  1. The Angry Ethiopian/ቆሽቱ የበገነውSeptember 30, 2013 at 10:04 PM

    I'm not down with this non-sense at all. tehadiso is nothing but a pentae strategy and pentae has no principle ; hate everything about the church , envious about her possessions, rich tradition and her place in Ethiopian history. There is an outside force guiding these kehadis.

    ReplyDelete
  2. ይቅርታ አስፈላጊነቱ አጠራጣሪ አይደለም እኔ የምለው ጊዜው አልፏል፡፡ አዎ እንመለሳለን ካሉ ደግሞ የወሰዳቸው ክፉ መንፈስ ከልቡናቸው መውጣቱን በአባቶች ቀኖና ተረጋግጦ እንጂ ዘማሪ ፋንቱ ስላሸማገለች መሆን የለበትም፡፡ እናከብራታለን እንወዳተ ለን፡፡ ግን በምን መልኩ ጀመረች? እውን ስለቤተክርስቲያን ብላ ወይስ ሸውደዋት ? እርሷን ሰይጣን እባብ እንደተዋሀደና ገነት እንደገባ አዳምንና ሔዋንንና እንዳሳተ ዘማሪ ፋንቱን በመዋሃድ /በሀሳብ፣ በጥቅም፣አለያም ለማኅበረ ቅዱሳን ያላትን ክፋ ጥላቻ እርካታ ልታገኝ/ ወይስ ለሌላ እግዚአብሔር ይፍታው፡፡ በጥቅም በዝና ፣ በውዳሴ ከንቱ ይህንን አደረግኩ ለማለት…… አድርጋው ከሆነ በቅርብ የምታውቋት ወዳጆችዋ ጅማሬሽን ወይም የእርቅ መነሻ ፍላጎትሽን ጠንቀቅ ብለሽ መርምሪው ክብርት ዘማሪት ፋንቱ አንቺ እንኳ ዘመንሽን ሁሉ በቤተክርስቲያን ስታገለግይ ቀይተሽ አነሆ በእግዚአብሔር እርዳታ ልጅሽን ተካሽ እነዚህ ልጆች ያንቺን ልጅ ለተንኮላቸው መሣሪያ እንዳያደርጓትም እርቀሽ አስቢ በጎ የሚመስል ነገር እንዳይሆን ተጠንቀቂ፡፡ …… እናንተ ደግሞ የወሰድነውን ሕዝብ እንመልሳለን ማለትስ ምን ማለት ነው ሣያውቅ ያስከተላችሁት ሕዝብ ፍሬን እኛ ነን ማለታችሁስ የንስሐ አመጣጥ ነውን? ነገስ እርቅ እንቢ ስለተባልን ደግሞ ወደ ሲዖል እንመራችኋለን ልትሏቸው ይሆን? አሁንም ንግግራችሁ ልባችሁን ይገልጣልና « የወሰድናቸውን » ብላችሁ በእግዚአብሔር እጅ ያሉ ነፍሳትን መደራደሪያ ለማድረግ በራሱ ችግር ነው፡፡ እና ልባችሁን አጥሩ ቤተክርስቲያንን አታውኩ ቤተክርስቲያንንና ሕዝቧን እግዚአብሔር ይጠብቃት ዘንድ እወቁ፡፡
    ሁላችንንም ከሠይጣን ሥውር ተልዕኮ በነፍስም በሥጋም ይጠብቀን ይጠብቃችሁ፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. የኔ ሃሳብ የተለየ ነው። እውነት የ አንድነት ብሎግ ጸሃፊዎች ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናችሁ ወይ? ይቅርታ ከጠየኩ እና ከተመለሱ ቤተክርስቲያን ሁሌም ይቅር ለማለት የተዘጋጀች ናት። ይቅር የሚለው እግዚአብሔር ነው። ምን አቃጠላችሁ? እናንተ ውስጥ ያለው መንፈስ የእግዚአብሔር መንፈስ አይደለም። እርሱ ባለበቱ ከፈቀደ ይሆናል። የእናንተ ማንነት ግን ሁሉንም ግራ እያጋባነው። ለነገሩ ይቅርታን የሚቃወም አባቱ ማን እንደሆነ ይታወቃል። ቤተክርስቲያንን በእውነት አትወክሉም የጥፋት ልጆች ናችሁ። ልቦናችሁን ለ ንስሓ አዘጋጁ። ሁለቱም ቡድን ጸቡ የሃይማኖት ሳይሆን እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ የሚል የስጋ ጸብ ነው ያለባችሁ። ስለዚህ ንስሓው ለሁላችሁም መሆን አለበት። ትውልዱን ከቤተክርስቲያን በማራቅ ሰይታንን ተባብራችሁታል። ነገ ደግሞ በዝች በቤተክርስቲያን ላይ ገጀራ ይዞ እዲመጣ ነው እያደረጋችሁ ያላችሁት። እግዚአብሔር ቤቱን ይጠብቅ።

      Delete
    2. ጎበዝ በሃይማኖት ዕዉቀት ያን ያህል ነኝ፡፡ ነገር ግን የሚሰማኝ ይህ ነው፡፡
      መደራደሪያ ይዞ ይቅርታ መጠየቅ ከልብ አይመስለኝም፡፡ ይቅርታው ተቀባይነት ካላገኘ የተወሰዱት ሰዎች እንደተወሰዱ ይቀራሉ ማለት ይመስለኛል፡፡ ይሁን እንጅ ለእኔ የሚጥመኝ ይቅርታውን ያግኙም አያግኙም ስህተት ከነበሩና ስህተታቸውን አምነው ይቅራታ ከጠየቁ ‹‹ የወሰዷቸውን ሰዎች›› መመለስ የቅድሚያ ተግባራቸው ሊሆን ይገባል፡፡
      ተመላሾቹ ይህን ቢመልሱልኝ ደስ ይለኛል ‹‹የወሰዷቸው ሰዎች ን ልንመልሳችሁ ነው ሲሏቸው ምን ይላሉ ካሁን በኋላስ ያምኗቸዋል ወይ መሄድ መመለስ በሰው ፈቃድ ነው ወይ››
      ብሎጉን ለተጠራጠርከው ሰው ልልህ የምሻው ‹‹ያልጠረጠረ ተመነጠረ ›› ነው፡፡ መመለሳቸውን መሻትና መመለሳቸውን መጠርጠር ሁለቱ ይለያያሉ፡፡ ቐደም ጠንቅቀን እናውቀዋለን ያሉትን ቤት ጥለው የሄድ አሁን ተመልሻለሁ ሲሉ በጥርጣሬም ቢሆን መቀበሉ መልካም ለው (ዘመኑን መዋጀት ነውና) የመናፍቃንና ተሃድሶ ሴራ በረቀቀበት ወቅት የዋህ በሆን ልጆችን ማስነጠቅ ነው፡፡ እስከ አሁን ያጣናችው ይበቃልና፡፡
      አመሰግናለሁ

      Delete
  3. I'm not down with this non-sense at all. tehadiso is nothing but a pentae strategy and pentae has no principle ; hate everything about the church , envious about her possessions, rich tradition and her place in Ethiopian history. There is an outside force guiding these kehadis.

    ReplyDelete
  4. The truth has let free every body soon or later.still then could you shut your mouth?no body lesson you the whole world knows about u guys .that church doesn't have enemy from outside.that is you guys don't put your finger to some body else,you need to look your self what else you need what is your vision?God he goon clean his house near future.he gave you a chance to look your self if you don't he goon clean &shut his door behind you PS you not let if you awake?this is your day.tomorrow is not promising for any body,it's beyond our expectations,look at you?take a deep breath and think what you did in the past?God bless you bra.

    ReplyDelete
  5. Woohoo!! I don't trust them !!!!!!

    ReplyDelete
  6. are you sure , you guys do not believe the ethiopian orthodox church should be reformed again because the church is out of apostles teaching. Begashaw is not enough man to change the church . He has no enough church knowledge . He has only talk spirit. In genearl I am a orthodox priest in London and I am struggling to bring reformation in our church.
    it is very soon

    ReplyDelete
  7. ለንስሃ ያብቃቸው...ግን ማንም ኣያምናቸውም

    ReplyDelete
  8. Who are you? you give justice for others! Why you hate the people who tell the real way to God! I wish you God open your heart and mind!

    ReplyDelete
  9. መናፈቃን ከመቼ ወድ ነው ደሞ እንዲህ አይነት ልብ ያገኙት ?እንደተለመደው ቤተክርስትያንን ለማመስ እንጂ ?ሌላው ደሞ ፋንቱ የማን አሽቃባጭ ነች?በቅዱስ ሲኖዶስ የተያዘን ነገር ለመማለድ የምትሞክረው ?

    ReplyDelete
  10. Egziabhear Awaki neaw ewnetegna agelgayochun beQidus menfesu yabertachew:: Amen egnam BeEgziabhear fit honen Ewnetun bicha siga ena dem sayqebaba le me'amenu makireb bilemdibn enitenanetsalen, chigir yalebetim golto yetayal neger gin bezih zemen menfesawi blogochn mayet ena poleticawi tsihufochn manbet be qalat atekakem AND honebn...tilacha!!! ...endinitelala..kezihm belay.. seau yesenakelal...wedemot.. Fitsameyachinin yasamrln! Minale leMe'amenu beye betekrsteanu massasebyaw eyetenegerew yeBetekrsteanin seta-geba badebabay yemiasker Hawaria binoren ena be ye betu be mediawoch nitrk ech! Eyale ke betu ena ke Amlaku yemileyew bikens..man yehon yemitekew? Egziabhear yeLib ena yeMenfesu kenategnoch yadrgen

    ReplyDelete
  11. Guys we never ever trust you, that is " CROCODILE TEARS"

    ተሀድሶያውያን ባገኙት አጋጣሚ የነበራቸውን ቦታ ለማግኝት የማይፈነቅሉት ድንጋይ ፤ የማይወጡት ተራራ ፤ የማይገቡበት ቢሮ ፤የማይከፍሉት ዋጋ አለመኖሩን አስረግጠን መናገር እንችላለን፡፡ ይህ ጉዳይ እርቀ ሰላም የማውረድ እና ያለማውረድ ጉዳይ አይደለም ፤ ቤተክርስቲያን አንድም ሰው እንዲጠፋባት አትፈልግም ፤ ሰዎቹ ቀድሞም ከእኛ ዘንድ አልነበሩም ፤ አይን ባወጣ በክህደት ጎዳና ነጎዱ በአንድም በሌላም መንገድ የቤተክርስቲያኒቱን አስተምህሮ በማጣመም እና በመበረዝ በርካታ ደጋፊዎችን በማፍራት በርካታ ጉዳቶችን ምዕመኑ ላይ እና ቤተክርስቲያኒቱ ላይ አደረሱ ፤ የምንፍቅና እና የክህደት ትምህርታቸውን በመጽሀፍቶታተቸው ፤ በሲዲዎቻቸው እና በተለያዩ መናፍቅ መናፍቅ ከሚሸቱ ብሎጎቻቸው ማር የተለወሰ መርዛቸውን ሲረጩ ከርመው ካበቁ በኋላ ያሉበት ጎዳና የት እንደሚያደርሳቸው ፤ የቆሙበት ቦታ የት እንደሚወስዳቸው ሲገነዘቡ ፤ ‹‹እርቅ›› ብሎ መምጣት አግባብ መስሎ አይታየንም ፡፡ ቤተክርስቲያን ለመናፍቅ ፤ ለከሃዲ እና ለእናት ጡት ነካሽ ይቅርታ አታደርግም አይደለም ፤ ነገር ግን አካሄዱ ጉዳያቸው በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶ ፤ ስራቸው ተመዝኖና በቅዱስ ሲኖዶስ መክሮበት ከሚሰጠው ውሳኔ በኋላ እንጂ ጉዳያቸው እየታየ ባለበት ሰዓት ‹‹እርቅ›› ብሎ መነሳት በአምስተኛው ፓትርያርክ ሞት የተነሳ የተስተጓጎለውን መዝገብ ዳግም እንዳይነሳ የማድረግ ሃሳብ የማስቀየስ ሥራ መስሎ ይታየናል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ግራና ቀኛቸውን ያልተመለከቱ በርካታ ምዕመናን በመያዝ እሁድ ጠዋት ጠዋት ቤተክርስቲያን በማስቀደስ ከሰዓት ከሰዓት አዳራሻቸው እንደ መናፍቃን እያዘለሏቸው በሚገኙበት ሰዓት መሆኑም መዘንጋት የለበትም ፡፡ ‹‹ምንፍቅናን ይቅርታ ይመልሰው ይሆን!››

    ReplyDelete
  12. "እርቅ የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው" ተብሏል እውነት ነው እርቅ ማድረግ የተገባ ነገር ነው፥ ዳሩ ግን እውን ይህ የእርቅ ጥያቄ ከማን ነው የመጣው? እውን ተሃድሶዋውያኑ አዝነው፣ ቤተክርስቲያንን በድለናል ብለው ነው? ወይስ ወይዘሮ ፋንቱ የጠነሰሰችው? ልንመረምረው ይገባል ወይስ እርሷ ለቤተክርስቲያን ተቆርቁራ ይሆን? የሁለት መናፍቃን ከክርስቲያን አንድነት መለየት ደግሞ ቤተክርስቲያንን አያናውጻትም እውነት ቢሆን እኮ ኖሮ ተደራዳሪ ሳያስፈልጋቸው በራሳቸው አባቶች እግር ላይ ወድቀው ይቅርታ ጠይቀው፣ ይቅርታ ሲጠይቁም የጠየቁበትን ምክንያት እና በምን ምክንያት ይቅርታ እንደጠየቁ በትክክል ማስረዳት ይኖርባቸውል።
    እስከምናውቀው ድረስ ከዚህ በፊት በተከሰሱበት የሃይማኖት ሕፀፅ ምክንያን እንደነበረ እናስታውሳለን፣ ነገር ግን እንዚህ ሰዎች ያኔም እንኳን እኛ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊያን ነን ነበር የሚሉት እንደውም የእነሱን ክፉ ሥራ እና ምግባር ያጋለጠውን መምህር ለእስር ተዳርጓል ስማችንን አጠፋ ተብሎ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ጥፋት የለብንም ብለው ሰውን እስከ ማሳሰር ደርሰው ዛሬ ምን መጥቶ ነው ስለምን ብለው ነው ይቅርታ የሚጠይቁት? እላይ እንደገለጽኩት ይሄ ጥያቄ የመናፍቃኑ ሳይሆን የወይዘሮዋ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም ምክንያቱም ሴትዮይቱ በስተርጅና በብዙ ጉዳዮች ውስጥ ተተብትባ አፍቅሮተ ንዋይ ሊገላት ደርሷል አሁንም ለቤተክርስቲያን አስባ ወይም ተቆርቁራ ወይንም ለመናፍቃኑ አስባ ሳይሆን የፈለገችው ነገር ቢኖር እንደሚከተለው ነው:-
    ፩ኛ/ ወይዘሮይቱ ከፍተኛ አፍቅሮተ ንዋይ ስላለባት ከነዚህ ሰዎች ጋር እየዞረች ገንዘብ ማግኘት ትፈልጋለች፥ ነገር ግን ዝም ብላ ከነሱ ጋር ብትሄት እድሜ ዘመኗን በመዝሙር የሚያውቃት ምዕመን አንቅሮ ሊተፋት ነው ስለዚህ ያላት አማራጭ ላስታርቅ ብላ (የትም እንደማይደርስ ስለምታውቅ) እርቅ ወርዷል ብላ አብራ በመዝለል አፍቅሮተ ንዋይዋን ለማርካት።
    ፪ኛ/ እስከዛሬ ድረስ ብዙ ሰዎች በቤተክርስቲያን ሲያቅቋት በዝማሬዋ፣ በአገልጋይነቷ ነበር ነገር ግን ከጥቂት ዓመታት በፊት ይሄ አፍቅሮ ንዋይነቷ በግልጽ ወጥቶባት በርካታ ምዕመናን፣ ዘማሪያት፣ እንዲሁም አገልጋዮች ሳይቀሩ በወይዘሮይቱ ተታለው በርካታ ገንዘብ ወስዳባቸው እምነት አጉዳይ ሆና ተገኝታለች። በርካቶችን አስለቅሳለች አሳዝናለች የገዛ አባቷን ጨምሮ ገንዘብ ወስዶ መካድ፣ እምነት ማጉደል፣ ስለት መብላት የመሳሰሉት እጅግ ዘግናኝ ስራዎችን ስትሰራ ነበር በዚህ ምክንያት ያጣችውን እምነት ማጉደል ለመተካት እና ዳግም ሰው እንዲያምናት ለማድረግ የምታደርገው ሙያ ነው፥ ሙያዋም ከዘማሪነት በተጨማሪ ደምበኛ ቲያትረኛ ነች አስመሳይ ነች ስም መጥራት ስለማፈልግ እንጂ በርካታ ዘማሪያን የዚች የፍቅረ ንዋይ የሰከረች ሴት አዝነዋል
    ፫ኛ/ ሥራ የፈታ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል እንደሚባለው ወይዘሮይቱ ሥራ የሌላት በመሆኗ እራሷን አስታሪቂ ብላ እላይ ታች የምትለው የምትሰራው ስለሌላት ነው። በአሁን ሰዓት በርካታ ችግሮች ቤተክርስቲያን ላይ እንዳሉ ሁላችንም እናውቃለን ከነዚህ ችግሮች ዋነኛው እነዚህ መናፍቃን የሚያደርሱት ውዥንብር እና እሰጣ ገባ ሲሆን ይሄንን ሰላም አውርዶ ምዕመኑ በሰላም በቤተክርስቲያን ገኝቶ አገልግሎቱን አግኝቶ በሰላም ወደ ቤቱ እንዲሄድ ማድረግ እራሱን የቻለ ስራ ነበር። ለምሳሌ በምሥራቅ ሐረርጌ ሃገረ ስብከት ያለው ችግር በእነዚህ ቢጻሳውያን የተነሳ ነው ይህንን መፍታት እራሱ ትልቅነት ነበር ነገር ግን ለራስ ክብር እና ዝና መሮጥ ትንሽነት ነው ብየ አምናለው
    በተረፈ ልቦና ይስጥሽ ገዳም ገብተሽ ቀሪ ሕይወትሽን የበደልሽውን ምዕመን እና እግዚአብሔር ብታገለግዪ ይሻላል እላለው
    ከሚዛን ተፈሪ

    ReplyDelete
  13. can i ask you one thing? who are you in the first place to talk about other sin? tell me you one thing, YOU never do any mistake in your life? if you not, that's a big lie. if you are a true christian, we can tell by your way of talking and the views you have for others. God never hate anyone and he never tells our sin for others. if this happen, no one can come to church to see His face. because we know what did every minute" we not perfect" . but your altitude towards to this guys are the same that the " Ayhudes" have, they were so hateful for people who is above them. look you are talking about Fantu's life, which is not your business. your business must be about you private life,,you will not get any credit form God by finding other sin and let other to judge them. and please before asking people to get in "Neseha", begain your work by cleaning your sin, and pray for others who lost God's way and cry for them to come to the sprite we do have. God has many mercy, he will forgive them if they ask him, and what is our end!
    we never know a thing about tomorrow, we all do have weak side whether we do it in private or in public it doesn't make any difference, it's a sin and God knows it.
    Let's Love each-other!!!! Let's Pray for others!!!!!!!! Let's Pray forgiveness!!! and God will Mercy all!!!!
    Um sure He will!!!!!!! PLEASE WE NEED TO REMEMBER THAT GOD DIE FOR LOVE

    ReplyDelete
    Replies
    1. Dear Hiwotie,
      I can understand your point about loving each other and stand for one another. I totally agree with your point once again. However, what I can't agree stand and wait for this "Bitsasawian" to ruin out our church in the name of LOVE. I can't do that, I will testify what they have done and planing to do in the future. the difference between my and them is big so huge. I know very well that am so sin full, which I always ask God's mercy. However, this people are suppose to be roll model and look what they are doing.
      If anyone see me committed adultery or get drunk, no one would say anything or no one falls because of me. With this people like Fantu and the rest of this people, our mother church gave them a whole lot of place above all of the congregation and imagine one of them committed adultery or get drunk or eat in public on the day of lent (Wednesday and Friday) then every one would say if so and so done this why not me. It's only because they have been telling us not to do it and they are not abide by this church law which will be bad for everyone.
      That's why if they do something wrong we judge them to get it write once again, if we kept quite about that they will continue to do so some of our future generation might think it's the church law to commit adultery or anything they do.
      Fantu for instance has been in this church all of her life, but lately she associate her self with Ato Begashaw and his gangster group, what does she really need from them? think about it. Fantu is in need of money and she will do anything to get that money including being with them as one of them who are trying to ruin our forefathers teaching.
      Are you saying we should just wait and let them do what ever they choose, ruin our way of life? is that really God's way? the gospel say "you die for your faith" if necessary and I can't wait for them do what they were doing in the past.
      We know exactly what she is after trying to reconcile with the public, hell no. . . it's not Fantu's job we have church leaders or fathers out there if this is necessary they would have done this way before, all she need would be cheep popularity, fame and trying to cover what she has been done in the past.
      We should not let her do what she want. Stay out of this !!! if not we will tell the public what she has done, we know you let's not be on the wrong position.
      Stop what you are doing. . .
      መናፍቅ፣ ምንፍቅናውን የሚያቆመው ጴንጤ ሲሆን ብቻ ነው፥ ነገር ግን ተመልሶ የአባቶቹ ልጅ ኦርቶዶክሳዊ ሲሆን ታይቶ አይታወቅም እና
      ወይዘሮይቱን ይቅርብሽ ውርድ ከራስ ብለናል።
      አሻሮሽን ይዘሽ አርፈሽ መቀመጥ ነው፣ አለዚያ ግን ያደረገችውን በሙሉ ጉዷን እንዘረግፈዋለን ስለዚህ ስለስምሽ ብለሽ ከልጅነትሽ እስከ እርጅናሽ ስላገለገልሻት ቅድስት ቤተክርስቲያን ብለሽ ይቅርብሽ። ብዙዎችን ምእመናን አሳዝነሻል ድጋሚ ማንም ባንቺ ባያዝን ይሻላል ወይም መጨረሻው ጥሩ ስለማይሆን ጠንቀቅ ብለሽ ተመላለሺ
      ከድሬደዋ ወደ ዲላ መመላለሱ የትም አያደርስሽም፣ የራስሽን እንጀራ እጋግራለው ብለሽ ከሆነ ቤተክርስቲያናችንን ለቀቅ፣ አነ አቶ በጋሻውን ጠበቅ ብታረጊ የተሻለ ነውና እወቂበት
      እኔው ነኝ
      ከሚዛን ተፈሪ

      Delete
  14. አይ ፋገቱ ወልዴ ይሄ ፍቅ ረ ነዋይ ቤተከርስቲያንን ለመሸጥ አስነሰሳሽ እስቲ እግዚአብሄር ልብ ይስጥሸ

    ReplyDelete
  15. I think their business is almost dead. That is why they are asking mercy. It is clear all songs that were fabricated by those Protestants now a day cheap and unwelcome.

    ReplyDelete
  16. If all of you are belonging to the true Orthodox church ( original church based on our LORD JESUS CHRIST ) Go and read the HOLY BIBLE then you know YOURSELF personaly first then you know how much you need correction before trying correcting/condemning others,even the Bible tells you if you a real christian or not ,GBU ALL

    ReplyDelete
    Replies
    1. የድንግል ልጅ ሇይ ! ዘመኑ ከፍቶአልና አንተ ጠብቅ።

      Delete