(አንድ አድርገን መስከረም 17 2006 ዓ.ም)፡- ቦታው በሶርያ ሀገር ነው፡፡ የቤተክርስቲያኑ ስም saydania ይባላል:: ቤተክርስቲያኒቱ እንደተለመደው የዘወትር ፀሎት ለህዝቡ ፤ ለዓለምም እያደረሰች ባለችበት ሰዓት አንድ ሰው ወደ አንድ መነኩሴ እማሆይ Marina Almaloof ቀርቦ ‹‹ስለት ለመስጠት ነበር እባክዎን
ይሄን ብር ሳጥን ውስጥ ያስገቡልኝ›› ይላቸዋል ፤ በእጅ የያዘውን 160ሳ.ሜ የሆነውን ሻማ ‹‹ይሄን ደግሞ በስዕለ ማርያም ፌት ያብሩልኝ ፤
እኔ በጣም ሰለምቸኩል ነው›› ይልና በፍጥነት ከቤተመቅደሱ ይወጣል ፡፡ መነኩሴዋም ክብሪት በማንሳት ‹‹አቤቱ የሰራዊት ጌታ የዚህን ሰው ስለቱን ተቀበለው›› እያሉ ክብሪቱን ጫሩ ፤ ሻማው ጫፍ አቀረቡት
ሻማው ሳይቃጠል ክብሪቱ ተቃጥሎ አለቀ ፤ በድጋሚ ሞከሩ ሞከሩ ሻማው ባለመቃጠሉ እየተገረሙ ከወደ ቤተክርስቲያኒቱ ደጃፍ ጩህት ተሰማ
መነኩሴዋም ወደ ጩህት ቦታው በፍጥነት ወጡ ፤ ከታች ከበስተመጨረሻ ደረጃው ላይ አንድ ሰው ወድቆ የሞተ ሰው ተመለከቱ፡፡‹‹ ይሄ
አሁን ስለት የሰጠኝ ሰውየ አይደለምን?›› በማለት የተፈጠረውን ሁኔታ ለማስረዳት ስልክ ለአካባቢው ፖሊስ ደወሉ ፤ ፖሊስም በፍጥነት
ቦታው ላይ በመገኝት ነገሩን አጣራ ፤ ሁኔታውን ሁሉ ከመነኩሴይቱ በመጠየቅ ተረዳ ፤ ልጁ ቤተመቅደስ ይዞ ገብቶ እንዲለኮስ የፈለገውን
ሻማ ፖሊስ ተቀብሎ ሲመረምረው በውስጡ ዳይናሜት TNT የተባለ አደገኛ ተቀጣጣይ ፈንጆች የተሞላ ሁኖ አገኝው፡፡ ይህን ያደረገውን
ሰው የሚያውቅ አልተገኝም ፤ ሰውየው በልብ ድካም ነው የሞተው ተባለ ፤ ወላዲተ አምላክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ህዝቧንም
ቤተክርስቲያኑንም በዚህ ተዓምር ታደገች ልመናዋ ምልጃዋ በእኛ ላይ ይሁን አሜን!
ቃለ ሕይወት ያሰማልን ! እንደዚህ ዓይነት ታምር ከሰማን ቆይተን ነበር በርቱ ለእግዚአብሔር ምን ይሳነዋል ገና ብዙ እናያለን ከእናቱ ጋር ብዙ ታምራትን ያደርጋሉ !!!!!!
ReplyDeleteድንግል የኛንም አገር ትታደገን
ReplyDelete