Monday, September 16, 2013

ድንቅ ስራውን መስክሩ





(መስከረም 4 2005 ዓ.ም አዲስ አድማስ ጋዜጣ)፡- በአቃቂ ቃሊቲ፣ በቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ፣ ባለፈው ነሐሴ 23 ቀን በቀስተ ደመና፣ በመብረቅና በነጐድጓድ ታጅቦ ከሠማይ እንደወረደ የተነገረለት መስቀል፣ በጳጳሳት የተጐበኘ ሲሆን፣ ከሁለት ሳምንት በኋላ ለህዝብ እይታ እንደሚቀርብ ተገለፀ፡፡ 

መስቀሉን ከወደቀበት ለማንሳት የሞከረ ወጣት ተስፈንጥሮ በወደቀበት ለ4 ቀን ራሱን እንደሳተ የሚናገሩ የቤተክርስትያኑ አገልጋይ፣ ከምሽቱ 9 ሰዓት ከፍንዳታ ጋር አካባቢው በብርሃን ተሞልቶ ስናይ የእሳት ቃጠሎ መስሎን ነበር ብለዋል፡፡ እያንፀባረቀ በሃይለኛ ግለት ያቃጥል ነበር የተባለው መስቀል፤ በማህበረ ቅዱሳን መሪዎችና በጳጳሳት የተጐበኘ ሲሆን የኢየሱስን ስቅለት የሚያሳይ ወርቃማ ቅርጽ ያለው ነው፡፡ ወደ አቃቂ ከተማ ከሚያስገባው ዋና የአስፓልት መንገድ በስተግራ በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ገላን ጉራ በሚባለው ስፍራ የዛሬ 5 አመት የተቋቋመው የገብርኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ነሐሴ 23 ቀን የክርስቶስ ሰምራ በአለ ንግስ እየተከበረ እያለ ከሌሊቱ 9 ሰዓት የተከሰተው ግርግር ነው የዚህ ሁሉ መነሻ፡፡ ከባድ የፍንዳታ ድምጽ የሰሙ እና የቀስተ ደመና ቀለማትን የተላበሰ ብርሃን የተመለከቱ ነገሩን ከዝናባማው የአየሩ ሁኔታ ጋር በማያያዝ ብዙም ትኩረት አልሰጡትም ነበር የሚሉት የቤ/ክርስትያኑ መጋቢ፤ በነጎድጓድና በኢትዮጵያ ባንዲራ ቀለማት የታጀበ መስቀል ከሠማይ ሲወርድ አይቻለሁ ብለዋል፡፡
 

ከዚያን ጊዜ ወዲህ ባሉት ቀናት መስቀሉን ለማየት ወደ ቤተክርስትያኗ የሚጐርፉ ምዕመናን በርክተዋል፡፡ባለፈው ሃሙስ ከአቃቂ ከተማ በማለዳ ተነስተን ከ2 ሠአታት የእግር ጉዞ በኋላ ከቤተ ክርስቲያኑ ስንደርስ፣ በጥቂት ምዕመናን ተሣታፊነት የእለቱ ቅዳሴ እየተከናወነ ነበረ፡፡ ከቆይታ በኋላ ግቢው ከየአቅጣጫው የመስቀሉን ታሪክ ሠምተው በመጡ ምዕመናን ተሞላ፤ መስቀሉ ከሰማይ ሲወርድ አይቻለሁ የሚሉት መጋቢ ሃዲስ ፍስሃ፣ ስለ መስቀሉ አወራረድ ገለፃ ማድረግ የጀመሩት ከቅዳሴው በኋላ ነው፡፡ ግቢው ውስጥ ከቤተ ክርስቲያኑ ህንፃ አጠገብ መስቀሉ የወደቀበትን ስፍራ እያመለከቱ ይናገራሉ -ቦታው በቆርቆሮ ታጥሮ ድንኳን ተተክሎበታል። መስቀሉ አርፎበታል ከተባለው ስፍራ አፈር እየቆነጠረ የሚቀርብላቸው ምዕመናን አፈር እየተመለከቱ የመጋቢ ሃዲስን ገለፃ ያዳምጣሉ፡፡ ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በአል ነሐሴ 23 ቀን የፀሎት ስርአት ከምሽቱ አምስት ሠአት አካባቢ እንደተጀመረ የሚያስታውሱት መጋቢ ሃዲስ፣ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ አካባቢው በቀስተደመና ብርሃን ደምቆ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ አገልጋዮችና ምዕመናን ለዚህ ልዩ ክስተት ብዙም ትኩረት አልሰጡትም፤ ከዝናባማው የአየር ፀባይ ጋር በማዛመድ አቅልለው ነው የተመለከቱት ብለዋል መጋቢ ሃዲስ፡፡ የቀስተ ደመናው ብርሃን አንዴ ሲደምቅ፣ አንዴ ሲደበዝዝ መቆየቱን መጋቢ ሃዲስ ጠቅሰው፣ ከሌሊቱ 9 ሠአት ንፋስ ለማግኘት በካህናት መውጫ በር በኩል ስወጣ ግን ደብዛዛ የነበረው ብርሃን የበለጠ ደምቆ፣ እንደቀን ብርሃን ወገግ ብሎ ታየኝ ብለዋል፡፡ 

“አሻቅቤ ስመለከት ሠማዩ በነጭ ደመና ተከቦ ተመለከትኩ፡፡ አፍታም አልቆምየ፤ በኢትዮጵያ ባንዲራ ቀለማት የተጠቀለለ አንዳች ነገር በዝግታ ከሠማይ እየተገለባበጠ ሲወርድ አየሁ” ይላሉ መጋቢ ሃዲስ፡፡ከቤተክርስቲያኑ ቤተልሄም አጠገብ ያለውን የአገር አቋራጭ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ተሸካሚ ማማ እያመለከቱ፣ “ከሠማይ እየተጠቀለለ የሚወርደው ነገር ከማማው አካባቢ ሲደርስ ነጐድጓዳማ ድምፅ ማሠማት ጀመረ” የሚሉት መጋቢ ሀዲስ፤ “መሬት ላይ ሲያርፍ በከፍተኛ የፍንዳታ ድምፅ አካባቢውን የእሣት ንዳድ በመሰሉ ብርሃን ሞላው” ይላሉ፡፡ “ቤተልሄሙ ተቃጠለ እያልኩ ብጮህም ድምፄን የሰማ ሰው አልነበረም፤ ለደቂቃዎች ያህል ለሠዎች እንዳይሠማ ሆኖ ታፍኖ ነበር” የሚሉት መጋቢ ሀዲስ፤ “ድምፄ መሰማት ሲችል ግን ፣ ካህናቱ ጩኸቱን ሰምተው ተደናግጠው ወደ ውጭ መጡ” ብለዋል፡፡ አንዳች አደጋ ደርሶ እሳት ተቀጣጥሎ ሊሆን ይችላል በሚል ድንጋጤ ሁሉም እሣቱን ለማጥፋት እንደተሯሯጠ ጠቅሰው፣ ነገር ግን በአካባቢው ከብርሃን በቀር የእሣት ቃጠሎ ማግኘት አልተቻለም ብለዋል - መጋቢው፡፡ 

“አንድ የቤተክርስቲያናችን ወጣት አገልጋይ ወደ ደመቀው ብርሃን ተጠግቶ ለማየት ሞከረ፡፡ አንዳች ነገር ወደ ላይ አስፈጥንሮ መሬት ላይ ጣለው፡፡ ምዕመናን ተደናገጡ፡፡ የኤሌትሪክ መስመር ተበጥሶ ኮንታክት ፈጥሮ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ ነበር ያደረብን” ሲሉም ተርከዋል፡፡ “የወደቀው ወጣት ምላሱ ተጐልጉሎ በወደቀበት ራሱን ስቶ ተዘርግቷል” የሚሉት መጋቢ ፍሰሃ፤ ከወደቀበት በጥንቃቄ አንስተን ፀበልና ቅባ ቅዱስ ብናደርግበትም አልተሻለውም ብለዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ነው ካህናቱ እንደምንም ወደ ብርሃኑ አካባቢ ተጠግተው የተመለከቱት፡፡ እናም በብርሃን የታጀበ መስቀል መሬት ላይ ወድቆ አዩ ብለዋል መጋቢው፡፡ ካህናቱና ምዕመናኑ በአግራሞት ሲመለከቱ ቢቆዩም የእሣቱ ወላፈን ይፋጃል ያሉት መጋቢ ፍሰሃ፤ በርቀት መጐናፀፊያ ተወርውሮበት እንዲለብስ እንደተደረገ ይገልፃሉ፡፡ የተቋረጠው ስርዓተ ማህሌት ከ10 ሰዓት በኋላ እንደቀጠለ የተናገሩት መጋቢ ፍሰሃ፣ በካህናቱ ትዕዛዝ ጠዋት 12፡30 ላይ መስቀል በወረደበት ቦታ ላይ ድንኳን ተተከለ፤ ብፁዐን አባቶችም በስልክ እንዲያውቁ ተደረገ ብለዋል፡፡ ይሁን እንጂ በማግስቱ የአቡነ ተክለሃይማኖት ክብረ በል ስለነበረ ብዙዎቹ ጻጳሳት ወደ ደብረሊባኖስ፣ ቀሪዎቹም ወደየአድባራቱ ሄደው ስለነበረ መምጣት አልቻሉም ብለዋል - መጋቢው፡፡ ከበላይ አካላት በተነገረን መሠረት ለወረዳው ፖሊስ ካሳወቅን በኋላ፣ የፖሊስ ሃይል አካባቢውን ተቆጣጠረ” የሚሉት መጋቢ ሃዲስ፤ ቅዳሜ እለት የማህበረ ቅዱሳን አባላት መጥተው መመልከታቸውን ገልፀዋል፡፡ በዚያው እለት ከሰአት በኋላ ለመምጣት ቀጠሮ የሰጡ ጳጳሳት ግን ከአንድ ሰአት በላይ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በመጣሉና ጭቃው የማያስገባ በመሆኑ ከመንገድ ተመልሰዋል። በማግስቱ እሁድም አክራሪነትን በመቃወም ሰልፍ የሚካሄድበት ቀን በመሆኑ መምጣት አልቻሉም፡፡ ሰኞ እለት ነሐሴ 27 ቀን ግን በርካታ ጳጳሳት በቦታው ተገኝተው በበርካታ ምዕመናን ታጅቦ መስቀሉ ከወደቀበት መሬት ተነስቶ፣ ወደ መቅደሱ እንዲገባ መደረጉን መጋቢ ፍሰሃ ተናግረዋል፡፡ በደረሰበት አደጋ ራሱን ስቶ የቆየው ወጣት ፤  በ4ኛው ቀን መንቃቱንና በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ መጋቢ ሃዲስ ጠቅሰዋል፡፡   ወጣቱ ሲጠየቅም፣ መስቀሉን ተመልክቶ ሊያነሳው እጁን ሲሰነዝር ከኋላው አንዳች ህፃን ልጅ የመሰለ ነገር ጐትቶ መሬት ላይ እንደጣለውና ከዚያ በኋላ የሆነውን እንደማያውቅ መግለፁን እኚሁ መጋቢ ተናግረዋል፡፡ 

መስቀሉ ከወደቀበት መሬት ተነስቶ ሲገባ ከፍተኛ ግለት እንደነበረውና የተሸከሙት አባት “እያቃጠለኝ ነው” ሲሉ እንደነበር መጋቢ ፍሰሃ ገልፀዋል፡፡ መስቀሉ የሰው ስራ እንዳይሆን የተጠራጠሩ ካህናት መኖራቸውን ያመኑት መጋቢ ፍሰሃ፣ መስቀሉ ከምን እንደመጣ የሚያውቀው ፈጣሪ ነው ብለዋል፡፡ 

አቶ እንግዳው የተባሉ የአካባቢው ነዋሪ፣ መስቀሉ ከሠማይ ሲወርድ እንዳልተመለከቱ ጠቅሰው፤ በጳጳሣቱ ተነስቶ ወደ መቅደሡ ሲገባ ወርቃማ ብርሃን ነበረው ብለዋል፡፡ አንዳንድ የአካባቢው ሠዎችም ሌሊቱን ነጐድጓዳማ ድምፅ መስማታቸውንና በማግስቱም ይህን ክስተት በቤተክርስቲያኑ ከነበሩ ሰዎች ታሪኩ እንደተነገራቸው ገልፀዋል፡፡ ለአካባቢው ፀጥታ በማሰብ መስቀሉ በየእለቱ ለምዕመናን እንዳይታይ ከቤተክህነት ትዕዛዝ እንደተላለፈ ጠቅሰው፤ መስከረም 19ቀን 2006 ዓ.ም በቤተክርስቲያኑ ቅፅር ግቢ መስቀሉን በይፋ ለእይታ ለማብቃት ቀጠሮ መያዙን መጋቢ ሃዲስ ተናግረዋል፡፡

8 comments:

  1. ዓለምን ሁሉ ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት መስቀል እሰግዳለሁ
    መስቀል ኃይላችን ነው
    ኃይላችን መስቀል ነው
    የሚያፀናን መስቀል ነው
    መስቀል ቤዛችን ነው
    መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው
    አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን
    ያመንነው እኛም በመስቀሉ እንድናለን ድነናልም

    ReplyDelete
  2. ዓለምን ሁሉ ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት መስቀል እሰግዳለሁ
    መስቀል ኃይላችን ነው
    ኃይላችን መስቀል ነው
    የሚያፀናን መስቀል ነው
    መስቀል ቤዛችን ነው
    መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው
    አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን
    ያመንነው እኛም በመስቀሉ እንድናለን ድነናልም

    ReplyDelete
  3. ለምን ሁሉ ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት መስቀል እሰግዳለሁ
    መስቀል ኃይላችን ነው
    ኃይላችን መስቀል ነው
    የሚያፀናን መስቀል ነው
    መስቀል ቤዛችን ነው
    መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው
    አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን
    ያመንነው እኛም በመስቀሉ እንድናለን ድነናልም

    ReplyDelete
  4. ሰላም እንደምን ከረማችሁ። እግዚአብሔር አምላክ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰን። ምስጋና ለመድኃኔዓለም።

    በርግጥም የአምላክን ተዓምር መናገር ያስፈልጋል። ንገሩ፣ እንንገር።

    ለመሆኑ የዚህ ተዓምር ምስጢሩ ምን ይሆን? ይህ ምልክት የአዲስ አመት መምጣትን ብቻ ሳይሆን የአዲስ ዘመን መምጣትን አብሳሪ ይሆን ወይ? አዲስ ዘመን እያንዣበበ ይመስለኛል። በአሁኑ ሰዓት ሳናስተውላቸው ቀርተን ይሆናል እንጂ ብዙ የእግዚአብሔር ተዓምራት ሲከናወኑ እናያለን። ከታላቁ ገዳም ከዋልድባ ጋር በተያያዘ የእግዚአብሔርን ተአምራት በነዚህ ባለፉት ሁለት አመታት አየን። አሁንም ተአምራቱ በመቀጠል ላይ ናቸው።

    እንደገናም ላለፉት አምሳ አመታት ቅድስት አገር ኢትዮጵያን ለመበታተንና ኃይማኖቷን ለማጥፋት የተረባረቡትን አገሮችን በሙሉ አንድ ባንድ የእግዚአብሔር ቅጣት አሁን ሲጎበኛቸው እያየን ነው።

    የዛሬ አስራ ሁለት ዓመት በኢትዮጵያ አዲስ አመት መስከረም አንድ ቀን (በፈረንጆች ሴፕቴምብር ኢለቨን) በአረቦች ተቀነባብሮ በተለይ በኑዮርክ የደረሰው አንድ አደጋ እስከዛሬ ድረስ በአሜሪካ ላይ ያስከተለው መዘዝ በጣም ብዙ ነው። አሁንም ልክ በአስራ ሁለት ዓመቱ፤ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት እለተ ቀን ( በፈረንጆች ሴፕቴምብር ኢለቨን ሁለት ሺህ አስራ ሶስት ዓ.ም.) በሩስያው መሪ በቭላድሚር ፑቲን የተጻፈ ደብዳቤ በኒዮርክ ታይምስ ላይ ወጣ። ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፕሬዚዳንት ኦባማ በተናገሩት ንግግር ላይ በመነሳት እናንተ አሜሪካኖች ልዩ ነን አትበሉ፣ አምላክን ይቅርታ ስንጠይቅ በሱ ፊት ሁላችንም እኩል ነን የሚል የመደምደሚያ መልእክት አለበት። ይህን ደብዳቤ ያነበቡ የአሜሪካ ባለስልጣኖች እንደታወኩ በቴሌቪዚን አየን። ሰላይና ኮምኒስት የነበሩት ቭላድሚር ፑቲን በድንገት አሜሪካኖች ሳያስቡት በአሜሪካኖች ላይ የግብረገብነት (የሞራል) የበላይነትን አሳዩ። “በእግዚአብሔር ፊት እኩል መሆን ጌይና ሌዝቢያኖችንም ይጨምራል ወይ?” በማለት የኮንግረስ መሪ ወይዘሮ ናንሲ ፔሎሲ ለፕሬዚዳንት ፑቲን ህዝብ በተሰበሰበበት አፋዊ መልስ ሰጡ። ይህን መልስ የሰጡት ፕሬዚደንት ፑቲን ሶዶማዊ ጋብቻን በህግ ስለከለከሉ እሱን ለመቃወም በመሆኑ ተቃውሞው ለፕሬዚዳንት ፑቲን ቢመስልም በይዘት ግን ተቃውሞው ለእግዚአብሔር ነበር። ከዚህ ጊዜ በኋላ የፕሬዚዳንት አቦማን ሥራወች ብታዩ እየተከናወነላቸው አይመስልም። ምንም ሲያዩት ትንሽ ቢመስልም በኢትዮጵያ አዲስ አመት የተፈጸመ ነገር መዘዙ እጅግ ትልቅ ስለሚሆን ያሰጋል። እኔ እንደሚመስለኝ ዘመን ተቀይሯል። ኢትዮጵያውያን ወደ አገራችን የምንገባበት ጊዜ አሁን ይመስለኛል። ኢትዮጵያም ያለው እግዚአብሔርን የማይቀበል አስተዳደር በመሆኑ በኢትዮጵያ ላይ ቅጣት መምጣቱ አይቀርም። የእግዚአብሔር የሆነው እስኪሰየም ድረስ ብዙ ቅጣት ሊኖር ይችላል። ለማንኛውም ባገር መገኘቱ መልካም ይመስለኛል። አስቡበት።

    ክብርና ምስጋና ለመዳኃኔዓለም።
    ኃይለሚካኤል።

    ReplyDelete
  5. oh my God! I don't have a word to express your mercy. If this holy cross came from u who can able to touch it or it can cure a lot of handicap or patient from their ill.it can show a lot of miracle. Not as a simple thing can move with out nothing.

    ReplyDelete
  6. Ye Amlakachin chernet ena bereket silaliteleyen Temesgen Be Orthodox emnete Korahu

    ReplyDelete
  7. Dear And Adrgin

    I am not feeling good about this news. Even though I am full of sin, I am a member EOTC . Do not run to label me. I beliveie God can do any thing, but this news do not look true. This Mergata and Dn create the dram. I advise for Addis ababa heger sibket to write a leterr for police to investigate the case. Once it is approved as it is false, the EOTC need to announce for the public.

    Tnx

    ReplyDelete
  8. Dear Anonyous Sept 20, 2013,

    Instead of hiding the cross, why didn't we allowed it to cure the ill people,.......... that is how we know our Fathers would have done to KNOW IF IT IS FROM GOD!!!!!!! All we have here is the words of peoples, believe I found it hard to trust anyone at this time.... God won't lead by heresay but by Action..... Let the Cross do what we know it could do, and then we know if it is REALLY comes from above or not

    ReplyDelete