- ለህዝብ የሚታየው ፓትሪያርኩ በተገኙበት ነው ፤
- በየእለቱ ከ3ሺህ ሰው በላይ ቦታውን እየጎበኘ ነው
(አዲስ አድማስ ቅዳሜ መስከረም 11 2006 ዓ.ም)፡- በአቃቂ ቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ከሰማይ ወረደ የተባለው መስቀል ፓትርያርኩ በተገኙበት ለህዝብ እንዲታይ መግቢያ መንገድ እስኪሰራ ድረስ የተራዘመ ሲሆን፣ በመስቀሉ ላይ የሳይንስ ምርመራ እንደማይፈቀድ
ተገለፀ፡፡ ከሶስት ሳምንት በፊት በፍንዳታ ድምፅና በብርሃናማ ቀስተደመና ከሰማይ ወረደ
የተባለው መስቀል፣ በሚቀጥለው ሳምንት መስከረም 19 ቀን ለህዝብ ይታያል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ፓትርያርኩ የሚገኙበት ስነስርዓት ለማዘጋጀት ጊዜው እንደተራዘመ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪዎች ተናግረዋል፡፡
መስቀሉ ለህዝብ የሚታየው ቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ በተገኙበት ስነስርዓት መሆን አለበት መባሉን አስተዳዳሪዎች
ጠቅሰው፤ መንገዱ ጭቃ ስለሆነ ጠፈፍ
ብሎ ለመኪና እስኪስተካከል
ድረስ ቀኑ
መራዘሙን ገልፀዋል፡፡ ቀኑ ገና እንዳልተወሰነና
ለፓትሪያርኩ ጋር
ውይይት እየተደረገበት ነው ያሉት የቤተክርስቲያኒቱ
አስተዳዳሪዎች፤ ስነስርዓቱን ህዳር 11 ቀን ለማካሄድ እንደታሰበ ጠቁመዋል፡፡
ከአዲስ አበባና በአቅራቢያዋ ከሚገኙ አካባቢዎች በየእለቱ ከ3ሺ
በላይ ሰዎች
ቦታውን እየጎበኙ መሆናቸውን የገለፁት የቤተክርስቲያኗ መጋቢ ሃዲስ ፍሰሃ፤ እኛም በየእለቱ ከ15 ጊዜ በላይ ስለ ተከሰተው ተዓምር ገለፃ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ መስቀሉ ባረፈበት ሳር
ላይ እንዲሁም ወደ ቤተ መቅደሱ ከገባ በኋላ የተነሱ ፎቶዎችን የያዘ ካርድ ታትሞ ለምዕመናን በ10
ብር እየተሸጠ ነው፡፡ በፎቶግራፍ ላይ
የሚታየው መስቀል በሰው የተሰራ የዕደ
ጥበብ ውጤት
እንደሚመስል በመጥቀስ ከሰማይ ወረደ መባሉን የሚጠረጥሩ መኖራቸውን በተመለከተ መጋቢ ሃዲስ ፍስሃ፣ እውነቱን የሚያውቀው ፈጣሪ ነው ብለዋል፡፡
በምድራችን የተሰራ የሚመስል መስቀል ከሰማይ ሊወርድ አይችልም የምንል ከሆነ፣ በምድራችን የምናረባው አይነት በግ ለአብርሃም ከሰማይ ወርዶለታል የሚለውን የመፅሃፍ ቅዱስ ቃል መጠራጠር ይሆናል ብለዋል መጋቢ ሃዲስ ፍስሃ፡፡ የመስቀሉን ስሪት
እንዲሁም መስቀሉ አረፈበት የተባለውን ሳርና
አፈር ለመመርመር ሃሳብ ተነስቶ እንደሆነ ተጠይቀው መጋቢ ሃዲስ ሲመልሱ፤ “ይህ
መስቀል የቤተክርስቲያኒቱ የክብር መገለጫ ነው”
በማለት ተቃውመዋል፡፡
Ene Negru almarengm enja bicha....
ReplyDeleteenem!
Deleteተዐምር እየታየ፣ ተዐምር ያልሆነ ነገር ላይ ሩጫ ምን ይባላል?
ReplyDeleteየዛሬ አመት በአንድ ወር ውስጥ ፀረ ኢትዮጵያ እና ፀረ ቤተክርስቲያን የነበሩትን ሁለት መዥገሮች አባትና ልጅ መልአከ ሞት ነቃቅሎ ሲዎስድ፣ ሁኔታው እንደተዐምር ሳይታይ እንደ አገር አቀፋዊ ሃዘን ሆኖ ታየ። እስቲ አባቶች አገሪቷን ያጥለቀለቁትን የቻይኒ ጎግማንጎግ ሠራዊቶች ባሉበት እንዲተኑና እንዲከስሙ፣ ከቅድስት ኢትዮጵያችሁም ፈርጥጠው እንዲጠፉ ምህላና ፀሎት እንዲደረግ ያድርጉ። ያ ራሱን የቻለ ተዐምር ይሆን ነበር። ወይስ ህዝቡ አባቶችን ለቀቅ አድርጎ በያለበት ያለመንግስት እና ቤተክርስትያን ድጋፍ፤ ጎግማንጎችን ሲጥጥ ማድርግ ይጀምር ?
tert new
ReplyDeletediro diro endi yale neger simeta..... meskelu beshetegna lay himemetegna lay eyetederege tameratu yeregaget neber ............... ahun ahun.............. negeru hulu tayeta eyehone new......... new silalun anamenem mallet sayhon lemen meskelu betegebar endiregaget altederegem???????? Ende abatochachen BILIHAT binechemer tiru neber
ReplyDeleteAhunes abezachehut ke Addis Admas copy paste madreg aykeribachehum? Do a bloger job like Daniel Kibret.
ReplyDeleteWhat you token about?they are the same page,that is there newspaper if
ReplyDeleteYou don't know it get it know.
ክርሰቴያኖች ሆይ ፤ ብናምን እንጅ ብንጠራጠር ምን አናገኛለን?ቆም ብለን ብናስተውል እውን ለኢትዮጽያ ኦርተዶክስ ቤተክርስትያን ይህ የመጀመሪያ ተአምር ነውን??? በዘመኑ ያለን ምእመን ፤ማንበብ ፤ መጻፍ ከዜያም አልፎ ለመተቸት መቻኮል የተሰጠን ሆን አንጅ ልብ ብንል ከወደ መጀመሪያው የጻፈው ሰው ጨርሶት ነበር። ከዜያ በላይ ተአምር ምን ያስፈልጋል ።
ReplyDeleteየድንግል ልጅ የምናስተውልበት ልቦና ይስጠን።