Sunday, September 22, 2013

“ይህ መስቀል የቤተክርስቲያኒቱ የክብር መገለጫ ነው” መጋቢ ሃዲስ ፍሰሃ


  • ለህዝብ የሚታየው ፓትሪያርኩ በተገኙበት ነው
  • በየእለቱ 3ሺህ ሰው በላይ ቦታውን እየጎበኘ ነው
(አዲስ አድማስ ቅዳሜ መስከረም 11 2006 ዓ.ም)፡- በአቃቂ ቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ከሰማይ ወረደ የተባለው መስቀል ፓትርያርኩ በተገኙበት ለህዝብ እንዲታይ መግቢያ መንገድ እስኪሰራ ድረስ የተራዘመ ሲሆን፣ በመስቀሉ ላይ የሳይንስ ምርመራ እንደማይፈቀድ ተገለፀ፡፡ ከሶስት ሳምንት በፊት በፍንዳታ ድምፅና በብርሃናማ ቀስተደመና ከሰማይ ወረደ የተባለው መስቀል፣ በሚቀጥለው ሳምንት መስከረም 19 ቀን ለህዝብ ይታያል ተብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ፓትርያርኩ የሚገኙበት ስነስርዓት ለማዘጋጀት ጊዜው እንደተራዘመ የቤተክርስቲያኗ አስተዳዳሪዎች ተናግረዋል፡፡ መስቀሉ ለህዝብ የሚታየው ቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ በተገኙበት ስነስርዓት መሆን አለበት መባሉን አስተዳዳሪዎች ጠቅሰው፤ መንገዱ ጭቃ ስለሆነ ጠፈፍ ብሎ ለመኪና እስኪስተካከል ድረስ ቀኑ መራዘሙን ገልፀዋል፡፡ ቀኑ ገና እንዳልተወሰነና ለፓትሪያርኩ ጋር ውይይት እየተደረገበት ነው ያሉት የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪዎች፤ ስነስርዓቱን ህዳር 11 ቀን ለማካሄድ እንደታሰበ ጠቁመዋል፡፡

ከአዲስ አበባና በአቅራቢያዋ ከሚገኙ አካባቢዎች በየእለቱ 3 በላይ ሰዎች ቦታውን እየጎበኙ መሆናቸውን የገለፁት የቤተክርስቲያኗ መጋቢ ሃዲስ ፍሰሃ፤ እኛም በየእለቱ 15 ጊዜ በላይ ስለ ተከሰተው ተዓምር ገለፃ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ መስቀሉ ባረፈበት ሳር ላይ እንዲሁም ወደ ቤተ መቅደሱ ከገባ በኋላ የተነሱ ፎቶዎችን የያዘ ካርድ ታትሞ ለምዕመናን 10 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ በፎቶግራፍ ላይ የሚታየው መስቀል በሰው የተሰራ የዕደ ጥበብ ውጤት እንደሚመስል በመጥቀስ ከሰማይ ወረደ መባሉን የሚጠረጥሩ መኖራቸውን በተመለከተ መጋቢ ሃዲስ ፍስሃ፣ እውነቱን የሚያውቀው ፈጣሪ ነው ብለዋል፡፡
በምድራችን የተሰራ የሚመስል መስቀል ከሰማይ ሊወርድ አይችልም የምንል ከሆነ፣ በምድራችን የምናረባው አይነት በግ ለአብርሃም ከሰማይ ወርዶለታል የሚለውን የመፅሃፍ ቅዱስ ቃል መጠራጠር ይሆናል ብለዋል መጋቢ ሃዲስ ፍስሃ፡፡ የመስቀሉን ስሪት እንዲሁም መስቀሉ አረፈበት የተባለውን ሳርና አፈር ለመመርመር ሃሳብ ተነስቶ እንደሆነ ተጠይቀው መጋቢ ሃዲስ ሲመልሱ፤ይህ መስቀል የቤተክርስቲያኒቱ የክብር መገለጫ ነውበማለት ተቃውመዋል፡፡
እስካሁን በስፍራው የተፈፀመውን ተአምር ሰምተው የሚያደንቁ እንጂ በመስቀሉና በቦታው ላይ እንመራመራለን የሚሉ ምሁራን አላጋጠሙኝም ያሉት መጋቢ ሃዲስ፤እንዲህ ያለ ጥያቄ ያላቸውም ካሉም፣ የማይሞከር ነውያሉት መጋቢ ሃዲስ፤ የሃይማኖት ጉዳይ ስለሆነ ቦታውን እንፈትሻለን፣ የወረደውን መስቀል እንመረምራለን ለሚሉ የሳይንስ ባለሙያዎች ፈፅሞ አይፈቀድም ብለዋል፡፡ መስቀሉ ከሰማይ ከመውረዱ አስቀድሞ ራዕይ ታይቶኛል የሚል ሰው እስካሁን አላጋጠመን ያሉት መጋቢ ሃዲስ፤ ቤተክርስቲያኒቱን ያቋቋሙት አባት ግን፣ ቦታው የእግዚአብሔር ክብር መገለጫ እንደሚሆን በራዕይ እንደታያቸው ተናግረው ነበር ብለዋል፡፡

8 comments:

  1. Ene Negru almarengm enja bicha....

    ReplyDelete
  2. The Angry Ethiopian/ቆሽቱ የበገነውSeptember 23, 2013 at 7:14 AM

    ተዐምር እየታየ፣ ተዐምር ያልሆነ ነገር ላይ ሩጫ ምን ይባላል?
    የዛሬ አመት በአንድ ወር ውስጥ ፀረ ኢትዮጵያ እና ፀረ ቤተክርስቲያን የነበሩትን ሁለት መዥገሮች አባትና ልጅ መልአከ ሞት ነቃቅሎ ሲዎስድ፣ ሁኔታው እንደተዐምር ሳይታይ እንደ አገር አቀፋዊ ሃዘን ሆኖ ታየ። እስቲ አባቶች አገሪቷን ያጥለቀለቁትን የቻይኒ ጎግማንጎግ ሠራዊቶች ባሉበት እንዲተኑና እንዲከስሙ፣ ከቅድስት ኢትዮጵያችሁም ፈርጥጠው እንዲጠፉ ምህላና ፀሎት እንዲደረግ ያድርጉ። ያ ራሱን የቻለ ተዐምር ይሆን ነበር። ወይስ ህዝቡ አባቶችን ለቀቅ አድርጎ በያለበት ያለመንግስት እና ቤተክርስትያን ድጋፍ፤ ጎግማንጎችን ሲጥጥ ማድርግ ይጀምር ?

    ReplyDelete
  3. diro diro endi yale neger simeta..... meskelu beshetegna lay himemetegna lay eyetederege tameratu yeregaget neber ............... ahun ahun.............. negeru hulu tayeta eyehone new......... new silalun anamenem mallet sayhon lemen meskelu betegebar endiregaget altederegem???????? Ende abatochachen BILIHAT binechemer tiru neber

    ReplyDelete
  4. Ahunes abezachehut ke Addis Admas copy paste madreg aykeribachehum? Do a bloger job like Daniel Kibret.

    ReplyDelete
  5. What you token about?they are the same page,that is there newspaper if
    You don't know it get it know.

    ReplyDelete
  6. ክርሰቴያኖች ሆይ ፤ ብናምን እንጅ ብንጠራጠር ምን አናገኛለን?ቆም ብለን ብናስተውል እውን ለኢትዮጽያ ኦርተዶክስ ቤተክርስትያን ይህ የመጀመሪያ ተአምር ነውን??? በዘመኑ ያለን ምእመን ፤ማንበብ ፤ መጻፍ ከዜያም አልፎ ለመተቸት መቻኮል የተሰጠን ሆን አንጅ ልብ ብንል ከወደ መጀመሪያው የጻፈው ሰው ጨርሶት ነበር። ከዜያ በላይ ተአምር ምን ያስፈልጋል ።
    የድንግል ልጅ የምናስተውልበት ልቦና ይስጠን።

    ReplyDelete