Thursday, September 12, 2013

‹‹ኢትዮጵያን የሚያሰጋት የክርስቲያን አክራሪነት ነው›› ኡስታዝ ሀሰን ታጁ


  • የእንቅስቃሴው ሌላ አደጋ በሚስጢር እየተመራ መሆኑ ነው፡፡

(አንድ  አድርገን መስከረም 03 2006 ዓ.ም) ፡- ኡስታዝ ሀሰን ታጁ የእስልምና ሃይኖትን በተመለከተ በርካታ መጻህፍቶችን በትርጉም አሳትሟል ፤ በአሁኑ ሰዓት በእስር ላይ የሚገኙት በእነርሱ አጠራር ‹‹መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ›› ሃሳቡ ሲጀመር ፤ አሀዱ ተብሎ ነገር ሲጠቀለል ከፊት ከነበሩት 20 ተመራጭ ሰዎች ውስጥ ኡስታዝ ሀሰን ታጁ አንዱ ነው ፡፡ ‹‹‹አሁን የሙስሊሞች ጉዳይ ላለበት ደረጃ የፊት መስመር ቀያሹ ሰው አንዱ ኡስታዝ ሀሰን ነው›› በማለት ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁት ሰዎች ይናገራሉ ፤ የጀመሩት ‹‹ትግል›› መነሻው ሃይማኖታዊ ቢሆንም በሂደት እያደር ፖለቲካው ይዘት እንደተላበሰ በቃለ መጠይቁ ላይ ገልጿል፡ በዚህ ንቅናቄ መሰረትም መንግሥትን የመጣል ፍላጎት ያላቸው ዲያስፖራዎች እንደበረከቱ ሁኔታውን ወደ ሌላ ምዕራፍ ለማሸጋገር በታሳሪዎች ስም በአውሮጳ እና በመካከለኛው ምስራቅ በርካታ ብር በስማቸው እየተሰበሰበ እንደሆነ ገልጿል ፡፡ ኡስታዝ ሀሰን ታጁ በእርሱ አባልነት የተጀመረውን እቅስቃሴ እንዲህ ብሎ ገልጾታል፡፡

‹‹.. ወጣቱን ፤ የታሰሩትን የኮሚቴ አባላት ወንድሞቼንና እንቅስቃሴውን አውቀዋለሁ ብዬ አምናለሁ ፡፡ ብዙ ሰው ነገሩን መርምሮ እና ጥቅምና ጉዳቱን ለይቶ ሳይሆን በስሜት ነው የሚሄደው፡፡ ስሜት ጥሩ ነገር ሆኖ ግራና ቀኙን ማየት ግን ያስፈልጋል ፡፡ ስሜት ቁጭት እልህ የሚባሉት ነገሮች አስተሳሰብህን ከሸፈኑት እንደ አደንዛዥ እጽ ናቸው፡፡  ያሰክሩሃል ፤ የእንቅስቃሴው ሌላ አደጋ በሚስጢር እየተመራ መሆኑ ነው፡፡ ሚስጢራዊው እንቅስቃሴ መሀል ላይ ተጠልፎ ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ ሊያመራ ይችላል፡፡ ›› በማለት ያለበትን ሁኔታ እና የወደፊቱን አስቀምጧል፡፡ እኛም ‹‹ከባለቤቱ በላይ ያወቀ ቡዳ ነው›› ብለናል፡፡


በተጨማሪም መንግሥት እስረኞቹን እንዲፈታ የማይፈልጉ ብዙ ወገኖች እንዳሉም ተናግሯል ፤ ይህ ማለት እስረኞች ተፈቱ ማለት አርብ በመጣ ቁጥር ተቃውሞውን የሚያሰማው ድምጽ ሊቀንስ ይችላል ፤ ይህ ደግሞ ሕዝቡም ተጋግሎ የነበረውን በመንግሥት ላይ የተነሳውን ተቃውሞ በመተው ወደ ቤቱ ይገባል ተብሎ ስለሚታሰብ እንደሆነ አክሎ ገልጿል ፡፡ ታዲያ መልስ እንዲያቆመው የማይፈለገው መንገድ የት ያደርስ ይሆን? ከሚታየው የፊት ጥያቄ የማይታየው የጀርባ ጥያቄ ምን ይሆን ?  ሲጀመር ኡስታዝ ሀሰን ታጁ   መነሻው ሃይማኖታዊ መድረሻው ያልታወቀውን ንቅናቄ እንዲፈጠር በጽሁፎቹ ብዙ ተግቷል ፡፡ አሁን ደግሞ የእምዬን ወደ አብዬ እንዲሉ ‹‹ኢትዮጵያን የሚያሰጋት የክርስቲያን አክራሪነት ነው››  በማለት ለ‹‹ፋክት›› መጽሄት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ ኡስታዝ ሀሰን ታጁ የቀድሞ የፍትህ ጋዜጣ ባልደረቦች ዳግም ባቋቋሟት ‹‹ፋክት›› መጽሄት የጳግሜ 2005 ዓ.ም እትም ላይ ባደረገው ቃለ መጠይቅ እንዲህ ብሏል፡፡

ጥያቄ፡- በመንግሥት ወገን በተለይም ከተወሰኑ ጊዜያት ወዲህ ‹‹አክራሪዎች›› ሲባል ተደጋግሞ ይደመጣል ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት አክራሪነት አለ ብለህ ታምናለህ ?

ኡስታዝ ሀሰን ታጁ፡- ምን ማለት ነው አክራሪነት ? እሱን በቅድሚያ መፍታት ያስፈልጋል፡፡ በመንግሥት ፍቺ መሰረት ሃይማኖትና መንግሥት የተለያዩ ናቸው፡፡ የተለያዩ መሆናቸውን የማይቀበል ፤ ሁሉም ሃይማኖቶች በእኩልነት የሚኖሩባት ሃገር መሆኗን የማይቀበል ፤ በሃገሪቱ መንግሥታዊ ሃይማኖት አለመኖሩንና ሊኖርም የማይችል መሆኑን የማይቀበል ነው አክራሪ  የሚባለው፡፡ በዚህ ትርጉም መሰረት ከሄድን ኢትዮጵያ ውስጥ አክራሪነት አለ ለማለት ያስቸግራል ፡፡ ኢትዮጵያ ኢስላማዊ አክራሪነት አያሰጋትም፡፡ ከሚሊዮን አንድ የሚቃዥ ሊኖር ይችላል፡፡ ‹‹አንድ ሃገር እና አንድ ሃይማኖት›› እንደሚሉት ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ለ700 ዓመታት በክርስቲያን መንግሥት ነው ስትተዳደር የነበረው፡፡ ስለሆነም ኢትዮጵያን ካሰጋትም የክርስቲያን አክራሪነት ነው የሚያሰጋት፡፡

የቀድሞውን ከመቶ ዓመታት በፊት በዚች ቤተክርስቲያን ላይ የሆነውንና የተደረገውን በታሪክም የተቀመጠልንን ብንተወው እንኳን አሁን በእኛ ዘመን ከአስርና ከአስራ አምስት ዓመታት በፊት የደረሰው እየደረሰ ያለው አክራሪነት መሰረቱ የት እንደሆነ ፤ ምንጩ ከየት እንደሆነ ለማወቅ የታሪክ ምሁር መሆንን አይጠይቅም ፡፡ በ1997 ዓ.ም በርካታ አብያተ ክርስቲያናት የተቃጠሉት ፤ አገልጋይ ካህናት በሰይፍ የተቀሉት በጅማ አካባቢ በሚገኙ አክራሪዎች ነበር ፡፡ ከዓመት በፊት በስልጤ ዞን በጠራራ ፀሃይ ‹‹አላህ ዋክበር›› እያሉ ቤተክርርስቲያን ላይ እሳት የለኮሱት እስልምና ሃይማኖቱ ያስጠለላቸው ብሎም ያፈራቸው አክራሪዎች ናቸው፡፡ በተመሳሳይ በውድቅት ሌሊት በደቡብ ክልል ጋዝ ፤ ክብሪትና ተቀጣጣይ ነገሮች በመያዝ ቤተክርስቲያን ሊያቃጥሉ ሲሉ በጥበቃዎች በተደረገ መከላከል ምኞታቸው የከሸፈባቸው አክራሪዎች ከማን ወገን ናቸው ? በአዲስ አበባ ኮልፌ አካባቢ በሚገኝ በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ በመግባት እንዳበደ ሰው ‹‹አላህ ዋክበር›› ‹‹አላህ ዋክበር›› እያለ ተይዞ ለህግ አካላት ተላልፎ የተሰጠው በፍርድ ቤት ውሳኔም 6 ወር የታሰረው ከማን ወገን ነው? በቦርደዴ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ‹‹በጾማችን ወቅት ቅዳሴ መስማት አንፈልግም›› በማለት አደጋ ከማድረሳቸው በፊት በመከላከያ ልዩ ኃይል እርምጃ የተወሰደባቸው አህዛቦች ከማን ወገን ናቸው? በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች አክራሪነት  ወደ ተሻለ ደረጃ ለማስፋት በኬንያ ፤ በሱዳንና በተለያዩ በመካከለኛው ምስራቅ ኢስላማዊ መንግስታት በትምህርት ላይ የሚገኙት ሙስሊም ወጣቶች ከማን ወገን ናቸው ? በደሴ ፤ በከሚሴ ፤ ሀረር ፤ ጅማ ፤ እና አርሲ ውስጥ ውስጡን በረብጣ የአረብ ሀገር ብር ቤት ለቤት በሃይማኖት ሽፋን የሚደረገው ወጣት ምልመላ እና አስተምህሮ የሚያካሂዱ ሰዎች ከማን ወገን ናቸው ? እኚህ ሁሉ ግለሰቦችም ይሁኑ ቡድኖች መጠለያ ድንኳናቸው ፤ መብቀያ አፈራቸው  እስልምና እንጂ ክርስትና አይደለም፡፡

7 comments:

  1. The Angry Ethiopian/ቆሽቱ የበገነውSeptember 13, 2013 at 12:35 AM

    Post the whole interview please

    ReplyDelete
  2. yebelubetn wecht regach mehon now enji eslmna wede Ethiopia sigeba qesawtu chmr bedesta endeteqebalachew tarik yngeral.Ngusum krstiyan honew eslmnan mech telu.Hlina bisnet now.
    Lelaw krstiyan biyaker mesgid ayaqatlm eslamm aygelm le emnetu erasun eskemot asalfo ysetal enji.Le Ethiopia aydelem le alem asgi yehonut yesntun hywet yeseyefut eslam akrariwoch nachew.Alem endih yemtnawetew beman hono now slekrstiyan akrari yemiyaweraw.Esu erasu akrari mehonun yemiyamelakt mels now yesetew.

    ReplyDelete
  3. egziyabehar yestachue ebakachu kechalachu ESAT yembalewen radio tabiyam hakune satawke atleflef belut legizawi ypolitica terfe sel becha Ethiopian wedtefat eymeruwat new O amlaka kedest hager Ethiopian ant tebek

    ReplyDelete
  4. A hidden motive never be hidden for long.It will be exposed.Muslims are our
    brothers and sisters.Jesus died for them too.He loves His creatures.As we are
    children of God we are in favor of love.If they want to be against christians,
    it is He who will punish them.we love our neighbours even though they want to hate us.

    ReplyDelete
  5. በግድ አክራሪ ናችሁ አለ እንዴ?

    ReplyDelete
  6. eslam yeselam tenk/telat new.

    ReplyDelete
  7. He don't know about christaian . Eslam selam yelewum bealem laye endate endtsefafachew tarikachun anbebe

    ReplyDelete