(አንድ አድርገን ነሀሴ 2
2005 ዓ.ም)፡- መንግሥት ራሴን ከማንኛውም ሃይማኖት ጋር ባለማገናኝት ነጻ ነኝ ብሎ ቢያስብም በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሚዲያው
በየወቅቱ ወደ አንድ ወገን ብቻ ያዘነበ መሆኑን የሰሞኑ የኢቲቪ ከዜና በኋላ የሚያስተላልፈው የረመዳን ወር የጾም ስግደት አንዱ
ምልክት ነው፡፡ በመሰረቱ ሃገሪቱ ውስጥ ያሉ ሃማኖቶች እኩል እስከተስተናገዱ ድረስ ሚዲያው ከየትኛውም ወገን ሳያዘነብል ሚዛናዊ
የአየር ሰዓት ክፍፍል ሊኖረው ይገባ ነበር ፤ ነገር ግን ይህ ሲሆን በየጊዜው መመልከት አልተቻለም ፤ በአመት አንድ ጊዜ ብቻ ከትንሳኤ
በፊት የሚመጣው የህማማት ሳምንት የአንድ ቀን የቤተክርስቲያን የስግደትን ስርዓት ከቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ማስተላለፍ ያልቻለው
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ባሳለፍናቸው 30 ቀናት የሙስሊሞችን ጾም ምክንያት በማድረግ ከመካ እና ከአንዋር መስኪድ የቀጥታ የስግደት
ስነስርዓት ማስተላለፉ ብዙዎችን ምን እየተሰራ ነው የሚል ጥያቄ እንዲጠይቁ አስገድዷቸዋል ፡፡ በመሰረቱ ብዙዎች ይህን ሳምንት ምክንያት
በማድረግ ኢቲቪ በማታው የአየር ሰዓቱ የሚያስተላልፈው የቀጥታ ዝግጅት በአሁኑ ሰዓት ያለውን ትኩሳት ለማብረድ ያለመ መሆኑን ሲናገሩ
ይስማ ፤ ግራም ነፈሰ ቀኝ ለፖለቲካ ግብዓት ጥቅም ይኑረውም አይኑረውም ፤ ወደፊት ሃማኖታዊ ስርዓቶችን በማመልከት ኢቲቪ ላይ የሚሰጡ
የአየር ሰዓቶች ሊታሰብባቸው ይገባሉ፡፡ አባቶቻችን ‹‹ከአያያዝ ይቀደዳል
፤ ከአነጋገር ይፈረዳል›› እንደሚሉት መንግሥታችን እንደሞኝ የያዘውን የሃይማኖት አክራሪነት ላይ ለማለዘብ ከብዙሀኑ ጋር ነኝ ለማለት
የሚያደርገውን ድርጊት ነው በማለት ጥቂቶች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
በዓመት ውስጥ ከምታከብራቸው ታላላቅ በዓላት ውስጥ መስቀል ፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ፤ ጥምቀት እና
ትንሳኤ ትልቁን ቦታ ይይዛሉ፡፡ ሲጀመር መንግሥት በመስከረም በባተ በአስራ ሰባተኛው ቀን የሚከበረውን የመስቀልን በዓል እና ከጥር
10 ጀምሮ እስከ 13 ድረስ በሃገሪቱ በሁሉም ቦታዎች የሚከበረውን የጥምቀት በዓል የሚፈልገው የሃገሪቱን የቱሪስት ፍሰት ጋር በማያያዝ
እንጂ በሌላ አይደለም ፤ ለዚህም አሳማኝ መረጃ በጎንደር ላይ የጥምቀትን በዓል ወደ ካርኒቫል ለመቀየር የተሄደው መንገድ አንዱ
ማስረጃ ነው ፤ በሌላ በኩል ስለ በዓላቱ ከቤተክርስቲያን የተወከሉ አባቶችን ከማናገርና ለምዕመኑ የበዓሉን ምንነት ፤ ለምን እንደሚከበር
? እንዴት እንደሚከበር? ፕሮግራም ከመስራት ይልቅ ጋዜጠኞቹ የውጭ ዜጋን በማባረር ቃለ መጠይቅ ማድረግ ይቀናቸዋል፡፡ በመሰረቱ ኢቲቪ እነዚህን በዓላት ምክንያት በማድረግ በሚሊየን የሚቆጠር ብር
በማስታወቂያዎች እና በተለያዩ ስፖንሰር አድራጊዎች ምክንያት ወደ ካዝናው የሚያስገባበት በዓላት በመሆናቸው የአየር ሰዓቱ ለሃማኖታዊ
ጉዳዮች ብቻ እንዲሆኑም አይፈልግም ፤ ተቋሙ በዓላቱን ክርስቲያንም ሆነ ክርስቲያን ላልሆነው ለኢቲቪ ሰራተኛ እና ለሚዲያው ባለሙያው
ይዘውላቸው የሚመጡትን የቀን አበል ብቻ እንደሆነ በማስመልከት ትልቁን ነገር እንዲዘነጉት አድርጓቸዋል፡፡
በእነዚህ በዓላት በሚከበሩበት ጊዜያት
ቤተክርስቲያኒቱ በምትፈልገው መንገድ ሳይሆን ፕሮግራሞች የሚሰሩት የኢቲቪ የቀረጻ እና የሚዲያ ሰዎች በሚፈልጉት መንገድ ብቻ ነው፡፡
ጋዜጠኞቹ በበዓላት ቀኖቹ በሚሰሩት ያለ አዋቂ ስህተት አንድም ቀን ተጠያቂ የሆኑበት ጊዜ የለም ፤ ስለሆነም ቤተክርስቲያኒቱም የምታከናውናቸውን
ስርዓቶችን ራሷንም ሆነ ሃገሪቱን በሚገልጽ መልኩ ሳይሆን ጥቂት አብዮታዊ
ዲሞክራሲን በተጠመቁ ሰዎች አይዲዎሎጂ መሆኑን እጅግ ያበሳጫል፡፡ የሚሉትን ነገር ቢያጡ እንኳን ‹‹ይህን በዓል የምናከብረው ታላቁን
መሪያችንን ባጣንበት …….ምናምን እያሉ ሲቀበጣጥሩ ለሰማቸው ‹‹ምኑን ከምኑ ያሰኛል…››
የአዲስ አመት በዓል የሁሉም ነው
ብለን ብናልፈው እንኳን በታህሳስ 29 እና አብዛኛውን ጊዜ በሚያዚያ ላይ የሚውለውን የትንሳኤ በዓል ኢቲቪ የሚያስተላልፈው ስለ
በዓላቶቹ አከባበር ስነ ስርዓት ሳይሆን በተለያዩ ቦታዎች ላይ ለኢቲቪ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኙ የፌሽታ ፕሮግራሞችን ነው፡፡ የእኛን
በዓል በኢቲቪ የዘፋኞች መድረክ ሲያደርጉት ሲስተዋል የእነሱን ግን
እንዲህ ሲያደርጉት አይስተዋልም፡፡ ታዲያ ይህን ሂደት እኛም ለምድነው ኖሮ በየትኛውም የቤተክርስቲያን ኦፊሺያል በዓል ላይ ጭፈራ
፤ ቀልድ ፤ ዘፈንና ዘፋኞችን ከኢቲቪ መስኮት የምንጠብቅ ጥቂቶች አይደለንም፡፡ በሙስሊሞች በዓል ጊዜ በተቻላቸው መጠን ስርዓቱ
ሳይዛነፍ ከስታዲየም ጀምሮ ፀሀይ
እስክታዘነብል ድረስ ነገሮችን በጥንቃቄ ሲያስኬዱት ይስተዋላሉ፡፡ ለማንኛውም ከአንድ ወይም ከሁለት ቀናት በኋላ በጨረቃ ዝቅ ወይም ከፍ
ማለት ላይ የሚወሰነውን የበዓል ሂደት እና ከወር በኋላ የሚከበረውን የመስቀል በዓል የኢቲቪ ዝግጅቶችን በመመልከት ልዩነቱን ይመልከቱ፡፡
ቁራን የወረደበት ቀን ነው በማለት
በጾሙ በ27ኛው ቀን የቀጥታ ስርጭት ከመስኪዶችና ከመካ መዲና ኢቲቪ ሲያስተላልፍ ተመልክተናል ፤ ለእኛስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ
ክርስቶስ የተሰቀለበት ቀን ነው በማለት በህማማት ሰሞን በእለተ አርብ የሚካሄደውን የቤተክርስቲያናችንን ስርዓት የቀጥታ ስርጭት
የአየር ሰዓት ያስተላልፉ ይሆን ? ለነገሩ ሲጀመር ጠያቂ ቤተክህነትም አይኖርም ፤ ቤተክህነት አካባቢ ያሉ ሰዎች ይህ ልዩነት አይታያቸውም
ሊታያቸውም አይችልም ፤ ሹመት ሽረት እስካልመጣ ድረስ በመገናኛ ብዙሃን ብቂ ሲሉ ጥያቄም ለምን ብለው ሲጠይቁ አይስተዋልም ፤ እነሱን
የሚያሳስባቸው ሌላ ትልቅ ጉዳይ አለባቸው፡
ቸር ሰንብቱ
I totally agree the writer. The government is in favor of Islam but Muslims don't think like that and they are going extreme. We know that EPDRF is against orthodox church from the beginning. We see that the current officials are either non-orthodox or very libral people.
ReplyDeleteIf the gov broadcasts religious ceremonies, it has to give appropriate coverage otherwise there is no need totally to broadcast.
For the past month ETV almost has talked about Islam and Muslims every day. But I think it is because there is problem between TPLF gov and Muslims currently.
Excellent point. I have no words except to say thank you for your outstanding comment !!!
ReplyDeleteከዚህ በፊት እንዳልኩት ወያኔ የሚባለው የአውሬ ቡድን አገሪቱ ላይ ዕቃ ዕቃ መጫወት ከጀመረ ወዲህ፣ ገዢዎቻችን ጴንጤና እስላሞች ሆነዋል። ቤተክርስትያናችንን ደግሞ ከውስጥም ከውጭም ሆነው የገዛ መሪዎችዋ ይገዘግዝዋታል፣ያቆረቁዝዋታል፤ህዝቡንም በአቦ-ሰጥ ፈረስ እያስጋለቡ ጉልበቱ እንዲበክን ያደርጋሉ። በቤተክርስትያን ውስጥ የተለያዩ አሳሳች ትርኢቶች እንዲከናውን በመፍቀድ፤ ምዕመኑን በስነልቦናዊ ጨዋታ ያዋዥቁታል። በየትኛው የአንጎል ክፍል እያሰቡ እንደሆነ ለማወቅ በጣም ያዳግታል።
ReplyDeleteGiru Ababl New Yasazinal Ethiopia Yemusilim Hage
ReplyDeleteIf the government keep ignoring us, then we may need to take other measures to demand equal treatment.
ReplyDeleteSew esk ahun yegebawem alemeselegnem end enie eyita, mikinayatum siltanun bemulu yetekotaterut muslimoch ena menafikan nachew silezih endet lihone yichilale, mejemeriyawenem ehiadig ajenda keretso yemetaw ORTHODOXn mebetaten muslimen mobilize maderege ye mile nebere silezih tegebarawi eyaderege new. Mengist ena wehabiya betechristianene lematifat abirew yiseru nebere gin egiziabhere hulutun atalachew beserut siram huletum waga eyetekefelachew new, gena bizu enayalen egiziabhere edimie ena tena yisten. Yihich betechristian be christos deme yetemeseretech nat silezih enersu yitefalu enji betechristian atitefam
ReplyDelete