Sunday, August 18, 2013

የአቡነ ጳውሎስ አንደኛ ዓመት መታሰቢያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን 20 ዓመታት በአምስተኛ ፓትርያርክነትና ርእሰ ሊቃነ ጳጳስነት የመሯትና አምና ያረፉት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንደኛ ዓመት መታሰቢያ ነሐሴ 10 ቀን 2005 .. በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዓት ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምዕመናንና ቤተ ዘመድ በተገኙበት ታስቧል፡፡ ለቤተ ክርስቲያኒቱ  በሁሉም አቅጣጫ ያስመዘገቧቸውን የሥራ ውጤቶች የተዘከሩ ሲሆን፣ በከፊል በተጠናቀቀው የመታሰቢያ እብነ በረድ ላይም መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል፡፡ የአበባ ጉንጉንም የተለያዩ ወገኖች አስቀምጠዋል፡፡ ከረፋድ እስከ እኩለ ቀን የዘለቀውን የማሕሌት፣ የጸሎተ ፍትሐትና የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት የመሩት አዲሱ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ናቸው፡፡  
from REporter

No comments:

Post a Comment