Tuesday, July 17, 2012

ሰዎች ምን አሉ ?



የመጀመሪያ አስተያየት ሰጪ
''አይቴ ለነውር ብሔረ ሙላዱ
በውስተ ኩሉ ብሔር እስመ ከመ ነግድ ይሄሉ
ጠይቆተ ዝኒ ነገር ከመ ይትገሀድ ለኩሉ
ኃጥእ ይሣለቅ ላዕለ ጻድቅ ከመ ዘንጹሕ ወሠናይ ባህሉ፥
እስመ እንዘ ሠርዌ በውስተ ዐይኑ  
እምነ ቢጹ ብሩህ አውጽኦተ ሐሠር ያስተዴሉ።
አይሁድኒ ሐዋርያተ በጽእሎቶሙ ጸዐሉ፥
ጊጉያነ ወአብዳነ ወሐሳውያነ እንዘ ይብሉ፥
ወብእሴ ጻድቀ ዘሀለዎሙ ይስቅሉ፥
እንዘ ውጹኣን እምነ ጽድቅ በጽድቀ ርእሶሙ ይትሌዐሉ። '' 
መወድስ ቅኔ ዘአለቃ ንጉሤ።

አባ ጳውሎስና ተከታይ የሥጋና የግብር ልጆቻቸው ያፈረሱትን እኮ ነው ገነባን የሚሉት። ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን አፍርሰው በጦር መሳርያ ሃይል ቀምተው የተቀመጡበትን መንበር ማፍረሻ እንጅ መገምቢያ እንዳላደረጉት የሚታወቀውን ነገር ለራሳቸው ካልሆነ በስተቀር ለማንም ሊሸጡት የማችሉት የረከሰ ሸቀጥ መሆኑን መረዳት የሚያስችል አዕምሮ እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠንቅቆ ያውቃል። ተዋቸው የራሳቸውን ጽድቅ ለራሳቸው እያስተጋቡ ለጊዜው ይቀጥሉ።


ሁለተኛ አስተያየት ሰጪ
በአባ ጳውሎስ ዘመነ ሥልጣን ቤተክህነት የደረሰባትን አስተዳደራዊና መንፈሳዊ ውድቀት ለሚረዳ ሰው እውነትም ኮሜዲ ነው:: የሚገርመው ውጤትን በምን መስፈርት ቢለኩ ነው እንዲህ ለማለት የቻሉት:: መቼስ የቤተክርስቲያንን አተዳደራዊ እድገትና የምእመናንን በሐይማኖት መጠንከር ሳይሆን ፓትርያርኩንና ግብረ አበሮቻቸው በግል ያካበቷቸውን ንብረቶች ቆጥረው ከሆነ ከልብ ያሳዝናል:: ምክንያቱም ፓትርያርኩ ሱሾሙ የተሰጣቸው ኃላፊነት ይህ አይደለምና:: በጣም እንዳላዝን የሚያደርገኝ ነገር ቢሮር እንዲህ ብለው የጻፉ ሰዎች ትናንትና ሐውልት ያቆሙላቸው ግለሰቦች ስለሚሆኑና ሐውልት ከማቆም የበለጠ ቀልድ ስለሌለ ነው:: ለማንኛውም 20 ዓመታት እናት ቤተክርስቲያን ተጎድታ ቆይታለችና ለቀጣይ 20ዓመታት ተመሳሳይ ፈተና እንዳያጋጥማት የሁል ጊዜ ምኞቴ ነው:: እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን::

ሶስተኛ አስተያየት ሰጪ (  ሐመረ ኖህ )
እኛ ዝም እስካልን ድረስ በተዋህዶ እምነታችንንና በኛም ላይ ገና ብዙ ግፍ ይሰራል የኑፋቄ የውርደት የዘረኝነት የመከፋፈል የአምባገነንነት የሙስና የዝቅጠት የአድርባይነት የፈተና ሁሉ ፈተና የቅንጦተኞች ዘመን አሳልፈናል አሁንም ዝም ካልን ይቀጥላል ሌላው ሁሉ ይቅርና ማለትም ዘርዝረን ስለማንጨርሰው የለበሱት ልብስ ለ፳ኛ ሲመታቸው ይሆን እጅግ በጣም ውድ ነው ስንት በገዳም የሚጋኙ በቀን አንዴ መመገብ ላልቻሉ ለታረዙ መነኮሳትና የአብነት ተማሪዎች ለዓመት ቀለብ ይሆን ነበር እኔስ ከአሕዛብ በእምነታቸው ሳይሆን በትግላቸው ቀናሁ ከሞተ አንበሳ ሕይወት ያላት ትሻላለች
ከደጀ ሰላም የተወሰደ

3 comments:

  1. በአባ ጳውሎስ ዘመነ ሥልጣን ቤተክህነት የደረሰባትን አስተዳደራዊና መንፈሳዊ ውድቀት ለሚረዳ ሰው እውነትም ኮሜዲ ነው:: የሚገርመው ውጤትን በምን መስፈርት ቢለኩ ነው እንዲህ ለማለት የቻሉት:: መቼስ የቤተክርስቲያንን አተዳደራዊ እድገትና የምእመናንን በሐይማኖት መጠንከር ሳይሆን ፓትርያርኩንና ግብረ አበሮቻቸው በግል ያካበቷቸውን ንብረቶች ቆጥረው ከሆነ ከልብ ያሳዝናል:: ምክንያቱም ፓትርያርኩ ሱሾሙ የተሰጣቸው ኃላፊነት ይህ አይደለምና:: በጣም እንዳላዝን የሚያደርገኝ ነገር ቢሮር እንዲህ ብለው የጻፉ ሰዎች ትናንትና ሐውልት ያቆሙላቸው ግለሰቦች ስለሚሆኑና ሐውልት ከማቆም የበለጠ ቀልድ ስለሌለ ነው:: ለማንኛውም ለ20 ዓመታት እናት ቤተክርስቲያን ተጎድታ ቆይታለችና ለቀጣይ 20ዓመታት ተመሳሳይ ፈተና እንዳያጋጥማት የሁል ጊዜ ምኞቴ ነው:: እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን::

    ReplyDelete
  2. የወጡበት ማኅበረሰብ ማፈር ማለት ምን እንደሆነ የሚያውቅ አይደለም ልበል? በቤተ መንግሥቱም በቤተ ክህነቱም የተሰገሰጉት በሙሉ ማለት ይቻላል የትንሿ የአድዋ አካባቢ ሰዎች ናቸው:: ትንሿ ያልኩት በሙሉ ትግራይን እንዳይመስልብኝ ብየ ነው::

    ReplyDelete
  3. ወንድሜ ፖለቲካና ሀይማኖት መለየት የቻልክ አልመሰለኝም የዐድዋ ኅዝብ ከትግራይ ልትነጥለው ትሞክራለህ አንተ ከነሱ በምን ትሻላለህ ለማንኛውም የዐድዋ ኅዝብ ካንተ የበለጠ ሀይማኖተኛ ነው::

    ReplyDelete