Friday, July 13, 2012

የኦርቶዶክሳውያንና የጨለማው ቡድን ትንቅንቅ ከቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ስብሰባ ማግስት እስከ በዓለ ሢመት

  •   ፓትሪያሪኩ በአራት የቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነባቸው አጀንዳ ቃለጉባኤ በብዙ ጫናዎች ባለፈው ሳምንት ፈረመዋል፡፡
  •  ቋሚ ሲኖዶስ ፓትሪያሪኩ በአጀንዳዎቹ ላይ ካለመፈረማቸው ጋር ተያይዞ የቅዱሰ ሲኖዶስ የበላይነት አምነው ስላልተቀበሉና ለውሳኔዎቹ ተገዥ ስላልሆኑ  ከቅዱስነታቸው ጋር መሰብስብ እንደማይችሉ በመግለጽ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ አልተሰበሰቡም፡፡
  •  “ጉባኤ አርድእት ዘተዋህዶ”  አባላት እርስ በእርሳቸው ተከፋፍለዋል፡፡ ቡድኑም በጠቅላይ ቤተክህነት እንዳይሰባሰብ ታግድዋል፡፡ የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ኅላፊዎችና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተቃውሞ እንዲሁም የመንግስት ማስጠንቀቂያን ተከትሎ ቡድኑ ፓትሪያሪኩ አግደወታል፡፡
  •  እገዳው በጠቅላይ ቤተክህነቱ ጠቅላላ አገልግሎቱ ደብዳቤ እንደሚጸና እየተጠበቀ ነው
  •  በዓለ ሢመት ጠንካራና ተጽእኖ ፈጣሪ አባቶች እንደማይገኙ በማሰብ የጨለማው ሲኖዶስ አባላት የጠነሰሱትን ሴራ ለማክሸፍ ብጹአን ሊቃነጳጳሳት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
  •  ምንደኛው ኃ/ጊየርጊስ ጥላሁን በጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥአስኪያጅ አቶ ተስፋየ ውብሸት ብርቱ ትግል አቡነ ጳውሎስ መኪናው እንዲነጠቅ አድርገዋል፡፡
  • ሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተመስርቷል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ለመስራች ጉባኤው የምግብ ወጭ 35,000 ብር ስፖንሰር አድርጓል፡፡ 
  •  “የመለስ አባት ነው ትሉኛላችሁ፤ አዎ የመለስ አባት ነኝ” አቡነ ጳውሎስ       
  •  ማኅበረቅዱሳን በመላው ዓለም ፳ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉ እያከበረ ነው

 (አንድ አድርገን ሐምሌ 6 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ከነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር ጋር በመተባበር ባዘጋጀውና ከአርባ ስምንት አኅጉረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች ኃላፊዎች፣ የታላላቅ አብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ሰንበት ት/ቤት አመራር ተወካዮች፣ የአዲስ አበባ አድባራት 135 ሰንበት ት/ቤቶች አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በድምሩ 200 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙበት ሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ  ከግንቦት 25-26 ተካሂዷል፡፡

ጉባኤው ይጀመራል ተብሎ ከታሰበበት ከጠዋት 3፡00 በፓትሪያሪኩ መዘግየት ምክንያት 4፡45 ላይ ለመጀመር ተገድዋል፡፡ ለፓትሪያሪኩ መዘግየት እንግዶች በመቀበል ሌላ አስቸኳይ ስራ  ምክንያት እንደሆነ ከመድረክ ለመግለጽ የተሞከረ ቢሆንም ዋነኛ ምክንያቱ  የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባኤ ከነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር ጋር በመተባበር ማዘጋጀቱ (የተሃድሶ መናፍቃን ከማኅበሩ ከፍተኛ አመራርነት በማሰናበቱና የ“ማኅበረ ቅዱሳን” ነው በማለት ፊት የነሱት  የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር ) እውቅና እንደማይሰጡት እንዲሁም በተሃድሶ መናፍቅነት የሚጠረጠረውን  አእመረ አሸብር በቦሌ  መድኃኔዓለም አንድነቱ ከነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የሕዝብ ጉባኤ ካላስተማረ ጉባኤው ላይ አልገኝም፣ ዕውቅና አልሰጠውም በማለታቸው በተፈጠረ ውዝግብ ምክንያት መሆኑን የቤተክህነት ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡ አንድነቱ ፓትሪያሪኩ ባልተስማሙባቸውና ጉባኤው ላይ ለመገኘት እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጡት ሁለት ሃሳቦች እንደማይቀበላቸው ቁርጥ ውሳኔ ስላሳወቃቸው ስልታዊ ለውጥ በማድረግ ጉባኤው ላይ ከአራት ሊቃነጳጳሳት(አቡነ ፊሊጶስ፣ አቡነ ጴጥሮስ፣ አቡነ ገሪማ፣ አቡነ ድሜጥሮስ) ጋር በመገኘት ጉባኤውን በይፋ ከፍተዋል፡፡

በጉባኤው ላይ የተገኙት ፓትሪያሪኩ አወዛጋቢ የሆነ ቃለምዳን ሰጥተዋል፡፡ ብጹዕ ዶክተር አቡነ ገሪማ ጰራቅሊጦስ አስመልክቶ ያቀረቡትን ጽሑፍ “ሃያ ዓመት ሙሉ አብረን ነን፣ ጰራቅሊጦስ አስመልክቶ ብጹዕ ዶክተር አቡነ ገሪማ ጽሑፍ ሲያቀርቡ አይቼ አላውቅም፤ እርሳቸው ስለ ሃዲስ ኪዳን ነግረውናል፡፡ እኔ ደግሞ ስለ ብሉይ ኪዳን ትንሽ ልጨምር ……ታቦተ ጽዮን የአባቱ ድርሻ ነው ያመጣው … መብቱ ነው፤…..እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መምህሩ የሆነ ትውልድ ማንነቱን ማወቅ የለበትም? ….. ስህተቱ የህዝቡ አይደለም ጥፋቱ የእኔና እኔን መሰል  ሃላፊነት የተሰጠን ነው…. ቤተክርስቲያን በሰራቸው ስርዓት ሁሉም ኃላፊነቱን በአግባቡ ካልተወጣ ይጠየቃል፡፡…..ከእግዚአብሔር ያልተሰጠን ምን አለና ነው ወደ ሌላ መቀላወጥ የሚያስፈልገን? ምን ጎደለና ነው እኔ ያልሁት ካልሆን የምለው? “እኔ ነኝ” ባዩ በዝቷል መሰለኝ፡፡ ….ገልጦ መሄድ ንቃተ ህሊና አይደለም፣ ቶሎ ቶሎ መናገር ማጨብጨብ ንቃተ ህሊና አይደለም፣ ዙሪያ ገባችሁ አይታችሁ እንዳትታለሉ፡፡”  የሚል ረጋ ያለ የሰሚውን ልብ የማረከ ጣዕመ ስብከታቸውን ከተሰማ በኋላ በጸሎት መርሐግበብሩ ሲዘጉ ለጸሎት ጉባኤው ቆሞ እንደገና ንግግራቸውን በመቀጠል “ ጉባኤው ከመዘግየቱ በስተቀር መካሄዱ ጥሩ ነው…… ወንጌል ከተሰበከ ከ2004 ዓመት በኋላ ተሰባስባችሁ እንዳደንቃችሁ ትፈልጋላችሁ?” በማለት ጉባኤው ፈገግ ያሰኙ ሲሆን “ በዚህ ዕድሜችሁ ብዙ ነገር ስሩበት፣ እኔ በደጉ ጊዜ አልፊያለሁ፣ አይዟችሁ ገና ነኝ አልሞትም፣ ገና ብዙ እቆያለሁ፡፡” ለቤተክርስቲያን ችግር መፍትሔ “የፓትሪያሪኩን ሞት ለሚናፍቁ” ተስፋ እንዲቆርጡ የተናገሩ ሲሆን፤ “ ….ሁለተኛው ፓትሪያሪክ (አቡነ ቴዎፍሎስ) ለቤተክርስቲያን ያልሰሩት ነገር የለም፡፡ ያኔ እኔ ተላላኪ ነበርኩ፡፡ ልክ እንደ አሁኑ ጋዜጣዊ ሃሜት ነበር፡፡….” በማለት በእርሳቸው ላይ የሚነሱት ቅሬታዎች ለማስተባበል ሞክረዋል፡፡ በዚህ መሃል ነው ቅዱስነታቸው “…… የመለስ አባት ነው ትሉኛላችሁ፤ አዎ የመለስ አባት ነኝ ….”  በማለታቸው የጉባኤውን ድባብ የቀየሩት፡፡ ለዚህ ንግግራቸው እንዲጨበጨብላቸው መ/ር ዕንቁ ባህርይ ከመድረክ በኩል በከፍተኛ ድምፅ ማጨብጨብ የጀመረ ቢሆንም ጉባኤው በንግግራቸው አግባብ ግራ ታጋብቶ ስለ ነበረ ጭብጨባው ለማቋረጥ ተገድዋል፡፡

በጉባኤው  “ወጣትነትና ቤተክርስቲያን” እና “በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ን ሰንበት ት/ቤቶች ትላንት፣ ዛሬና ነገ” በሚል ርዕሶች ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦአል፡፡ የአንድነት ጉባኤው መሪ (ስልታዊ) ዕቅድ ቀርቦ በውይይት እንዲበለጽግ ሆኖአል፡፡ በመጨሻም የአንድነት ጉባኤው አደራጅ አስራ ሦስት አባላት ያሉት አመራር ተሰይሟል፡፡

ይህንን ተከትሎ በመላ ሃገሪቱ የስንበት ት/ቤቶች አንድነት ወረዳዎች ድረስ በመመስረት  ላይ ነው፡፡ በዚህም ሰንበት ት/ቤቶች በቤተክርስቲያን አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ በንቃት በመሳተፍ ቤተክርስቲያን የወጣቱ ተስፋ፣የቤተክርስቲያን ተስፋ ወጣቱ መሆኑን በተግባር እንደሚያሳዩ ተስፋ ተጥሏል፡፡ከዚህ ጋር ተያይዞ ማኅበረቅዱሳን ለመስራች ጉባኤው ሠላሳ አምስት ሺ ብር እንደሰጠ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የማኅበሩ ዋና ጸሃፊ ዲ/ን መምህር ሙሉጌታ ኃ/ማርያም በዋናው ማእከል በተዘጋጀው የሃያኛ አመት የምስረታ በዓል ጉባኤ ላይ ለተገኙ ከአስራ አማስት ሺ በላይ ምእመናን እንደተናገሩት ማኅበሩ የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር ለማጠናከር አብሮአቸው ከሚሰሩት አካላት አንዱ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ማኅበረቅዱሳንም በመላው ዓለም ፳ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን እያከበረ ነው፡፡ እስከ አሁን ድረስ  በዋናው ማእከል እንዲሁም በአገር ውስጥና በውጭ ባሉት ማእከላትና ወረዳ ማእከላቱ  ከ አንድ መቶ ሺ በላይ ምእመናን ያሳተፈ ጉባኤና የእግረ ጉዞ በማድረግ አክብሮአል፡፡ በተለይ በዋናው ማእከል ተዘጋጅቶ የነበረውን የእግር ጉዞ አቡነ ጳውሎስ የፍቃድ ደብዳቤው እንዳይጻፍ በማድገረግና ወ/ሮ አጅግአየሁ በየነ(ኤልዛቤል) የጉዞ መዳረሻ የሆነውን የቅዱስ ሚካኤል ደብር አስተዳዳሪ በማስፈራራት የእግር ጉዞው እንዲደናቀፍ ለማድረግ የሞከሩ ቢሆንም የእግር ጉዞው ወደ ጉባኤ ተቀይሮ በጠቅላይ ቤተክህነቱ ግቢ ተካሂዶአል፡፡ በዚህም አቡነ ጳውሎስ ቤታቸው ሆነው ማኅበሩ በምእመናን ዘንድ ያለውን ተቀባይነት፣  ማኅበሩ ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫ የቤተክርስቲያኒቱን አስተዳደር ማጠናከር መሆኑን እንዲሁም ማኅበሩ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና በቤተክህነቱ የሥራ ሓላፊዎች ዘንድ ያለውን ተቀባይነት ለማድመጥ ተገደዋል፡፡

በጉባኤው ሰባት ብጹዓን ሊቃነጳጳሳት የተገኙ ሲሆን አቡነ ዲዮስቆሮስ “ ቅዱስ ሲኖዶስ ከማኅበሩ ጋር ነው፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ከማኅበሩ ጋር ያለው አንድነት ምንደኞች  ዘመኑ ባመጣው ቴክኖሎጅ ተጠቅመው እንደሚያወሩት የኮሚሽን ጉዳይ ሳይሆን የሃይማኖት ጉዳይ ነው፡፡” ብለዋል፡፡ በአገር ውስጥና በውጭ ባሉት ማእከላትና ወረዳ ማእከላቱ  ከአካባቢያቸው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት አመቺ ቀን በመምረጥ የምስረታ በዓሉን እያከበሩ እንደሚገኙ ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በርክበ ካህናት ስብሰባው ከወሰናቸው ውሳኔዎች ውስጥ የጨለማ ቡድኑን ህገወጥ አካሄድና የአቡነ ጳውሎስ አምባገነንነት የገቱትን ውሳኔዎች ቃለጉባኤ ባለመፈረም ተፋጻሚነታቸው እንዲጓተትና አስተዳደራዊ በደል እንዲባባስ ምክንያት ሆኗል፡፡ የክርስቲያናዊ በጎ አድራጎትና ልማት ኮሚሽንን በቦርድ መመራት፣ የማኅበረቅዱሳንን ለብጹዕ ሥራ አስኪያጁ ተጠሪ መሆንን፣ የአሜሪካ አኅጉረስብትን በተመለከተና የአቡነ ገብርኤልን የነገሌ ቦረና አገረስብከት ሊቀጳጳስ ምደባ የተመለከቱ ቃለጉባኤ ፓትሪያሪኩ ላለፉት አንድ ወር ባለመፈረም ያጎተቱት ሲሆን ከውሰጥም ከውጭ ጫናዎች በመበርታቱ ባለፈው ሣምንት ፈርመዋል፡፡ በተለይ ማኅበረቅዱሳንን የሚመለከተውን ቃለጉባኤ ቀደውት ስለነበር እንደገና ፕሪንተ ተደርጎ መፈረማቸውን ተዘግቧል፡፡ ይህን ተከትሎ ቋሚ ሲኖዶስ የቅዱስ ሲኖዶስ የበላይነት ስለማያከብሩ ከቅዱስነታቸው ጋር መሰብሰብ እንደማይችል በመግለጥ ባለፈው አንድ ወር እንዳልተሰበሰበ ለማወቅ ችለናል፡፡

ከአጀንዳዎች አለመፈረም ጋር ተያይዞ ማኅበረቅዱሳን ከቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ ጋር የሥራ ግንኙነት ለማድረግ መገደዱን ተነግሮአል፡፡  ከባለፈው ጥቅምት ጀምሮ የአገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ያልነበረው የነገሌ ቦረና አገረ ስብከትን አቡነ ገብርኤል ደርበው እንዲያስተዳድሩት ቅዱስ ሲኖዶስ ቢወስንም ክብረ መንግስት ያሉ የተሃድሶ መናፍቃን መንበረ ፓትሪያሪክ ጽ/ቤት ባላቸው ሠንሠለት ምክንያት አቡነ ጳውሎስ እንዳይፈርሙ ሆኖአል፡፡ በተሃድሶዎች ሴራ አቡነ ጳውሎስ የአገረስብከቱን ሥራአስኪያጅ መጋቤ ጥበባት ሲያምር ተክለ ማርያም ያላግባብ እንዲነሳ ያደረጉ ቢሆንም መምህር ሲያምር ፍርድ ቤት ተከራክራክሮ በማሸነፉ ወደ  ሓላፊነቱ በመመለስ አገረ ስብከቱን በጥሩ ሁኔታ እየመራው ቢገኝም ክብረ መንግስት የሚገኙ የተሃድሶ መናፍቃን ተላላኪዎች በአቡነ ጳውሎስ አይዞአችሁ ባይነት የሚፈጠጥሩት ውዝግብ ለመፍታት የሊቀጳጳሱ አገልግሎት መጀመር ቁልፍ ተግባር መሆኑ እየተገለጸ ነው፡፡ ቋሚ ሲኖዶስ የቅዱስነታቸውን እምቢተኝነት ለበዓለ ሢመት ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በማቅረብ እልባት እንዲያገኝ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በምንደኛው ኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን፣ በተሃድሶ ኑፋቄ የሚጠረጠረው አእመረ አሸብር፣ በዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ በንቡረ እድ ኤልያስ አስተባባሪነት እንዲሁም በአሜሪካ አገረስብከት ተስፈኛዎቹ አቡነ ማርቆስ ቡራኬ  አቡነ ጳውሎስ ለባለፉት አምሰት አመታት ሲያስቡት የቆዩትን ማኅበረቅዱሳንን የሚገዳደርና ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ የርሳቸውን አምባገነንነት ለመግታት በጥብዓት የሚታገሉተን አባቶችን ለማሸማቀቅ የሚሰራ “ማኅበር” እንዲቋቋም የነበራቸውን ፍላጎት እውን ለማድረግ በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ነበር፡፡ የቡድኑን መሰሪ አካሄድ በተለይ በደጀ ሰላም ይፋ ከተደረገ በኋላ ቡድኑ ተፈረካክሷል፡፡

 የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥራአስኪያጅ ተስፋዬ ውብሸት፣ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ዋና ኃላፊ እስክንድር ገ/ክርስቶስና የገዳማት መምሪያ ዋና ኃላፊ ሰለሞን ቶልቻ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ራሳቸውን ከምስረታው በፊት ራሳቸውን አግልለዋል፡፡ የሃሳቡ ባለቤት አቡነ ጳውሎስ ቢሆኑም የተሃድሶ ኑፋቄ አራማጆች አጋጣሚውን ተጠቅመው ቤተክርስቲያነቱን በሂደት በሁለት ለመክፈል እንደቋመጡ ተነግሮአል፡፡ የዚህን ህገ ወጥ ቡድን እንቅስቃሴ የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በጥንቃቄ እየተመለከቱት መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና አቡነ ፊሊጶስ የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራአስኪያጅ  ቡድኑን ቤተክርስቲያን እንደማታውቀው ለስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ ገልጸዋል፡፡ የብጹዓን ሊቀነጳጳሳትን አቋምና ጠቅላይ ቤተክህነት ላይ ያለውን ተቃውሞ በመመልከት አቡነ ጳውሎስ ስልታዊ ለውጥ በማድረግ የቡድኑ ጉዳይ በቋሚ ሲኖዶስ ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደሚታይ ለአስተባባሪዎቹ እንደነገሯቸው ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡ከውስጥ የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ኅላፊዎችና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተቃውሞ እንዲሁም የመንግስት ማስጠንቀቂያን ተከትሎ ቡድኑ ፓትሪያሪኩ አግደወታል፡፡እገዳው  በጠቅላይ ቤተክህነቱ ጠቅላላ አገልግሎቱ ደብዳቤ እንደሚጸና እየተጠበቀ ነው 
ምናልባትም በበዓለ ሢመት በሚገኙ አባቶች የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ  “ጉባኤ አርድእት ዘተዋህዶ” እውቅና ለመስጠት እንደታሰበ እየተነገረ ነው፡፡ የርክበ ካህናቱን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አተገባበር እንዲሁም አሁን እየታዪ ላሉ አስተዳደራዊ ችግሮች ዙሪያ ለመምከር አይገኙም ተብለው በጨለማ ቡድን የሚገመቱ ብጽኑዓን ሊቃነጳጳሳት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ 

ቸር ወሬ ያሰማን!


9 comments:

  1. የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥራአስኪያጅ ተስፋዬ ውብሸት፣ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ዋና ኃላፊ እስክንድር ገ/ክርስቶስና የገዳማት መምሪያ ዋና ኃላፊ ሰለሞን ቶልቻ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ራሳቸውን ከምስረታው በፊት ራሳቸውን አግልለዋል፡፡ የሃሳቡ ባለቤት አቡነ ጳውሎስ ቢሆኑም የተሃድሶ ኑፋቄ አራማጆች አጋጣሚውን ተጠቅመው ቤተክርስቲያነቱን በሂደት በሁለት ለመክፈል እንደቋመጡ ተነግሮአል፡፡ የዚህን ህገ ወጥ ቡድን እንቅስቃሴ የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በጥንቃቄ እየተመለከቱት መሆኑን የተገለጸ ሲሆን ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና አቡነ ፊሊጶስ የጠቅላይ ቤተክህነት ሥራአስኪያጅ ቡድኑን ቤተክርስቲያን እንደማታውቀው ለስምዓ ጽድቅ ጋዜጣ ገልጸዋል፡፡ የብጹዓን ሊቀነጳጳሳትን አቋምና ጠቅላይ ቤተክህነት ላይ ያለውን ተቃውሞ በመመልከት አቡነ ጳውሎስ ስልታዊ ለውጥ በማድረግ የቡድኑ ጉዳይ በቋሚ ሲኖዶስ ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ እንደሚታይ ለአስተባባሪዎቹ እንደነገሯቸው ምንጮቻችን ዘግበዋል፡፡ከውስጥ የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ኅላፊዎችና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተቃውሞ እንዲሁም የመንግስት ማስጠንቀቂያን ተከትሎ ቡድኑ ፓትሪያሪኩ አግደወታል፡፡እገዳው በጠቅላይ ቤተክህነቱ ጠቅላላ አገልግሎቱ ደብዳቤ እንደሚጸና እየተጠበቀ ነው
    ምናልባትም በበዓለ ሢመት በሚገኙ አባቶች የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ “ጉባኤ አርድእት ዘተዋህዶ” እውቅና ለመስጠት እንደታሰበ እየተነገረ ነው፡፡ የርክበ ካህናቱን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አተገባበር እንዲሁም አሁን እየታዪ ላሉ አስተዳደራዊ ችግሮች ዙሪያ ለመምከር አይገኙም ተብለው በጨለማ ቡድን የሚገመቱ ብጽኑዓን ሊቃነጳጳሳት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

    ReplyDelete
  2. gude bele goneder

    we ethiopia mechawecha honeche eko endihe yemenafeqane mefencha tehune

    egiziabehere betekirstiyanenen yetebeqe!!!

    ReplyDelete
  3. አምስት ኪሎ ቅ/ማርያም መንበረ ፓትርያርክ ላይ ከፓትርያርኩ ፎቶ ቀጥሎ የተጻፈው
    ‹20 ውጤታማ አመታት›

    ReplyDelete
  4. thanks for the nfo and very good. God will protect our church from all these "ጉደኞች" but these "ብጽኑዓን ሊቃነጳጳሳት አዲስ አበባ ገብተዋል" is not polite way of describing the "ብጹዓን ሊቃነጳጳሳት". I know the felling and some of them deserve like Abune Fanuel.

    ReplyDelete
  5. Ebakachihu, Abune Fanuel Seattle Limetu newina, Mi'emenan endiyawikut Zena Tsafulin ebakachihu. Betechale akim mulu tinikirun enilikilachihualen, lahunu gin Abune Fanuel will be here in Seattle on July 20th 2012.

    Yihe hone tebilo yetesera debba new. Yawim beAba Woldesemayat yekidus michael astedadari sherr, keza mi'emenanin ke Kidus Amanuel betekirstian lemerebesh yetesera new. Aba Fanuel beketita Kidus Amanuel betekirstian endemimetu tawikoal. Mulu zirzirun enilikilachualen. Please help us on distributing the news to Seattle peoples.

    ReplyDelete
  6. ጉባዔ አርድዕት ዘኦርቶዶክስ በቤተክርስቲያን ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ ማህበረ ቅዱሳን የበተናቸውን የቤተክርስቲያን ልጆች ጉባዔ አርድዕት ይሰበስባቸዋል፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. Egziyabhare sil betekristiyan lijoj yemichenek lib(ማህበረ ቅዱሳን )yfterlh: MK silemitefaw sayhon silemaytefaw yemiyasbu shiwochin Be Egziyabhare hayl eyesebesebe new....lewedefitum ysebesibal...Egziyabhare mastwalun ystih!!

      Delete
  7. ማኅበረ ቅድሳንን የሚጠላ ከመጀመሪያዉ ማኅበሩን አያውቀዉም ወይም የቤተክርስቲያንን መጥፋት የሚናፍቅ ጠላት ነዉ ወይም የጥቅም ሰዉ ነዉ፡፡ ለቤተክርስቲያን ልማት አንድነቱ ተጠናክሮ ይቀጥል፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. ሀሳብህን ኣታሳንስ እንዲያውም ማቅን መጥላት ያለበት ቤተክርስቲያንን የሚወድ ሰው ነው፡፡ የነብሰ ገዳይ እና የአውሬ ድርጅትን ወዋጋት ያስፈልጋል፡፡ሀሳብህን ኣታሳንስ እንዲያውም ማቅን መጥላት ያለበት ቤተክርስቲያንን የሚወድ ሰው ነው፡፡ የነብሰ ገዳይ እና የአውሬ ድርጅትን ወዋጋት ያስፈልጋል፡፡

      Delete