Wednesday, July 11, 2012

የደብረብርሃን ቅድሥት ሥላሴ ቤተክርስትያን 100ኛ ዓመት በዓል በታላቅ ድምቀት ሐምሌ 7/2004 ዓ.ም ይከብራል፡፡



ከአፄ ዘርአያዕቆብ እስከ ንጉስ አዝማች ወሰን ሰገድ
(አንድ አድርገን ሐምሌ 4 ፤ 2004ዓ.ም)፡- የቀድሞ ስሟ ደብረ ኤባ በመባል የምታወቀዋ የአሁኒቷ ደብረ ብርሃን ከተማ በዘመኑ በአፄ ዘርአያዕቆብ ዘመነ መንግስት በዚች ከተማ እስጢፋና ተከታዮቹ ለማርያምና ለመስቀሉ አንሰግድም የሚሉ ሀይማኖት ተቃዋሚዎች በማንሳታቸው የእስጢፋን ተከታዮች ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ለመመለስ በአምስት መቶ የሀይማኖት ሊቃውንት በደብረ ኤባ ጉባኤ ተደርጎ የሀይማኖት ክትትል ከተደረገ በኋላ የእምነቱ ተከታዮች የኦርቶዶክስን ሃይማኖት አንቀበልም በማለታቸው በወቅቱ እንዲለዩ መደረጋቸው ታሪክ ይናገራል፡፡

ይህ የታሪክ ክስተት ከተፈፀመ በኋላ ከተደረጉ ተአምራቶች አንዱና ዋነኛ ከኦርቶዶክስ ከተለዩ በ38ኛው ቀን መጋቢት 10/1446 ዓ.ም 3 ጊዜ ሁለቱ በስረአት ቁርባን አንዱ ካህናቱ ስበሀተ እግዚአብሔር በሚያደርሱበት ሰአት ብርሃን ከሰማይ እንደወረደ በዚህም ምክንያት የከተማዋ ስም ደብረ ብርሃን ተብሎ እንደተሰየመ ዜና መዋዕላቸው ይገልፃል፡፡


  “ይህ ብርሃን የወረደበት ስፍራ በአሁ ጊዜ ለደ/ብርሃን ቅድስ ሥላሴ ቤተክርስቲያ ግቢ ውስጥ በምስራቅ ፊት ለፊት በግንብና በብረት የተከበበች ቦታና በላይዋ ላይም ፅጌሬዳ፣ቀጋ በቅሎባት የምትገኝ ስፍራ ናት “፡፡
ከዚያም ንጉሡ በገቡት ቃል መሰረት አሁን ደብረ ብርሃን ቅድስ ሥላሴ ቤተክርስቲያን ባለበት ቦታ ላይ ቤተ- እየሱስ፣ቤተ-ማርያም እና ቤተ-መስቀልን አብያተ ቤተክርስቲያናትን አሳንፀው ነበር፡፡ ይሁንና ንጉሱ ጳጉሜ 3/1460 ዓ.ም አረፉ ከዚህ በኋላ ብዙ ነገሥታት ተፈራርቀው በአህመድ ግራኝ ዘመን 3ቱ አብያተ ክርስቲያናት በሚያሳዝን ሁኔታ የያዙትን ቅርስ ጨምሮ ተቃጥለው ወደሙ፡፡

 ከመርዕድ አዝማች ወሠን ሰገድ እስከ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ
ከደረሰበት ውድመትና መረሳት በኃላ በ1800 እስከ 1805 ዓ.ም ደብረ ብርሃን ከተማና ቅድስ ስላሴን ቤተክርስቲያን አሁን ባለበት ቦታ ላይ መርዕድ አዝማች ወሰን ሰገድ እንዳሳነፁ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገ/ስላሴ በጽሁፋቸው አስፍረዋል፡፡

ከዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ እስከ አሁን
ከበርካታ ዓመታት በኋ እንደገና እግዚአብሔር ፈቅዶ አሁኑ 100 አመቱን ሐምሌ 7/2004ዓ.ም ልናከብረው የፈቀደልንን የደብረ ብርሃን ቅድስ ስላሴ ቤተክርስቲያን በኖራ በእንግዳ አይነት ስራ በአዲስ ተሻሽሎ በ1897 ተጀምሮ በ1904 ዓ.ም በንጉስ ዳግማዊ ሚኒሊክ እንደተጠናቀቀ የንጉሱ ፀሐፊ ትዕዛዝ ደብረ ስላሴ በፁሑፋቸው አስቀምጠዋል ፡፡  ይህን ታላቅና ታሪካዊ  ቤተክርስቲያን በዘመናዊነትና ለትውልድ እንዲተላለፍ እና አሁን የያዘውን ውበት በጠበቀ መልኩ ያነፀው ባለሙያ መሐንዲስ የግሪክ ተወላጅ የሆነው ዩሐንስ አርጌኒ ሲሆን  ቤተክርስቲያንኑ አንፆ  ጨርሶ አስረክቦ በመሄድ ላይ ሳለ በመንገድ ላይ ደብረ ብርሃንን ሳይወጣ ሕይወቱ  በማለፉ እዚሁ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደተቀበረ በስተ ሰሜን በኩል የሚገኝው ሃውልቱ ይናገራል፡፡

  በተጨማሪም ከግብፅ አፄ ዘርያዕቆብ ያስመጧቸው በተዓምረ ማርያም ላይ የምናገኛቸው ሊቃነ ጳጳሳት ፣አባ ሚካኤል ያረፉት በዚሁ ቅዱስ ቦታ ሲሆን መካነ መቃብራቸውም  ከቤተ ክርስትያኑ በስተ ምስራቅ ብርሃን ከወረደበት ሥፍራ አጠገብ የሚገኝ ሲሆን ታላላቅ ወይራዎች በቅሎበት በአሁኑ ወቅት ይታያል፡፡ በአጠቃላይ ይህ ሥፍራ በታላላቅ በቅዱሳን የተከበበ ፤ በርካታ አብያተክርስትያናት የሚገኙበት፤ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በርካታ አሻራዎች የሚገኙበት ፤ ከሺህዎች የሚቆጠሩ የአብያክርስትያናትን ያቀፈ ሀገረ ስብከት ባለቤት መሆኑ ይታወቃል፡፡

 ቤተ ክርስቲያኒቷ በአሁኑ ሰአት ከአባቶች የተቀበለችውን ስርዓትና አገልግሎት ጠንቅቃ ጠብቃ ለአገር ሰላም ምህረት የሚሰጥ አገልግሎት ከአመት አመት የቅዳሴ ፣ የሰአታት ፣የማህሌትና ስብሀተ-ነግህ እንዲሁም በሰሞነ ህማማት የግብረ ህማማትና የልዩ ልዩ የቅዱሳን ፣ የፃድቃን ፣ የሰማዕታት ገድል ድርሳና ታዕምር የሚፀለይበትና አገልግሎት የማይቋረጥበት ታላቅና በረከት የሚገኝበት ስፍራ መሆኑን እየገለፅንላችሁ የ100  አመት በዓሉን ምክንያት በማድረግ በዓሉን አክብራችሁ ለቦታው የተሰጠውን ክብርና ፀጋ እንዲሁም ቃል ኪዳን አግኝታችሁ እንድትሄዱ እያልን ጥራችንን በአጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ ስም እያስተላለፍን በአሁኑ ሰአት ቤተክርስቲያኒቷ በልዩ ልዩ ልማት ተሰማርታ የምትገኝ መሆኑን በመሆኑ ለዚህም ልማት የበኩላችሁን ድጋፍ ተሳትፎ እንድታደርጉ ስንል በድጋሚ  ጥሪያችንን እናስተላፋለን፡፡
እናስተላልፋለን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

አድራሻ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን 130 ኪ.ሜ ደ/ብርሃን ከተማ

5 comments:

  1. te welge yadekuteg D/B selasy akababy new bewnet 100 ametun sakeber hegy balmakbery betam new yazenkut melkam beal yehun

    ReplyDelete
  2. May GOD bless you I know the church before 14 years when I was college student it is really very intersting church having numerous orthodox church "qerses" inside it. so it is nice to participate for this interesting idea for this a century old church.

    ReplyDelete
  3. esey temelesachu degmo? yaw yelemedachutena mk weye mote zefenzchun gemerachu aydel? setasetelu

    ReplyDelete
  4. Dear Andadrgen wellcome back guys

    Excellent information May God bless u all.

    ReplyDelete