Monday, June 27, 2016

ከኤጲስ ቆጶሳት እጩ አንዱ ‹‹አባ ተክለ ማርያም አምኜ››




(አንድ አድርገን ሰኔ 20 2008 ዓ.ም )፡- እስከ አሁን ድረስ በተለያዩ መንገዶች የተጠቆሙ እና አስመራጭ ኮሚቴው እንደተቀበላቸው ከተገለጹት ቆሞሳትና መነኮሳት ስም ዝርዝር ውስጥ  አባ ተክለ ማርያም አምኜ ይገኙበታል ፡ ስለዚህ ሰው የጀርባ ታሪክ አስመራጭ ኮሚቴው ለማወቅ  የኢትዮጵያ ፀረ ሙስና ኮሚሽን ፤ የጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ የየካ ሚካኤል አገልጋዮች ፣ ሰበካ ጉባኤና //ቤት፡፡  የጊዮርጊስ አገልጋዮች ፣ ሰበካ ጉባኤና //ቤት ፡፡ የምስካዬ ኅዙናን መድኃኔ ዓለም ገዳም አገልጋዮች፣ ሰበካ ጉባኤና //ቤት ፡፡ የልደታ ለማርያምና የመድኃኔ ዓለም  አገልጋዮች ፤ ሰበካ ጉባኤና //ቤት ቢሄዱ  የአባ ተክለ ማርያም አምኜን ታሪክ በቀላሉ ማግኝት ይቻላል፡፡


ሲጀመር ስንዴውን ከእንክርዳድ መለየት ግድ ነው ፤ ይህን ፈቃደ እግዚአብሔር የሚያስፈልገውን ሹመት ፍላጎትን መሰረት ብቻ አድርገው ከሚመጡ ሰዎች ሊጠበቅ ይገባል፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ ወሳኝ አካል ቅዱስ ሲኖዶስ ሲሆን ተመራጮች ከተመረጡበት ጊዜ በኋላ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እንደሚሆኑ እሙን ነው ፤ እነዚህን 14 አዲስ  ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሂደት ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡  ‹‹አንድ አድርገን›› ኮሚቴው ስለኝህ ሰው ታሪክ ከላይ የተጠቀሱትን አካላት ጋር መሄድ ብቻ የዚህን ሰው የቀድሞ ማንነት ለማወቅ ብቁ ነው ብላ ታምናለች፡
ስለዚህ ‹‹አንድ አድርገን›› ካላይ የጠቀሰቻቸው አብያተ ክርስቲያናት የምታገለግሉ ካህናት ዲያቆናት እንዲሁም ሰንበት ትምህርት ቤቶች ምዕመናትና ምዕመናን ስለዚህ ሰው የምታውቁትን ፣ያያችሁትን ፣ስለ እሱ እጃችሁ ላይ ያለውን መረጃ ለአስመራጭ ኮሚቴው በመሰጠት ይተባበሩ ዘንድ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም ትማጸናለች፡፡

ይቀጥላል .. 

3 comments:

  1. I know this priest before he came to Addis or US. He has a very ugly back ground please check him from his previous churches he worked in like in Bahir Dar

    Thank you

    ReplyDelete
  2. Please indicate the address of the committee to provide information for the candidate.

    ReplyDelete