Monday, June 27, 2016

‹‹ያለ ነውጥ ለውጥ አይገኝም› ከእጩዎቹ ውስጥ የተገኙት አባ ናትናኤል(አንድ አድርገን ሰኔ 20 2008 ዓ.ም )፤- አባ ናትናኤል ይባላሉ በአሁኑ ወቅት ለጵጵስና እየተጠቆሙ ካሉ አባቶች ውስጥ ስማቸው  ይገኛል፡፡ አባ ናትናኤል ከዚህ በፊት ያላቸው የኋላ ታሪክ ምን ይመስላል የሚለውን ምዕመናን እንዲያውቁትና አስመራጭ ኮሚቴው በራሱ መንገድ ማጣራት ያካሂድ ዘንድ ፤  ለቤተክርስቲያን ያለፉት አመታት የተከናወኑት ድርጊቶች ዳግም እንዳንመለከታቸው አሁን ላይ ሆነን ሃላፊነታችንን ከመወጣት ምዕመኑን ከማንቃት አንጻር እንዲህ አቅርበነዋል፡፡


አባ ናትናኤል ከአራት ዓመት በፊት   የሀዋሳን   ህዝብ  ሲያስለቅሱት   የነበሩት ደብረ ገነት  ቅድስት ሥላሴ  ቤተክርስቲያን   አስተዳዳሪ ለአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን  አስተዳዳሪ ተደርገው  ከቤተክህነት  ተሾሙው ነበር ፤ ነገር ግን ህዝቡ በጊዜው እኝን አባት አስተዳዳሪ አድርገን አንቀበልም ብሎ እሳቸው በእግራቸው ቢመጡም በኮንትራት ታክሲ ከቤተክርስቲያን አባሯቸው ነበር ፤  በተሐድሶ እና ከፕሮቴስታንት  አራማጆች (ተስፋኪዳነምህረት ማህበር እና ከመሰሎቻቸው ) ጋር  በመሆን የእግዚአብሔርን  አውደ ምህረት  እንዲፈነጩበት ካደረጉ ሰዎች መካከል ግንባር ቀደሙን የሚይዙ ሰው ናቸው ፡፡


በጊዜው  ገንዘብ  አይናቸውን  አሳውሯቸው ፤ ለአውደ ምህረት  የማይመጥኑ ፤ ትምህርቱ የሌላቸው  ሰዎችን በመጋበዝ ህዝቡን  እዚህ  ደረጃ  እንዲደርስ  ካደረኩ  ሰዎች  መካከል አንዱ ናቸው፡፡ የአየር ጤና ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ አስተዳዳሪ ተደርገው ተሹመው የነበሩት አባ ናትናኤል መላኩ  በተጠረጠሩበት ወንጀል ጥቅምት 2 ቀን 2 005 ዓ.ም በአዋሳ  ፖሊሶች  ተይዘው  ተወስደው ነበር፡፡  የአዋሳ  ቅድስት ሥላሴ  አጥቢያ ህዝብ  ከ170 ሺህ ብር  በላይ እና  በቤተክርስቲያኗ መኪና ዝርፊያ ክስ  በመመስረቱና ፍርድ ቤቱ  ተይዘው እንዲቀርቡ  በማዘዙ  አለምገና  አካባቢ  ከሚገኘው  መኖርያ  ቤታቸው ተይዘው ተወስደው ነበር፡፡ በጊዜው አባ ናትናኤል ለአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን  አስተዳዳሪ ተደርገው ሲመደቡ ፤   የሃይማኖት ሕፀፅ እንዳለባቸው ፤ ሐዋሳ ላይ ከእነ በጋሻው ጋር ግሩፕ በመፍጠር ‹‹ያለ ነውጥ ለውጥ አይገኝም› ብሎ በመስበክ ፤ ሰውን ለአመፅ በማነሳሳት ፤ እና በከፍተኛ ሁኔታ የገንዘብ ምዝበራ ወንጀል ክስ የቀረበባቸው በመሆኑ እንደዚህ ዓይነት ሰው መመደቡ ለቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑ በጊዜው እንዲመለሱ እንዲደረግ በማለት ለሕዝቡ አስፈላጊው መግለጫ ከተደረገ በኋላ ሕዝቡም የ‹‹አንፈልጋቸውም›› ድጋፉን  በመግለጹ በመጡበት እግራቸው በሰላም ሌላ ብጥብጥ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ከመከሰቱ በፊት  ሸኝተዋችዋል ነበር ፡፡


በጊዜው የቤተክርስቲያኗ አባቶች ተሰብስበው ቤታቸው ያለ አስተዳዳሪ በመቆየቱ ቤተክህነት ድረስ በመሄድ “አባት ይሾምልን ያለ አስተዳዳሪ ወራት ቆጠርን” ብለው በአንድነት ጥያቄያቸውን አቅርበው ነበር፡፡ ከቀድሞ ፓትርያርክ ከአቡነ ጳውሎስ የተሰጣቸው መልስ ግን ‹የተሸመላችሁን አባት ለምን አልተቀበላችሁም›የሚል ነበር ፡፡ ያልተቀበሉበትን ምክንያት አስረግጠው በመነጋገር “በቃ እሺ ይሾምላቿል” ብሏቸዋቸው ካበቁ በኋላ  ‹‹ማነው ደግሞ አልቀበልም ያለው›› ብለው በፊት የሾሟቸውን የተሀድሶ አቀንቃኝ አባ ናትናኤልን ደግመው ሾመውላቸዋል፡፡ እሳቸውም እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ አስተዳዳሪ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ 


ጊዜያት ሊያልፉ ይችላሉ ወራት ሊፈራረቁ ይችላሉ ዓመታትም ሊቆጠሩ ይችላሉ ፤ ሰዎች ግን ቤተክርስቲያን ላይ በፈጸሙት ወንጀል ተጠያቂ የማይሆኑበት አንዳች ምክንያት አይኖርም፡፡ አባ ናትናኤል  ጥቅምት 20 ቀን 2005 . በድጋሚ ታስረው ከአዲስ አበባ ወደ አዋሳ ተወስደዋል፡፡  ግለሰቡ ባለፈው ከመኖሪያ ቤታቸው አዋሳ ድረስ ታስረው  ከተወሰዱና  በዋስ ከተፈቱ  በኋላ  ጥቅምት 11  ቀን  እሁድ  በአየርጤና  ኪዳነ  ምህረት  / አውደ  ምህረት ላይ  “ሰዎች በክፋት ወንጅለውኝ ነበር፣  የህግ  አካላት  ግን  አባታችን  ይቅርታ  ብለው  አሰናብተውኝ መጥቻለሁ፡፡  እነኝህ  የሚሳሳቱ  ሰዎችን  እግዚአብሔር  ይቅር እንዲላቸው ምዕመናን  ጸልዩላቸው  ብለው ነበር፡፡ 

በዕለቱም ሲወጡና ሲገቡ  ልዩ ጥበቃ እንዲያደርጉላቸውና  በየምክንያቱ  ህገወጥ እገዳ በሚያደርጉባቸው  ምዕመናን ላይ መሳሪያ  ይዘው  እንዲያስፈራሩ  ከቀጠሯቸው  5 ዘበኞች አንዱ ፣ ከጽጌ ማዕድ ትርፍራፊ  ለመቃረም  ከተሰበሰቡ  ነዳያን መካከል  አንድ ምስኪን በዱላ አንገቱን መትቶ ገሏል፡፡  በጊዜው ሁኔታው  እንደተፈጠረ  አባ ናትናኤል  ግቢውን  ትተው  ቢሸሹም  ጥበቃውና  አንድ ካህን ፣ እንዲሁም  የሟች አስክሬን በፖሊሶች ተወስዷል፡፡


ከዚህ በተጨማሪም ለክሊኒክ መገንቢያ በሊዝ የተገኘን  የደብሩን  ይዞታ  ለቱርኮች  ያለሰበካ  ጉባዔው  ዕውቅና  በማከራየትና  የተሳሳተ መረጃ  አውደ  ምህረት  ላይ በማቅረብ  ምዕመኑን  ለመከፋፈል  ሲሞክሩ  ቆይተዋል፡፡

በወቅቱ የደብሩ  ምዕመንም  ሁሉ ነገር  ከአቅሙ በላይ  ስለሆነበት ምእመናንንና ወጣቶችን ሳይከፋፍል ፣ የደብሩን ሰላም ሳያደፈርስ፣  ስብከተ  ወንጌልን  ሳያዳክም  የደብራችንን  ንብረት ከብክነት  ጠብቆ፣  መልካም አስተዳደር አስፍኖ፣በመንፈሳዊ ሕይወት አርአያ ሆኖን የደብራችንን ልማት የሚያፋጥን አስተዳዳሪ እንዲመደብልን እኛ የአየር ጤናአ// ኪዳነ ምህረት / ምዕመናን ቅዱስ ሲኖዶስን እንለምናለን !”  የሚል መሸኛ ያለው ፊርማ በማሰባሰብ አቃቢ መንበሩንና የቋሚ ሲኖዶስ አባላትን በወቅቱ ሲለምኑ ነበር፡፡


‹‹አንድ አድርገን›› ከብዙ በጣም በጥቂቱ ለአስመራጭ ኮሚቴው የማጣሪያ መንገድ ይሆን ዘንድ ስለእኚ እጩ ይህን ብለናል፡፡ እኚህን የመሰሉ ሰዎች ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ቢቀርቡ ቤተክርስቲያኒቱ ላይ የሚመጣው ቀውስ ከሕንድ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ቢብስ እንጂ የሚሻል አይሆንም ፤  ሁሉም ምዕመን የተጠቆሙትን አባቶች የቀድሞ ታሪካቸውን ለአስመራጭ ኮሚቴው የማድረስ ሃይማኖታዊ ግዴታ አለበት ፤ ስለ እጩዎቹ ያላችሁን መረጃ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ያላችሁ የቤተክርስቲያን ልጆች በ‹‹አንድ አድርገን›› የፌስ ቡክ አድራሻ ታደርሱን ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን፡፡ ለነገ ሰላማዊ አውድ ዛሬ ትብብራችንን እናጠንክር፡፡


2 comments:

  1. Good information!

    ReplyDelete
  2. ይቅርታ አድርጉልኝና በአየር ጤና ኪዳነምህረት አሁን ባለፈው ሆሳዕና እና ፀሎተ ሐሙስ እንኳን ያየሁት የስርዓት መፋለስ በጣም በወቅቱ በጣም አሳዝኖኝ ነበር በየዕለቱም አንዳንድ የስርዓት መዛባት አያለሁና ሊታረም ይገባል፡፡ ለምሣሌ ከአሁኑ እሁድ በስተቀር በቅዱስ ቁርባኑ ሰዓት የእመቤታችን ታምር የሚነበብበት ብቸኛዋ ቤ/ክርስቲያን የአየር ጤና ኪዳነምህረት ትመስለኛለች እንዲህ እንዲህ እያለ ነውና ስርዓት እየተፋለሰ የሚሄደው ከአሁኑ ሊታረም ይገባል፡፡

    ReplyDelete