Monday, February 23, 2015

ሃያ አንደኛው ሰማዕት



አንድ አድርገን የካቲት 16 2007 ዓ.ም
/ ሄኖክ ኃይሌ
 henoktsehafi@gmail.com

  •   '' ክርስቲያንና ዕጣን አንድ ናቸው:: ሁለቱም መዓዛቸው የሚታወቀው እሳት ውስጥ ሲገቡ ነው'' ፓትርያርክ ታዋድሮስ

ሰሞኑን በሊቢያ ባሕር ዳርቻ ላይ የግብፅ ኦርቶዶክስ ምእመናን የሆኑ ወጣቶች አምላካችንን አንክድም ብለው እንደ በግ ተነድተው ሲታረዱ ተመልክተናል፡፡ የቤተ ክርስቲያን ራስ ክርስቶስ ነው፡፡ አንዱ አካል ሲሰቃይ ሌላው አካል መታመሙ አይቀርምና የእነርሱ ስቃይ የክርስቶስ አካል ክፍሎች ለሆንን ሁላችም ተሰምቶናል፡፡ የአምላካቸውን ስም እየጠሩ የታረዱት ምእመናን በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚገኙ ሥራ ፍለጋ ወደ ሊቢያ የሔዱና አንዳንዶቹም ጋብቻ ለመመሥረት እየተዘጋጁ የነበሩ ናቸው፡፡ ሆኖም የአምላካቸውን ስም ጠርተው ሰማያዊ ሙሽሮች ሆኑ፡፡ ምንም እንኳን በምድራዊ ዓይን ስናየው እጅግ አሰቃቂ ቢሆንም እነዚህ ኦርቶዶክሳዊያን ወጣቶች ያለ አንዳች ተቃውሞ በፈቃደነት የተቀበሉት ሰማዕትነት እጅግ የሚያስቀና እና ሰማያዊ አክሊል የሚያጎናጽፋቸው ነው፡፡ በሰማይም ከመሰዊያው አጠገብ ቆመው ከሚያማልዱ ቅዱሳን ሰማዕታት ማኅበር ተደምረው ‹‹በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም›› እንደሚሉ ነጭ ልብስም ተሰጥቷቸው እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንደሚያርፉ›› እናምናለን:: /ራእ 6:11/

እነዚህ ሰማዕታት ሃያ አንድ ሲሆኑ የግብጽ ኦርቶዶክስ ምእመናን የሆኑት ሃያዎቹ ናቸው:: ሃያ አንደኛው ከግብጻውያኑ ጋር አብሮ ይሠራ የነበረ የቻድ ዜጋ የሆነ በቀለሙም ከእነሱ የተለየ ወጣት ነበር:: የግብጻውያኑን የሃይማኖት ጥንካሬ ባየ ጊዜ አምላካቸው አምላኬ ነው አለ:: ከጌታ ቀኝ እንደተሰቀለው ወንበዴ ከሞት አፋፍ ላይ በመንግሥትህ አስበኝ ብሎ አመነ:: የደም ጥምቀት ተጠምቆ ለክብር በቃ::

ከዓመት በፊት ፓትርያርክ ታዋድሮስ እንዲህ ብለው ነበር:: '' ክርስቲያንና ዕጣን አንድ ናቸው:: ሁለቱም መዓዛቸው የሚታወቀው እሳት ውስጥ ሲገቡ ነው'' በእርግጥም የሃያዎቹ ክርስቲያኖች መዓዛ የዚህን የቻድ ወጣት ልብ ማረከው:: ''በሚድኑት ዘንድ የክርስቶስ መዓዛ ነን'' 2 ቆሮ 2:15

ከሰማዕታቱ በረከት ያሳትፈን!


/Sources for the News : Indian Orthodox Diaspora /Fb page/ , Radio Vatican news/
በታላቁ ጾም መጀመሪያ ሰማዕትነትን የተቀበሉትን የኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ወንድሞቻችንን እስከ እለተ ትንሳኤ እናስባቸው፡፡

5 comments:

  1. awen ezame enasbachawal egzabeher mengesta samyeten endamywersatchew anetraterm!!

    ReplyDelete
  2. Below, please find the most recent list of names of the 21 New Martyrs of Libya for use in prayers and publications.

    Milad Makeen Zaky
    Abanub Ayad Atiya
    Maged Soliman Shehata
    Youssef Shukry Younan
    Kirollos Boshra Fawzy
    Bishoy Astafanous Kamel
    Samuel Astafanous Kamel
    Malak Ibrahim Sinyout
    Tawadros Youssef Tawadros
    Gerges Milad Sinyout
    Mina Fayez Aziz
    Hany Abdel Mesih Salib
    Samuel Alham Wilson
    Ezzat Boshra Naseef
    Luka Nagaty Anis
    Gaber Mounir Adly
    Essam Baddar Samir
    Malak Farag Abrahim
    Sameh Salah Farouk
    Gerges Samir Megally
    Mathew Ayairga (from Ghana)

    So, is he from Chad or Ghana? just out of curiosity.

    ReplyDelete
  3. ‹‹በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም››

    ReplyDelete
  4. ‹‹በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም››

    ReplyDelete
  5. kesemaetatu gar yichemirachew amen eskemechreshaw yetsena ersu yidnal yetebalewn kal enersu fetsimewtalna genet botachew endemitihon anteraterm!!


    ReplyDelete