Sunday, July 17, 2016

አባ ሚካኤል ገ/ማሪያም ፡ እንኳን ለጵጵስና ላሉበት ምንኩስና የሚያበቃ ሥነ-ምግባርና የመምራት አቅም የላቸውም


ቀን፡-  08/11/08 .
 ለኢ/////////ቤት
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፦ ቆሞስ መላከ ጽዮን አባ ሚካኤል /ማሪያምን ይመለከታል
በስም ተጠቃሹ አባት የከምባታ ጠምባሮና ሀላባ /ስብከት /ቤት ሥራ አስኪያጅ ሲሆኑ በአሁን ሰዓት ለጵጵስና ማዕረግ መታጨታቸውን በመገናኛ ብዙሓን ተገልፆ ሰምተናል። ዳሩ ግን እኒህ አባት እንኳን ለጵጵስና ላሉበት ምንኩስና የሚያበቃ ሥነ-ምግባርና የመምራት አቅም ያላቸው አባት ሳይሆኑ ለምዕመናን መሰናከያ ከመሆናቸውም ባሻገር የቤተክርስቲያንን ህልውና ደፍረው የሚያስደፍሩ ናቸው። ለዚህም መገለጫ ከሚሆኑት ጥቂቶቹን ብንጠቅስ፦
1) ኮረዳዎችን ከዱራሜ ከተማ ወደ አዲስ አበባ ከተማ በመውሰድ ቤት ተከራይተው በቅምጥነት የሚያኖሩና ለሥራ ወደሄዱበት ሁሉ ይዘው በመዘዋወራቸው አገር ጉድ ያላቸው ናቸው።

2)የሥነ-ምግባር ጉድለት ያለባቸውን መንገደኛ የሆኑ መነኮሳትን በየአድባራቱ እያሰማሩ ቤተመቅደሶችን ያስመዘበሩ ናቸው። ለአብነት ብንጠቅስ፦
  • ለሀላባ ///ማርያም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ብለው የመደቡት መነኩሴ የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብና ማህተም ይዞ የተሰወሩ መሆኑን የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ /ቀለምንጦስ የሚያውቁትና በዚህ ሰበብ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ በተፈጠረውና እስካሁንም ባልበረደው የብጥብጥና የመከፋፈል ስሜት ሲመላለሱ ከቆዩ በኋላ አዲስ ማህተም እስከማስቀረጽ ተደርሷል።
3) ለቤተክርስቲያን ጥቃት ደንታ የሌላቸው ናቸው። ለዚህም ማስረጃ፦
  • በአንጋጫ ወረዳ የሚገኘው የሹጳ /ጊዮርጊስ /ያን መፍረስ ጉዳይ በወረዳው /ክህነት ክትትል ሰበር ችሎት ደርሶ ውሳኔ ያገኘ ቢሆንም የወ//ክህነት /ቤቱን በመደገፍ እና በአፈጻፀም አስወስኖ የቤ/ያኒቱን ይዞታ በመረከብ ፈንታ ቆመው ያዩበት።
  • በዳምቦያ ወረዳ የመገሬ /ሲና ኪዳነምህረት /ያን የጥምቀተ ባህር ቦታ ሲነጠቅ መከትታተል ያለመቻል *በሀደሮና ጡንጦ ዙሪያ ወረዳ በበንጫ /ባለወልድ ቤተክርስቲያን ካህናት የተደበደቡበትን ጉዳይ ተከታትሎ እልባት ያለማሰጠት።
  • በጠምባሮ ወረዳ 2000 በላይ ምዕመናን ወደ /ቤተክርስቲያናችን ከተቀላቀሉ በኋላ ለቤተክርስቲያን ተከላና ለጽላት ማስቀረጫ አሰባስበው የሰጡትን ገንዘብ ለግል ጥቅም ማዋላቸው።
  •  በመንበረ ጵጵስና /ፀሐይ /ተክለኃይማኖት ቤተክርስቲያን የጥምቀ ተባህርና የቅ/ሩፋኤል /ያን መሥሪያ ቦታ በፕላን የተያዘውን ለማስከበር ባለመቻላቸውና የደብሩን ህዝብ ጥያቄ ባለመመለሳቸው ህዝብ ያኮረፈባቸው መሆኑ።
  •  የሚሽጊዳ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ /ያን ክልል ጉዳይ አንጠልጥለው መተው።
  • 3000 . በላይ የሆነውን የሀ/ስብከት /ቤት ቦታ 920 . ከመለወጣቸውም በላይ የጽ/ቤቱን ግምት ያለድርድር ግምቱን ከፋይ አካል የሰጠውን ብቻ ተስማምተው በመቀበል / ቤቱን ማፍረስ።
  •  የሠነድና የገንዘብ ጉድለት በኦዲት የተደረሰባቸውን በአስተዳዳሪነት መመደብ። ለአብነት ያህል፦ የመ/ጵጵስናው ///ተክለ ሐይማኖት /ያን አስተዳዳሪና መሰሎቻቸው። በዚሁ መነሻ ህዝብ ቅሬታውን ቢያቀርብም የሀ/ስብከቱ ፀሐፊ በመሆናቸው ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ ባለመሰጠቱ በህዝብ መካከል ክፍፍል መፈጠሩ።
  • *በወረዳዎችና በአጥቢያዎች ሥራ በጣልቃ ገብነት በመሥራት ወራዳወችን ያለአግባብ መጫን... ክፍተቶች የታዩባቸው ስለመሆኑ ለሀ/ስብከታችን /ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቀለምንጦስ እንግዳ ባይሆንም ለህዝቡ ጥያቄ መልስ መስጠት አልቻሉም።
~ለእጩነት እንዲቀርቡም የተሰበሰበው ድጋፍ በግልፀኝነት ሳይሆን በህቡዕ ነው። ስለዚህ የመ/ ፓትሪያርኩ //ቤት ችግራችንን በጥልቀት ተመልክቶ ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ የሆነ ጳጳስ እንዲመድብልን በትህትና እንጠይቃለን።

No comments:

Post a Comment