(አንድ አድርገን ሰኔ 25
2008 ዓ.ም )፤- እስከ
አሁን ድረስ በተለያዩ መንገዶች የተጠቆሙ እና አስመራጭ ኮሚቴው እንደተቀበላቸው ከተገለጹት ቆሞሳትና መነኮሳት ስም ዝርዝር ውስጥ ‹‹አባ›› እንቁ ሥላሴ ተረፈ የመዝገበ
ምሕረት ካራ ቆሬ ፋኔኤል አስተዳዳሪ ይገኙበታል፡፡ እኚህ በፎቶ ላይ የሚታዩት አባት እጅግ በብዙ ነገር ስማቸው የሚነሳ ‹‹አባት››
ናቸው ፤ ከአጥቢያ ቤተክርስቲያን ምዕመን እስከ አህጉረ ስብከት ፤ ከጸረ ሙስና ኮሚሽን እስከ አዲስ አበባ አስተዳደር ሴቶችና ሕጻናት
ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ስማቸው የሚነሳ ‹‹አባት›› ናቸው፡፡ አባቶች ‹‹እኽ ካሉ ብዙ ይሰማል›› እንደሚሉት የእኚህ ሰው የጀርባ ታሪክም
ረዥም ነው፡፡ እዚህ ጽሁፍ ላይ የተለጠፈው መረጃ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ፤ በጠቅላይ ቤተክህነት እና በካራቆሬ መዝገበ ምኅረት ቅዱስ ፋኑኤል ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት
በማስረጃነት እንደሚገኝ ‹‹አንድ አድርገን›› ለማረጋገጥ ትወዳለች፡፡
ይህ መረጃ መራጭ ኮሚቴው
ጋር እንደሚደርስ ሙሉ እምነት አለን ፤ አሁን በምንገኝበት ሰዓት በሴሰኝነት ፤ ገንዘብን በማምለክ ፤ ሹመትን አብዝቶ በመፈለግ
፤ የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ስርዓት በመናድ ስማቸው የሚነሱ አባቶችን መረጃ ሁሉም ምዕመን ለአስመራጭ ኮሚቴው የማድረስ
ሃይማኖታዊ ግዴታ አለበት ፤ ስለ እጩዎቹ ያላችሁን መረጃ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ያላችሁ የቤተክርስቲያን ልጆች በ‹‹አንድ
አድርገን›› የፌስ ቡክ አድራሻ ታደርሱን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን፡፡
ለነገ ሰላማዊ አውድ ዛሬ ትብብራችንን እናጠንክር፡፡
- ስለ አባ ገብረ ኢየሱስ መኰንን /እንጦጦ ቅድስት ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ/ይቀጥላል
አባ ገብረኢየሱስ ላይ ደጋግማችሁ አስቡ ስተት እንዳሰሩ
ReplyDeleteEgzio
Delete
Deleteየእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። . . ." የሐዋሪያት ሥራ ፳ ፥ ፳፰