Tuesday, December 1, 2015

በመጀመሪያ ቀን ፡ በድርቅ የተጎዶ አካባቢዎች




(አንድ አድርገን ህዳር 21 2008 ዓ.ም)፡- በአሁኑ ሰዓት ባለሙያዎች እንደሚሉት በአየር ንብረት ለውጥ አማካኝነት ከተጎዱ አካባቢዎች በግንባር ቀደምነት አፋር ክልል የመጀመሪያውን ቦታ ሲይዝ ቀጥሎም ሰሜን ወሎ ፤ የሀረርጌ ወረዳዎች እና ኦሮሚያ በቅደም ተከተል ይቀመጣሉ፡፡ 


እኛ ችግሩን ለማየት ከአዲስ አበባ ከ12 ቀናት በፊት ስንነሳ አንድ አላማን ይዘን ነበር ፤ እርሱም ‹‹ የችግሩ ተጋላጭ አካባቢዎችን በመመልከት ለአንባቢያን ማድረስ›› የሚለው ነበር፡፡ ጉዞው ከአዲስ አበባ በመነሳት ደሴን መዳረሻ በማድረግ ከደሴ እስከ 200 ኪሎ ሜትር ድረስ የሚገኙትን ወረዳዎች ማለትም መቅደላ(ማሻ)  ፤ ሳይንት  ፤ አምባሰል ፤ ለጋምቦ ፤ መግዲ ፤ መካነ ሰላም ፤ ወረ ኢሉ ፤ ወረ ባቦ ወረዳዎችን እና በስራቸው የሚገኙ  ቀበሌዎችን አቅም በፈቀደ መጠን ለመቃኝት ያለመ ነበር፡፡



በጉዞ መስመራችን የምስራቁ በር በኩል በደብረ ብርሃን ስንወጣ በየቦታው የሚገኙትን ጉደበረት ፤ ጣርማ በር ፤ ሸዋ ሮቢት ፤ ቀይት ፤ሰንበቴ ሚካኤል ፤ ጨፋና ሀርቡን በተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ወደ ውስጥ ዘልቀን በመግባት እርሻውን ፤ ከብቶች እና የሰው ኑሮ ለማየት ሞክረናል፡፡


እስከ ሸዋሮቢት ድረስ ያለው አካባቢ ዝናብ የዘነበለት ጥቂት ጊዜ ቢሆንም የተወሰነ ፍሬ በማፍራቱ ገበሬው እህሉን በጊዜው በመሰብሰብ የከመረበት ሁኔታ ይስተዋላል ፤ አንዳንድ ቦታም የተሰበሰበው እህል ተወቅቶ ወደ ምርቱ የተሰበሰበበት ቦታ ተመልክተናል፡፡ እነዚህን አካባቢዎች በመቃኝት ወደ ሸዋሮቢት ስንዘልቅ ያየነው የዚህ ተገላቢጦች ነበር ፤ ብዙ ቦታ ላይ ማሽላ ብቻ የተዘራ ሲሆን ዝናብ በቂ ባለማግኝቱ እና የአካባቢው ሀሩር ተደራርበው ማሽላው ፍሬ ሳይሰጥ አድርቆት ይስተዋለላ፡፡ አንዳንድ ቦታዎች ማሽላው ለከብቶች መኖ ለመሆን እንኳን ሳይችል ቀርቶ ይታያል፡፡

 
ከሸዋሮቢት ቀጥለን ያገኝነው ቀይት ወረዳ ሲሆን ይህ ሲታይ እህል የሚያበቅል ቦታ አይመስልም ፤ ነገር ግን መሬቱ ባገኝው ዝናብ ጥቂትም ብትሆን ብዙዎች ሰብላቸውን የሰበሰቡበት እና ወደ ጎተራ ያስገቡበትን ሁኔታ ተመልክተናል፡፡ ቀጥለን ጨፋ( ይህ ቦታ የኦሮሞ ብሔረሰብ የሚገኝበት ወረዳ ነው )  በመባል የሚታወቅ አካባቢን ስናገኝ ቦታው እጅግ ለቁጥር የሚታክቱ ከብቶች የተሰማሩበት ነው ፤ይህም የሆነበት ምክንያት ቦታው በሳር የተሸፈነ እና ረግራጋማ ከመሆኑ በተጨማሪ በአካባቢው ወረዳዎች የሚገኙ ገበሬዎች ግጦሽ ለከብቶቻቸው የሚያገኙበት እና ውሃ በቀላሉ የሚገኝበት ስፍራ በመሆኑ ብዙዎች አንድ ቦታ ላይ ከብቶቻቸውን አሰማርተው ተመልክተናል ፡፡ እዚህ ቦታ ባገኝነው መረጃ መሰረት ቀድሞ ከአፋር ክልል ድረስ ከብቶችን በመንዳት እዚያው የበጋውን ወራት የሚያሳልፉበት ቦታ መሆኑን ተነግሮናል፡፡ ይህ አካባቢ አሁንም የዝናብ እጥረት ያለባቸው አካባቢዎች ቄያቸውን በመተው ከብቶችን ያሰማሩበት ቦታ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡


ከጨፋ ቀጥለን ያገኝነው ቀዬ ሀርቡን ሲሆን ፤ ሀርቡ ማለት በኦሮምኛ ቋንቋ ሾላ ማለት ሲሆን ቀድሞ ብዙ ሾላዎች የሚገኙበት ቦታ መሆኑ ተነግሮናል ፤ የአካባቢው እርሻ የተዘራበት ማሽላ ሲሆን ከ50 በመቶ በላይ ሲያፈራ ግማሽ እርሻዎች በድርቅ የተመቱ ቦታዎችን ተመልክተናል፡፡


ኮምቦልቻ
ኮምቦልቻ ስንደርስ  ብአዴን 36ተኛ ዓመቱን በሚያከብርበት ዋዜማ ላይ ሕዝቡን የአማራ ክልል ባንዲራን እና የኢትዮጵያን ባንዲራ ይዞ እንዲወጣ በማድረግ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ነበር፡፡ አስራ አምስት ሚሊየን ሕዝብ ርዳታ ያስፈልገዋል ተብሎ በአለም ሚዲያዎች በተነገረበት ማግስት ፤ ኮምቦልቻና አካባቢዋ እህል በደረቀበት ፤ ከብቶች የሚጠጡት አጥተው ለሞት እየተዳረጉ ባለበት ሰዓት የብአዴንን በአል ለማክበር ይህ ሁሉ ሰው መመልከታችን እጅግ እስገርሞናል፡፡ 


በ1966 ዓ.ም የወሎ ህዝብ ችግሩ ከድርቅ ወደ ርሀብ ተሸጋግሮበት በአዲስ አለም አካባቢ የመጀመሪያዎቹ 104 በርሀብ የተጎዱ ወገኖች ከታዩበት ጊዜ ወዲህ ኃ/ሥላሴ ችግሩ ሳይነገራቸው በበታች አላፊዎች ‹‹ንጉሥ ሺህ ዓመት ይንገሱ›› በሚባሉበት ጊዜ ደሴን ለመጎብኝት እቅድ ይዘው ነበር፡፡በወቅቱ የወሎው አስተዳዳሪ 20ሺህ የሚያህሉ ሞት ያንዣበበባቸውን ርሀብተኞች ሰኞ ገበያ ውስጥ በነጭ ለባሽ በማስጠበቅ ንጉሱን ለመቀበል ኮምቦልቻ ላይ ርጥብ ቄጤማ ጎዝጉዘው እንደተቀበሏቸው ታሪክ ያስታውሰናል፡፡ 


አሁንም ያየነው ይህንኑ ነው ፤ ሰዎችና እንስሶቻቸው የሞት ዳመና አደምኖባቸዋል እየተባለ በሚገኝበት ጊዜ ፤ ይህን ወገን እንዴት መርዳት እንደሚገባን ቆም ብለን በማሰብ እንደ አንድ ሰው አሳቢ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነን ፤ መርፌ እና ክር በመሆን መስራት በሚገባን ሰዓት የአንድን ድርጅት ልደት ለማክበት ያ ሁሉ ሕዝብ ፤ ባንዲራና ሆሆታ ማየት ውስጥን ያስቆጫል ፤ ሲብስም ያንገበግባል፡፡ ከብቶች የሚበሉት ደረቅ ሳር ባጡበት ሰዓት ለሰዎች መረጋገጫ ርጥብ ቄጤማ የምንጎዘጉዝ ሰዎች መሆናችን ያሳዝናል፡፡


 ጉንዶ ወይን መገንጠያ
ጉንዶ ወይን መገንጠያ በመባል የሚታወቀው ቦታ ላይ ስንደርስ ከ 70 የማያንሱ የአማራ ክልል ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስን ልብስ የለበሱ ፖሊሶች ወደ ደሴ የሚገባውን መኪና ፤ ከገጠራማው አካባቢ የሚመጡትንና የሚወጡትን መኪናዎች መርፌ የሚፈልግ ሰው በሚመስል ሁኔታ ሲፈትሹ ነበር፡፡ ይህ ፍተሻ አላማው ጠይቀን እንደተረዳነው ከመንግሥት ፍቃድ ውጪ ፎቶ ካሜራ ፤ ቪዲዮ ካሜራ እና መቅረጸ ድምጽ ይዘው ወደ ከተማ የሚገቡ ወይም ወደ ገጠር የሚወጡት ላይ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ መሆኑን ተገልጾልናል፡፡ ፎቶ ካሜራ ይዞ የተገኝ ሰው ውስጡ ያሉትን ምስሎች በማየት እሰጣ ገባ ውስጥ የገቡ ሰዎችም ለማየት ችለናል፡፡


የህዝብን ችግር መደበቅ መፍትሄ ያመጣል የሚል እምነት የለንም ፤ ችግሩን ፖሊስ እና በብረት ማስቆም አይቻልም ፤ እንደ መፍትሄ መቀመጥ ያለበት ጉዳይ ችግሩን በማውጣት ሁሉም ዜጋ እንደዜጋ ፤ መንግሥትም እንደ መንግሥት ፤ ተራድኦ ተቋትም እንደ ተቋምነታቸው ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማድረግ ሲቻል ብቻ ነው፡፡


የ1966 ቱን ርሀብ ለዓለም ያሳወቀው ለንጉሱም መውረድ ብዙዎች አንደ ምክንያት አድርገው የሚያቀርቡት የህዝቡን ርሀብ መደበቅ በመቻላቸው ነበር ፤ የተበደቀውን ርሃብ ዓለም ባወቀበት ሰዓት ብዙ ነፍሳት መርገፍ ጀምረው ነበር ፤ አሁንም ድርቅ አለ ብሎ መንግሥት ካመነ ፤ 15 ሚሊየን ሰዎች ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ካረጋገጠ መፍትሄ መሆን የሚችለው በየመገንጠያው ፖሊስ ማቆም ሳይሆን ተቀራርቦ መነጋገር ብቻ ነው፡፡


በአዲስ ዓለም አካባቢ በ1966 የታዩት የመጀመሪያዎቹ በርሃብ የተዳከሙ 104 ሰዎች ተመልካች ስላጡ ብቻ ከቀናት በኋላ 738 ደርሰው ነበር ፤ በጊዜው አቤት የሚል አካል ፤ ጆሮ የሚሰጥ መንግሥት ባለመኖሩ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስ 1500 ሰዎች ከተማዋን ወረዋት ነበር፡፡ አሁንም ርሃብ የዳመነበትን ህዝብ በፖሊስ ሃይል ፤ በቀበሌ እና በወረዳ ሰዎች ዲስኩር ቀዬውን ለቆ ከመውጣት የሚያግደው እንደሌለ ታሪክ ሊያስተምረን ይገባል፡፡


ደሴ መናኽሪያ
ከአዲስ አበባ ተነስነት ደሴ መዳረሻ ካደረግን በኋላ ወደ መቅደላ አምባ እና አካባቢዎቿ ለማድረግ በጠዋት በአውቶቡስ ተራ መናኽሪያ ደርሰን ነበር፡፡ ነገር ግን ያላሳብነው አደጋ ፤ ሳንጀምር የሚያስቀረን ችግር አጋጠመን ፤ እርሱም ከመሀከላችን አንዱ የምንሄድበትን አካባቢ ኪሎሜትሩን እና አውቶቡሱን በካሜራ ለማስቀረት ባደረገው ሙከራ  በግቢው ውስጥ የሚገኙ የአውቶቡስ ተራ አስከባሪዎች ለምን እንደሚያነሳ ? ለምን እንደፈለገው አምባጓሮ አስነሱ በስተመጨረሻም ጉዳዩ ወደ ፖሊስ ዘንድ ሳይደርስ በጥቂት ሰዎች አማካኝነት እዚያው ሊቀር ቻለ፡፡ ይህ ችግር ወደ ፖሊስ አካል ቢወሰድ ኖሮ መዘዙ እጅግ ያልታሰበ እደሚሆን የታወቀ ነበር ፡፡ ተራ አስከባሪዎቹም ጸጉረ ልውጥ ፤ አዲስ አንቅስቃሴ ፤ ካሜራ እና ቪዲዮ መሰል ነገሮች ጋር የተያያዘ ጉዳይ ካገኙ ግቢው ውስጥ ላለ የፖሊስ አካል አሳልፈው እንዲሰጡ መመሪያ ተሰጥቷቸው ነበር፡

3 comments:

  1. እናንተን እግዚአብሔር ይባርካችሁ፡፡ ሀገራችን ግን በጣም የሚያሳዝንና የሚገርም ትውልድ በመፍጠሯ ያሳዝናል፡፡ ግማሹ ይጨፍራል ግማሹ ይራባል፡፡ በከተማ ያለውም እንደዚሁ ነው የከረመው፡፡ እኔ የገረመኝ እኛ ስለቅዱሳን አባቶቻችን እግዚአብሔር ስላደረገው ድንቅ ስራ ስንዘክር ሁሉም ያርጎመጉማል፡፡ ነገር ግን የራሱን የጭፈራ በዓል ግን ማንም ሲቃወመው አይሰማም፡፡ ይህ የጭፈራ በዓል ግን መቼ ነው የሚያበቃው???????? ቀኑ እንኳን በትክክል አይታወቅም እኮ!!!!!!!!!!እንዴት አንድ ወር ሙሉ በዓል ይከበራል??????????? 15 ሚሊየን ህዝብ እየተራበባት ያለች ሀገር፣ 4ዐዐ ቢሊየን እዳ ያለባት ሀገር በዓልና ስብሰባ በማድረግ ብቻ ዓመቱን ይጨርሳል!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! ኡፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍፍ ማስተዋል ይስጠን!!!!

    ReplyDelete
  2. egezabher ybarkach mcame bhune yalafew mtfew tarikachen ybkale ebkatche mrwcachen ylfawen astwes bza askafe rhbe ylfachm alach ebakatch lzh hezb endr endreslet egadachun akemw ylblezy gen kegzabher ferd medan aycalem ydbkewet ekow ynzy twhezbwech enb ymtawen mzaz twktalech wa ezgabher hezbune ytadagl!!

    ReplyDelete
  3. thank u guys! that is a heros job u all did! let my almighty GOD bless u all! please u should hurry to unleash ur storys on hand as much as possible the truth must be known and aid must be there for our peoples as soon as possible! thanks again!

    ReplyDelete