Tuesday, April 7, 2015

አቶ በጋሻው ደሳለኝ እና መሰሎቹ በሀረር ራስ ሆቴል ከሚያዚያ 16-18 የሚቆይ ጉባኤ ከለባት ሊያዘጋጁ ነው


 • የመግቢያ ዋጋ 300 ብር

በምንፍቅና ትምህርት ምክንያት ጉዳያቸው ቅዱስ ሲኖዶስ የደረሰው እና እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው የሚባል መፍትሄ ያልተሰጣቸው ፤ ላያቸው ተዋሕዶ ውስጣቸው ተሀድሶ የሆኑ ሰዎች መናገሻ ከተማ ባደረጓት ከተማ ሀረር ላይ የተጎዱ ቤተ ክርስቲያንን ምክንያት በማድረግ በመጪው ወር ከሚያዚያ 16-18 የሚቆይ ‹‹ጉባኤ›› ሊያዘጋጁ መሆኑን በቦታው ተገኝተን ያገኝነው መረጃ ያመለክታል፡፡ ባሳለፍነው እለተ ሰንበት በታላቅ ድምቀት የተከበረው የመድኃኒዓለም እና የሆሳዕና በዓል ላይ በሀረር መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ሰርክ ጉባኤ ላይ በተገኝንበት ወቅት መርሀ ግብር መሪው ለምዕመኑ ባስተላለፈው መልዕክት መሰረት ‹ጸጋው የበዛላቸው ፤ እግዚአብሔር አብዝቶ የባረካቸው ወንድሞቻችን የገጠሪቱን ቤተ ክርስቲያን ለመርዳት በማኅበረ እስጢፋኖስ አማካኝነት ከሚያዚያ 16-18 ድረስ በሀረር ራስ ሆቴል አዳራሽ ታላቅ የምሳ ግብዣ እና የወንጌል መርሀ ግብር ስለተዘጋጀ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል ፤ ወጣኒያን ማህበሩን እንድትቀላቀሉ መልዕክተን አስተላልፋለሁ ፤ በጉባኤው ላይ ‹ጸጋ› የበዛላት ‹ዘማሪት› ትርፌ እና ‹መጋቢ ሐዲስ› በጋሻው ደሳለኝ ይገኛሉ›› ካለ በኋላ ‹ጉባኤውን ለመታደም የመግቢያ ዋጋ 300 ብር ›› ነው በማለት ምዕመኑ ‹ጉባኤ›ያቸውን እንዲሳተፍ  መልዕክት አስተላልፏል፡፡


ከአምስት ዓመት በፊት በሚሊኒየም አዳራሽ የሰበሰቡትን ብር ለራሳቸው ጥቅም ያዋሉት እነዚህ ግለሰቦች አዲስ አበባ እና አካባቢዋ ላይ መንቀሳቀስ አለመቻላቸውን ፤ የትኛውም ቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት እንደማይፈቀድላቸው ሲገነዘቡ አሁን ላይ በክፍለ ሀገራት ሆቴሎች ላይ ዘመቻ ጀምረዋል፡፡ ለየትኛው ቤተክርስቲያን በአግባቡ እንደሚደርስ የማይታወቅ ፤ ለግል ጥቅማቸው ሊያውሉ ያሰቡትን ገንዘብ ለመሰብሰብ  ማስታወቂያ አትመው ፤ ገንዘብ መሰብሰቢ ደረሰኝ አዘጋጅተው ከምዕመኑ ገንዘብ እየሰበሰቡ ይገኛሉ፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በአዳራሽ እና በሆቴሎች የሚደረግ ማንኛውንም ጉባኤ ከአራት አመት በፊት መከልከሉ ይታወቃል ፤ ሆኖም አህጉረ ስብከቶች ይህን ክልከላ እያወቁ ስለምን ሆቴሎች ላይ እና አዳራሾች ላይ የሚደረጉ የምንፍቅና አካሄድ ያላቸውን ጉባኤያትን መከልከል መቻል አለባቸው ፤ ቤተ ክርስቲያን ከፈቀደችላቸው አውደ ምሕረቷን ትስጣቸው ፤ ቤተ ክርስቲያን ካልፈቀደችላቸው ደግሞ በየትኛውም ቦታ የሚደረግ ጉባኤ መሰል ስብሰባን በአህጉረ ስብከቶች አስተዳዳሪዎቿ ምክንያት መከልከል መቻል አለባት ብለን እናምናለን፡፡

የእግዚአብሔርን አውደ ምህረት ለደቂቃዎች እንዲያገለግሉበት እድሉ የተሰጣቸው ሰዎች ምዕመኑን ወዳልሆነ መስመር ገፍተው እንዳይከቱት መጠንቀቅ መቻል አለባቸው ፤ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪዎችም በአውደ ምህረት ላይ ለሚደረጉ እያንዳንዷ ተግባራት ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው ብለን እናምናለን፡፡

የፀጋ ትርጉሙ ያልገባቸው ፤ እንደ መናፍቅ መዝለልን ተግባራቸው ያደረጉ ፤ ከስርዓተ ቤተክርስቲያን ጋር ስምምነት የሌላቸው ፤ የያሬዳዊ ዜማ ትርጉሙ ያልገባቸው ፤ ፍቅረ ነዋይ አይኖቻቸውን ያሳወሯቸው ፤ ከዘመን በፊት ቤተክርስቲያን መፍትሄ የሰጠችውን የምንፍቅና ትምህርት በዘመናቸው እንደ አዲስ የሚያነሱ ፤ የቅዱስ ሲኖዶስን ክርና ተግሳጽ ለመስማት ጆሯቸውን የደፈኑ ፤ ላለመመለስ ልባቸውን ያደነደኑ  ሰዎችን በአውደ ምህረት ላይ ‹ፀጋ የበዛላቸው› እያሉ መጥራትም ተገቢ አይደለም፡፡  

አንድ አድርገን መጋቢት 29 2007 ዓ.ም
ሀረር

10 comments:

 1. ቅዱስ ሲኖዶስ በአዳራሽና በሆቴሎች ጉባኤ እንዳይደረጉ መከልከሉ የሚታወቅ ሆኖ እንዲህ ዓይነት የአባቶችን ምክር ወደ ዳር ትቶ እንደዚህ ማድረጉን እሱ እግዚአብሔር ይከላከልልን እንጂ ሰዎቹ የሚገባቸው አይደሉም፡፡ እሱ ልቦናቸውን ከሄደበት ይመልስላቸው እላለሁ፡፡ ይህቺን ቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ያቆዩልን ስንቱን መከራ ተቀብለው ነበር እኛ ግን የአሁን ትውልድ የትንቢቱ መፈጸሚያ እንዳንሆን እሰጋለሁ፡፡ ለነገሩ ሁሉም የዘራውን ያጭዳል፡፡ ጌታ እየሱስ ክርስቶስም በደሙ የዋጃትን ቤተክርስቲያንን እንዲሁ አይተዋትም፡፡ እግዝአብሔር ኢትዮጵያን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን፡፡ አሜን፡፡ መጋቢት 29 ቀን 2ዐዐ7 የትምወርቅ

  ReplyDelete
  Replies
  1. ቅዱስ ሲኖዶስ በአዳራሽና በሆቴሎች ጉባኤ እንዳይደረጉ መከልከሉ የሚታወቅ ሆኖ እንዲህ ዓይነት የአባቶችን ምክር ወደ ዳር ትቶ እንደዚህ ማድረጉን እሱ እግዚአብሔር ይከላከልልን እንጂ ሰዎቹ የሚገባቸው አይደሉም፡፡ እሱ ልቦናቸውን ከሄደበት ይመልስላቸው እላለሁ፡፡ ይህቺን ቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ያቆዩልን ስንቱን መከራ ተቀብለው ነበር እኛ ግን የአሁን ትውልድ የትንቢቱ መፈጸሚያ እንዳንሆን እሰጋለሁ፡፡ ለነገሩ ሁሉም የዘራውን ያጭዳል፡፡ ጌታ እየሱስ ክርስቶስም በደሙ የዋጃትን ቤተክርስቲያንን እንዲሁ አይተዋትም፡፡ እግዝአብሔር ኢትዮጵያን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን፡፡ አሜን፡፡ መጋቢት 29 ቀን 2ዐዐ7 የትምወርቅ

   Delete
 2. Ene yalgebagn neger sint sinodos new yalen kidus sinodos endew bemigeba yebetekrstian lijinetachewin aregagto fekdolachewal .
  Lemin egna yefeleginew alhonem kehone betam yasazinal ebakachihu bilogun kale Egziabhyr memarya adrgut ende tinte abatachihu mekasesha atadrgut.

  ReplyDelete
 3. እስከምናውቀው፡- ማኅበረቅዱሳን፣ደጆችሽ አይዘጉ፣ብዙ የገጠር ቤ/ክ አሰሪ ኮሚቴዎች ዝግጅቶችን እያዘጋጁ በአክሱም ሆቴል፣በግዮን፣በስብሰባ ማዕከል፣በጠ/ቤ/ክ አዳራሽ፣በሚሊኒየም አዳራሽ፣በኢትዮጵያ ሆቴል….የለለያዩ ጉባኤያት በተለያዩ ጊዜዎች ተካሂደዋል፡፡የጉባኤያቱ ዐላማ በዋናነት ለቤ/ክ እና አብነት ት/ቤቶች እንዲሁም ገዳማት እርዳታ ማሰባሰብ ነው፡፡ወይም ነው ብለን በቅንነት እናምናለን፡፡የማኅበረ እስጢፋኖስ ዝግጅት ዐላማም ከነዚህ ጉባኤያት የተለየ አይመስለኝም፡፡ማኅበረ እስጢፋኖስ የተሐድሶ ነው እየተባለ ባላዋቂ ሰዎች ሲሳደድ ማዕተቡን አጥብቆ በጽንአት ያስመሰከረ መንፈሳዊ ማኅበር መሆኑን እናውቃለን፡፡ብፁዕ አቡነ አብርሃም ምስክር ናቸው፡፡የሐረር ምዕመንና ሀ/ስብከትም ሌላው ምስክር፡፡እርግጥ ይቺ-ይቺ የገፊነት ወሬ ከነማን እንደምትመነጭ አይጠፋንም፡፡ቅሉ ሥም መጥራቱ ቅድስት ቤተክርስቲያንን ማስነቀፍ ነውና ይቅር፡፡
  በእውነት ግን፡- በጋሻው የተገኘበት ጉባኤ ሁሉ ርጉም ይሑን በሚል የጥላቻ መንገድ መንጎድ አስጸያፊ ነው፡፡በቃ!!ይበቃችኋል!!ያቀናበራችሁት ክሊፕ እንኳንስ ቅ/ሲኖዶስ ፊት ሊደርስ ቀርቶ ገና የሊቃውንት ጉባኤ ሲያየው በኖ ቱሽ ብሎ ጠፍቷል፡፡ማስረጃችሁ ቱሽ!!እንግዲህ የልጁን የተቀብዖ መዐርግ ይቅርና ዲቁናውን ግን በምንም መንገድ የምትሽሩበትና “አቶ” እያላችሁ የምታቃልሉበት የቤ/ክ ሥርዓት የለም፡፡ለነገሩ የት የምታከብሩትን ሥርዓት!!
  ብቻ እንድታውቁት:- የልጁን ሥልጣነ - ክሕነት ለመሻር ሥልጣኑም፣አቅሙም፣መብቱም የላችሁ፡፡የበጋሻውን ሥልጣን መንጠቅ የሚችለው ወይ ሊቀጳጳስ ነው ወይ ቅ/ሲኖዶስ ነው፡፡ስለዚህ በአቅማችሁ ልክ ተናገሩ፡፡አታደናግሩ፡፡ከሊቀ ጳጳሳትና ከቅ/ሲኖዶስ በላይ የሃይማኖት ተቆርቋሪ መስላችሁ አታደናግሩ፡፡እርቁን ለማሰናከል የታተራችሁት አጓጉል መታተር ይበቃል፡፡አታደናግሩ፡፡ተው!! ከዚህ የቃኤል መንገዳችሁ ተመለሱ፡፡የአንድ ወገን የሆነ ወገንተኛ መረጃ እየዘራችሁ ራሳቸውን ለመከላከል እድል የማትሰጡዋቸውን የቤ/ክ ልዩ-ልዩ አገልጋዮችን ስሜት መጉዳት ሳያንሳችሁ ማኅበረ ምዕመናንን አታደናግሩ፡፡አታደናግሩ፡፡ወንድሞቻችንን የብሎግና የፌስቡክ አንባቢ መጨመሪያ፣ላይክና ሸር መሸመቻ አታድርጓቸው፡፡

  ReplyDelete
 4. እኔ የሚገርመኝ ማህበረ ቅዱሳንን ከምእመናን የሚሰበስቡትን ገንዘብ መቆጣጠር አለብን እያሉ ቡራ ከሬዩ ሲሉ የነበሩ የነበጋሻው ሲሆን ዝም የሚሉት ለምንድን ነው፡፡ፓትርያልኩስ ቢሆኑ እውነት ያን ሁሉ የደከሙት ስርአት ከማስያዝ ከሆነ አሁን ለምንዝም አሉ፡፡ለማህበራችን አባለት ‹‹ ፊል 1፤28 ይህ ለእነሱ የጥፋት ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው››የሚለውን የሐዋርያውን መልእክት አትርሱ ፡፡

  ReplyDelete
 5. ቅዱስ ሲኖዶስ በአዳራሽና በሆቴሎች ጉባኤ እንዳይደረጉ መከልከሉ የሚታወቅ ሆኖ እንዲህ ዓይነት የአባቶችን ምክር ወደ ዳር ትቶ እንደዚህ ማድረጉን እሱ እግዚአብሔር ይከላከልልን እንጂ ሰዎቹ የሚገባቸው አይደሉም፡፡ እሱ ልቦናቸውን ከሄደበት ይመልስላቸው እላለሁ፡፡ ይህቺን ቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ያቆዩልን ስንቱን መከራ ተቀብለው ነበር እኛ ግን የአሁን ትውልድ የትንቢቱ መፈጸሚያ እንዳንሆን እሰጋለሁ፡፡ ለነገሩ ሁሉም የዘራውን ያጭዳል፡፡ ጌታ እየሱስ ክርስቶስም በደሙ የዋጃትን ቤተክርስቲያንን እንዲሁ አይተዋትም፡፡ እግዝአብሔር
  እኔ የሚገርመኝ ማህበረ ቅዱሳንን ከምእመናን የሚሰበስቡትን ገንዘብ መቆጣጠር አለብን እያሉ ቡራ ከሬዩ ሲሉ የነበሩ የነበጋሻው ሲሆን ዝም የሚሉት ለምንድን ነው፡፡ፓትርያልኩስ ቢሆኑ እውነት ያን ሁሉ የደከሙት ስርአት ከማስያዝ ከሆነ አሁን ለምንዝም አሉ፡፡ለማህበራችን አባለት ‹‹ ፊል 1፤28 ይህ ለእነሱ የጥፋት ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው››የሚለውን የሐዋርያውን መልእክት አትርሱ ፡፡ኢትዮጵያን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን፡፡ አሜን፡፡ መጋቢት 29 ቀን 2ዐዐ7 የትምወርቅ

  ReplyDelete
 6. እግዚአብሔር ልቦና ይመልስ!!እግዚአብሔር ልቦና ይመልስ!!

  ReplyDelete
 7. ፎቶሾፕአችሁ የበጋሻውን ማዕተብ መቁረጥ ስላልቻለ ነው ከነማዕተቡ ፎቶውን የለጠፋችሁት?የበጋሻው ማዕተብ ሊቆርጡዋት እንዳሰፈሰፉት ብዛት አለመቆረጡዋ ተአምር ነው፡፡ጽኑዕ ኦርቶዶክሳዊ ማለት በጋሻው ነው፡፡ሺህ ጠላት ተሰልፎበት ሃይማኖቱን በእልህ ያልካደ፡፡ቡድንና ሃይማኖትን ለይቶ ያወቀ የቁርጥ ቀን የቤ/ክ ልጅ፡፡ለገፊዎቹ ያልተንበረከከ፡፡ሌሎቹንማ አየናቸው፡፡የስድብ ካሴትና መጽሐፍ አውጥተው ራሳቸውን በሰው አበሳ የሚክቡ፡፡ለምሳሌ፡-ማኅበረቅዱሳንና ተንሸራታቹ ነጋዴ ዘመድኩን በቀለ፡፡
  በጋሻውን በማዕተቡ ያጽናልን፡፡፡፡የቤተክርስቲያን አምላክ የውስጥ ገፊዎችን ያስታግስልን፡፡፡፡ኦርቶዶክሳዊነታቸውን ገፍተው ባስወጡት ምዕመን ልክ ከሚያሰሉ ተመጻዳቂዎች ይሰውረን፡፡፡፡የግእዝ እውቀታቸው ከጥቂት የስድብ ቃላት ያላለፈ የስድብ አፎችን ይያዝልን፡፡፡፡ተቆርቋሪነታቸውን መረን በለቀቀ ፍረጃ ለማሳየት ለሚጥሩ የምግባር ድኩማን ልቡና ይስጥልን፡፡፡፡፡አሜን!!!

  ReplyDelete
  Replies
  1. እና ተሃድሶ እኮ መጠረሻ ግብ አለው ያጨውን እስኪወስድ ድርስ ታማኝ ሆኖ ይታያል

   Delete
 8. ይህቺን ቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ያቆዩልን ስንቱን መከራ ተቀብለው ነበር እኛ ግን የአሁን ትውልድ የትንቢቱ መፈጸሚያ እንዳንሆን እሰጋለሁ፡

  ReplyDelete