Monday, January 18, 2016

ፕትርክና እንዲህ ነበር 1 !
አንድ አድርገን ጥር 2008 .

ሶስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት
፩ኛ. ሹመታቸው በመንፈስ ቅዱስ ነበር፡፡ ለመጨረሻ ከቀረቡ ሶሰት ዕጩዎች መካከል በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ረጂም ጸሎት ከተደረገ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ይምረጥ ተብሎ በዕጣ ነው የተመረጡት፡፡

፪ኛ. ጵጵስናም ሆነ ፕትርክና ከተሾሙ ጊዜ አንስቶ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው አለባበሳቸው የገዳማውያን አባቶቻችን ልብስ ነበር፡፡ አልፎ አልፎ ለክብረ በዓላት የጵጵስና ልብሳቸውን ይለብሱ ነበር፡፡
 
፫ኛ. ፕትርክና እስከተሾሙበበት ቀን ድረስ የሚጓዙት ባዶ እግራቸውን ነበር፡፡

፬ኛ. በበዓላት ቀን ወደ አብያተ ክርስቲያናቱ የሚሄዱት በግብዣ/በጥሪ ሳይሆን በራሳቸው ፈቃድ ነበር፡፡

፭ኛ. የሚጠበቁት በሰለጠነ ጠባቂ ወታደር(Security Guard) ሳይሆንጠባቂዬ መንፈስ ቅዱስ ነው!” ብለው ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩት እንደ አንድ ምዕመን ነበር፡፡ ከመንበረ ፓትርያርክ ወጥተው በአቅራቢያው ወዳሉት አብያተ ክርስቲያናት የሚጓዙት በእግራቸው ስለነበር መንገድ ላይ ብዙ ምዕመናንን ለረጅም ጊዜ ሳይሰለቹ ቆመው መስቀል እያሳለሙ ይባርኩ ነበር፡፡

፮ኛ. ከቦታ ቦታ የሚዘዋወሩት ሕዝብን እንደሚፈሩ የመንግስት ባለስልጣናት በጥቋቁር ሽፍን መኪኖች ሳይሆን በእግራቸው ነበር፡፡
 
፯ኛ. ዘመናቸውን በሙሉ ልክ እንደ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ሁሉ ፀጥታ ከሠፈነበት ከገዳም ወጥተው ጫጫታ በበዛበት ከተማ መኖራቸው ያስለቅሳቸው ነበር፡፡

፰ኛ. እስካሁን በሕይወት ያሉ ጳጳሳት እንደሚመሰክሩት ሹመት፣ የቤተ ክህነት ሥራ፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪነት ሰው ሲሾሙ ዘር፣ ዝምድና፣ የፖለቲካ ሁኔታ እና ከዚህ ጋር የሚያያዙ ቆሻሻ አስተሳሰቦች ቦታ አልነበራቸውም፡፡

፱ኛ. በቅርብ የሚያውቋቸው ሲናገሩ ቅዱስነታቸው ሌትና ቀን የሚያሳስባቸው ጠባቂ ሆነው ለተሾሙለት ምዕመን ድኅነት፣ የአብያተ ክርስቲያናት፣ የገዳማት እና የአብነት ትምህርት ቤቶች ጉዳይ እንጂ ስለራሳቸው ክብር አልነበረም፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ የአባቶቻችንን የተቀደሰ ዘመን መልስልን!

2 comments:

  1. አሜን፣አሜን፣ አሜን እኔም እራሴ እንደዚህ አይነት አባት እንደናፈቀኝ!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  2. አሜን፣አሜን፣ አሜን እኔም እራሴ እንደዚህ አይነት አባት እንደናፈቀኝ!!!

    ReplyDelete