Monday, January 18, 2016

ፕትርክና እንዲህ ነበር 2 !



 አባ ባስልዮስ ዘቂሳርያ እና አባ ማትያስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ

አንድ አድርገን ጥር 8 2008 .

አባ ባስልዮስ በአፍ በመጣፍ መናፍቃንን ሲቀጠቅጥ የኖረ ቅዱስ አባት ነው። አባ ማትያስ ግን የቤተ ክርስቲያን ደጆቿን ሀራጥቃዎች ይቀጠቅጧት ዘንድ እሺታቸውን እንደገለፁ ሰማን።

አባ ባስልዮስ መናፍቃን ምእመናንን ባሳደዷቸው ጊዜ ምእመናንን አይዟችሁ እያለ ያጽናናቸው ነበር፣ አባ ማትያስ ግን የቤተክርስቲያንን ልጆች የሚያሳድዱ ተሀድሶ መናፍቃንን አይዟችሁ እንዳሏቸው ሰማን።
አባ ባስልዮስ ምእመናን ከተሳደዱባት ቤተ ክርስቲያን ከሀድያን እንዳይገቡባት ቤተ ክርስቲያንን በዘጸሎቱ ዘግቶባቸው ነበር፣ አባ ማትያስ ግን ለሀራጥቃዎች ቤተ ክርስቲያንን ወለል አድርገው እንደከፈቱላቸው ሰማን።

 
ስለአባ ባስልዮስ በአንድ ወቅት ከሰይጣን ደብዳቤ እንዳስመለሰ ሰምተን ነበር፣ ነገሩ ወዲህ ነው። አንድ ሎሌ በሴት ፍቅር ምክንያት ያፈቀራትን ሴት ለማግኘት ሲል ብቻ ሃይማኖቱን ፈጣሪውን ክዶ የካደውንም በደብዳቤ ጽፎ ነበር። ያችንም ደብዳቤ ሰይጣን ለማስረጃ ወስዷት ነበር። ታዲያ ሰውዬ ወደ ልቡ በተመለሰ ጊዜ ወደ አባ ባስልዮስ ሂዶ ቀኖናውን ተቀብሎ ሲጨርስ ያች ደብዳቤ ግን አሁንም በሰይጣን እጅ ናትና " አባቴ ምን ይሻለኛል? የደብዳቤዋ ነገርስ? " አለው። አባ ባስልዮስም በገድል በትሩፋት የጸና ቅዱስ ነበርና የደብዳቤዋን ጉዳይ አስመልክቶ በጾም በጸሎት በስግደት ሰይጣንን አስጨነቀው። በዚህ ጊዜ ሰይጣን " ባስልዮስ! አትዘብዝበኝ! ደብዳቤው ያውልህ! " ብሎ ደብዳቤዋን ወርውሮለት ሄደ። ታዲያ የኢትዮጵያው አባ ማትያስ ግን ከአሁን በፊት በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በተለያዩ ጊዜያት በሀራጥቃዎች እጅ የገቡ ቤተ ክርስቲያንን የእናድሳት/እናፍርሳት/ የፈቃድ ደብዳቤ በማስመለስ ፋንታ ሌላም ደብዳቤ እንደጨመሩላቸው ሰማን። በእርግጥ ደብዳቤ የያዘ ሁሉ ሊያሳድድ አይችልም። ሳውል ደብዳቤ ይዞ ነበር ግን ክርስቲያኖችን ሊያሳድድ አልቻለም። ምንም ቢሆን እግዚአብሔርን የያዘ እንጅ ደብዳቤ የያዘ የትም እንደማይደርስ እናውቃለን።

አባ ባስልዮስ ዘቂሳርያ በአንድ ወቅት ሊቀ ጳጳስ ጴጥሮስ /ወንድሙ ነው/ ከሴት ጋር ይውላል ያድራል፣ ክህነቱን አርክሷታል አቃሏታል በማለት ሕዝቡ ሁሉ መጥቶ ለአባ ባስልዮስ በነገሩት ጊዜ አባ ባስልዮስም " ነገሩ እናንተ እንደምትሉት አይደለም" ካለ በኋላ ለጸሎት ቆመ። ከዛም ሊቀ ጳጳስ ጴጥሮስ ዘማዊ አለመሆኑን፣ መላእክት በሌሊት ለሴቲቱም ለሊቀ ጳጳስ ጴጥሮስም በክንፋቸው ከልለዋቸው እንደሚያድሩና ክፉም ከማሰብ እንደሚጠብቋቸው ሕዝቡ ሁሉ እንዲያዩ አደረገ። ልክ ኤልሳዕ ግያዝን መላእክትን ያይ ዘንድ እንደረዳው አባ ባስልዮስም ያን ሁሉ ሕዝብ በአንዴ ነጽሮተ መላእክት ከሚባለው የቅድስና ደረጃ ላይ አስቀመጣቸው። አባ ማትያስ ዘኢትዮጵያ ግን ቅዱሳን መላእክትን ሳይሆን ተሀድሶ መናፍቃን በቤተ ክርስቲያን ዐውደ ምህረት ሲዘሉና ሲጮኹ፣ ሥርዓቷን ሲሽሩ አጥሯን ሲነቀንቁ አስተምህሮዋንም ሲቆነጻጽሉ ብናይ ደስስስ እንደሚሰኙ ሰማን። ሰማን ሰማን ሰማን ...

ታዲያ እነዚህ ሁለቱ ማለቴ የቂሳርያውና የኢትዮጵያው ሐዋርያት የሰበሰቧትን፣ ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን፣ ሰማዕታት የሞቱላትን፣ እነ አትናቴዎስና ዮሐንስ አፈወርቅ የተሰደዱላትን፣ እነቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጺማቸውን የተነጩላትን፣ ቆራጦቹ በእሳት የተለበለቡላትን የተቃጠሉላትን፣ እንደ ጎመን የተቀረደዱላትን እንደ ሽንኩርትም የተከተፉላትን አንዲቷን ቤተ ክርስቲያን ለመጠበቅ የተቀመጡ እረኞች ናቸው ብሎ ሁለቱንም /አባ ባስልዮስንና አባ ማትያስን/ አንድ አድርጎ መናገር ይቻል ይሆን

እኛስ እንደሰማን እናይ ይሆን

የማይተኛው የማያንቀላፋው እረኛችን ቤተ ክርስቲያናችንን ከክፉ ሁሉ ይጠብቅልን።

3 comments:

  1. aman egezabher anlek btkrestanachenn ytabk ydengle Maryam legwech nkew ymchersaw sat eydres new!! mchem mchem bhewn ydengle Maryam legwech btcrestyanchenn asalfan lher tkawech asalfan endmansat ergtga nez ensile!! enswem!! ymnwazaw kzh alme gage krkuse manfes gare mhanwen anersa bartw btam ensalylachew klbanachew endmalesw teftaw endyatfwen egzaw mharen Christos!! bent Maryam mharen christos!! bent sadkan smaetat mharan christos!!krriso! krriso! aman!!

    ReplyDelete
  2. Amen becherenetu yiker yibelen

    ReplyDelete
  3. እዉነት ነዉ ቤተ ክርስቲያናችን ሃቀኛ መንፈሳዊ አባቶችን ካጣች ሰነባብታለች። ይህ እጅግ የሚያሳዝን እና ሁላችንንም የሚያስለቅስ የዘመናችን ታሪክ ነዉ። ግን አንድ ያልገባኝ ነገር አለ። ለመሆኑ ይህች ቤተ ክርስቲያን እዉነተኛ እረኛ ያጣችዉ በአባ ማቲያስ የፕትርክና ዘመን ብቻ ነዉ እንዴ? ምነዉ ከእሳቸዉ በቀደሙት «አባት» ዘመን ጥፋቶችን እንዳላየ ሆናችሁ ከረማችሁ? ብዙዎቻችንን ያስገረመ ጉዳይ በመሆኑ ነዉ ይህን የጠየኩት። እስኪ ለሁላችንም ራሳችንን የምናይበት ዓይን ይስጠን። እኝህንም «አባት» ልቦናቸዉን ይመልስ። አሜን!

    ReplyDelete