Saturday, October 10, 2015

ኢ.ቢ.ኤስ: ሃይማኖታዊ የቲቪ ፕሮግራሞች የታደሰ ፈቃድ እንዲያስገቡ አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጠ



(አዲስ አድማስ መስከረም 29 ቀን 2008 ..) የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ(ኢቢኤስ) በሳምንት አንድ ቀን በጣቢያው መንፈሳዊ ዝግጅት የሚያስተላልፉ ሃይማኖታዊ ፕሮግራሞች፣ የታደሰ የፈቃድ ማስረጃዎቻቸውን እንዲያስገቡ አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጠ፡፡

የቴሌቪዥኑ ፕሮግራሚንግ ኮሚቴ መስከረም 21 ቀን 2008 .. ለአራት የሃይማኖታዊ ፕሮግራም ክፍሎች በጻፈው ደብዳቤ፤ ከጣቢያው ጋር በገቡት ውል መሠረት ለሚወክሉት የሃይማኖት ተቋም ወይም የሃይማኖት ትምህርት ለመስበክ ያስፈቀዱበትን ወይም እያደረጉ የሚገኙትን አገልግሎት የሚደግፍ የታደሰ ፈቃድ ወይም ደብዳቤ በአስቸኳይ እንዲያቀርቡለት ጠይቋል፡፡

የታደሰ ፈቃድ ወይም ደብዳቤ እንዲያስገቡ የታዘዙት÷ ታዖሎጎስ፣ ቃለ ዐዋዲ፣ ማኅበረ ቅዱሳን እና ኤንሼንት ዊዝደም የተባሉ አራት ፕሮግራሞች ሲኾኑ ተቋሞቻቸው ከሚመለከተው የመንግሥት ይኹን የሃይማኖት አካል ለአገልግሎታቸው ይኹንታ ያገኙበትን የታደሰ ፈቃድ ወይም ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት እትማችን፣ በታዖሎጎስ እና ቃለ ዐዋዲ የኢ..ኤስ ፕሮግራሞች ላይ ተቃውሞ ተነሣ በሚል ርእስ፣ ፕሮግራሞቹ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ እና ክብር የሚጋፉ በመኾናቸው በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እንዳጠቀሙ የሚቀሰቅስ የሕዝባዊ ተቃውሞ ድጋፍ ፊርማ በመሰብሰብ ላይ መኾኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በሌላ በኩል በስም ተጠቃሾቹ የሃይማኖታዊ ፕሮግራሞች አዘጋጆች፣ በወጣው ዘገባ ላይ ቅሬታቸውን ገልጸዋል፡

2 comments:

  1. እኔ ቃለአዋዲን እከታተላለሁኝ፡፡ ከሁሉም የሚቀርበው መዝሙር በጭራሽ ቤተክርስቲያንን አይወክልም፡፡ ቅዱሳንንና እመቤታችንን ለማንሳት እንዴት አንደበታቸውን እንደሚቆጥቡ እኔ በጣም ነው የሚገርመኝ፡፡ አንድ አባት አሁን አርፈዋል፡፡ ጅማ ለልመና ሄደው፡፡ እንደሚታወቀው ጅማ እስላም ይበዛል፡፡ ምን በለው እንደለመኑ ታውቃላችሁ፡፡ በግእዙ አቡነ ዘሰማያት ላይ አላ ድነነ የሚለውን ቃል ተጠቅመው ‘አላ ድነነ’ እያሉ ይለምኑ እንደነበር በቅርብ የሚያውቃቸው ሰው ሲናገር ስምቻለሁኝ፡፡ከእነዚህ አባቶች ብዙ እንማራለን፡፡ እነቃለአዋዲ እነርሱ በእውነት ቤተክርስቲያን ያደጉ ናቸው? እኔ በእርግጥ ከቃለአዋዲ አቅራቢ ማንንም ከዚህ በፊት አላውቃቸውም በዚሁ ጣቢያ ነው የማውቃቸው እና ይገርመኛል፡፡ ህሊናቸው መፍቀዱ ነው ያስገረመኝ፡፡ ታኦሎጎስ አቅራቢ ውስጥ ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያምን ከልጅነቴ ጀምሬ አውቀዋለሁ በመዝሙሩና በስብከቱ በጣም የምወደውና የማከብረው ወንድም ነበር ነገር ግን ከእነዚህ ጋር በመመልከቴ ግን ውስጤ በጣም ተጨንቋል፡፡ ህሊናዬ ብቻ አልቀበል ያለው የእርሱን በተሀድሶ ከሚጠረጠሩት ውስጥ በማግኘቴ ነው በእርግጥም በራሴ መንገድ ለማጣራት ግን ተግቼ መስራት እንዳለብኝ ሁሉ ይሰማኛል፡፡ እንዴት የሚለውን ግን እርሱ እግዚአብሔር ይርዳኝ፡፡ ሌሎቹ ድሮም አይመቹኝም አንድ ችግር እንዳለባቸው ያስታውቃል፡፡ እንደተባለው የእውቀት ወይ ደግሞ የሚጠረጠሩት የተሀድሶ ጉዳይ፡፡ ይህንኑ ለማጣራት ግን ኘሮግራማቸውን ባገኘሁት አጋጣሚ እከታተላለሁኝ፡፡ ነገር ግን ዲ.ዳንኤል እንዳለው አረሙን ሲያርሙ እህሉ እንዳይነቀል እንደምንጠነቀቅ ሁሉ እንደዚሁ ነው መጠንቀቅ ያለብንና ድንገትም እንዳንሳሳት እሰጋለሁኝ፤ ያማላውቃቸውም አሉ ሁሉንም ግን በተሀድሶ ለመፈረጅ ትንሽ ያስቸግራል ጉዳዩ ግን በእርግጥም ተቃውሞ የሚያስፈልገው ነው፡፡ እነርሱ ከምእመኑ ጋር ተገናኝቶ መወያየት አለባቸው፡፡ ጀርባቸውን በደንብ መጣራት አለበት፡፡ ጉባኤያቸው መፈተሽ አለበት፡፡ በትክክል ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነን የሚሉ ከሆነና ከተሀድሶ ነፃ ነን የሚሉ ከሆነ ስለወንጌል እንሰራለን የሚሉ ከሆነ ቤተክርስቲያኗ ስርአት መከተል አለባቸው፡፡ እኛ አራተኛ ዜማ መስማት አንፈልግም፡፡ እነርሱ በተሀድሶ እንደሚጠረጠሩ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ በአስቸኳይ ቤተክርስቲያኗ ይህንን ጉዳይ ተመልክታ አንድነቷን መሳየት አለባት፡፡ ተሀድሶን ቶሎ ከእንጭጩ ማስቀረት አለብን፡፡ እንደህንዶች ስር ሰደው አንድነታችንን እንዳያደፈርሱት እንደግብጸች ተግተን እንስራ፡፡ ተዋህዶ በሰው ልጅ ልብ ውስጥ ተቀብራ እንድትቀር የሚሰሩትን ተሀድሶችን እንቃወማለን፡፡ ትንሳኤዋን እናውጃለን፡፡

    ReplyDelete
  2. እባካችሁ ፊርማው የት እንደሚገኝና አላማውን በደንብ የሚያስረዳ መረጃ በግልጽ ሁሉም እንዲደርሰው ተደርጎ ይሰራጭ፡፡ ብዙ ኢንተርኔት የማይጠቀም አለና በበራሪ ጽሁፍም ሆኖ ተዘጋጅቶ መረጃው ይበተን እንደውም ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ኘሮግራሙ ወንጌልን ለማሰራጨት የሚደረገው ጥረት መልካም ቢሆንም ግን ቤተክርስቲያኗ ካለችበት ችግር አንፃር ሲታይ አካሄዳቸው ችግር እንዳለበት ግልጽ ስለሆነ ቤተክርስቲያኗ ያለፈውን ነገር ተመልክታ ነው መፍቀድ ያለበት፡፡ መስተካከል ያለበትን ነገር መስተካከል አለበት፡፡ መመከር ካለባቸው ይመከሩ፡፡ አለበለዚያ ግን በዚህ መንገድ ነው የምንቀጥለው የሚሉ ከሆነ ግን አስቸጋሪ ነው፡፡ እስከአሁን እያካሄዱ ያሉት የአስተምሮ መንገድ ችግር እንዳለበት ስለአመንኩበት የት እንደሚገኝ በደንብ ንገሩን፡፡ በድምጽም ከሆነ ድምጻችንን እንስጥ አድራሻውን ግለጹልን፡፡

    ReplyDelete