Monday, July 15, 2013

ቤተክርስቲያን ላይ ብዙ ጉዳት ያደረሰው ቀበሮ መነኩሴ በእስርና በገንዘብ ተቀጣ


(አንድ አድርገን ሚያዚያ 1 2005 .)በደብረ ብርሐን ከተማ‹‹አባ›› በረከት የሚባል ሰው በገዳማት እና በአድባራት ላይ ብዙ ጉዳትእንዳደረሰ ገልጸን ከወራት በፊት መጻፈችን ይታወሳል፡፡ ‹‹አባ›› በረከትመጀመሪያ ጎንደር ይኖር የነበረ ከዚያም ደንጨት ዮሐንስ ገዳምሲያገለግል የነበረ ሰው ሲሆን ከመንዝ አካባቢ እንደመጣ የጀርባ ታሪኩይናገራል ፡፡ የካቲት 2004 . በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረብርሐን ከተማ በደብረ ማዕዶት ቅድስት አርሴማ ገዳም በመግባትሲያገለግል እንደነበር መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ገዳም የሚመጡበርካታ እህቶችን በማታለል ዝሙት ለመፈጸም ሲንቀሳቀስስለተደረሰበት ይህን ድርጊቱን እንዲያቆም ከወንድሞች ምክርተሰጥቶትም ነበር፡፡  በቤተመቅደስ ውስጥ ድፍረትና ክህደትየተሞላበት የአማኙን እምነት የሚቀንስና ለትልቅ ድፍረት የሚያደፋፍርእንቅስቃሴዎች ሲያደርግ እንደነበር በጊዜው በቦታው የነበሩ የአይን እማኞች  ገልጸዋል ፡፡ አርሴማ ገዳምላገለግል ነው ብሎ ሲገባ አብራው የመጣች ወለተ መስቀል የምትባል  መነኩሴ የነበረች ሲሆን  በገዳሙበነበረው ቆይታ ለገዳማውያን አገልጋይ ካህናት ‹‹ከአንድ እናት ማህጸን የወጣን እህቴ ነች›› እያለ ሲያወራ እናሲያስወራም ነበር ፡፡(ሴትየዋ በአሁኑ ሰዓት ከ‹‹አባ›› በረከት የልጅ እናት ሆናለች)፡፡

ይህ ሰው በደነባ በዓታ ለማርያም አንድነት ገዳም አባ ገብረ ሥላሴ በሚል አዲስ መጠሪያ ስም ተቀጥሮ አንድ ወርበገዳሙ በመቆየት  የገዳሙን በርካታ ንዋየ ቅዱሳን በመስረቅ ነሀሴ 19 ቀን 2004 . በፖሊስ እንደተያዘ እናፖሊስም ባደረገው ማጣራት በርካታ የቤተክርስቲያኒቱ ንብረቶች  በተለያዩ ስሞች የወጡ መታወቂያዎች የገዳማትና የአብያተክርስቲያናት ሕገ-ወጥ ማህተሞች እና መሰል ለወንጀል የሚገለገልባቸው ቁሳቁሶች በፖሊስቁጥጥር ስር ውሎ ነበር፡፡ ፖሊስ ይህን ማስረጃ በመያዝ ለደነባ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ በመመስረት ከሙሉማስረጃ ጋር በማቅረብ በወቅቱ የፍርድ ውሳኔ አሰጥቶበት  ነበር ፡፡  

‹‹አባ›› በረከት በሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ማክሰኝት ከተማ በመሰል ተግባር ሲሰማራ ተገኝቶ የአካባቢው የሰንበት  ተማሪዎች ከፖሊስ ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር አውለውት ነበር፡፡ ፖሊስ ይህንሰው ጥፋተኛ ሆኖ በማግኝቱ በአካባቢው ፍርድ ቤት በማቅረብ  የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆበት በሰውየውን ጀርባየወንጀል ታሪክ በማጥናት  የሰራቸውን ወንጀሎች በመሰብሰብ  ስለሰራው ወንጀል የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችንምንኩስናን ከተቀበለበት ገዳም ፤ ከደብረብርሐን አርሴማ ቤተክርስቲያን ፤ ከደነባ ፐከተማ ፖሊስና ፍርድ ቤትእና ከተለያዩ ቦታዎች በመውሰድና በማጠናቀር ጠንከር ያለ ክስ ለፍርድ ቤት አቅርቧል፡፡ ፖሊስም የተሰጠውንመረጃ በመቀበል ስለ ትክክለኝነቱ ከደነባ ፖሊስ እና ከደነባ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጋር በመነጋገር ትክክለኝነቱንከማረጋገጥ በተጨማሪ ያስፈልጉኛል ያላቸውን ማስረጃዎች በፊት ከተከሰሰበት ወረዳ ፖሊስ እንደወሰደ ለማወቅተችሏል፡፡ የጎንደር አካባቢ ፖሊስ የ‹‹አባ›› በረከትን ሚስት ለመረጃ ከደብረ ብርሐን ወደ ጎንደር ሊያስመጣት መሞከሩንም መረጃ ምንጮቻችን ጠቅሰውልናል፡፡

ይህ ቀበሮ መነኩሴ የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት 23/09/05 . በዋለው ችሎት በተከሰሰበት ጉዳይ የሚያስቀጣ ሆኖ በማግኝቱ ፍርድ ቤቱ ዓመት ወር ጽኑ እስራት እና 1000 ብር ቅጣት ተወስኖበታል፡፡በዚህም መሰረት ሰውየው 28/09/05 . ወደ ሰሜን ጎንደር ማረሚያ ቤት መግባቱን ከቦታው ያሉምንጮች ገልጸውልናል፡፡

‹‹አባ›› በረከት እስሩን ጨርሶ ሲወጣ ወደ የት እንደሚሄድ አይታወቅምና ሁሉም በያለበት ከመሰል ሰዎች ራሱንና ቤተክርስቲያንን ይጠብቅ መልዕክታችን ነው፡፡

 ቸር ሰንብቱ

No comments:

Post a Comment