- ከሳውዲ አረቢያ እና ከሱዳን ቀጥሎ ኬንያ ሶስተኛ ትምህርት መስጫ ቦታ አድርገዋታል
(አንድ አድርገን መስከረም 2
2005 ዓ.ም)፡- በአሁኑ ሰዓት መንግስትና ሙስሊሙ ማህበረሰብ ያልተግባቡባቸው ጥያቄዎች እንዳሉ ይታወቃል ፤ መንግስት ከጀርባችሁ
በመሆን ሌላ ጥያቄ ያነገበ ኃይል አለ ሲል ፤ የሙስሊም ማህበረሰብ ተወካዮች ደግሞ “አይደለም የእኛ ጥያቄ አንድና አንድ ብቻ ነው”
በማለት ሙግት ከገጠሙ ወራት ተቆጥረዋል ፤ በተለያዩ መስኪዶች በአረብኛ “ይህ መንግስትና ይህ መጅሊስ እኛን አይወክለንም” የሚል
ትምህርት እንደሚሰጥ መንግስት የድምጽ መረጃው ደርሶት ክትትል መጀመሩ እና ከየቦታው አመጽ ሊያነሱ ይችላሉ ብሎ ጥርጣሬ ያሳደረባቸውን
ሰዎች በመያዝ በመመርመር ስራ ላይ መጠመዱ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ ፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጨረሻ የፓርላማ
ንግግር ላይ “….አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት….” በማለት የሰጡትን መልስ ብዙዎች
በግልጽ መቃወማቸው የሚታወቅ ሆኖ ጥያቄው መልስ ሳያገኝ የአቶ መለስ ሞት በመቅደሙ ተንጠልጥሎ መቅረቱ ይታወቃል ፤ ባለስልጣኖቻን
የ”አዲስ ራዕይ” መጽሄት እሳቤያቸው ተቀይሯል ወይስ አሁንም አብሯቸው አለ?
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በዚህ ላይ ያላቸውን አቋም ምን እንደሆነ እስካሁን አይታወቅም ፤ የእሳቸው ተልዕኮ አቶ መለስ
የጀመሩትን ስራ ማስጨረስ እንደሆነ በአንደበታቸው ተናግረው በጆሮዎቻን ሰምተናቸዋል ፤ ስለሆነ አዲስ ነገርና አዲስ አካሄድ ከአቶ
ኃ/ማርያም እንደማይጠብቁ ብዙዎች ሀሳብ እየሰጡ ይገኛሉ ፤ አቶ መለስ በህይወት እያሉ እንዳሉት ሽግሽግ ነው የተካሄደው ፤ ሽግሽግ
ደግሞ መሰረታዊ ለውጥ ያመጣል ተብሎ አይጠበቅም፡፡
የአሜሪካ መንግስት የውሀቢዝም እንቅስቃሴ
ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ መሆኑን ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን የላከውን መልዕክት ከዚህ በፊት ማቅረባችን ይታወቃል ፤ አሁን
እየሆነ ያለውን ሁኔታ ግን ነገ ይችህ አገር ምን አይነት ነገር እንደሚያጋጥማት ጠቋሚ ምልክት ይመስለናል ፤ በጊዜው የውሀቢዝም
እንቅስቃሴ ሲጀመር በጅማ ፤ በሐረር ፤ በአርሲ ፤ በደሴ እና በተለያዩ ቦታዎች ሰዎችን የመመልመል እና አስተሳሰቡን የማስረጽ ስራ
በሰፊው እየተሰራ መሆኑን መንግስት ደርሶበት ከፍተኛ የእስልምና እምነት ሃላፊዎችን በመጥራት ከፌደራል ጉዳዮች ፤ ከፊደራል ፖሊስና
ከፍተኛ የመንግስት ተወካዮች ጋር በመሆን የአንድ ቀን ስብሰባ በማድረግ “እጃችሁን ያስገባችሁ ወይም ማስገባት የምትፈልጉ ሰዎች
ተጠንቀቁ” የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወቃል ፤ ነገር ግን ማስፈራሪያው ብቻ እቅስቃሴውን ሊያቆመው አለመቻሉን አሁን ላይ
የሚታዩ ነገሮች ያመለክታሉ ፤ መንግስት የሚሄድበት አካሄድ እና ውሀቢያን የሚሄዱበት አካሄድ “አልተገናኝቶ” እየሆነ ነው፡፡ሲጀመር
ከዓመት በፊት መንግስት ውሃቢዝምን በተመለከተ በርካታ መረጃዎች እጁ ውስጥ እያሉት በጊዜው እርምጃ መውሰድ ሳይችል ቀርቶ ጉዳዩን
እዚህ ደረጃ እንዲደርስ የበኩሉን አስተዋጽዎ አድርጓል የሚሉ ሰዎች አልታጡም፡፡
ከወራት በፊት ይህን ትምህርት በማስተማር
የተደረሰባቸው እና በመስኪድ እንዳያስተምሩ የተከለከሉ ሰዎች መቀመጫቸውን ኬንያ በማድረግ አዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች
መስፈርታቸውን የሚያሟሉ መልማዮችን በማስቀመጥ ስራውን እንደቀጠሉበት ታውቋል ፤ እነዚህ እየተመለመሉ በስደተኝነት መልክ ከሀገሪቱ
እየወጡ የሚገኙት ሰልጣኞች በቂ ስልጠና ከተሰጣቸው በኋላ ወደ ትውልድ ቀያቸው በመመለስ አመለካከቱን እንደሚያሰፉ እና እንደሚያስፋፉ
እምነት ተጥሎባቸዋል ፤ ይህን አይነት አካሄድ አደገኛ የሚያደርገው ካልተማረው ማህበረሰብ እስከ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን
መመልመልን በማካተቱ ነው፤ በቅርቡ በአካል የምናውቃችው ጥቂቶች የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በማቋረጥ ወደ ቦታው ማምራታቸውን ማየት
ችለናል ፤ የዩኒቨርሲቲን ትምህርት በማቋረጥ ለውሃቢያን ወታደር ሆኖ ራስን በመንገርና አመለካከቱን ለማራመድ ረዥም ርቀትን ለመጓዝ
ራስን ማሳመን በጣም ከባድ ነገር መስሎ ይታየናል፡፡ እስከ አሁን ድረስ ለዘመናት ትምህርቱን እዚህው ባሉ የእምነት ተቋሞቻቸው ውስጥ
መውሰድን በመተው ለምን ኬንያ ድረስ ሄዶ መማር አስፈለገ ? መልስ የሚያሻው ጥያቄ ይመስለናል፡፡
ማህተመ ጋንዲን እና ኔልሰን ማንዴላን የመሰሉ ሰዎች አንድ ሰው ሆነው ለአንድ
ሀገር እንደበቁ ሁላ ፤ ሀገርን ለማመስ እና ሀገርን ለመበጥበጥ አንድ ሰው የሚበቃበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል መንግስት ያጤነ
አይመስልም ፤ ስለዚህ ነገ ሰዎቹ ሰልጥነው ወደ ቀያቸው መመለስ ሲጀምሩ ፈተናው ለማን እንደሆነ ሲደርስ የምናየው ይሆናል፡፡
በአሁኑ ሰዓት መንግስት ከደሙ ነጻ
የሆነውን አካል አክራሪነትን ያስፋፋል በማለት በጥቂቶች ወሬ ፤ ባልተጨበጠ ማስረጃ ፤ ምንጩ ባልታወቀ መረጃ እና አሉባልታ ጉልበቱን
ሲያባክን ከኬንያ የተማሩ እና ረዥም ርቀት ለመጓዝ የቆረጡ ሰዎች እንደሚመጡለት ግምት ውስጥ ያስገባ አልመሰለንም ፤ ባልተጨበጠ
መረጃ ላይ በመመስረት በየስልጠና ጣቢያው አባላትን በመሰብሰብ ቤተክርስቲያንን ስላገለገሉ እና በእምነታቸውና ለእምነታቸው ስለቆሙና
ስላደሩ ብቻ በአክራሪነት መመደብን በመተው የሚታይና የሚጨበጠውን ነገር ላይ አትኩሮት ሰጥቶ ቢሰራ መልካም ይመስለናል ፤ ዛሬ ካጠገባችን
የምናውቃቸው ሰዎች ይህን አመለካከት ለመማርና ለትውልዱ ለማስተላለፍ ሲንቀሳቀሱ አይቶ መንግስት ዝም የሚል ከሆነ ነገ ሊሚመጣው
እና ለሚፈጠረው ችግር የመጀመሪያ ተጠያቂ መሆኑን መዘንጋት የለበትም ፤ ፍራቻችን ፍሬዋን አብረን እንዳንቀምሳት ጭምር ነው ፤ አዲስ
ራዕይን በመሰሉ ወቅታዊ መጽሀፍት የሌሎችን ሀገሮች ተሞክሮ በመውሰድ ስለ ሃይማኖት አክራሪነት ከመፃፍ ይልቅ በአይን የሚታየውንና
መሰረቱን ሀገር ውስጥ ያደረገውን እንቅስቃሴ ተከታትሎ ከእንጭጩ እንዳያድግ ማድረግ የተሻለ ይመስለናል ፡፡
የአንድ ሰው አመለካከት ብዙዎችን
የእሳት ራት ያደርጋል ፤ የጥቂቶችም እርምጃ በማወቅ ሆነ ባለማወቅ ብዙዎችን ተሰላፊ ሊያደርግ ይችላል ፤ የቀድሞ መንግስት “ባለህበት
ሂድ” እያለ 17 ዓመት ራሱም ፤ ህዝቡም ፤ ሀገሪቱም ለዓመታ ቆመው ሰንብተው ነበር ፤ ይህ የተሳሳተ አመለካከት ከግለሰብ እስከ
ሀገር ድረስ ብዙ ዋጋን አስከፍሏል ፤ ከህዳር 14 1967 ዓ.ም ጀምሮ ከተነሳው የግፍ ግድያ እስከ 1983 ድረስ ብዙውን አይተናል
ሰምተናል ፤ የጥቂቶች አመለካከት አዘቅት አውርዶናል ፤ እርምጃችንን
የኋሊት አድርጎታል ፤ ህዝቡ ከደም እንባ ማልቀስ እንባ ማልቀስን የተመኝበትን ጊዜ አሳልፈናል ፤ ስለዚህ አሁንም በዚህ በ21ኛው
መቶ ክፍለ ዘመን ሌላ ሃሳብ ይዘው የተነሱ ሰዎች ቢያጋጥሙን ነገን በማሰብ የታቀፏን እንቁላል በመካከላችን እንዳይፈለፍሏት የአቅማችንን
መጣር መቻል አለብን፡፡
በቤተክርስቲያን ስትገቡ ስለ እምነቱ ለምን ? ብሎ የሚጠይቅ አማኝ ልታገኙ ትችሉ ይሆናል ፤ ነገር
ግን እንደሌሎች ሀገራት አክራሪ በማለት የሚያደርስ አመለካከት ያለው
የእምነቱ ተከታይ ለማግኝት ግን የሚያዳግት ይመስለናል ፤ የመንደር ወሬ እየሰሙ ምእመኑን ማወክ እና ሰዎች ስራቸውን እንዳይሰሩ
ማድረግ ተገቢ አይመስለንም ፤
የተኛቹ ንቁ
አሁን ላይ የሚደረግን እንቅስቃሴ
አጽንኦት በመስጠት ካልተከታተልን ነገ ለምን ሆነ ብለን ጠያቂ መሆን
የለብንም ፤ ፍሬዎቹ አፍርተው አሁን ባንመለከታቸው እንኳን ነገ እንደሚያፈሩና የእግር እሳት እንደሚሆኑብን ማወቅ መቻል አለብን
፤ ዛሬ በንዝህላልነት ያሳለፍናት እያንዳንዷ ትዕይንት ነገ ዋጋ እንደማታስከፍለን እርግጠኞች ሆነን መናገር አንችልም ፤ ስለዚህ ስለ ራሳችን ስለ አካባቢያችንና ስለ እምነታችን ብለን በአጠገባችን የሚሰራን ነገር በአንክሮ በመከታተል ለሚመለከተው አካል
ማቅረብ መቻል አለብን ፤ መንግስትም የማይመለከታቸውን እጃቸው የሌሉበት
አካባቢዎችና ማህበራት ላይ ጉልበት እና ገንዘቡን ከሚያባክን ይልቅ መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ቦታዎች ላይ ትኩረቱን ቢያደርግ መልካም ነው እንላለን፡፡ ከበላይኛው የምትገኙ ኃላፊዎቻችንም
መረጃ በአግባቡ ይኑራችሁ ፤ የመረጃ እና የመረጃ ሰዎች ብቻ ለመሆን ሞክሩ ፤ እኛም ለዚህ እንቅስቃሴ ከሁሉም ጋር መረጃ ለመስጠት
የተዘጋጀን መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን ፤ የተኛችሁ ንቁ፡፡
ቸር ሰንብቱ
በቅድሚያ ይህን አስተያየት ብታወጡም ባታወጡትም ግድ እንደሌለኝ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ አላማየ የዚህ ጽሁፍ ባለቤት እንዲመለከተው ነው እና!!!
ReplyDeleteሙስሊም ነኝ ሙሐመድ እባላለሁ።
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለብዙ ዘመናት ችለን ኖረናል።ያም ሆኖ ግን ይቅር ብለን ለሃገራችን እድገት ደፋ ቀና እያልን ባለንበት ሰአት መንግስት ለራሱ የማያምንበትን አህባሽን ከሊባኖስ አምጥቶ ተጠመቁ አለን።እኛም አንጠመቅም በሃይማኖቶች ውስጥ ጣልቃ እየገባህ አትበጥብጠን በማለት ተቃውሞ እያሰማን እንገኛለን።የሚገርመው ግን የ እናንተ ስለ ሙስሊሙ ያላችሁ ቅንነት የጎደለው አመለካከት ነው።እናንተ በ እርግጥ አይፈረድባችሁም።ራሳችሁ መንግስት ናችሁ ስለሆነም ነው በዚህ አስቸጋሪ ሰአት እንኳ በ እምነታችን ጣልቃ ተገብቶ በሰላም እየታገልን ባለበት ወቅት እናንተ በጤነኛ አስተያየት የማታዩን።ለመሆኑ መብት መጠየቅ ወንጀል ነው?እናንተ በዋልድባ ጉዳይ እንዴት ነው እየተንገበገባችሁ ያላችሁ?እኛም እንዲሁ ለ እምነታችን እንንገበገባለን።ያውም የባእድ እምነት ልጫንባችሁ የሚለንን አካል እንቃወማለን።መስጊድ ውስጥ ብቻ አሏሁ አክበር ብለን የምንቀር እንዳይመስላችሁ!!!ገና አደባባይ እንወጣለን!!!በዚሁ አያበቃም እስልምናችን እስኪከበር እና መንግስት ከ እምነታችን እስኪወጣ ድረስ እንታገላለን።ከትግል የሚያቆመን ሞት ብቻ ነው።እናንተ የፈለጋችሁትን ስም ልትሰጡን ትችላላችሁ አያስጨንቀንም።ነገር ግን አላህ በጠላቶቻችን ላይ ብዙ ተአምር እያሳየን ስለሆነ የወያኔ መንግስት እና ግብረአበሮችን ፈርተን ዝም አንልም።
የጠየቅነው መሰረታዊ ጥያቄ ወደ ጎን ተተርጉሞ ሰድባችሁ ለሰዳቢ ብትሰጡንም ትርፉ ትዝብት ነው እንጅ አላህ ከሚወስነው ውሳኔ 1 ሜትር ፈቀቅ ልታደርጉን አትችሉም።እናንተም ከመንግስት ጋር ተባብራችሁ ሙስሊሞችን ለመበደል ከሆነ ሃሳባችሁ አትልፉ!የበላዩቹ በላይ የታላቆቹ ታላቅ አላህ አለን።መመኪያችንም እሱ ነው።እኛ ሙስሊም ሆነ መሞታችን በቂ ነው እንኳንስ ሙስሊም ሆነን አንገታችንን ቀና አድርገን መኖር እየቻልን።ለሃገር እና ለወገን የምታስቡ ከሆነ ፕሮፓጋንዳችሁን አስተካክሉ።ይህ መንግስት እምነት ያለው መስሏችሁ ከሆነ አንድ ቀን ታውቁታላችሁ።እኛ ግን ወደፊት እንጅ ወደኋላ የማንመለስ መሆኑ ታውቁ ዘንድ ምኞታችን ነው።የሰው መብት አንነካም የ እኛንም አንሰጥም።የሰው እምነት አንዘልፍም ፡እናከብራለን።ተከባብረን እንኖራለን።በ እምነታችን የመጣብንን ግን እንዴት እንደምንቃወመው ጠንቅቀን ስለምናውቅ ኬኒያ ሳኡዲ ምናምን ብትሉ ምንም አይመስለንም።መብታችን ሲነካ የትግል ስልታችን ቁርአን ላይ አለ።ኬኒያ መሄድም አያስፈልግም።እናንተ ግን በጣም ጠባብ ነው አስተሳሰባችሁ።እናዝናለን።ሁሉም ከመንግስት ጋር ቢያብር አላህ ከጻፈብን ውጭ ቅንጣት ነገር አይመጣብንም። አላህ በቂያችን ነው።እናንተ ግን ሚዛናዊ ላልሆነ አስተያየታችሁ በጣም ታሳዝናላችሁ።በ እርግጥ የወደፊት የኢትዮጵያ እጣ ፈንታም ያሳዝናል።ትውልዱ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል መሆኑ።አይ አንች ሃገር መጨረሻሽ ናፈቀኝ?
Selam Mohammed,
DeleteI think your idea is good and one Ethiopian Muslim could raise it. However, we all know that how Bokoharam in Nigeria and Alqaida in the whole world make the hell. We all ethiopian afraid that this group idea could come to our contry. I believe this should be all ethiopian without religion difference... Ethiopian muslim particulary have more responsiblity to protect their endigounious faith because they know where those people are organized for this evil action.
I think you have a good point and we, other ethiopians, also share your point, but you guys also have to do you assignment to stand for the truth, not for bliendly supporting those groups. By the way, I grown up in majority muslim area, and know lots of innocent people as well as extrimely hateful people. Those hateful people were going to Pakistan, not I think it's in Kenya. May God protect our country! I hope we all love our contry and we have to stand together for Ethiopia.
Mohamud PLS dont generalized the hall Cristian b/c of one person opinion.Z R a lots of peopel which are thinking posetive about 2 but 1 People. So We are ETHIOPIANS not like other Countries.WE both religins have enemy . If we pray for our God he knows the solution .No one stope his willing !
DeleteThanks Andadrigen!
ReplyDeleteEven though Mk has no good strategy to solve the problems related to Tehadiso (according to my view), Mk by no means cannot be considered as Extremist. The Ethiopian Government has the following major problems related to EOTC and tolerance:
1. It hates EOTC, as agreed among TPLF members at its establishment; the government knows that EOTC is the core for unity among Ethiopian Christians. So the unity among Christians and strength of the church does mean EOTC will not allow it to do oppression on the people. We know that all the parties in EPDRF are followers of TPLF. Others will not have different idea if TPLF members who came from Orthodox family think like that.
2. The Ethiopian Government afraid to speak problems explicitly. It is known that there are Muslim extremists in the country. But instead of identifying them and telling them explicitly, the government is insulting Christians also for problems ignited by Muslims.
At the time of Jimma Massacre, the late prime minister had condiment the slaughters and those who record the massacre and distribute to the people. This is by no means right.
We always appreciate for tolerance and good understanding to solve the problem properly. This is not religious tolerance. People who committed crime and who are preparing for crime should be punished properly. Where are the people who killed the people around Jimma? Are they jailed upto now? The public doesn’t have any information about them. If the government has sent them for free to their home, where is justice?
I agree.
DeleteGod bless u for the information Andadrgen
ReplyDeleteDear Mohamed, The government is against Tewahedo religion,even government strategy to mobilize muslim over orthodox that their intention but it won't happen. please read the foloowing from Deje selam website.
የኢሕአዴግ ቤተ ክርስቲያንን የተመለከተው “ፖለቲካዊ ትንታኔ” ገና ከትግሉ ዘመን ጀምሮ ፈር በያዘ መልክ የተጠናና አቋም የተያዘበት እንደሆነ የህወሐት መሥራች አረጋዊ በርሄ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ባደረጉት የምርምር ሥራቸው (A Political History of the Tigray People’s Liberation Front (1975-1991): Revolt, Ideology and Mobilisation in Ethiopia/ Amsterdam 2008) ላይ ጽፈውልናል። የፓርቲው ሃይማኖትን በተመለከተ የያዘው ይህ አቋም በተለይም ነባሮቹን የኢትዮጵያ ቤተ እምነቶች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እና እስልምናን የተመለከተ መሆኑን፣ ኮሚኒስታዊ ፓርቲዎች ሁሉ ባላቸው “የጨቋኝ - ተጨቋኝ” ትንታኔ መሠረትም እነዚህ ሁለቱ ቤተ እምነቶች በተለያየ ጎራ እንዲቀመጡ መደረጋቸውን፣ ክርስትና ጨቋኝ፣ እስልምናም ተጨቋኝ ተብሎ መፈረጁን አንብበናል።
ዶ/ር አረጋዊ ባብራሩት የኢሕአዴግ ትንታኔ መሠረት “ቤተ ክርስቲያን ከቀድሞቹ መንግሥታት ጋር “በነበራት ቁርኝት” ከገዢው መደብ ጋር የተሰናሰለ የጥቅም እና የጨቋኝነት ግንኙነት ነበራት። በነዚህ ረዥም የጭቆና ዓመታት ከተጨቆኑት መካከል ደግሞ ሙስሊሞች” ይገኙበታል፤ ስለዚህም ኢሕአዴግ ይኼንን የጭቆና ቀንበር “ለመስበር” እና እኩልነትን ለማስፈን የተከተለው ፖሊሲ፣ “ቤተ ክርስቲያንን ማምከን/ፍሬ ቢስ ማድረግ” እና “ሙስሊሞችን ማንቀሳቀስ” ("neutralizing the Church and Mobilizing Muslims) ነው። (ገጽ. 300)
እንደ ዶ/ር አረጋዊ ገለጻ ከሆነ “በኢህአዴግ እና በቤተ ክርስቲያን መካከል የነበረው ግንኙነት ከመጀመሪያው ጀምሮም ችግር ያልተለየው” ነበር። የትግሉ ማዕከል ከነበረው ከትግራይ ስንነሣ በሕዝቡ መካከል የሚደረገው ማንኛውም ግንኙነት በቤተ ክርስቲያኒቱ እና በአገልጋይ ካህናቷ ቁጥጥር ሥር የወደቀ ነው። ሰርጉ፣ ክርስትናው (የሕጻናት ጥምቀቱ)፣ ቀብሩ እና በጎረቤቶች አለመግባባት ወቅት ያለው ሽምግልናውና እርቁ በሙሉ የሚፈጸመው በቤተ ክርስቲያን በኩል ነው። ያንንም ለማከናወን ደግሞ በቂ ካህናት አሉ። በተጨማሪም እያንዳንዱ ቤተሰብ ሕይወቱን የሚከታተሉ አባቶች (የነፍስ አባቶች) በነፍስ ወከፍ አለው። ስለዚህም በያንዳንዱ አካባቢ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከሕዝቡ ሕይወት ጋር ከፍተኛ ቁርኝት አላት።
በሁለተኛ ደረጃ ቤተ ክርስቲያን በሕዝቡ እና በመንግሥታት መካከል ድልድይ ሆና ትሠራለች። ዶ/ር አረጋዊ እንዳሉት “ቤተ ክርስቲያኒቱ ሁልጊዜም ካለፉት ነገሥታት ጋር አብራ ቆማለች፤ መንግሥታቱም ቤተ ክርስቲያኒቱ እንድትኖር፣ እንድትስፋፋ እና አንድነቷ እንዲጠበቅ” ረድተዋታል። ቤተ ክርስቲያን ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ አገር አቀፍ ድረስ ተቋሟን ከመዘርጋቷም በላይ በመንግሥትና በተቀናቃኞች መካከል ለሚፈጠር ቅራኔ በአስታራቂነት እስከመግባት ትደርሳለች። ምእመናኗም ለመንግሥታቸው እንዲገዙ ታስተምራለች፣ አገራዊ ብሔርተኝነት እንዲዳብርም በማዕከልነት አገልግላለች። ባንዲራን የመሳሰሉ አገራዊ ምልክቶችን በበዓላቷ ሳይቀር ከፍ አድርጋ በማውለብለብ ብሔራዊ ማንነትን (national consciousness) ገንብታለች። የቤተ ክርስቲያን በዓላት ካለ ሰንደቅ ዓላማ በጭራሽ አለመከበራቸውን ልብ ይሏል።
በሦስተኛ ደረጃ በየዘመኑ የነገሡ ነገሥታት በቤተ ክርስቲያን እስካልተቀቡ ድረስ ንግሥናቸው ተቀባይነት አልነበረውም። ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን የነገሥታቱ ሥልጣን አረጋጋጭ እና ወሳኝ ሆና አገልግላለች። በአኩሱም ጽዮን ለሚፈጸመው ለዚህ ቅብዓ መንግሥት ነገሥታቱ በበኩላቸው ርስት እና ጉልት በመሥጠት ቤተ ክርስቲያኒቱን ጠቅመዋል። አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሳይቀሩ መተዳደሪያ እንዲኖራቸው፣ የአጥቢያው ምእመንም እንዲንከባበከባቸው፣ አገልጋይ ካህናቱም የሚያስፈልጋቸውን ነገር እንዲያገኙ የአጼዎቹ አስተዳደር ጠቅሟቸዋል።
“አጼያዊው አስተዳደር ከወደቀና ቤተ ክርስቲያን ርስት ጉልቷን ሁሉ ካጣች በኋላ በወታደራዊው መንግሥት እና በሰሜን በሚዋጉ ተቃዋሚዎች መካከል አጣብቂኝ ውስጥ ገባች” ይላሉ አረጋዊ በርኸ። “ኢ.ዲ.ዩን በመሳሰሉ ፓርቲዎች ላይ ተስፋ አሳድራ ብትቆይም ሳይሳካ” ቀርቷል።
it is the matter of time today for muslims and tomorrow for shure for ortodox chrstians specially mahbere kidusan.this is woyane strategy.but let protestant remain in the power for the SAKE of america and western countries.
ReplyDeleteif the governmet answer those very resonable questions for muslims it is good for our country stability because if no peace we will suffer from it & we will pay the price togeter.
belive me time will speak loud.that is why haylemaryam is there.very sensitive and key postions now dominated by protestants,this is usa strategy.do you think they are 12%of the popoulation?man wach your step more to come about them.imagine how there church is 5 meter far from the maint street in addis,i dont care about it but what was the reason?if respect your religion and work for church like MK woyane will stop against you.meles is mentiond it deplomatically.am i correct?let us wait tommorow together.thank you.
ይሄን ፔጅ ሁሌም እከታተላለሁ በአብዛኛው ስለ እስልምና ትክክለኛ መረጃ የላችሁም ይሄን አስተካክሉ ። ብቻችሁን ሰላም ማምጣት አትችሉም 100%። ስለዚህ ከ እውነት በመወገን መታገል ጥሩ ነው ካልሆነ ዝም ማለት የተሻለ እና ተመራጭ ነው። በተረፈ ሁላችሁም አስተያየት የሰጣችሁት በጠም ጥሩ ነው።
Deleteእንደምን ዋላችሁ ሙሐመድ ነኝ ከላይ የተሰጡት አስተያየቶች በሙሉ ሚዛናዊ በመሆናቸው ውስጥን ይኮረኩራሉ።በ እርግጠኝነት ግን አንድ ነገር መናገር እችላለሁ እስኪ ልብ ብላችሁ የሙስሊሞችን ተቃውሞ እስከ አሁን ያለውን ተመልከቱ?በፌዴራል እየተደበደቡ እየቆሰሉ አንድ ጠጠር እስከ አሁን አልተወረወረም።ከዚህ በላይ ሰላማዊነት አለ?ምክንያቱም ወታደሩ ታዛዥ ስለሆነ ውሎ አድሮ እውነታውን ሲርረዳው በወገኖቹ አይጨክንም የሚል አስተሳሰብ ነበረን።እስከ አሁንም ተስፋ አልቆረጥንም።እኛ ሙስሊሞች የተደበቀ አጀንዳ የለንም።ከወለድ ነጻ ባንክ ዘምዘም እንኳ ሲከለከል ከዝምታ ውጭ ምንም አላልንም።አሁን ለምን ሆድ ባሰን?መንግስት ወደ አህባሽ ከሚያስገድደን ወደ ኦርቶዶክስ ኑ ቢል ይሻለው ነበር።ምክንያቱም እምነቱ ስለሆነ ነገር ግን እንዴት ወደማያምንበት እምነት እንድንጓዝ ያስገድደናል?መጅሊስ በቀበሌ እንዲመረጥ ማስገደድ ምን ይባላል?ሲኖዶስ ቀበሌ ይመረጥ ቢባል ያስኬዳል?በአላህ ስም እምላለሁ ሲኖዶሱ ቀበሌ ይመረጥ፡ቢባል በጣም ነው የሚገርመኝ እና የምቃወም።ታዲያ መንግስት እንደዚህ ሲረብሸኝ ጥያቄያችንን እያጣመመ ከአልሸባብ ጋር ግንኙነት አለው፣ኢስላማዊ መንግስት ሊያቋቁሙ ብሎ ሰድቦ ለሰዳቢ ሲሰጠን ለምን ከጎናችን አትቆሙም?እውን የኢትዪጵያ ሙስሊሞች ለክርስቲያኖች አስጊ ናቸው? የኢትዪጵያ አምላክ በ እውነት ይፍረድ!!አንድ ነገር ግን አትርሱ!ሰላም ስናጣ እናንተም ታጣላችሁ፡በ እኛ ጥይት ሲተኮስ እናንተጋ ጭሱ ይደርሳል።መርካቶ ቢታመስ የ እናንተም መርካቶ ነው አንዋር ቢቆስል ራጉኤል ያለቅሳል።እውነታው ይህ ነው ካልመሰላችሁ ለታሪክ እንተወው።ሙስሊሞች በጣም ታጋሽ ነን።የሰው እምነት እናከብራለን።ኬኒያ 20% ሙስሊሞች 3 ከወለድ ነጻ ባንክ አላቸው እኛ 33.9% አንድ ባንክ እንኳ ተነፈገን ይህ ፌር ነው?ወለድ እኮ በ እናንተም እምነት ክልክል ነው ታዲያ ምኑ ላይ ነው ክወለድ ነጻ ባንክ የመጠየቅ ነውሩ?የ እኛ ሴቶች ሂጃብ ሲለብሱ አክራሪ ይባላሉ ማርያም እራሷ ላይ ያደረገችው ሂጃብ አይደለምን?ሙስሊሞች ጺማቸውን ሲያሳድጊ አክራሪ ይባላሉ እስክ የሲኖዶሱን ከፍተኛ አባላት ተመልከቱ ጺሙን ያላሳደገ አለን?ለምንድን ነው የሙስሊሞች ሁሉ ነውር የሚመስለው?እኛ ምክንያቱን እናውቀዋለን። ስለዚህ እባካችሁ እኛ ድብቅ አላማ የለንም።ችግሩ ይህችም ጥያቄ ሆና አትመለስላችሁም ተብለን እንደ እባብ ልቀጥቅጣችሁ ከተባልን እምነታችንም እንደዚህ ሆነን እንድንኖር አልፈቀደልንም።እና የ እኛ ሰላም ሲደፈርስ እናንተም ትረበሻላችሁ ትምህርት ይቆማል ሱቅ ይዘጋል ለ እኛ የተተኮሰ ተባራሪ ጥይት አትፈሩም?ለ እኛስ አላህ አለን ።
ReplyDeleteHey! please make it a professional one. This one has bised information with illogical conclusion. Only open mindedness help the better future of EMMEYE ETHIOPIA.
ReplyDelete