ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም (አዲስ አበባ) :- የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በባለፈው በጀት ዓመት የተሰሩ በርካታ ክንዋኔዎችን ዛሬ ጥቅምት 7 ቀን 2015 ዓ.ም 41ኛው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በተካሄደበት ላይ በሪፖርት አቅርበዋል ። ብፁዕነታቸው በሪፖርቱ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ሐዋርያዊ ክንውን ፣ ሐዋርያዊ ተልዕኮና መንፈሳዊ አገልግሎትን በተመለከተ የተሰሩ ሥራዎችን ፣በአስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ የተሰሩ ስራዎችን ፣የምግባረ ሠናይ ዘርፍን በተመለከተ ፣ የልማት ድርጅቶችን እነዚህንና ሌሎችም መሰል ተግባራትን በተመለከተ በንባብ አሰምተዋል ።
ብፁዕነታቸው በመጨረሻም መሠረታዊ የመወያያ አጀንዳዎች የሚሆኑ መነሻ ሐሳቦችን አቅርበዋል። ብፁዕነታቸው ካቀረቧቸው መነሻ ሀሳቦች መካከልም
Ø
ስለ ሀገራችን ሰላም የቤተ ክርስቲያን አስተዋጽኦ ምን ይሁን ?
Ø
በቤተክርስቲያን እና በምእመናን የሚደርሰውን ግፍ በምን መልኩ ማስቆም ይቻላል ?
Ø
የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ለማረጋገጥ (አብነት ትምህርት ቤት ለማስቀጥል፤ ሰንበት
ትምህርትን ከማጠናከር
አንጻር፤ ስብከተ
ወንጌል ከማስፋፋት
አንጻር ?)
Ø
በጀት አጠቃቀም ላይ ያለውን ችግር እንዴት እንፍታው?
Ø
የቤተ ክርስቲያንን ምጣኔ ሀብት እንዴት እንጠብቀው?
Ø
ከመንበረ ፖትርያርክ እስከ አጥቢያ ድረስ ተናበን እንዳንሰራ እንቅፋት የሆነብን ምንድን ነው ?ተናቦስ ለመሥራት ምን እናድርግ ?
Ø
የቤተ ክርስቲያንን ክብር እንዴት ጠብቀን እናስጠብቅ ?
Ø
ቤተ ክርስቲያናችን ለተጎዱት
ከመድረስ ይልቅ ጉዳት ደረሰብኝ ባይ ሆናለች ስለዚህ ከዚህ ለመላቀቅ መፍትሄው ምንድን ነው ?
Ø
ሙስናን እንዴት አድርገን ከቤተ ክርስቲያን እናላቀው? የሚሉ መሰል ጥያቄዎች ከብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ሪፓርት ቀጥሎ ለተሰብሳቢዎቹ የተሰጠ ሲሆን ከቀትር በኋላ ውይይት ይድረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
No comments:
Post a Comment