አዲስ አበባ ፣ ሰኔ
25 ፣ 2007 (ኤፍ ቢ ሲ)
በስዊዘርላንድ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን በአይ ኤስ ለተገደሉ ወገኖች ቤተሰቦች ከ400 ሺህ ብር በላይ ስጦታ አበረከቱ። ድጋፉ የተደረገው ለ11
ተጎጂ ቤተሰቦች ሲሆን፥ ለእያንዳንዳቸው 27 ሺህ
500 ብር በአጠቃላይ ከ 400 ሺህ
ብር በላይ
ተብርክቶላቸዋል። እጅግ ችግረኛና በእድሜ ለገፉ ስድስት ቤተሰቦችንም ለመደገፍ ቃል ገብተዋል። የቤተክርስትያኗ
ሊቀ ጳጳስ
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባስተላለፉት መልዕክት ቤተክርስትያኗ ይሄን
አሰቃቂ ድርጊት ከሰማችበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ተግባራት አከናውናለች።
የተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት ሌሎች ኢትዮጵያዊያን ምንም
ዋስትና ወደ
ሌለበት አገራት እንዳይሰዳዱ ትልቅ ትምህርት ነው ያሉት ብፁእነታቸው በቀጣይም ቤተክርስትያኗ
ዜጎች በአገራቸው ሰርተው እንዲለወጡ ትሰራለች ብለዋል።ከውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተወከሉት አምባሳደር ሙሌ ታረቀኝ በበኩላቸው መንግስት ችግሩን ከምንጩ ለመድረቅ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ነው ብለዋል።
ምንጭ:-ኢዜአ
No comments:
Post a Comment