Tuesday, February 28, 2012

በስልጤ ዞን ሊካሄድ የታሰበው እርቀ ሰላም ተሸጋገረ


(አንድ አድርገን የካቲት 20 ፤ 2004ዓ.ም )፡-  በስልጤ ዞን ከቅበት ከተማ 2 ኪሜ ርቀት ላይ የምትገኝው የቅድስት አርሴማ ቤተክርስትያን አካባቢን ለማረጋጋት መንግስት የሰጠውን የመፍትሄ አቅጣጫ በብሎጋችን ላይ ማስነበባችን ይታወሳል ፤ የካቲት 17 ቀንም እርቀ ሰላም ለማካሄድ ፕሮግራም መያዙንም ጠቅሰን ነበር ፤ የክልሉ  ጸጥታ ጉዳይ አቶ አሰፋ አብዮ እና የፌደራል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በጊዜው ተደራራቢ ጉዳይ ስላጋጠማቸው በቀኑ መገኝት እንደማይችሉ የገለፁ ሲሆን እርቀ ሰላም የሚካሄድበትን ጊዜ ለቀጣይ ሳምንት እንዲሆን ወስነዋል ፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ሰዓት በአንዳንድ ክርስትያኖች በእርቀ ሰላሙ ጊዜ ይነሳሉ ተብለው የሚጠበቁ ጥያቄዎች ‹‹ ለምን ቤተክርስያን በቦታው ላይ መስራት አንችልም ? ‹‹ቤተክርስትያኗ የፈረሰችበት ቦታ ላይ ቤተክርስትያን እንዳንሰራ ለምን ተከለከለ ? ‹‹እዚያ ቦታ ላይ ቤተክርስትያን እንዳይሰራ በመከልከል ሌላ ቦታ መፍቀድ መፍትሄ ሊሆን ይችላል ወይ ?›› የሚሉ ይገኙበታል ፤ ይህን የመሰሉ መሰረታዊ ጥያቄዎች በእርቁ ሰላም ላይ የሚያመጣውን ለውጥ ቀኑ ሲደርስ የምናየው ይሆናል ፤
ባለፈው የውሳኔ ሀሳብ ላይ በ15 ቀናት ውስጥ ለቅድስት አርሴማ ቤተክርሰትያን መስሪያ ቦታ ይሰጥ የሚል ውሳኔ ከበላይ አካል ቢተላለፍም ውሳኔው ተፈፃሚነት እንዳያገኝ በወረዳው የሚገኙ የመንግስት ሹማምንቶች ጉዳዩን ላለማስፈጸም ይዘውት ይገኛሉ ፤ ይህ እንዲህ እንዳለ ይህን ውሳኔ ላለማስፈጸም ቀበሌው ባዶ የሚሰጠው ቦታ የለኝም የሚል መልስ ሰጥቷል ፤ ህዝበ ክርስትያኑም ከእርቁ በፊት ይህን ጥያቄ እንዲመለስላቸው ጥያቄውን ለቀበሌው ሃላፊዎች እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡


በተያያዘ ዜና ባስቀመጥነው ስልክ አማካኝነት ብዙ ሰዎች ከሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ ቤተክርስትያኗ ስትሰራ የበኩላቸውን እርዳታ ለማድረግ ቃል እየገቡ ይገኛሉ  ፤ አንዳንዶችም ከዚህ በኋላ የምትሰራው ቤተክርስትያን ምን መምሰል እንዳለባት ከስራ አስኪያጁ ጋር ረዘም ላለ ሰዓት የተወያዩም አሉ ፤ ሌሎችም ሰዎችም ከቻሉ በግል ለመስራት ካልቻሉ የቻሉትን ክርስትያናዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ለመስራት ያቀዳችኋትን ቤተክርስትያን ካርታ ካላችሁ አቅርቡልን ያሉ ሰዎችም መፈጠራቸውን ሰምተናል ፤ ቤታችን ፈርሶ አይቀርም ፤ ብዙ እጥፍ በሚበልጥ መልኩ እንሰራዋለን ፤ ክርስትያን እንደ ሚስማር ሲመቱት የሚተብቅ መሆኑን እናውቃለን ፤ እግዚአብሔርም ይረዳናል አንጠራጠርም፤ መፅሀፉ እንዲህ ይላል ‹‹ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት›› የያዕቆብ መልእክት 5 ፤ 3 ‹‹በፈተና የሚጸና ሰው የተባረከ ነው፤ ከተፈተነ በኋላ ለሚወዱት ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን የሕይወትን አክሊል ይቀበላልና።›› ወደ ሮሜ ሰዎች 112 ለኛም ይህ ፈተናችን ነው ፤ ፈተናችንን ከእግዚአብሔር ጋር እንደምንወጣው እናምናለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ ቤተክርስትያኗን ለመርዳት የተዘጋጃችሁ ክርስትያኖች በእግዚአብሔር ስም ሳናመሰግን አናልፍም ፤ ወደፊትም የምትሰራውን ቤተክርስትያን ዲዛይኑን እና የሚያስፈልገውን ወጪ በመዘርዘር ህዝበ ክርስትያን በመስራቱ ሂደት ላይ እንዲረባረብ መረጃውን በብሎጋችን ላይ የምናሰፍር መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡


የሀገረሥብከቱ ሥራአስኪያጅ   መጋቢ ሀይማኖትአብርሐም   ስልክ  0911551516 ሲሆን አዲስ ለምትሰራው ቤተክርስትያን የምትረዱበት መንገድ በዚህ ስልክ ደውለው ማነጋገር የምትችሉ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፡፡

ተዓማኒና ፈጣን የቤተክርስትያን መረጃ እናቀርብሎታለን

‹‹አንድ አድርገን››

4 comments:

  1. Good job AndiAdrigen!!! We have raised the issue of helping in our church and we will try to send our breakfast expences that left because of Abiy Tsome to help build the damaged Church.

    TsegaSilase from USA.

    ReplyDelete
  2. Dear Andadrgen
    Ejeg betam Kale hiywot yasemachu

    Ageliglotachihun Egzibhere besemay yesafilachu.

    Bertu

    ReplyDelete
  3. kidist Arsema teaneran tasayen zend tegten entsley.

    ReplyDelete