Sunday, February 12, 2012

አስር አውቶቡስ ወደ ቤተክህነት


(አንድ አድርገን የካቲት 5 ፤ 2004ዓ.ም)፡- ከቀናት በፊት በጉባኤ የደብሩን አስተዳዳሪ ያገዱት የአዲሱ ሚካኤል ምዕመናን አሁንም ድረስ የታገዱት አስዳዳሪ እጃቸውን ከካቴድራሉ ላይ ባለማንሳታቸው በ01/06/2004 ዓ.ም 10 የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች እና የቤት መኪናዎች በመሆን ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ያመሩት በብዙ መቶ የሚቆጠሩ ምእመናን የካቴድራሉ አስተዳዳሪ ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ተክለ ጊዮርጊስ በአስቸኳይ ተነሥተው አዲስ አስተዳዳሪ እንዲመደብላቸው ለሁለተኛ ጊዜ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል፡ ፡ በሀገረ ስብከቱ እና በፓትርያሪኩ ትእዛዝ በተለያዩ ጊዜያት ወደ ካቴድራሉ የተላከው አጣሪ ኮሚቴ የደረሰበት ውጤት እንዳልተገለጸላቸው የተናገሩት የምእመናኑ ተወካዮች በአሁኑ ወቅት የካቴድራሉን አገልግሎት የሚመራ አስተዳደር ባለመኖሩ የደብሩን ካህናት እና የካቴድራሉን ት/ቤት መምህራንና ሠራተኞች ደመወዝ እንኳን ለመክፈል እንዳልተቻለ አስታውቀዋል፡ ፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ፊልጶስ ስለምእመናኑ ጥያቄ የሚያውቁት ነገር ባለመኖሩ ጊዜ ይሰጠኝ ማለታቸው የተዘገበ ሲሆን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ በበኩላቸው በአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርት መሠረት አስተዳዳሪው ምንም በደል እንዳልተገኘባቸው ነገር ግን ደግሞ ችግሩን በአጭር ጊዜ እልባት እንደሚሰጡት መናገራቸው በምእመናኑ ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፤ ምእመናኑን በበቂ ሳያወያዩና ሐሳባቸውን ሳያደምጡ መሄዳቸውም ቅሬታ ፈጥሯል፡፡  የተሻለ አስተዳዳሪ ለማግኘት ለአራት ወራት መጠበቃችን አግባብ አይደለም ያሉት ምእመናኑ፣ ያለአንዳች ሥራ ደመወዝና የነዳጅ አባል በሚል የካቴድራሉን ሀብት እስከ አሁን በመጠቀም ላይ ያሉትን ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራንና ተባባሪዎቻቸውን በሕግ ለመጠየቅ የሚያስችል በቂ ማስረጃ እንዳላቸው አስታውቀው ችግሩ ከዚህ የበለጠ ሳይከፋ አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው በድጋሚ አሳስበዋል፡፡
ምንጭ ፤- ፍትህ ጋዜጣ

5 comments:

  1. meche yehon yebet christiyan wezegeb yemiyabekaw?

    ReplyDelete
  2. mecha new wanawe cheger "Abuna Paulos" bekawote yemebalwte?

    ReplyDelete
  3. @Anonymous መቼ ይሆን የቤተ ክርስትያን ውዝግብ የሚያበቃው ላልከው? ለቤተ ክርስትያን ቀና የሆኑ ሁለ ገብተው በቤተ ክርስትያን በሰንበት ት/ቤት፣ በስብከተ ወንጌል፣ በልማት ኮሚቴ፣ በሰበካ ጉባዔ ገብተው ሲያገለግሉ ችግሩ ይፈታል። ነገር ግን ሁሉም በብልሀት መከናወን አለበት። አለበለዚያ ከጥቅሙ ጉዳቱ/ግጭቱ/ ይሰፋል።
    ኪዳነማርያም ዘደብረ ይድራስ

    ReplyDelete
  4. ere lidetam cheger west nen erdun

    ReplyDelete
  5. በጣም የሚገርመው ነገር እኝሁ የአዲሱ ሚካኤል አስተዳዳሪ የነበሩት አባት መጋቢት 09/07/04 ዓ.ም የታሪካዊው የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ ሆነው ተሹመዋል፡፡ በእውነት እኝህ አባት ለረጅም አመታት ጥሩ አባት ያጣውን የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያንን ምን ያደርጉት ይሆን?
    እግዚአብሔር አምላክ ቅድስት ቤተክርስቲያንንና ህዝቦቹዋን ይጠብቅ፡፡

    ReplyDelete