Wednesday, February 8, 2012

ሐውልቱ ስር ምን አለ?




‘ Ethiopia shall soon stretch out her hands unto God.’

(አንድ አድርገን ጥር 30 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- ቅዳሜ ጥር 17 ቀን 2004 ዓ.ም. አዲስ አበባ አንድ ዓቢይ ታሪካዊ ክሥተት አስተናገደች ፤ በ “ዓለም በቃኝ” (ከርቸሌ) መቃብር ላይ የተገነባው አዲሱ የበረከተ ቻይና ሕንፃ ፤ የአፍሪካ ኅብረት ለወለደው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት (አአድ) ጠንሳሿ ኢትዮጵያ ብኵርናዋን አሳልፋ የሰጠችበት መሪዎቿም አባሪና ተባባሪ ኾነው ያጸደቁበትን ፣ በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት ሕንፃ የተተከለውን የጋና ቀዳማዊ ፕሬዚዳንት ክዋሜ ንኩሩማ ሐውልት ቄጠማ ተነስንሶ እልል ተብሎ ሲመረቅ አይታ አንገቷን  የደፋችበትን ትዕይንት አስተናግዳለች፡


አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ዋና ፅ/ቤት በቻይና ለጋስነት ለአፍሪካ ገጸ በረከተረ ተደርጎ ከተሰራ በኋላ ይህው ተመርቆ የሳምንታት እድሜ አስቆጥሯል፤ ዛሬ አነሳሴ ስለ አፍሪካ ህብረት ህንጻ አሰራሩን ፤ የወጣበትን ወጪ ፤ የፈሰሰበት ቴክኖሎጂ ልነግራችሁ አይደለም  ፤ ባይሆን ህንጻው ሲመረቅ እኔም በቦታው ላይ የመገኝቱ እድል ገትሞኝ ነበር (እንዴት ተገኝህ ? በየት  ? የሚለውን ነገር መናገር ጥሩ ስላልሆነ አልፌዋለሁ) ፤ የተመለከትኩት ነገር አግራሞትን ፈጥሮብኛል ፤ ያየሁትን ብፅፈው ጥሩ ነው ብዬ በማሰቤ እንጂ ፤ ህንፃው ሲመረቅ ለአፍሪካ ህብረት ምስረታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ አፍሪካዊ መሪ በማለት አንድ ሀውልት መቆሙን ቀድሞ መረጃ ነበረኝ ፤ ነገር ግን የኔ ሀሳብ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ይሆናሉ የሚል ግምት ነበር ፤ ነገር ግን  የተሰራው ሀውልት ጨርቁ ሲቀደድ ሳይ ፤ አይኔን ድንግዝግዝ አደረገኝ ፤ ሀውልቱ ተራማጅ ህሳቤ ያለው ሰው ይመስላል ፤ ትንሽ ስቆይ ግን የቀድሞ የጋና ፕሬዝዳንት ክዋሜ ንክሩማ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ ፤ ይህ ሀውልት ጋና አክራ ላይ ከቆመላቸው ሀውልት ጋር በብዙ ነገሩ ተመሳሳይ ነው ፤ ለራሴ ‹‹ቀዳማዊ ኃይለስላሴ እያሉ ለምን?›› የሚል ጥያቄ ውስጤ ተጭሮ ዝም አልኩኝ ፤ ‹‹ነብይ ድሮም በሀገሩ አይከበርም›› ፤ ከግማሽ ምእት ዓመት በፊት ነፃነታቸውን የተጎናጸፉ አርነታቸውን ያረጋገጡ የአፍሪካ አገሮችን በነፃይቱ ኢትዮጵያ አስተባብራና አዛምዳ በንጉሠ ነገሥቷ አማካኝነት ሰብስባቸዋለች፣ የአሁኖቹ የአፍሪካ መሪዎች አባቶች “የአፍሪካ አባት” ብለው ባጸደቁላቸው በ“አባ ጠቅል” በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ  አማካኝነት እውን ይሆናል ብለው ባልጠበቁበት ጊዜ በብዙ መስዋትዕነት ፤ በብዙ ዲፕሎማቲክ ጥረት ፤ ብዙ ገንዘብ በማፍሰስ ህልማቸውን የፈቱት ኃይለ ሥላሴ ነበሩ   ፤ ለአፍሪካ ህብረት መመስረት ከኢትዮጵያ በፊት ሊቆም የሚችል ማን ነው? ከኃይለ ሥላሴስ ቀድሞ ስሙ የሚጠራስ?

በጊዜው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሲመሰረት በአቋማቸው ሸርተት  ያሉ መሪዎችን በጽናት የታገሉት ንጉሠ ነገሥቱ የመሪዎቹን ጉባዔ ሲከፍቱ ባደረጉት ታላቅ ንግግር 
“. .  . . ስብሰባችን የአፍሪካ አንድነት የሚመሠረትበትን ቻርተር ለማጽደቅ ሳይስማማበት ሊበተን አይገባውም፤. . .የተባበረ ጥረቱን ከዚህ በበለጠና በተቀደሰ ዓላማ ላይ የሚያውለውን የአፍሪካን መንግሥታት ጎዳና አሁን ዕርምጃ እንውሰድ፡፡ ይህንንም ስናደርግ ነፃ ለሆነች ብቻ ሳይሆን ለተባበረች አፍሪካ ዓላማ ነው፤” በማለት  በመናገራቸው እስከ ሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በቆየው ጉባዔ የአፍሪካ አንድነት ቻርተር እንደተፈረመ የዛሬ 49 ዓመት ታሪክ ይነግረናል ፤
 ክዋሜ ንክሩማ አገራቸውን ከኮሎኒያሊቶች ክራንቻ ፈልቅቀው አውጥተው ለነጻነት ያበቁ የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ ናቸው፡፡ ይህ የሚካድ አይደለም ፤ ሆኖም ለአፍሪካ ህብረት ስኬታማ ሰዎች እና በአፍሪካውያን መሀከል ሰላም እንዲሰፍል በማድረግ አንድ የሚበልጧቸው መሪ አሉ ፤ ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃ/ስላሴ ንጉሰ ነገስ ዘኢትዮጵያ፡፤ ሌሎች አፍሪካውያን በነጮች እግር ስር ተረግጠው ሲገዙ ኢትዮጵያ ግን በእግዚአብሔር ጥበቃነት የእነርሱን እድል ገፈት ቀማሽ አልሆነችም ፤ አፍሪካውያን ነጻ ሀገር እንዲኖራቸው ከፍተኛ ሚና የተጫወሩት ኃይለስላሴ በቅን ልቦና ስራቸው ቢመዘን በአፍሪካ ህብረት ውስጥ አይደለም አንድ ሀውልት ሌላም የሚያስፈልጋቸው መሪ ነበሩ ፤ ምን ያደርጋል ከላይ እስከ ታች የራስን አይከን አለማየት እና ዋጋ አለመስጠት ነገር ተጸናውቶን ኖሯል ፤ መንግስት እንኳን በጥያቄ መልክ ጉዳዩን ማንሳት አለመቻሉ ያስገርማል ፤ በጠቅላላ ‹‹ባለቤቱ ያቀለለውን…›› የሚባል ብሂል  አለ ፤ እኛም አይከኖቻችንን የማቅለል ነገር ከየት እንደተጸናወትነው አላውቅም ፤ ህዝብም መንግስትም  ዋጋ ያልሰጠነውን ሌላው እንዲቀበል ማድረግ አይቻልም ፤

ከቅጥር ግቢው ውስጥ ቀልብን ከሚቡ ነገሮች መካከል የቀድሞ የጋና ፕሬዝዳንት የክዋሜ ንክሩማ ሐውልት በዋንኝነት የሚቀስ ነው ፡፡ መዝሙረ ዳዊት 68፤31 ‹‹ ኢትዮጵያ ታበጽእ እደዊሃ ሃበ እግዚአብሔር››  ፤ ‹‹መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።›› ይላል፡፡  አፍሪካ ህብረት የሚገኝው የንክሩማ ሀውልት ስር ‘ Ethiopia shall soon stretch out her hands unto God.’ ጽሁፍ በግርጌው በኩል ተቀርፆበት ሳይ በጣም ነው የገረመኝ ፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት በመዝሙረ ዳዊት ላይ ቅዱስ ዳዊት የተናገረውን ትንቢት በዘመናችን ለዚያውም 54 ሀገሮችን በሚወክል አለም አቀፋዊ በሆነ አዳራሽ ይህ ነገር ተቀርፆ መመልከት በጣም ደስ ያሰኛል፡፡ አውቀውትም ሆነ ሳያውቁት የዳዊትን ትንቢት ደግመው የተናገሩ ያህል አድርጌ ነው የወሰድኩት ፤ ስለ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ምስክርነት ሲሰጡ መመልከት ደግ ነው ፤ የዚቺ ጥቅስ መኖር መልካም ቢሆንም   ጥቅሱ በእንግሊዘኛ ብቻ መጻፉ አግራሞትን ፈጥሮብኛል ፤ አማርኛም ከበታች ቢኖረው መልካም ነበር ፤ ይህን ሲፅፉ ጠቆም የሚያደርግ ሰው ቢገኝ መጻፉ ከባድ እንዳሆነ አውቃለሁ ፤ ከቀናት በኋላ ለምን ጻፉት የሚል ነገር ውስጤ ተጭሮ ኖሮ ጉዳዩን ጉዳዬ ብዬ መረጃ ሳጣራ ከርሜ መልስ አግኝቼለታለሁ  ፤ ይህን ክዋሜ ንክሩማ ዋሺንግተን ዲሲ በሚገኝው በሃዋርድ ኒቨርሲቲ ለዶክትሬት ድግሪ ማሟያ ሲፅፉ የተጠቀሙበት አርእስ መሆኑን ለማወቅ ችያለው፡፡ በጣም ደስ ይላል ፤ እኛ ትንሽ ስንማር ሁል ጊዜ እውቀታችን ከቤተክርስያንና ከመፅሀፍ ቅዱስ ጋራ ሲያጋጨን  እንመለከታለን ፤ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ነገር ግን ስለ ኢትዮጵያ በደንብ የሚያውቁ እንደ ንክሩማ አይነት ምሁራን ደግሞ በዶክትሬት ትምህርታቸው ስሟን ሳይጠቅሱ ማለፍ ተስኗቸው እንመለከታለን ፤ በዶክትሬት ደረጃ ከመዝሙር መፅሀፍ ውስጥ አንዷን ጥቅስ ስቦ መፅሀፍ መፃፍ ለዛውም ‹‹ ኢትዮጵያ ታበጽእ እደዊሃ ሃበ እግዚአብሔር››  ደስ ያሰኛል፡፡

ለእኔ ይህ ሀውልት ከግርጌው ‹‹ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።›› ብሎ መፃፉ በጣም ደስ ቢያሰኝኝም ፤ ሀውልቱን አተኩሬ ስመለከተው ግን “የበሬን ውለታ ወሰደው ፈረሱ. . . .” የሚለውን የአማርኛ ተረት ትዝ አስብሎኛል፡፡ ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ምን ነበሩ? ወደፊት እናየዋለን ፤
 አዎን በእኛ ስህተት ይሁን በእነሱ ፍላጎት የበሬውን ውለታ ፈረሱ የወሰደው ያህል ተሰምቶኛል ፤ አንዳንዴ ታሪክ መስራት ቢያቅተን እንኳን እንዴት ታሪክ ጠባቂ መሆን ያቅተናል ? ‹‹የእሳት ልጅ ነበልባል ›› ብለንም መሪዎቻችንን የምናወድስበት ቀን ይናፍቀኛል፡፡

ይህን ከፃፍኩ አይቀር ወደፊት ስለ ሚንስትሮቻችን እምነት ፤ አንድ በአንድ አንስቼ እነግሮታለሁ ፤ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በአንድ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ከሚንስትሮቻችን ጋር ሲጨዋወቱ ተመልክቼ ፤ በሁኔታው ያየሁትን የተመለከትኩትን ፤ ለአቡነ ጳውሎስ ያላቸውን ቀረቤታ ፤ መስቀል የተሳለሙትን ፤ ጉልበት የሳሙትን ፤ መስቀል የተቀበሉትን ፤ የመንግስት ባለስልጣናትን በፅሁፌ ዳሰሳ አደርግባችዋልሁ ፤ ሁኔታውን ቢያዩ ኦርቶዶክስ ሰው አላት ይላሉ (ምን አይነት ሰው ? እሱን አላውቅም) ፤ በጊዜው ‹‹የአባቶቻችን ክብር ለካ እንዲህ ነው›› ብያለሁ (አደራ ክብራቸውን እንጂ ስራቸው አላልኩም)፡፡ እኔም መስቀል ተሳልሜ ፤ ጉልበት ስሜ መስቀል ቢሰጠኝም ፤ ‹‹ አባታችን ቤተክርስትያንን አደራ›› ለማለት ጓጉቼ   ዝም ብዬ አልፌአለሁ ፤ 



ESAT – Ethiopian Satellite Television, reports that it is only Kwame Nikrumah’s statue that is present in the new Chines-made headquarters of the African Union in Addis Ababa. Emperor Haile Selassie who established the Organization of African Union (OAU) does not have a statue in the new AU compound. This is believed to be the works of anti-Ethiopia elements whose demise is approaching. Ethiopia shall prevail!



 ቸር ሰንብቱ

‹‹ ኢትዮጵያ ታበጽእ እደዊሃ  ሃበ እግዚአብሔር››

8 comments:

  1. The thing is the Ethiopian goverement do not want that ! They are talking something bad about Emperior Haileselasie to promote they stupid politics! doing that means it has it will be the opposite of what they are talking .The thing is like writing on a blackboard! it will be visible .U cannot fool people .Let me tell u what the people think ,everybody is waiting the time .It will burst one day.I dont know where u r , butI am living in Ethiopia I know in and out of .....

    Egzihabehere Ethiopian Yetebekate !!

    ReplyDelete
  2. ደስታ ወገኛው (Desta Wegegnaw)February 8, 2012 at 7:36 AM

    ብቻዬን የጮህኩ ሁሉ መሥሎኝ ነበረ ስለዚህ ነገር በራሴ በዚያ በመከረኛ "ፌስቡክ" ላይ አውጥቼ ስንገበገብበት:: የሞቱት የሊቢያው መሪ ሞአማር ጋዳፊ የሕብረቱን አዳራሽ ከኢትዮጵያ ለማስወጣት ከሌሎቹ የአፍሪካ መሪዎች ጋር ደፋ ቀና ሲሉ አቶ መለስ የኃይለሥላሴን ውለታ በኩራትና በልበሙሉነት ነበር የተናገሩት፤ የቀድሞ ጠላታቸውን ኮረኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያምንም እንደዚያው፤ ያኔ በውስጤ የማልክደው ደስታ ነበር የተሰማኝ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕውነታን እንጂ የግልና የቤት ውስጥ ጣጣን ማንጸባረቅ አልፈለጉም በወቅቱ::

    ዛሬ ግን ታሪክ እንኳን የማይሽረው ክፉ ሥራ ነው የሠሩት፤ አያፍሩም ነገም ለእርሳቸው (ለአቶ መለስ) ኃውልት እናሰራ የሚሉ ይመጣሉ:: ይሁን ይሠራ፤ ነገር ግን ትልቁ ኃውልት በታዳጊው ወጣት (ትውልድ) በሰው ዓዕምሮ የሚቀረጸው እንጂ በተራና ጊዜያዊ ታይታ ውስጥ የሚገነባ ኃውልት ከታለመለት ዓላማ ይልቅ የድንጋይነት መልዕክቱን ይዞ ነው የሚቀረው:: ጥቁር አንበሣ ጎን እንዳለው እንደ ደርግ ድንጋይና ቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፊትለፊት እንዳለው እንደ ፓትሪያርኩ የድንጋይ ምስል:: ዛሬ ወጣት ትውልድ ነኝ ይህንን ለቀጣይ ትውልድ ውሸትነቱን ጽፌ ማስተላለፍ እችላለሁ ድንጋይነቱን ማፍረስ ባልችል:: ንጉሱ ያጠፉትን ማጉላት ይቻላል፤ የሠሩትን ግን በፍጹም መደበቅ አይቻልም:: ኢጣሊያንን በሀገራቸው ሄዶ እጅ አስከንድቶ የተመለሰውን አብዲሳ አጋን የተቀበሉበትን መንግድ ሳስብ ንጉሱን አዝንባቸዋለሁ፤ ሊግ ኦፍ ኔሽንስ ፊት ብቻቸውን ቆመው ስለኢትዮጵያ ብሎም ስለ አፍሪካ የተናገሩትን ሳስብ ደግሞ ዛሬ በውስጤ ይቅርታን እማጸንላቸዋለሁ:: ምንም ይሁን ምን ግን ዛሬ ሁለቱም (አብዲሳም ሆኑ ኃይለሥላሴ) ከእኛ ዘንድ የሉም በሥጋ፤ ተግባራቸው ግን ትልቅ ኃውልት ሆኖ ውስጣችን ተቀርጿል:: ይህንን ኃውልት የሚያፈርስ ጦር ደግሞ አይመጣምም ቢመጣም ማፍረስ አይችልም ጽኑ ነውና!

    እናም መለስ ሆይ አባይን መገደብ ይቻላል ታሪክን መገደብ ግን በፍጹም!!!
    ደስታ ወገኛው (Desta Wegegnaw)

    ReplyDelete
  3. what are you expecting from a leader like Meles Zenawi? he is there just to sell Ethiopia nothing els.
    He gave up about some part of Ethiopia to Eritrea after he sacrificed those poor Soldiers. if we Ethiopians do nothing about it, for sure he still kill Ethiopia and every Ethiopians

    ReplyDelete
  4. ወገኖቼ ትልቁ ልንገነዘበው የሚገባ ቁም ነገር ቢኖር ኰሎኔል መንግሥቱም ሆነ አቶ ለገሠ (መለስ) ዜናዊ ችግራቸው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጥላ ከኋላቸው እየተከታተለ የሚያስደነግጣቸውና የሚያባንናቸው ትናንሽ ፍጡራን መሆናቸውን ነው:: በምንም መለኪያ የእርሳቸው ስምና የነዚህ የታሪክ ውዳቂዎች ስም በአንድ አረፍተ ነገር ውስጥ አብሮ ሊጠራ አይገባውም:: አሁን አቶ ለገሰ (መለስ) የአጼ ኃይለ ሥላሴ ሃውልት እንዳይሰራ በማድረጉ እሳቸውን ያንቋሸሸ መስሎት ይሆናል:: የሚያስበው ከአፍንጫው አያልፍምና አትደነቁ:: ዓለም በታላቅ ሥራቸው ያደነቃቸውን መሪ እሱና ባልደረቦቹ ስላላከበሩአቸው ምንም አይጎድልባቸውም ነገር ግን የርሱን ትንሽነት በጉልህ የሚያሳይ አሳፋሪ ተግባር ነውና መደነቅ አይገባም::

    ReplyDelete
  5. ዲ/ን ኃይለ ሚካኤል ወልደ መምህር ብርሃኑ በመንፈስ ወወልደ ሶማኖ በሥጋFebruary 9, 2012 at 6:29 AM

    "ይህን ከፃፍኩ አይቀር ወደፊት ስለ ሚንስትሮቻችን እምነት ፤ አንድ በአንድ አንስቼ እነግሮታለሁ ፤ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በአንድ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ከሚንስትሮቻችን ጋር ሲጨዋወቱ ተመልክቼ ፤ በሁኔታው ያየሁትን የተመለከትኩትን ፤ ለአቡነ ጳውሎስ ያላቸውን ቀረቤታ ፤ መስቀል የተሳለሙትን ፤ ጉልበት የሳሙትን ፤ መስቀል የተቀበሉትን ፤ የመንግስት ባለስልጣናትን በፅሁፌ ዳሰሳ አደርግባችዋልሁ ፤ ሁኔታውን ቢያዩ ኦርቶዶክስ ሰው አላት ይላሉ"
    ውድ የአንድ አድርገን ጦመር መድረክ ጦማሪዎች ከላይ ከጦመራችሁ በቀጥታ ያስቀመጥኩትን ሐሳብ ለምን እንዳላችሁ አልገባኝም:: እንደ እኔ የሚታወጡአቸው ጽሑፎችን መገምገም ያለባችሁ ለቤተክርስቲያን ካለው ፈይዳ አንጻር ነው እንጂ ማንም ዝነኛ ስለሆነ እንዲህ በዓል ላይ ተገኘ እንዲህ ሆነ እንዲህ ንግግር አደረገ እያላችሁ የግድ ማውጣት ያለባችሁ አይማስለኝም::
    በአብዘኛው ኦርቶዶክሳውያን ባለሥልጣን ብሆኑም በሃይማኖት ጉዳይ ዳንታ የሌላቸው መሆናቸው ይታወቃል:: ለዚህም ነው ከኛ ሃይማኖት ወጭ የሆኑት ያገኙአትን አጋጣሚ እየተጠቀሙ ለቤተ እምነታቸው ውለታ ሲውሉ ኦርቶዶክሳውያን ባለሥልጣናት እንደዚህ ለቤተክርስቲያን ውለታ መዋል ባይችሉ እንኩዋን ሕግ ስጣስ የማይከላከሉት::
    ይልቁን እስኪ እናንተ ቀጠሮ የሰጣችሁንን የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስቴርና ሚኒስቴር ዴኤታው በተከታታይ ከአሕዛብ ወገን የሆኑበት ምክንያት ምን እንደ ሆነ በመሆናቸውም የደረሰውንና ሊደርስ የሚችለውንም ተጽእኖ የአቡነ አኖርዎስ ዋሻ በምን ምክንያት ሶፍ ዑመር ዋሻ እንደተባለ በ2000 ዓ.ም አል ነጋሺ የሚባል የእስላም ንጉሥ በኢትዮፕያ ነበረ የሚል በሬ ወለደ ዓይነት ወሬ እንዴት በሚዲያ እንኩዋን እስከ መነገር እንደደረሰ አሕዛብና መናፍቃን ቤተክርስቲያንን ለማዳከም የሚያደርጉት ስትራቴጂ ወዘተርፈ (ሌሎቹን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እመለስበታለሁ) በመረጃ አስደግፋችሁ አስነብቡን: ለመፍትሔም አወያዩን::
    እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን እንደ አባቶቻችን የምናገለግልበትን ጥበብና ጽናት ለሁላችን ያድለን::
    ረድኤተ እግዚአብሔር :የወላዲተ አምላክ አማላጅነት አይለየን::
    ታናሹ ወንድማችሁ

    ReplyDelete
  6. እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን እንደ አባቶቻችን የምናገለግልበትን ጥበብና ጽናት ለሁላችን ያድለን::
    ረድኤተ እግዚአብሔር :የወላዲተ አምላክ አማላጅነት አይለየን::
    ታናሹ ወንድማችሁ "አሜን" "ቃለህይወት ያሰማልን"

    ReplyDelete
  7. Think as an African,Don't be sulfish

    ReplyDelete