Wednesday, February 15, 2012

እውነት ይህ አጋጣሚ ይሆን?

ማደሪያህን ቁጠር

ስንቶቹ ተፈቱ በማጣት በችጋር?
ስንቱ ተቃጠለ ትቢያ ሆነ አፈር?
ስንቶቹ ፈረሱ በሴራ በሸር?
ቢሆንም ነገሩ ከአንተ በላይ ላሳር
እባክህ ጌታ ሆይ ማደሪያህን ቁጠር፡፡
ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን ገለአድ የተማሪዎች መማሪያ ቤት እና የመንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም ቤተ-ክርስቲያን የመነኮሳት መማሪያ ቤት መቃጠል እውነት አጋጣሚ ይሆን???
‹‹አሁንም እግዚአብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅልን›› 




በጎንደር ከተማ ሁለት የአብነት ት/ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተቃጠሉ

  • አንዱ ቤተ ጉባኤ በኢትዮጵያ ብቸኛው የመጻሕፍተ መነኮሳት ትርጓሜ ማኼጃ ነበር ተብሏል:: (READ THIS ARTICLE IN PDF)

(ደጀ ሰላ የካቲት 8/2004 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 16/2012)፦ በሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ጎንደር ከተማ በሳምንት ልዩነት በሁለት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በተነሡ የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች አንድ ጥንታዊ የመጻሕፍት ትርጓሜ ቤት ሌላ የቅኔ ቤተ ጉባኤ ሙሉ በሙሉ ወደሙ፡፡ በጎንደር ከተማ የሚገኘው የሐመረ ኖኅ ሠለስቱ ምእት መጻሕፍተ መነኮሳት ትርጓሜ ት/ቤት ሙሉ በሙሉ የወደመው ከትላንት በስቲያ፣ ከየካቲት 6 ቀን 2004 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ላይ መንሥኤው ባልታወቀ አኳኋን በተነሣ የእሳት ቃጠሎ መሆኑን ደቀ መዛሙርቱ ተናግረዋል፡፡ የትርጓሜ ት/ቤቱ በኢትዮጵያ ከአራቱ ጉባኤያት አንዱ የሆነውን መጻሕፍተ መነኮሳትን ብቻ የሚያሄድ ብቸኛ ቤተ ጉባኤ እንደነበር ተገልጧል፡፡

‹‹እሳት አላያያዝንም፤ ከኤሌክትሪክ መስመር ጋራ የተገናኘ ችግርም አላየንም፤›› ያሉት ደቀ መዛሙርቱ በእሳት ቃጠሎው የተማሪዎች ማደሪያዎች እና የመምህሩ መኖሪያ የነበሩ በአጠቃላይ ዘጠኝ ክፍሎች በውስጣቸው ከሚገኙ በ1714 ዓ.ም ከተጻፉ የብራና መጻሕፍተ መነኮሳት(ማር ይሥሓቅ፣ ፊልክስዩስ፣ አረጋዊ መንፈሳዊ) እና ሌሎች የኅትመት መጻሕፍት ጋራ ጨርሶ መቃጠላቸውን አስረድተዋል፡፡ እሳቱን ለማጥፋት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእሳት አደጋ መከላከል መኪኖች እና የከተማው ምእመናን የተረባረቡ ቢሆንም ጉዳቱን ለመቆጣጠር የተቻለው ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት በማድረግ ብቻ ነበር፡፡
የመጻሕፍተ መነኮሳት ቤተ ጉባኤው በጠቅላይ ቤተ ክህነት እና በማኅበረ ቅዱሳን በጀት የተተከለላቸው በአጠቃላይ 15 መደበኛ ደቀ መዛሙርት እና ከከተማው አድባራት እየመጡ ትምህርቱን በግላቸው የሚከታተሉ በርካታ ተማሪዎች እንደነበሩት ደቀ መዛሙርቱ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ በሰጣቸው በታወቁት የአራቱ ጉባኤያት ሊቁ አየለ ዓለሙ በ1929 ዓ.ም የተመሠረተው ት/ቤቱ በአሁኑ ጊዜ ጉባኤው ማሄድ (መቀጠል) ያልቻለ ሲሆን መምህሩ ተሾመ ታደሰ እና ደቀ መዛሙርቱ በየምእመናኑ ቤት ተጠግተው እንደሚገኙ ተመልክቷል፡፡ ቤተ ጉባኤው የሚገኝበትና በ325 ዓ.ም ለአውግዞተ አርዮስ በኒቂያ በተሰበሰቡ 318ቱ ርቱዓነ አበው ሊቃውንት ስም የተሠራው - የሠለስቱ ምእት ቤተ ክርስቲያን በ1880 እና በ1881 ዓ.ም በወራሪው ድርቡሽ ጦር ለሁለት ተከታታይ ጊዜ ከተቃጠለ በኋላ ተመልሶ አልተሠራም፡፡
የጎንደር ከተማ አድባራት በአራቱ ጉባኤያት ማእከልነት የሚታወቁ ሲሆኑ በመንበረ መንግሥት መድኃኔዓለም የመጻሕፍት ሊቃውንት ትርጓሜ፣ በመካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም የመጻሕፍተ ሐዲሳት ትርጓሜ፣ በጻድቁ አቡነ ዐቢየ እግዚእ ቤተ ክርስቲያን የመጻሕፍተ ብሉያት ትርጓሜ፣ በተቃጠለው የሐመረ ኖኅ ሠለስቱ ምእት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ የመጻሕፍተ መነኮሳት ትርጓሜበመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡
በተያያዘ ዜና በዚያው በጎንደር ከተማ የደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የሚገኘውና በዐፄ አድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመነ መንግሥት(17ው መ.ክ.ዘ) በኖሩት የቅኔ ሊቅ መምህር ክፍለ ዮሐንስ የተመሠረተውየገለአድ የቅኔ ቤተ ጉባኤ የካቲት ሁለት ቀን 2004 ዓ.ም በደረሰበት የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተገልጾአል፡፡
በዕለቱ ከቀትር በኋላ ከተማሪዎች ጎጆ የተቀሰቀሰው የእሳት ቃጠሎው መንሥኤ ለጊዜው ያልታወቀ ቢሆንም ተማሪዎች ወደ መኖሪያ ቤታቸው የገባውን ጉንዳን ለማራቅ የተጠቀሙበት እሳት እንደሆነ ተገምቷል፡፡ በቃጠሎው 26 የቅኔ ደቀ መዛሙርቱ መኖሪያዎች የሆኑ ጎጆ ቤቶች በውስጣቸው ከሚገኙ የተማሪዎቹ አልባሳት፣ መጻሕፍት እና ጥሬ ብሮች ጋ መውደማቸውን የዜናው ምንጮች ተናግረዋል፡፡

 

ቸር ወሬ ያሰማን

አሜን

11 comments:

  1. medhanie alem Ethiopian ytebeke.

    ReplyDelete
  2. yaqatelewen medhanialem yifaredewal,betechiristianin lematfat kehone gin tesfa yiquretu amlak kegna ga new!

    ReplyDelete
  3. It is too much to take it now. We need to fight back. I am not a politician but I hate the game being played by the Hodam People (both mengisit and some hodam kahinats). I am full of tears and do not know what to do. Let us shout.

    Zebra

    ReplyDelete
  4. ማደሪያህን ቁጠር

    ስንቶቹ ተፈቱ በማጣት በችጋር?
    ስንቱ ተቃጠለ ትቢያ ሆነ አፈር?
    ስንቶቹ ፈረሱ በሴራ በሸር?
    ቢሆንም ነገሩ ከአንተ በላይ ላሳር
    እባክህ ጌታ ሆይ ማደሪያህን ቁጠር፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. I feel bad about it.But i like the poems u wrote .God bless u.

      Delete
  5. yet medhanealem new lemehonu ahunis beza

    ReplyDelete
  6. Ere yihe neger alamaregnim. Gimashun bemenged sebeb maferes,Gimashun makatel,lelawunim lemewures bememihirenet temedibo mshersher.....Meche new egna rasachinin yeminikelakelew? Patriarku,Papasatu(andandochu),Kahinatu(anidandochu),Diakonatu(anidandochu)Miemenanu(andandochu) Lehodachen ena legenzeb fiker eyadelan Tewahidon Asalifen sinishet eyetaye zimitaw minidin new? Tewu Yeminilibet wekit genanew ende? Woyis cheriso eskinitefa new Yeminitebikew? Mengist endehone BeOrthodox guday "YEWUSHON NEGER YANESA WUSHON YIHUN" Yale yimesilal. Sinikatel zim bilo kemayet yezelele neger yaderegew yelemina.
    AMLAKE KIDUSAN EBAKIH BEKA BELEN. LEGNA AYIDELEM LESIMIH SITIL DIABLOSINENA SERAWITUN ASAFIREH MELISACHEW. BEGNA DIKIMET YANTE BETINA SIMIH BEAHIZAB AYINAK. FETINEH SIMA. YEHIZIBIHINIM ENBA ABIS. YETEDEFAWUN ANGETACHININ KENA ADEREGEN YEMINIHEDIBETIN KEN AMITA. SILEENATIH BELEH MAREN. SILECHERINETIHIM TADEGEN.AAAMMEEEEEN!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  7. YE yememeleketwen amlakachenen alayenem belewe endhone yaketlut kidist betekerestian satehuhon ye mekatelewe bekumena nefsachewe eyalu zelealem endetekatelu yenoralu.

    KIDEST BETEKERSTEAYN EGZEABEHER AMELAK YETEBEK
    ASERARE BETEKERSTEYANEN YASTAGESELEN.

    ReplyDelete
  8. AMLAKE KIDUSAN EBAKIH BEKA BELEN. LEGNA AYIDELEM LESIMIH SITIL DIABLOSINENA SERAWITUN ASAFIREH MELISACHEW. BEGNA DIKIMET YANTE BETINA SIMIH BEAHIZAB AYINAK. FETINEH SIMA. YEHIZIBIHINIM ENBA ABIS. YETEDEFAWUN ANGETACHININ KENA ADEREGEN YEMINIHEDIBETIN KEN AMITA. SILEENATIH BELEH MAREN. SILECHERINETIHIM TADEGEN.AAAMMEEEEEN!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

    ReplyDelete
  9. Everybody must have to protect our historical sites and treasures from attack. This is not the only property of Tewahido but belongs to all Ethiopians.Let everybody took action saying it concerns me . Plus to that let us all pray to God to let pass the miserable thing happening to our church. God bless Ethiopia!!!

    ReplyDelete
  10. እግዚአብሔር ሆይ! ከሰው ዘንድ ማንም የላትምና ቤ/ክርስቲያንን አንተ ጠብቃት:: ጠላቶቿ በዘተው ተነስተዋልና::

    ReplyDelete