Tuesday, February 7, 2012

የሰበካ ጉባኤ ምርጫና ኮሮጆ ግልበጣ


(አንድ አድርገን ጥር 28 ፤ 2004ዓ.ም )፡- የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ምርጫ 27/5/2004 . የተካሄደ ሲሆን ምርጫው ግን የተጭበረበረ መሆኑን ከቦታው የደረሰን በአይን እማኝ ተገልፆልናል ፡፡ መጭበርበሩን የተገነዘቡ ምእመናን ጥያቄ ቢያቀርቡም የደብሩ አስተዳዳሪ ግን የምእመኑን ጩኸት ወደ ጎን በመተው ምርጫው ሳይፈጸም ቅዳሴው እንዲዘጋ ቀጭን ትዕዛዝ በማስተላለፍ ሁሉም ምዕመን ሳያምንበት ምርጫውን ቋጭተውታል፡፡ ሁሉም ክርስትያን ማወቅ ያለበት ስለ ዛሬ ተመራጮች ብቻ ሳይሆን እነዚህ ያለ አግባብ የተመረጡ ሰዎች ነገ በቤተክርስትያናችን ላይ ስለሚያደርሱት ጉዳትም ጭምር ነው ፤ ለዓመታት ሲያበጣብጥ የነበረው የሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ላይ በፊት እነሱ የሚመስሏቸውን ሰዎችን በመምረጥ  ለምእመኑ ህጋዊ በመምሰል ለብዙ ወራት እሾህ ሆነው መቆየታቸው ፤ በመጨረሻም ጉዳዩ ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር በመድረስ እልባት ያገኝበትን ሁኔታ የቅርብ ትውስታችን ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የእኛ ችግር የተመረጠውን የሰበካ ጉባኤ ችግር ሲፈጥር መጮህ እንጂ መጀመሪያ ላይ እኛው ያገባናል ይመለከተናል ብለን በሰበካ ጉባኤ ምርጫ ቀን ቤተክርስትያን በመሄድ ሀላፊነታችንን አንወጣም ፤ በዚህም ምክንያት ምእመኑ የማያውቃቸው የሰበካ ጉባኤ አባላት ተመርጠው ሲያበቁ ፤ ስርአተ ቤተክርስትያን ሳያከብሩ ሲቀሩ ፤ ሙዳየ ምጽዋት ሲገለብጡ ፤ እጃቸው በሙስና ሲጨማለቅ ፤ በብልሹ አሰራር ሲተበተቡ የዛኔ እኛ እንነቃለን ፤ እነርሱን  ከተሰጣቸው የሀላፊነት ቦታ ለመቀየርም  እንቸገራለን ፤ እና መፍትሄው ሲጀመር ነውና ይህን ጉዳይ አፅንኦት ብንሰጠው ጥሩ ነው የሚል ሀሳብ አለን፡፡

በአሁኑ ሰዓት መብትና ግዴታችንን አለማወቃችን ለቤተክርስትያናችን አንዱ ፈተና እየሆነ ነው ፤ ለምሳሌ እያንዳንዱ ምእመን አስራት በኩራ ማውጣት እንዳለበት ግዴታውን አውቆ ቢንቀሳቀስ ቤተክርስትያናችን ዣንጥላ ከመዘርጋት ፤ ሌሎች ምዕራባውያን እንርዳችሁ በሚል ሰበብ  መጥተው የምንፍቅና ትምህርት ከማሰራጨት እንገታቸው ነበር ፤ በትንሽ ነገር ተታሎ ክሩን የሚበጥሰውንም ምዕመን እንደርስለት ነበር ፤ ምን ያደርጋል ሰዎች መሄዳቸውን እንጂ ለምን እንደሄዱ ጠይቀን አናውቅም ፤ ለወደፊትም ሀላፊነታችንን አውቀን እስካልተወጣን ድረስ ወደ እኛ ከምናመጣቸው ይልቅ ከእኛ የሚኮበልለው የምዕመን ቁጥር ሊበዛ ይችላል ፤ የህዝብና ቤት ቆጠራ መረጃ የሚያሳየው በሁለት አስርት ዓመታት ከ10 ሚሊየን በላይ የምዕመን ቁጥር እንዳጣን ያሳየናል ፤ አሁንም ሁሉም ምዕመን የራሱን ሀላፊነት እስካልተወጣ ድረስ ይህን ችግር መፍትሄ ማስያዝ አይቻልም፡፡ሁሉም ምእመን ቤተክርስትያን የጣለችበትን ሀላፊነት መወጣት ቢችል አሁን ያለው በየቦታው የሚነሳው ማዕበል ጸጥ ረጭ ባለ ነበር ፤ በቤተክርስትያናችን ውስጥ የሚደረግ ማንኛውም ነገር የሀላፊነት ደረጃችን እንደ አስተዳዳሪዎቹ ባይሆንም ፤ ዝቅ ቢልም ፤ ሀላፊነት እንዳለብን ግን ልንዘነጋ አይገባንም ፤ ዛሬ ከስርዓተ ቤተክርስትያን ውጪ የሚደረግን ድርጊት አንድ ሰው መቃወም ቢችል ነገ በሺህ የሚቆጠር ሰው ብልሹ አሰራርን እንዲቃወም በሩን ይከፍታል፡፡ ዛሬ በዝምታ ፤ አይተን እንዳላየን ፤ ሰምተን እንዳልሰማን በንዝህላልነት የምናልፋቸው ሁኔታዎች ነገ ላይ ለማስተካከል ብንሞክር ብዙ ዋጋ የሚያስከፍሉ መሆናቸውን መገንዘብ ይኖርብናል ፤ 

የደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ የተካሄደ የኮሮጆ ግልበጣ ፤ የምርጫ ማጭበርበር ሂደት በጊዜው የነበሩ ምእመናን እያለቀሱና እየጮኹ ስርአተ ቤተክርስትያን ይከበር ቢሉም የሚሰማ ጆሮ የሰጣቸው አልነበረም ፤ የቤተክርስትያኒቱ አስተዳዳሪ የህዝቡን ጥያቄ ወደ ኋላ በማለት ስርዓተ ቅዳሴው እንዲዘጋ ማዘዛቸውም የሚገርመ ነበር፡፡  ከሶስቱ ከአስመራጭ ኮሚቴዎች ውስጥ አንዱ ትክክለኛና መንፈሳዊ ምርጫ አለመሆኑን ፤ ስርአተ ቤተክርስያን የተጣሰበት ፤ ህግ ያልተከበረበት ፤ የምዕመኑ ድምፅ ያልተሰማበት ፤ በጠቅላላ አካሄዱ ህገ ወጥ በመሆኑ  አልፍርምም በማለት አቋሙን ቢገልፅም ፤ ‹‹ምርጫው ተጠናቋል›› በማለት የአሸናፊዎችን ስም ቀድመው የታለሙትን  ሰዎች ስም ዘርዝሮ በማንበብ ምእመኑን ወደ ቤቱ በትነዋል፡፡ በምርጫው ያዘኑ ምዕመናን ስለቤተክርስቲያን ይገደናል ፤ ስለ ተመራጮቹ ይገደናል ፤ ያሉ በእንባ ሲታጠቡ በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ተመሳስለወ የገቡ ተኩላዎች እና አንዳንድ የቤተክርስቲያኒቱ ካህናትም ጭምር ሲስቁና ሲሳልቁ  አርፍደዋል፡፡


ጻዲቁ አባት ቅዱስ ዮሴፍ ቤቱን ይጠብቅ፡፡ ምእመናን እኛም ቤተክርስቲያናችንን የመጠበቅ ግዴታ አለብን:: 

4 comments:

  1. ሁሉም ምእመን ቤተክርስትያን የጣለችበትን ሀላፊነት መወጣት ቢችል አሁን ያለው በየቦታው የሚነሳው ማዕበል ጸጥ ረጭ ባለ ነበር ፤

    ReplyDelete
  2. When I think of church, I cry inside.The church is in Danger.If we see those who are in the country side they are begging and other are also begging in their name but for their personal use.But the church who is teaching to have good deeds to be written on the book of life is now in her own business of accumulating goods but no attention is given to lambs who are lost who is still awaiting to be lost.When she is happy of converting a few peoples many are going/leaving her due to her inability of assisting economically.EOTC the greatest church in Africa having enumerable human power is contributing nothing compared to our fathers and for fathers era.
    Let's GOD protect her from all her enemies!!!!!!!!!!!Amen

    ReplyDelete
  3. If you do it in PDF it will be visible to everyone,Please can you do it so?

    ReplyDelete