Friday, February 24, 2012

የቦረና ጉጂና ሊበን ዞን ሃገረ ስብከት በኪዳነምህረት ዓመታዊ ክብረ በዓል ቀን በተነሳው ግጭት ከ40 በላይ ክርስትያኖች ታሰሩ


  • በግጭቱ ምክንያት ንግስ አልነበረም ፤ ቅዳሴም ሳይቀደስ ቀርቷል
  • የሚጠቡ ህፃናት ቤት አስቀምጠው በእስር የሚገኙ እህቶች አሉ
  • አራት ሰዎች ያህል ከአንድ ቤት የታሰሩም ይገኛሉ
  • ምሽቱን የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው በእስር ላይ ከሚገኙት ምዕመናን ውስጥ የወረዳው ሊቀ ካህን መሪጌታ ልሳነወርቅ ወልዴ ፤ ቀሲስ ወርቁና  የ80 ዓመት እድሜ አዛውንት አቶ ዘውዴ አበሩ በእስር ላይ እንደሚገኙ  ለማወቅ ችለናል


(አንድ አድርገን የካቲት 16 ፤2004ዓ.ም) የቦረና ጉጂና ሊበን ዞኖች ሃገረ ስብከት የክብረመንግስት ከተማ  ህዝብ ትግል የተባረረውና ዛሬም የሃገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ነኝ የሚለው ተሾመ ሃይለማርያም አሁን መሽጎ በሚገኝበት በክብረመንግስት ከተማ ሌላ ቀውስ እየፈጠረ ይገኛል፡፡ ሳይጠሩ አቤት ሳይላኩ ወዴት የሚሉ ሰዎች ቤተክርስትያንን ከበዋት ይገኛሉ፡፡ የተሀድሶያውያን ርዝራዦች በየቦታው ጊዜ ጠብቀው በማድባት ቤተክርስትያናችን ላይ ጉዳት እያደረሱ ይገኛሉ ፤ ከበላይ ያለው አመራር ንዝህላልነት በጉዳዩ ዙሪያ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖበታል ፤ ችግሮች ሲፈጠሩ ለችግሮቹ ወቅታዊ መፍትሄ አለመስጠት ችግሮችን ሌላ ችግር እንዲፈጥሩ እድል እየሰጠ ይገኛል፡፡


በየኣመቱ በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የካቲት 16 የእመቤታችንን በዓል ለማክበር የተሰበሰበው ምእመን፤ ያለ ህግና ስርአት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ተሾመ ሃይለማርያም አጥቢያቸውን ሊረብሽ እነደሚመጣ ሰምተው ግቢያቸውን እንዳይረግጥ እንዲደረግ ለአካባቢው አስተዳደርና የጸጥታ አካል አስታውቀው መፍትሄ በማጣታቸው በራቸውን ዘግተው አናስገባም በማለት ኡኡታቸውን ለማሰማት ቢሞክሩም ከሌላ ደብር ፤በተለይም የግለሰቡ መፈንጪያ ከሆነው ቅዱስ ሚካኤልና ከማርያም ቤተክርስቲን ባሰባሰቧቸው የአላማ ተጋሪ ጎረምሶች ታግዘው በጉልበት ለመግባት ሙከራ በማድረጋቸው ህዝቡ በመጮሁ ሰውየው በቦታው ላይ እንዳይመጣ ከመከልከል ይልቅ የረብሻውን መነሳት ይጠባበቅ የነበረው  በአካባቢው የነበረው የፌዴራል ፖሊስና የአካባቢው ሚሊሺያ ከአርባ በላይ በአሉን ለማክበር የተሰበሰቡ  ቀናኢ ክርስቲያኖች በዱላ በመደብደብ በመኪና ጭኖ በከተማው ውስጥ በሚገኙ እስር ቤቶች አጉሯቸዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ዛሬ የእመቤታችንን ንግስ ማክበር ሳይቻል ቀርቷል ፤እመቤታችን ቃል ኪዳን በተቀበለችበት ቀን ፤  ቅዳሴ ሳይደረግ ተስተጓጉሏል ፤ ስለ ቤተክርስትያን የተቆረቆሩ ሰዎች ከየቤቱ ሶስት እና አራት ሰዎች ድረስ የታሰረባቸው መኖራቸውን ሰምተናል ፤ ቤታቸው የሚጠቡ ህፃናት አስቀምጠው ስለቤተክርትያን ብለው እስር ቤት የታሰሩ እህቶች በእስር የሚገኙም መኖራቸውን ለማወቅ ችለናል ፤ በሀገራችን ላይ ሁለተኛ ዜጋ ሁነን የምንኖረው እስከመቼ ነው ? በቤተክርስትያናችን ላይ ይህን የመሰለ ህገወጥ ተግባር እየተከናወነ እያየን የምንታገሰውስ ?  ቤታችንን ከእነዚህ አይነት ሰዎች የምናፀዳውስ?  ቤተክህነቱስ በስልጣን ተዋረዱ መሰረት የሰዎችን ጥያቄ በጊዜው እና በሰዓቱ መፍታ የሚችለውስ ? በጠቅላላው  ከአርባ በላይ ክርስትያኖች በአሁኑ ሰዓት በእስር ቤት መኖራቸውን ለማወቅ ችለናል ፤ ቦታው ላይ የሚገኝው ሚኒሻም ሆነ ፌደራል ፖሊስ ችግሩ ሳይፈጠር መከላከል እየተቻለ ሰዎች በቤተክርስትያን ላይ ችግር እስኪፈጥሩ ድረስ መጠበቅ ተገቢ ነው የሚል እምነት የለንም ፤ ቤተክርስትያኗ ይወክሉኛል ያለቻቸው የወንጌል መምህራን አሏት ፤ እሷን የማይወክሉ ፤ ተጠግተው ጥቅም ለማግበስበስ የሚፈልጉ ሰዎችም በርካታ ናቸው ፤ 


በቤተክርስትያናችን በቤታችን ላይ በዓላችንን በህገወጥ ሰዎች አማካኝነት ማክበር አልቻልንም ፤ ቀድሞ ቤተክህነቱም ጉዳዩን አይቶ እንዳላየ የማለፍ ነገር ነገሩን ለዚህ ደረጃ አድርሶታል ፤ ችግሮችን መፍታት አይቻሉም ወይስ እንዲፈቱ አይፈለጉም? ይህ የኛ ጥያቄ ነው ፡፡ ዛሬ በነገሌ ቦረና ላይ የተደረገው ነገር በጊዜው የነበረውን ህዝበ ክርስትያኑን ክፉኛ ልቡ እንዲደማ አድርጎታል ፤ በሁኔታውን እንባውም እንዲያፈስ ግድ ብሎታል ፤ እኛም ሲበዛ አዝነናል ፡፡ አሁንም ጊዜው አልረፈደም ሲኖዶሱ ለአካባቢው ተገቢውን ሊቀ ጳጳስ ይመድብ ፤ የምዕመኑን ችግሮቻቸውን የሚናገሩበት መፍትሄም የሚሰጥበት መድረክ ይፈጠርላቸው ፤ የቤተክርስትያን አማኝ ያልሆነ ጎረምሳ በብር እየገዙ እንደዚህ አይነት ቀውስ እየፈጠሩ የሚገኙትን ሰዎች መንግስት ዱካቸውን ተከታትሎ ለሀገር ፤ ለቤተክርስትያንና ለህዝብ ሰላም ሲባል ከእኩይ ተግባራቸው ያስታግሳቸው ፤ ካልሆነም ሀገሪቱ የምትተዳደረው በተፃፈ ህግ ስለሆነ ፍርድ ቤት ያቅርብልን ፤ ነገሮችን ዝም ብሎ ማለፍ ግን ነገሩን ይባስ ስለሚያከረው መፍትሄ ከማምጣት ይልቅ ችግር ችግርን እንዲወልድ ማመቻቸት ነውና ይታሰብበት ፤  


ቆይ አስኪ የኛ የቤተክርስትያን ልጅነት እስከምን ድረስ ነው ? ለችግሯ ካልደረስንላት ፤ የመፍትሄ አካል ሆነን ከፊት ካልቆምንላት ፤ በዚህ አይነት ችግር ውስጥ ያሉትን እህት ወንድሞቻችንን አኛም አለን ካጠገባችሁ ነን ካላልናቸው ፤ ነገ የሚመጣውን ችግር አውቀን ቀድመን የመፍትሄ አቅጣጫ ካላስቀምጥንላት ፤ ችግር የሚያደርሱትን ሰዎች ፊት ለፊት ተጋፍጠን የቁርጥ ቀን ልጅነታችንን ካላስመሰከርን ምኑን የቤተክርስትያን ልጆች ሆንን? የቤተክርስትያናችን ችግር የኛ የእያንዳንዳችን ችግር መስሎ ሊሰማን ይገባል ፤ እንደ ጉጂና ሊበን ዞኖች ሃገረ ስብከት ዳር ያሉትን አብያተክርስትያናት መጠበቅ ካልቻልን መሀሉ ዳር የማይሆንበት ምንም ምክንያት የለም ፤ ይህን ችግር አውቆ የሚፈታ ቤተክህነት ባይኖረንም ፤ መረጃው ጋዜጦችና ኤሌክትሮኒክ ሚዲያ ላይ እንዲወጣ ችግሩን ምዕመኑ እንዲያውቀው ለማድረግ በአድራዎቻቸው ልከናል፤ይህን መረጃ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ የታሰሩት ሰዎች አልተፈቱም ፤  ምን ደረጃ እንደደረሱ ተከታትለን እናቀርብሎታለን ፤


ከዚህ በፊት አካባቢው ላይ ያለውን ችግር አንድ ሳናስቀር ከቀናት በኋላ ሙሉ መረጃውን እናቀርብሎታለን

ሠላምና ፍትህ ለቤተክርስቲያን መች ይመጣ ይሆን!?
‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅልን››

15 comments:

  1. What shall we do?Isn't there any ear to lesson?No eye to see such anti-EOTC activities?What is the mission of the government?we have tolerated it,but now we can't!b/c nothing is more than our religion!

    ReplyDelete
  2. betam yazaznal yanaddal....beka awunm mefthe kelay betesfa entebik ke betechristian ena kemengist amerar yemntebkew ayenur

    ReplyDelete
  3. I'M SORRY MAY GOD KEEP OUR CHURCH WITH HIS POWERFUL HAND

    ReplyDelete
  4. Kidanemariam Ze Negelle BoranaFebruary 24, 2012 at 9:12 AM

    በጣም ያሳዝናል፡፡ እኔ አሁን ባለኝ መረጃ የወረዳውን ሊቀካህናት ጨምሮ በርካታ ካህናትና ከ80 አመት በላይ እድሜ ያላቸው አዛውንት ጭምር መታሰራቸውን ሰምቻለሁ...መታሰራቸው ለክብራቸው ነው.... ወህኒን ከፍቶ ደቀመዛሙርቱን ከወህኒ ያወጣ አምላክ ዛሬም እንደሚያወጣቸው እናምናለን፡፡ ሁላችንም ድምጻችንን በማሰማት በጸሎትም ልናስባቸው ይገባል፡፡

    ReplyDelete
  5. betam yigermal AMLAKE KIDUSAN ersu yeteKEDESUTIN hulu yitebik bilo kemalef wuchi beakime mela yatahulet guday new.sile akebabiw sinesa zendiro edel getmogn kekanazegelila magist yemikeberewun yeKidus EGZEABHER ABE beal lemakber akirabiyaw kalu ketemoch keandu wodeza heje neber gin min yadergal yasebkutin salfetsim wedeneberkubet temelesku miknyatum degimo tabot wedemenberu yemigebaw be10 seat new mebalu mikinyatum beletu yeKIDIST MAREYAM hintsa aseri yazegajew ye enibila enteta pirogram silalaleke kekibrebeal kibrehodena kibre bir mebletachew yigermal.....

    ReplyDelete
  6. እናመሰግናለን ለሰጣችሁን ፈጣን መረጃ፣ ነገር ግን፣ እኛም ወደፍርድ ከመግባታችን በፊት ልትነግሩ የምንፈልገው ነገር አለ ይኧውም
    1 ተሾም ሃ/ማርያምን የላከው ማን ነው? ጠቅላይ ቤተክህነት ልኮት ከሆነ ሰውዬው ህጋዊ ነው ፣ ካልሆነ ግን የመንግስት አካላት ሊታዘዙለት አይችሉም::
    2 የእመበታችን ንግስ የነበረበት ቤተ/ን ህዝብ ብቻ ያውም በከፊል(ጥቂት) ሰዎች ብቻ ለምን አናስገባም አሉ??? ምንድ ነው ከነዚህ ሰዎች በስተጀርባ ያለው??? እውነት ብቻ ከሆነ እኛም አብረን እንጮሃለን እግዚአብሔር የ እውነት አምላክ ስለሆነ ይሰማናል::

    ReplyDelete
    Replies
    1. እኔ በቅድሚያ ትንሽ ሰዎቸ ብቻ ስለመጮሃቸው በሪፖርቱ ውስጥ አላነበብንም፡፡ በተረፈ ግን ተሸመ የተባሉት ግለሰብ የሃገረ ስብከቴ ስራ አስኪያጅ አይሆኑኝም ዕኔ የምፈልገው ዕገሌን ነው ብለው ሌላ ስራ አስኪያጅ (ቀድሞ የነበረውንና ያለሊቀ ጳጳሱ እውቅና የተነሳውን) መልስው መሾማቸውን በግልጽ ደብባቤ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት አስታውቀው ነበር በወቅቱ ሃገረ ስብከቱን ያስተዳድሩ የነበሩት ሊቀ ጳጰስ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ፡፡ የሃገረ ስብከት ስራ አሰኪያጅን መሾም ያለበት ደግሞ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እንደሆነ ቃለ ዓዋዲው ያዛል፡፡ሁኔታው ያላማራቸው “የበላይ አካላት ሊቀ ጳጳሱ ደርበው የሚያስተዳድሩትን ሃገረ ስብከት እንዲተዉ ቀጭን ትእዛዝ ደረሳቸው ሃገረ ስብከቱም ያለ አባት ቀረ፡፡ በተጨማሪም ተሾመ የተባሉት ግለሰብ ክብረ መንግስት ብቻ ሳይሆን ነጌሌቦረናም ተቀባይነት አጥተው ህዝቡ ሁሉ ወጥቶ ስላባረራቸው፡፡ ከስርአት ውጭ መንብረ ጵጵስና በሌለበት ወረዳ ላይ የሃገረ ስብከት ጽ/ቤት ከፍቻለሁ በማለት ማህተም አስቀርጸው ህገወጥ ስራ እየሰሩ ነው የቆዩት.... ከላይ አስተያየት የሰጡት ግለሰብ ከዚህ መረጃ የሚረዱት ነገር ይኖራል በዬ አስባለሁ፡፡

      ጌታ ቤቱን ይጠብቅ

      Delete
  7. thanks for leting Christians to hear about this. I wish God with this fasting period to be near us and stop this un ending problem of the "Guji, Borena Liben Hagere Sibket". Concerning this we have a lot to say, i mean there is a lot to be publicised and reach to the Orthodoxians ear. first of all please release what you have and we can add more. from the begining up to now. what has happene and what is happening in Negelle town, Shakiso, and Hageremariam too. who are playing at the back of Teshome and his followers .... May God help us to lead our christianity especially during this period where our fasting bring us our wish. GOD BLESS EOTC.

    ReplyDelete
  8. I know the area very well and I have been following this since the news was released. and finally...ሌሎች መራራ መስዋዕትነትን ሲክፍሉ ዳር ቆሞ ማጨብጨብ ደግሞ የበለጠ ክፋት ነው፡፡ ሰሞኑን ዘራፊዎችና የተሃድሶ ምንፍቅና አቀንቃኞች አይግቡብን ብለው በር በመዝጋታቸው የዓላማ ተጋሪዎቻቸው በሆኑ የመንግስት ባለስልጣናት የታዘዙ በአብዛኛው ኢአማንያን (ሙስሊም) ና መናፍቃን በሆኑ የአድማ ብተና ፖሊሶች ተደብድበው ወህኒ ሲወረወሩ መጽሃፉም ጭጭ ቄሱም ጭጭ ሆነ፡፡ የወረዳውን ሊቀ ካህናት ጨምሮ የኪዳነምህረትን ጽላት ለመሸከም ሌት ተቀን በጦምና በጸሎት በውዳሴ ላይ ቆተው
    ተዘጋጅተው የነበሩ ካህናት ጨምሮ ወደ ሃምሳ የሚጠጉ ቀናኢ ምእመናን የሚናገርላቸው አጥተው በወህኒ ታጉረዋል፡፡ አብዛኞቹ ሰዎች የታደኑት የማህበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው በመባል ሲሆን ፤ በስሙ ሰዎች ወህኒ ሲወርዱ መርዳት የሚቻለውን ያህል ለማድረግ ጥረት ሲያደርግ ያልታየውን ማህበር በግሌ በጣም አዝኜበታለሁ፡፡ ቤተክርስቲያንን መጠበቅ የ 40 ና 50 ሰዎች ብቻ ነው እንዴ; በግሌ ከዚህ በሁዋላ ሳጥናዔል ከነክንፉ መቅደስ ገብቶ ቢቀድስ ምንም ላለመናገር ወስኛለሁ፡፡ ጌታ በፈቀደ መጠን ከቤተሰቤ ጋር የግልም የማህበርም ጸሎቴን በማደረግ አርፌ ቤቴ እቀመጣለሁ፡፡ በቃኝ!

    ReplyDelete
    Replies
    1. Ayezoachu kerestiyanoch yebedale tsewawe eyemola nwe bedngele maryam amalajent beegziabhare hayel enashenfaln teru zemenem yemetalnal!

      Delete
  9. ወ/ጊዮርጊስ
    የግልም የማህበርም ጸሎቴን በማደረግ አርፌ ቤቴ ቀመጣለሁ፡፡ በቃኝ!ያልከው ሰውዬ አንተ ማነህ?
    ወዴት ወዴት? እባክህ?

    ክርስትያን ግን መራራ መስዋዕትነትን ሲክፍል ግድ ብሎታል::እግዚአብሔር የእውነት አምላክ ስለሆነ ይሰማናል::

    ReplyDelete
  10. kibremengistin man new yeageresibketu mekemecha yaderegat? Ebakachehu sirat albegnoch yenegesubet "system" ayazalkim. Mengistim yihin medegefu yemitekm aymeslegnem.

    ReplyDelete
  11. እግዚአብሄር አምላክ እውነተኛ የቤተክርስቲያን አባት አስነስቶ ቤቱን ያስጠብቅ እኛም አንድ በመሆን የቤተክርስቲያን የውጪና የውስጥ/ተሃድሶ/ ጠላቶች እባካችሁ እንከላከል መላ በሉ የመላ አባት እግዚአብሄር መፍትሄ ይስጠን ፡፡ በተረፈ እዚሁ አዲስ አበባ መዲናችን ብሄረ ፅጌ ማርያም በ18/06/2004 ዓ.ም ጠዋት ከቅዳሴ በኃላ የተሃድሶያዊያን ትምህርት በኛው መድረክ ሲሰበክ ሰምቼ በጣም ነው ያዘንኩ ለማን ልጠቁም ማን መፍትሄ ይስጠን እረ መላ መላ እሺ መፍትሄው ምንድን ነው ?

    ReplyDelete
  12. i was born there and my dad is still in jail. know the situation very well so why don't you update it again. on Tuesday 14 people were out of jail as i heard they were not actual a honest christian that why they are out but the rest of them are still in court trial. the case was open by saying they violet the law of freedom of religion and genocide. in fact i don't know there it came from specially the genocide part. those people are trying to stop any kind of fighting and killing in side of the church. so please let every one know about the current situation. beside this try to put solution for this kind of situation all over the country. MAY GOD SEE THIS NEWS AND TAKE A CORRECTIVE ACTION AS SOON AS POSSIBLE. AMEN!!!!!!!! DAD I LOVE YOU. MAY GOD BE WITH YOU!!!! የ80 ዓመት እድሜ አዛውንት አቶ ዘውዴ አበሩ በእስር ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል. YE ZEWIDE LEGI!!!!!!!!!!!1

    ReplyDelete