Tuesday, February 14, 2012

አንድ የምንሆንበት ጊዜው የደረሰ ይመስላል




(አንድ አድርገን ፤ የካቲት 6 ፤ 2004 ዓ.ም)፡-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በውጭ የሚገኝው በብፁእ አቡነ መርቆርዮስ የሚመራው  ሲኖዶስ እና  በኢትዮጵያ የሚገኝው ቅዱስ ሲኖዶስ መካከል ድርድር ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ፡፡


ድርድሩም የሚካሄደው በሰሜን አሜሪካ አሪዞና ውስጥ ሲሆን ከአዲስ አበባ በብጹ አቡነ ገሪማ(የውጭ ግንኙነት ሃላፊ)  የሚመራውና ብጹእ አቡነ ቆስጦስ ፤ ብጹእ አቡነ አትናትዮስ (የደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)እና ንቡረእድ ኤልያስ አብርሀ (የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ) ያሉበት የልኡካን ቡድን ወደ አሜሪካ በማቅናት ውጭ ከሚገኙ በብጹ አቡነ መልከ ጸዴቅ (ዋና ጸሀፊ) የሚመራና ፤ ብጹእ አቡነ ኤልያስ (የአውሮፓ ሊቀ ጳጳስ) ሊቀ ካህናት ምሳሌ(በካናዳ የኢ//// ዋና አስተዳዳሪ)  እንግዳ  መላከ ገነት ገዛህኝን (ረዳት ጸሐፊ) ያካተተ ልዑክ ድርድር ለማካሄድ መዘጋጀታቸው ተጠቁሟል፡፡

ብፁእ አቡነ መርቆርዮስ ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ በመሰደደድ ወደ አሜሪካ የገቡት በመንግስት ጣልቃ ገብነት እንደሆነ የገለጹ ቢሆንም መንግስት ሲያስተባብል መቆየቱ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስቴር አቶ ታምራት ላይኔ የአቡነ መርቆርዮስ ከፓትርያርክነት መነሳት ከሀገር መሰደድ ላይ የመንግስት እጅ እንዳለበት ይህንንም እሳቸው ፈርመው በማጽደቅ ድርጊቱን መፈጸማቸውን እና ከእስር ከተፈቱም በኋላም በመንግስት ምክንያት ለሁለት የተከፈለው ቅዱስ ሲኖዶስ ማስታረቅ እንደሚፈልጉ ከ2 ዓመት በፊት የኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት ለዶናልድ ያማማቶ መግለጻቸውን ዊኪ ሊክስ ይፋ ማድረጉ አይዘነጋም፡፡ እውነቱ ከዚህ የራቀ አይደለም ፤ ቤተክርስትያኗ ባለፉት 20 ዓመታት በሁለት ሲኖዶስ ስትተዳደር መቆየቷ ጸሀይ የሞቀው ሀገር ያወቀው ጉዳይ ነው፡፡

አቡነ ጳውሎስም ከውጭ ሀገር ተጠርተው ሐምሌ 5 1984 ፓትርያርክ ሆነው ሲሾሙ የቤተክርስትያኗን ቀኖና በመንግስት ጣልቃ ገብነት እንደፈረሰ በስደት ያሉ አባቶች ቢገልጹም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሲኖዶስ ደግሞ አቡነ መርቆርዮስ ነሀሴ 8 ቀን 1983 ዓ.ም በጤና መታወክ ምክንያት ቅዱስ ሲኖዶስ እሳቸውን ስራ እንዲሰራ ጠይቀዋል በሚል አዲስ ፓትርያርክ መሾሙን ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን አቡነ መርቆርዮስ እስከ አሁን በጽሁፍ እሳቸው ስለማለታቸው የፈረሙበት ሰነድም ሆነ የድምጽ ማስረጃ የቀረበ የለም፡፡ ቀርቧል የተባለው ነሀሴ 28 ቀን 1983 ዓ.ም ‹‹ዜና ቤተክርስትያን›› ላይ የወጣው ዘገባ ዋቢ በማድረግ ነበር፡፡

 ይህ በእንዲህ እያለ ከረጅም አመታት በኋ ሁለቱን አካላት ወደ አንድ ለማምጣት እና የቤተክርስትያኗን ሰላም ለመጠበቅ በሚል በተደጋጋሚ ድርድር ለማድረግ ጥረት ቢደረግም ሳይሳካ መቅረቱ አይዘነጋም፡፡ይሁን እንጂ ይህን ድርድር ለመጀመር ከሁለቱ በኩል አጀንዳ ተዘጋጅቶ የአዲስ አበባው ልኡክ ቅዳሜ የካቲት 2 2004 ወደ አሪዞና አቅንቷል፡፡

በውጭ የሚገኝው በብጹእ አቡነ መርቆርዮስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሀፊ ብጹእ አቡነ መልከ ጸዲቅ እንደገለጹጽ በእነሱ በኩል ለድርድር 5 አጀንዳ ማቅረባቸውን  ይፋ አድርገዋል፡፡
1.      የቤተክርስትያኗን ቀኖና ማን እንዳፈረሰ መተማመን ላይ መድረስ
2.     ጠቅላላ የይቅታ አዋጅ እንዲታወጅ ስምምነት ላይ መድረስ
3.     ከዚህ በፊት በሁለቱም በኩል የተፈጸመው ግዝት እንዲነሳ እና ሁለቱ ፓትርያርኮች ፊት ለፊት ተገናኝተው የቤተክርስትያኗ ቀኖና በሚፈቅደው መሰረት የሚቀጥለው ፓትርያርክ ማን እንደሆነ በውይይት እንዲፈታ
4.     ከላይ የተጠቀሱት ድርርሮች ከተሳኩ የድርድሩ ውጤት በይፋ እንዲታወቅ መንግስት በውጤቱ ለይ ጣልቃ ገብቶ ጫና እንዳያደርግ  ፤ ምዕመኑ እና አባቶች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ
5.     ውግዘት ከእንግዲህ በኋላ እንዲቀር የሚሉ አጀንዳዎች ይፋ አድርገዋል
በብጹእ አቡነ ገሪማ የሚመራው ልኡክ የያዛቸው አጀንዳዎች ይፋ ባይደረጉም ከአጀንዳዎቹ አንዱ ብጹእ አቡነ ጳውሎስ በፓትርያርክነት እንዲቀጥሉ ብጹእ አቡነ መርቆርዮስ ደግሞ የቤተክርስትያኗ የበላይ ጠባቂ እንዲሆኑ የሚል እንደሚገኝበት ከድርድሩ በፊት የሁለቱም ተወካዮች ልኡካን በጋራ ጸሎት እንደሚያደርጉ የውስጥ አዋቂዎች ጠቁመዋል፡፡ እንደኛ እምነት ይህ ድርድር በተሳካ መልኩ የሚጠናቀቀው መንግስት እጁን ካነሳ ብቻ ነው፡፡


የእኛ የምን ጊዜም ህልማችንና ምኞታችንም በሀገር ቤት እና ከሀገር ውጪ የሚገኙትን አብያተክርስትያናት በአንድ ሲኖዶስ እና በአንድ ጳጳስ ስትተዳደር ማየት ነው ፤ በእኛ ጊዜ ያበላሸነውን ስርዓተ ቤተክርስትያን ከአባቶቻችን እደተቀበልነው አስተካክለን ለልጆቻችን የማስረከብ ሀላፊነት የሁላችንም ነው ፤ በዚህ ክፍፍላችን ጠላት ደስ መሰኝት የለበትም ፤ አሁንም ይህን መልካም አላማ ሰንቀው ከአዲስ አበባ ተነስተው አሜሪካን ሀገር አሪዞና ውስጥ የተገኙት አባቶቻችንን አላማቸውን አሳክተው  መልካም ዜና ያሰሙን ዘንድ  የእግዚአብሄር መልካም ፍቃድ ይሁን እንላለን ፡፡

‹‹አንድ አድርገን››
   

9 comments:

  1. temesgen.............

    ReplyDelete
  2. First of all do you think will accept the dictator of Ethiopia? because Ethiopian pop paulos G.medhin means melese(legese?

    ReplyDelete
  3. First of all do you think will accept the dictator of Ethiopia? because Ethiopian pop paulos G.medhin means melese(legese?

    ReplyDelete
  4. Thank you for this well balanced and impartial commentary. I applaud you for telling the truth. This is the kind of reporting you should do in the future. There are blogs that tilt the truth to fit their convictions, but please refrain from that and stick to the truth. I hope our Fathers will reconcile their differences and lead us towards unity and peace with the help of the Almighty.

    ReplyDelete
  5. endemayisaka minim tirtir yelewum. huletum wogen ke politicana ke midirawi astesaseb netsa mehon alebachew>

    ReplyDelete
  6. Bringing our Ethiopian Orthodox Tewahedo Church to the way it was is every genuine EOTC follower dream. However, this is a deliberate and intentional move by the tehadso's to shackle the resistance they have been facing in the church. it is just a part of the well- planned strategy to kill the orthodox church for once and for all. Also with all do respect, the former patriarch with a self -proclaimed synod in America and also the Patriarch in Ethiopia with his chorines they are- all birds of the same feather. Both Patriarchs lead by the nose by the tehadso's to serve the same purpose: mainly to destroy The Ethiopian Orthodox church in collaboration with their masters. PRAY PRAY PRAY.

    ቅድስት እመቤታችን ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችንን ትጠብቅልን !

    ReplyDelete