Sunday, October 18, 2015

አውሮፓን ጅብ ያስበላ የሉተር ስብከት በተዋሕዶ መድረክ




ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድኅን (ኮለምበስ ኦሀዮ)
(አንድ አድርን ጥቅምት 08 2008 ዓ.ም)፡- ከአስር ዓመት በፊት የፕሮቴስታንት ተሐድሶ መናፍቃን በቡድን በመደራጀት እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር፡፡እኛ ያልዘመርንበ ሰርግ ምኑን ሰርግ ሆነ፡፡እኛ ያልተገኘንበት ጉባኤ እንዴት ጉባኤ ሊባል ይችላል በሚል የሌላውን አገልግሎት ሁሉ ባዶ አድርገው እራሳቸውን ሲያስቀድሙ አስታውሳለሁ፡፡በወቅቱ ከጥቅም አንጻር ብቻ የሚደራጁ የመሰላቸው ጥቂቶች አልነበሩም፡፡አካሄዱ ግን ከጥቅም ባለፈ ሌላ የተለየ ዓላማ ከጀርባው እንደነበረበት ያስታውቃል፡፡ያን ጊዜ በተደጋጋሚ ሲናገሩት የሚሰማ ትልቁ አጀንዳቸውጌታ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አልተሰበከምና እርሱን መግለጥ አለብንየሚል ነው፡፡ይሄ አጀንዳ ደግሞ ምንጩ ማን እንደሆነ እናውቀዋለን፡፡እነዚህ ቀሚሳችንን ለብሰው በድፍረት የሚውረገረጉ ውሉደ መርገም የተሐድሶ ማናፍቃን ተላላኪዎች ናቸው፡፡እንዲህ የሚሯሯጡት የተሰጣቸውን ተናግረው የእለት ጉርስ ለማግኘት ነው፡፡ዋነኞቹ እና በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ይህ መልእክት እንዲተላለፍ የሚፈልጉት ግን በምዕራቡ ዓለም የዘሩት የሉተር እምነት የጠወለገባቸው ፕሮቴስታንቶቹ ናቸው፡፡ፕሮቴስታንቶቹ የሉተር እምነት በምድር አውሮፓ ጠውልጎና ደርቆ ሲመለከቱ ለጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያንጌታን ሊገልጡሚሴዎናውያንን ላኩ ሚሴዎናያኑ ደግሞ የፕሮቴስታንት ተሐድሶ አራማጆችን ልከው ሕዝቡን ማደናቆር ያዙ፡፡ለቀባሪ ማርዳት ይሉሃል ይሄ ነው፡፡

በአውሮፓ ተዘርቶ ያልበቀለ፣ሕዝቡን ለእስልምና እና እግዚአብሔር የለም ለሚል ፍልስፍና አሳልፎ የሰጠ ከንቱ እምነት፣ሉተር የመሠረተው የፕሮቴስታንት እምነት እኛ ሃገር ለመዝራት መሞከር ተሳልቆ ወይም ምቀኝነት እንጂ ሌላ ምን ይሉታል፡፡በምድረ አውሮፓ ወደ ሉተራውያን "ቤተ ክርስቲያን" የሚሄድ ሕዝብ ጠፍቷል፡፡ከዚህ ይልቅ ሕዝቡ እግዚአብሔር የለም በሚል ፍልስፍና ኢአማኒ ወደ መሆን ተሸጋግሯል፡፡በሚሺነሪ ታሪክ የምትታወቀው አፍሪካን በፕሮቴስታን እምነት ለማጥለቅለቅ ሌተ ተቀን የምትሰራው ስዊድን እንኳን ከሕዝቧ ቁጥር 34 ፐርሰንቱ እግዚአብሔር የለም ብሎ እንደሚያምን ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ የእግዚአብሔር መኖር የሚያምነው ደግሞ 27 ፐርሰንት የሚሆነው ብቻ ነው፡፡በፈረንሳይም 40 ፐርሰንት የሚሆን ሕዝብ የእግዚአብሔርን ሕልውና የማይቀበል ሰሆን የእግዚአብሐር መኖር አምኖ የሚቀበለው ደግሞ 18 ፐርሰንት ብቻ ነው፡፡ በመካከል የለም አለ ሳይል የሚኖር ብዙ ቁጥር ያለው ሕዝብ እንዳለም ልብ ይበሉ(1)፡፡

ሌላው 2011 እንደ አውሮፓ ዘመን አቆጣጠር የተደረገ ጥናት እንደሚያመለክተው በታላቋ ብሪቴን ክርስቲያን ነን ብሎ የሚያምነው 72 ፐርሰንት ሲሆን "ቤተ ክርስቲያን" የሚሄደው ህዝብ ግን 1.4 ፐርሰንቱ ብቻ ነው፡፡ሉተር በተፈጠረባት ሀገር በጀርመን 72 ፐርሰንቱ በተመሳሳይ ሁኔታ ክርስቲያን ነኝ ብሎ የሚያምን ሲሆን "ቤተ ክርስቲያን" የሚሄደው 1,2 ፐርሰንቱ ብቻ ነው(2)፡፡ከዚህ አንጻር ሁለት ፐርሰንት የሚሞላ ሕዝብ "ቤተ ክርስቲያን" የማይሄድባቸው ሃገሮች(እንግሊዝ፣ጀርመንን የመሳሰሉ ሀገሮች)“ዓይናችሁን በወንጌል እናብራ አዲስ ጌታ እንስበካቸሁበሚል መነሳታቸው ብቻ ሳይሆን ማሰባቸው በራሱ እጅግ እጅግ የሚያስገርም ነው፡፡ነገሩ የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች ይመስላል፡፡

ጥንታውያኑ አብያተ ክርስቲያናት ከጌታችን እና ከሐዋርያት የተቀበሉትን ክርስትና ይዘው በብዙ ፈተና ሳይፈቱ ዘመናትን ስለመሻገራቸው ዓለም በሙሉ የሚያውቀው እውነታ ነው፡፡ ሶሪያ፣ግብፅ፣አርመን፣ኢትዮጵያ ሕንድ፣ኤርትራ …… ለዚህ ሕያው ምስክሮች ናቸው፡፡ ከገጠማቸው ፈተና ከድህነታቸው አንጻር እግዚአብሔር የለም ለማለት የሚቀርቡት እነርሱ ነበሩ፡፡ነገር ግን የያዙት እምነት (ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ) በዓለት ላይ የተመሠረተች በመሆና ልጆቿ ችግር ሳይፈታቸው በመከራ ውስጥም እየጸኑ ወልድ ዋሕድ ሲሉ ይኖራሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰይጣን ኃይል እና ጉልበት በመጠቀም የእነዚህን አብያተ ክርስቲያናት ልጆች ሲያርድ እና ሲገድል የምናየውም ለዚህ ነው፡፡ አሁን አሁን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ትውፊት ምን እንደሆነ ለማወቅ ዓለሙ ወደ እነዚህ አብያተ ክርስተያናት መገስገስ ጀምሯል፡፡ የቅዱሳት መጻሕፍትን ትርጓሜ ለመረዳት ዓለሙ ወደ ጥንታውያኑ አብያተ ክርስቲያናት እየቀረበ ነው፡፡ በነገረ ክርስቶስ ላይ የሚያስተምሩትም ትምህርት ይህ ይጨመርበት ይህ ይጎድለዋል የሚባል አይደለም፡፡

ታዲያ የጥንካሬ ተምሳሊት ለሆኑ፣የጠራ ትምህርተ ሃይማኖት ላላቸው ለእነዚህ አብያተ ክርስተያናት አዲስ ወንጌል መላክ ምን ይሉታል ? እንዴትስ ያለ ድፍረት ነው ? ክርስቶስን አማላጅ የሚል የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ሌሎች ቅዱሳንን ክብር የሚያቃልል አዲስ ወንጌል፣ጾም ጸሎት አያስፈልግም የሚል አዲስ ወንጌል ለተዋሕዶ ልጆች ለምን አስፈለገን ? ይህ አዲስ ትምህርት በሉተራውያን ሻንጣ ወደ ሃገር ቤት ገብቶ ውሉደ መርገም በሆኑ የፕሮቴስታንት ተሐድሶ እምነት አራማጆች በኩል በተዋሕዶ አደባባይ ካልተዘራ የሚል ትንቅንቅ ተይዟል፡፡ተዋሕዶ ስዊድን እና ጀርመንን እንድትታደግ ድረሺልን የሚል ጥሪ መስማት ሲገባት ሕዝባቸውን አምላክ የለሽ ባደረጉ ፕሮቴስታንቶች ደጃፎቿ እየተንኳኳ ነው፡፡ለማንኛውም እኛ የክርስቶስ ወንጌል ሳይበረዝ እና ሳይከለስ የደረሰን ነን፣የድንግል ማርያም የቃል ኪዳን ልጆች ነን፡፡ስለዚህ አውሮፓን ጅብ ያስበላ የሉተር ስብከታችሁን ይዛችሁ ከመድረካችን ውረዱ፡፡


1-Christy, John (2013)The Decline of European Christianity. Available at <http://www.johnchristy.com/The-Decline-of-European-Christia…>
2-Beshears, Kyle R. (2015) Empty Churches: The Decline of Cultural Christianity in the West.


8 comments:

  1. ፕሮቴስታንቲዝም ክርስትናን ለሴኩላሪዝም ባሪያ አድርጎ የሚሸጥና እግዚአብሔርን መፍራት እንዲጠወልግና እግዚአብሔርን ማመን እንዲገረና የሚያደርግ የጠላታችን የረዥም ጊዜ እቅድ መኾኑን በአውሮጳና በአሜሪካ በተግባር አይተነዋል፡፡
    እኔ ነኝ የሚል ሄዶ ሳዑዲ ዐረቢያ “ጌታን ተቀበሉ!” ይበል፡፡ በፈሪሐ እግዚአብሔር የሚኖር ጭምት ሕዝብ ላይ ማጓራት ምን የሚሉት ወንጌል ነው፡፡ የክርስቶስን ቤዛነት ያመነ፤ በጥምቀትም ወደሞቱ የተቀበረ ሕዝብን ቆይ ጌታን ተቀበል ማለት ከጀርባው የገንዘብ ጥሜትና የሀብት ማግበስበስ ዓላማ ያለው እንጂ እውነት ነፍሳትን አርነት ለማውጣት አይደለም፡፡ ይህ ቢኾን ኖሮ በርግጠኝነት የኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ እንዲጠራባቸው እንኳን የማይፈልጉ ሚልዮኖች ከዚህ ሕዝብ ቅድሚያ ይሰጣቸው ነበር፡፡ ምን ያረጋል! አንገቱን ቆርጠው እንደሚጥሉለት ያቃል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ወንጌልን በርግጥ የሚያቃት ቢኖር ቀድሞ ለአላውያን ይሰብክላቸው ነበር፤ “በወንጌል አላፍርም!” -- እንደተባለ 1ቆሮ.9፣23፡፡

    ReplyDelete
  2. አዎ እውነት ነው ከአውደምህረታችን ይወረዱልን፡፡ አሁንማ በግልጽ ነው በየፊስቡክ እየለጠፉና ማንነታቸውን በግልጽ እያሳወቁን ያሉት፡፡በዛሬው እለት በታሪኩ አበራ የፊስ ቡክ ገጽ ላይ የተለጠፈውን ብታነቡት ግልጽ የሆነ ኘሮቴስታንታዊ አስተምሯቸውን ለጥፈው ታገኙታላችሁ፡፡ በጋሻው ያስተላለፈውን መልእክት የሚገርም ግልጽ የሆነ የሉተር ትምህርትን ነው በድፍረት እያሰተላለፉ ያሉት፡፡ ሁሉም እንዲገባውና እንዲደርሰው መሰራት አለበት፡፡ ተኩላው የተሳካለት እየመሰለ እራሱን እየገለጸ ነውና እናንተም በርቱ እኛም ማድረግ ያለብንን እንድናደርግ መንገዱን አሳውቁን፡፡ በርቱ የተዋህዶ ልጆች እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል፡፡ ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ ነው? ችግር ነው? ወይስ ረሀብ በተዋህዶ ቀልድ የለም፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. አዎ የተሳካላቸው ቢመስላቸውም እውነታው ፍንትው ብሎ እየለየና እየታወቀ ስለሆነ እግዚአብሔር ይክበር ... ይመስገን! የተዋህዶ ልጆች...
      አባቶች ... ማስተማሩ ላይ ብቻ ... በርቱልን!

      Delete
  3. ydengle marym yasrat legsoch bylachbet egezabher ytabcach!! bert gezaw ahwn new berttachu thdsowechen ymtagaltbet bert bysbkach lzh ladswe tweled astmerwt endytallwachw egezabher orthodox twhedow ementachnn ktfat ytabkelen amen!!

    ReplyDelete
  4. bemejemiria kesis yerasiwen gidfet yasiwegidu erisiwo lebetakiristian siriat gid yelewetim endet lelawun yikesalu erisewo bemiyastedadirut kidus gebiriel betekiristian yetehadiso siriat bemetenum bihon yitayal yihe ye adebabay mistir newu endet lelabet gebitewu yamasilalu balefewu yaferese siltan yelelewu yekedimo diyakon mekides wust endigeba aidrigewal yihe minalebet ayidelemin? andand gize be 1 kahin bicha yikedesal yihes andu yetehadiso milikit ayidelemin besebeka gubae abalat miricha yekalawadi tiset yelemin? bemebetachin werihawi beal yehawariyat kidase yikedisalu yih ye siriat mefales ayidelemin ene tehadiso yehonu gileseboch alu eyaliku ayidelem gin milikitu yitayal andan metarem yalebachewu siriate kidasewun yemiyawuku yerasiwo kegn eij yehonu sewoch alu yihin yastekakilu erisiwo keleloch columbus kalut betekiristiyan gar tenama ginignunet yelewetim gin silelela yaweralu min yimesilewetal? kesis enezihin yarimuna silelelawu yiderisalu.

    ReplyDelete
  5. ቤተ ክርስቲያን ማለት ከስሙ እንደምንረዳው በክርስቶ ሳይ የተመሠረተች ህብረት ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ የማይሰበክበት፤ የማይመለክበትና የክርስቶስ ስም የማይነሳበት የትኛውም ህብረት ቤተ-ክርስቲያን ነው ማለት አይቻልም፡፡ የመፅሃፍ ቅዱስ መዕከላዊ ሃሳብ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን ሃሳብ ቢጠቀለል ኢየሱስን ነው የሚነግረን አዲሰ ኪዳንም እንደዚያው፡፡ ስለዚህ ወንድሞቼና እህቶቼ ለሐይማኖትና ለወግ ከመቆማችሁ በፊት እውነቱን በደንብ ለማወቅ ትጉ ብዬ በወንድማዊነት እመክራለሁ፡፡ ምክንያቱም እየሱስን ያላማከለ አምልኮና ህይወት በእግዚአብሔር አምላካችን ፊት ከንቱ ስለሆነ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ፊት የምንቀርብበት በራችንና ድፍረታችን ነው፡፡ አሁንም በቤተክርስቲያናችሁ ኢየሱስን ከመናገርና ከመስበክ አትቆጠቡ፡፡ ምክንያቱም ሕይወት የሰጠን እርሱ ነውና፤ መዳናችን በእርሱ ነውና፤ ወደ አብ የምንገባበት በራችን እርሱ ነውና፡፡

    ReplyDelete