Saturday, October 3, 2015

በ “ታዖሎጐስ” እና “ቃለ ዐዋዲ” የኢቢኤስ ፕሮግራሞች ላይ ተቃውሞ ተነሳ


  • ·         7 ቀናት 100ሺህ በላይ የድጋፍ ፊርማዎች ተሰባሰቡ

(አዲስ አድማስ መስከረም 22 2008 ዓ.ም)፡- በኢትዮጵያን ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ (EBS) ቴሌቪዥን በሚተላለፉትታዖሎጐስእናቃለ - አዋዲበተባሉት ፕሮግራሞች ላይ ሰሞኑን ከፍተኛ ተቃውሞ ተነሳ፡፡ ፕሮግራሞቹ እንዲዘጉና በኦርቶዶክስ ስም እንዳይጠቀሙ የሚያግዝ የድጋፍ ፊርማ እየተሰባሰበ ሲሆን 7 ቀናትከ100ሺህ በላይ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መፈረማቸውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ወጣቶችና ጐልማሶች ማህበራት ህብረት ሰብሳቢ ፌቨን ዘሪሁን ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡


ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጣቢያ ህጋዊ ፈቃድ ለሌለው አካል ፈቃድ እየሰጠ ጥንታዊቱን እና የተከበረችውን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዶግማና ቀኖና እንዲሁም ያሬዳዊ ዝማሬን እያንኳሰሱ ይገኛሉያሉት / ፌቨን፤ ይህ ትውልድን ከመተካትና ትክክለኛውን እምነት ከማስቀጠል አንፃር ትልቅ አደጋ አለው ብለዋል፡፡ የአገራችን ህገ - መንግስት ማንኛውም ሰው ወይም ተቋም የፈለገውን ሃይማኖት የመከተልና የሀገሪቱ ህግ በሚፈቅደው መሰረት ማስተማርና ማስፋፋት እንደሚቻል ያስታወሱት ሰብሳቢዋ፣ ነገር ግን የሌሎችን የእምነት ተቋማት ስም በማናለብኝነት በመዝለፍ በሃይማኖቱ ስም ስብከትም ሆነ ትምህርት በብዙሃን መገናኛ ማስተላለፍ ወንጀልም ሃጥያትም ነው ሲሉ ኮንነዋል፡፡
 “ታዖሎጐስእናቃለ አዋዲየተባሉት የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ደንብ የተዘጋጁ መሆናቸውን ቢገልፁም የሚተላለፉት ፕሮግራሞች ግን ከኦርቶዶክሳዊ ትምህርት ፈጽሞ የሚቃረኑና የቤተክርስቲያኗን ክብር የሚጋፋ በመሆናቸው ፕሮግራሞቹን ለማዘጋት የድጋፍ ፊርማ እያሰባሰቡ መሆኑንና በተለያዩ የአምልኮ ቦታዎች በመዘዋወር ከመቶ ሺህ በላይ ምዕመናንን ማስፈረማቸውን / ፌቨን ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል፡፡በነዚህ መርሃ ግብሮች የሚራቀቁት ጥቂት የማይባሉ ሰባኪያንም ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ ኑፋቄ ሲጽፉና ሲያስተላልፉ የነበሩ ውስጠ ሌላዎች መሆናቸው በግልጽ ይታወቃልብለዋል ሰብሳቢዋ፡፡ 

ከሀገረ ስብከትና ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋር ግንኙነት አላችሁ ወይ ፊርማውንስ አስባስባችሁ ስትጨርሱ ለማን ነው የምታቀርቡት በሚል ላነሳንላቸው ጥያቄ፤ /ሪት ፌቨን ሲመልሱምሀገረ ስብከቱና ጠቅላይ ቤተክህነት ባላቸው የስራ ጫና ምክንያት አሁን እንቅስቃሴውን የሚያደርጉት ከምዕመናን ጋር እንደሆነ ገልፀው፤ ውሳኔውን ግን ጠቅላይ ቤተክህነት እንዲሰጥ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ከዚያ በፊት ግን ከቅዱስ ሲኖዶስ በታች በተዋረድ ካሉ /ቤቶች ጋር እንነጋገራለን ብለዋል፡፡ 

ለኢቢኤስ ቴሌቪዥን ቅሬታ አቅርበው እንደሆን የተጠየቁት ሰብሳቢዋ፤የጣቢያው ባለቤቶች ስህተት እንደሚሰራ በእርግጠኝነት ያውቃሉካሉ በኋላ የድጋፍ ፊርማውን 10 ቀን ቶሎ ቶሎ አጠናቀው ጥቅምት ላይ ስብሰባ ለሚቀመጠው ቅዱስ ሲኖዶስ ለማቅረብ እየተጣደፉ መሆኑን ጠቁመው ከዚያ በላይ ለጣቢያውም ጥያቄ እናቀርባለን ብለዋል፡፡ 

ጉዳዩን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት በአዲስ አበባ ለሚገኘው የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ተወካይ ኢንኮም ትሬዲንግ ደውለን፤ እነዚህ ፕሮግራሞች ፈቃድ የሚያገኙት አሜሪካ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ስለሆነ በጉዳዩ ላይ አስተያየት መስጠት እንደማይችሉ ነግረውናል፡፡ አሜሪካ ከሚገኙት የጣቢያ ሥራ አስፈጻሚዎች አንዱ፤ አቶ ነቢዩ ጥዑመ ልሳን፤ ለአዲስ አድማስ በስልክ እንደተናገሩት፤ ከሲኖዶሱም ሆነ ከሌሎች የቤተ-ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ ተቋማት በይፋ የደረሳቸውና በአካልም ቀርቦ ያመለከተ ባይኖርም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በማኅበራዊ ሚዲያዎች የሚካሄደውን እንቅስቃሴ ተረድተነዋል፤ ብለዋል፡፡
በማስረጃ ተደግፎ የሚቀርብ ነገር ካለም አስፈላጊውን እርምት እንደሚወስዱም አስታውቀዋል፡፡ 


No comments:

Post a Comment