ዳዊት ዘልደታ ፡ ከተክለ ሳዊሮስ ሰ/ት/ቤት
- የሁለቱም ስም ሲነሳ በየዘመናቸው የነበሩት ኦርቶዶክውያን ትዝ የሚላቸው ስማቸው የያዘው በጎ ትርጉም ሳይሆን ኑፋቄያቸው፣ዘረኝነታቸው ፣ትእቢታቸው…መሆኑ ተመሳሳይ ያደርጋቸውል፡፡
- ርዕሰ መናፍቃን አርዮስ ኑፋቄውን በግጥምና በዜማ እያረገ ያልተማሩ ገበሬዎችን፣ውሃ ቀጂዎችን እረኞችን ያስክድ ነበር ፤
እነዚህ ሁሉ መመሳሰሎች
በጥንታዊቷና በአሁኗ ቤተ ክርስቲያን ቢኖርም ይህ ሳምንት(መስከረም 21) በተለየ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያን ከመናፍቃን የታደጉ
ጥቡአን ቅዱሳን አበው 318ቱ ሊቃውንት አሾህ አርዮስን በኒቂያ ጉባዔ ተከራክረው ረተው እርሱንም የረከሰ ኑፋቄውንም
አውግዘው መለየታቸውንና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ስራ ምዕመናን ከኑፋቄ መጠበቅ መሆኑን በተግባር ማስተማራቸውን የምናስብበት
ነው፡፡በዚህም መነሻነት ለዛሬ በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ጉባዔ ስለተወገዘው አርዮስና በአሁኗ ቤተ ክርስቲያን
በምቾት እየተንደላቀቀ ስላለው በጋሻው ፍጹም መመሳሰል ዘወትር የሚገርመኝ አንዳንድ ነገሮችን ለማለት ወደድሁ፡፡እነዚህ መናፍቃን
በተለያየ ዘመናት የነበሩ ቢሆኑም የግብር አባታቸው የቤተ ክርስቲያን ጠላት አንዱ ዲያብሎስ ነውና ከጥቂት ልዩነቶች በስተቀር
ፍፁም አንድ እንደሆኑ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያነበበ ሁሉ የሚረዳው ነው፡፡
በመጀመሪያ አርዮስና በጋሻው የሚለያዩባቸው
ነገሮች ጥቂቶች በመሆናቸው ልዩነታቸውን በማየት እንጀምር፡፡የመጀመሪያው ልዩነታቸው ባላቸው የእውቀት ደረጃ ነው፡፡ አርዮስ
እጅግ የተማረ ፣ አይኑ ከማንበብ የማይቦዝኑ ፣ የብዙ እውቀቶች ባለቤት የነበረ ከመሆኑ በተጨማሪ ከእርሱ አስቀድሞ ነበሩ አባቶችን
(ሐዋርያነ አበው)ቅዱሳት መጻሕፍት በጥልቀት የመረመረ ሲሆን ፤ አቶ በጋሻው ደሳለኝ ግን ምንም ሊባል በሚችል መልኩ ከመንፈሳዊ
ሕይወት የተራቆተ ፣ በዚህ ጉባዔ ከእገሌ ሊቅ ተምሬአለሁ ብሎ አንገቱን ቀና አድርጎ መናገር ማይችል(ሊቅ ስል አስተምረው
የላኩት ፓስተሮች አይመለከትም) ፣ ከገባበትም ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መማር ከነበረበት የአምስት ዓመት ትምህርት
የስድስት ወር ‹‹ትምህርት›› ብቻ በመከራ ‹‹ተምሮ›› የወጣ የተማራትንም በደካማ ውጤት ፈጽሞ ኖህ እንደላከው ቁራ እንደወጣ
የቀረ ሰው ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስንም እንደሚገባ ባይረዳም እንኳ በጭራሽ በትውፊት ያገኘናቸውን የሌሎች ቅዱሳን አባቶች
ትምህርትና ገድል ለማንበብ የማይፈልግ አንብቦም የማያውቅ ነው፡፡ለዚህ ማሳያው በተለያዩ ማታለያዎች ባገኛቸው አውደ ምሕረቶችና
በካሴት ‹‹ስብከቶቹ›› እንድም ጊዜ የእነዚህን አባቶች ትምህርትና ገድል ጠቅሶ አለማወቁ ነው፡፡አንድ ‹‹ኦርቶዶክሳዊ ሰባኪ
ነኝ›› የሚል ሰው እንዴት የእነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን ፣ የእነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ፣ የእነ መልአከ ብርሃን አድማሱ
ጀንበሬ……ትምህርት ሳይጠቅስ እንዴት ሊያስተምር ይችላል? መልሱን ገብቷችሁ በዓላማ ሳይገባችሁ ባለማወቅ ‹‹መናፍቅ
አይደለም› › ለምትሉ ትቸዋለሁ፡፡
ሁለተኛው ልዩነታቸው አርዮስ ክህነት ሰጪው መታወቁና አርዮስ በክህነቱም
ያገለገለ ሲሆን በጋሻው ግን ‹‹ክህነቱም›› በተለያዩ ማታለያዎች የተገኘ በዚህ አሳፋሪ መንገድ ባገኘውም ‹‹ክህነትም››
የማያገለግልበት መሆኑ ነው፡፡በእርግጥ የክህነት ስሙን በሐሰት ደርበው የላኩትን መናፍቃኑን እያገለገለ አይደለም ወይ
ካለችሁኝ ተሳስታችኋል ልላችሁ አልችልም፡፡ከዚህ በተጨማሪ ‹‹መጋቢ ሐዲስ›› የሚለው የከበረ የመዓረግ ስም እርሱና ጀሌዎቹ ቤተ
ክርስቲያን ለማፈራረስ ለጀመሩት ስራ እንደመደበቂያነት ያገለግላቸው ካልሆነ በስተቀር ትምህርቱን ተምሮ እንዳላገኘው የታወቀ
ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን ስርአት መሠረት አንድ ሰው ‹‹መጋቢ ሐዲስ›› የሚባለው በጉባዔ ቤት ተገኝተው ንባብ፣ ዳዊት፣ዜማ
ከተማሩ በኃላ መጽሐፍተ ሐዲሳትን በግእዝ አንድምታውን ላስኬዱ ልበ ብሩኃን ለሆኑ ሊቃውንት የሚሰጥ ነበር፡፡ በጋሻው
እውነት በዚህ አድካሚ መንገድ ሔጄ ይህን ማዕረግ አገኘሁት ካለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና ልጆችዋ እንዲህ እያሉ ይጠይቃሉ፡- መጽሐፍተ ሐዲሳትን ከመማርህ በፊት የግድ መማር የሚያስፈልጉትን
ትምህርቶች ተምርሃልን?
ከተማርክስ በየትኛው ጉባኤ ተማርክ ?የአብነት
ትምህርት ቤት ሕይወትስ እንዴት አገኘኸው?
ረኃቡንና ጥሙን እርዛቱንና ‹‹በእንተ ስማ ለማርያም›› ብሎ
ፍርፋሪ መለመኑስ እንዴት ነበር?
በስብከቶችህስ ለምንድን ነው አንድ ጊዜ እንኳን ሰዎች የአብነት
ትምህርት እንዲማሩና እንዲደግፉ የማታስተምረው?
እንዲማሩ ስለማትፈልግ? ወይስ
ጣዕሙን ሳላውቅ እንዴት ተማሩ እላለሁ በማለት?
ለሎች ‹‹መጋቢ ሐዲስ› የሚባሉት ሲያተምሩ ግእዙን ጠቅሰው
ከዚያ በአማርኛ ተርጉመው ሲያስተምሩ አንተ ግን ካህናቱን ከመስደብና ከመናቅ ወጥተህ አንድ ጊዜ አንዲት ቃል እንኳን በግእዝ
ስትጠቅስ የማንሰማህ ለምንድን ነው?
ያስተማሩህስ ሊቅ ማን ናቸው?……….አርዮስና
በጋሻው እንዲህ የሚለያዩበት ነገር ቢኖርም ፍጹም የሆነ አንድነትም አላቸው፡፡
፩. በስማቸው ፡- አርዮስ ማለት ፀሐይ ማለት ሲሆን
በጋሻው የሚለውም ስም ከነገረ ሃይማኖትና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የተገናኘ ባይሆንም መጥፎ ስም አይደለም፡፡ ነገር ግን የሁለቱም ስም ሲነሳ
በየዘመናቸው የነበሩት ኦርቶዶክውያን ትዝ የሚላቸው ስማቸው የያዘው በጎ ትርጉም ሳይሆን ኑፋቄያቸው፣ዘረኝነታቸው
፣ትእቢታቸው…መሆኑ ተመሳሳይ ያደርጋቸውል፡፡ ለዚህ ነው አርዮስ ማለት ፀሐይ ማለት ቢሆንም ማንም
የማይጠቀምበትና እናቶቻችንም ክፉ ግብር ላላቸው ሰዎች ‹‹አርዮስ›› ሚል ስያሜ የሚሰጡት፡፡
፪. ኑፋቄያቸውን የሚያሰራጩበት መንገድ ፡- አርዮስ ‹‹ወልድ ፍጡር››
የሚለውን ኑፋቄውን በግልጥ ከማቅረብ ይልቅ ብዙ ጊዜ በግጥምና በዜና ማቅረቡ ብዙዎችን በቀላሉ ለመማረክና ኑፋቄውን
ለብዙዎች ተደራሽ ለማድረግ አስችሎታል፡፡ በጋሻው የግብር አባቱን አርዮስን ፍጹም አህሎና መስሎ የተገኘ ነውና ቤተ ክርስቲያንን
እንዲያፈራርስ የላኩት ፓስተሮች በየጊዜው የሚያወጡትን የሞት ትምህርትና የዘፈን እንክርዳድ ኦርቶዶክሳዎያን በገንዘባቸው
በራሳቸው ቤተ ክርስቲያን ሆነው እንዲለምዱትና
ጥንታዊውንና መንሳዊውን ያሬዳዊ ዜማ እንዲጠሉ በግጥምና በዜማ እያረገ በንጹሑ የቤተክርስቲያን ማሳ ላይ
ለመዝራት እየጣረ ይገኛል፡፡ለዚህም ማሳያው በየጊዜው የሚያወጣቸውን ‹‹ትምህርቶች›› አርዕስታቸውን ‹‹መዝሙሮቹን›› ደግሞ
ግጥምና ዜማቸውን በግልጽ ከመናፍቃኑ ላይ እንዴት እንደሚወስድ ለማወቅ ከዚህ በፊት በተለያዩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች
የቀረቡትን መረጃዎች ማየት ይጠቅማል፡፡
፫. ኑፋቄያቸውን ተደራሽ የሚያደርጉባቸው ሰዎች ፡-ርዕሰ መናፍቃን አርዮስ ከላይ እንደተጠቀሰው ኑፋቄውን በግጥምና በዜማ እያረገ
ያልተማሩ ገበሬዎችን፣ውሃ ቀጂዎችን እረኞችን ….ያስክድ እንደነበር ፤ በጋሻውም የቤ/ክ ትምህርት ምን አይነት እንደሆኑ ያላወቁ
፣ በዘረኝነት የታወሩ ፣ ሰንበት ትምህርት ቤት ጣዕም ያልቀመሱ(ለዚህ ነው ዛሬም እንደተለመደው ቅዱስ ሲኖዶስ ዝም ብሎ
እየተመለከተ በቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን የሚገኘውን ሰንበት ትምህርት ቤት ከቤተ ክርሰቲያኑ አስተዳደር አጣልተው ፣ ከሕዝቡ ነጥለው አገልግሎታቸውን
የሚያዳክሙት)ነፋስ በነፈሰበት የሚነፍሱ ፣ ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን የማይጨነቁ
ብዙ ግዴለሽ መንገደኞችን ‹‹አንተ የዘመናችን ቅዱስ ጳውሎስ ነህ ›› እያሰኘ ለመናፍቃኑ በስጦታ እየገበረ
ያለው፡፡ ለዚህም በዘረኝነት ስብከቱ ከቤተ ክርስቲያን የለያቸውን ከ3000 በላይ የሐዋሳ የዋሕ ምእመናን ጥሩ
ምሳሌዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በስርዓተ ቅዳሴ እንዳይሳተፉ ፣ የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤልን እንዲሰድቡ፤ በከቤተ
ክርስቲያን ትልቅ አገልግሎት እየሰጠ ያለውን ማኅበረ ቅዱሳንን ‹‹ካላጠፋን››
እንዲሉ ያደረጋቸው ማን ይሆን? ቤተ ክርስቲያንን ከዚህ በፊት እንደማያውቋት ጀርባቸውን የሰጧት
ስትበድላቸው እንደኖረች አምርረው እንዲጠሏት ከከበረች እናታቸው ተለይተው ወደ መናፍቃን አዳራሽ እንዲሄዱ ያደረጋቸው ምን
አይነት ትምህርት ይሆን?
፬.ጊዜውን እያዩ ከጎጂዎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ፡- አርዮስ ከተፍፃሜተ ሰማዕት ከቅዱስ
ጴጥሮስ ጀምሮ ከስተትህ ተመለስ ሲባል ‹አልመለስም› በማለቱ 318 ቱ ሊቃውንት አውግዘው ከቤተ ክርስቲያን አንድነት ለይተውታል፡፡ከዚህ በኃላ እንኳን ተጸጽቶ በንስሐ እንደመመለስ ‹‹እውነተኛውን
ትምህርት በማስተማሬ አወገዙኝ›› በማለት ቅዱስ አትናቴዎስ ለንጉስ ቆስጠንጢኖስ ስጋት እንደሆነ ደጋግሞ በመንገር ከንጉሱ
ጋር ያለውን ወዳጅነት አጠናከረ፡፡ቆይቶም ‹‹ተጸጽቻለሁ›› በማለቱ ተንኮሉን ያልተረዳው ንጉስ ቆስጠንጢኖስ አርዮስን ከማኀበረ
ምእመናኑ እንዲቀላቅለው ጥብቅ ማሳሰቢያ ቢልክም ቅዱሱ የንጉሱን ትእዛዝ ባለመቀበሉ የሚደርስበትን ቢያውቅም የሃይማኖት ጉዳይ
እንደእኛ ዘመን ተራ ጉዳይ አልነበረምና ‹‹በኑፋቄው ልጆቼን እንዲበክል አልፈቅድም›› በማለቱ ቅዱሱ
ተጋዘ፡፡አርዮስም ለጊዜው በድል አድራጊነት ግብጽ ገብቷል፡፡ በጋሻውም በ97 ዓ.ም ነበረው የፖለቲካ ትኩሳት ሰው
አስተውሎ ለመወሰን አቅም ያጣበት ጊዜ ነበርና ይህን ሁኔታ አጥንቶ ለቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ በመምሰል በሚያሳዝን መልኩ ፓትርያልኩን ጳጳሳቱን ካህናቱን
በማዋረድ ለጊዜውም የሰውን ልብ ማግኘት ቻለ፡፡ ነገር ግን ከጥቂት ዓመታት በኋላ ሕዝቡም እየተረጋጋ ነገሮችን በጥሞና መመልከት
ሲጀምር ‹‹ይሄ ሰውዬ ላህዩ ለምን እንደመናፍቃን ሆነ? ለምንድን ነው ስለ ቅዱሳን የማያስተምረው?
ታሪካቸውንስ
ለምን አይጠቅስም? ትምህርቶቹስ ‹‹ከሕይወት ትምህርት›› ውጭ ሰውን በሃይማኖት የሚያጸኑ የዶግማ
ትምህርቶችን ለምን አያስተምርም? …..››የሚሉ ጥያቄዎች በሰፊው መነሳት ሲጀምሩ
በሀሰት‹‹ እኛን የሚያሳድዱን ቀንተውብን ነው ፤ ኢየሱስን ስለሰበክን ነው…›› ቢልም የምዕመናኑ ጥያቄ
ጫናው እየጨመረ ሲመጣ የሚኖርለትም የሚሞትለትም ዓላማ ሌለው ዳግማዊ አርዮስ በጋሻው ከአባቱ እንደተማረው
ሕዝቡ ከእርሱ አየራቀ እየራቀ የሚጠለልበት ዋሻ ሲያጣ በአስገራሚ ሁኔታ መንገዱን ቀይሮ ትናንት ሲያላግጥባቸው
ከነበሩት ከአቡነ ጳውሎስ ጋር በዕንባ ጭምር ‹‹ተጸጽቻለሁ›› በማለት ታረቀ፡፡በእውነቱ ከሆነ ይሄ ጉደኛ በመጀመሪያም የተጣላው
ከፓትርያልኩ ጋር አልነበረም የተጣላው ከቤተ ክርስቲያንና ከቅዱሳን ጋር የበደለውም እግዚአብሔርን ስለሆነ ጸጸቱና
ለቅሶው እውነት ከልብ ከሆነ እነዚህንም ቢጨምር መልካም ነበር፡፡ ምክንያቱም በአቡነ ጳውሎስ በኩል የሚገባው ወደ ቤተክህነት
በእግዚአብሔርና በቅዱሳኑ በኩል የሚገባው ደግሞ ወደ ሕይወት ነውና፡፡ ከዚህ በኃላ በጋሻው እነ አርስዮስ በሔዱበት አዲስ
በሚመስለው አሮጌ መንገድ ጉዞውን ጀመረ ፤ ከግብረ አበሮቹ ጋር ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ውጭ ሐውልት ሲያቆም ታየ፡፡በበዓለ ሲመታቸውም አይኑን በጨው አጥቦ
‹‹ሁሉም ለፓትርያርኩ እንዲገዛ ››ሲል መመሪያ ሰጠ፡፡የበጋሻው ተጧሪ ያሬድ አደመም በድብቅ በተቀዳ ካሴት እንደተናገረው
ባይሳካም የ30ሚሊየን ብር አውሮፕላን ለመግዛት አቅዶ ነበር፡፡ ተመልከቱ ሁለቱም መናፍቃን ባይሳካላቸውም ቤተ ክርስቲያንን
የማፈራረስ ዓላማቸው እስካስፈጸመላቸው ድረስ የማይሔዱበት መንገድ አለመኖሩ ፍጽም አንድነታቸውን ያሳያል፡፡
እዚህ ጋር አንድ ማስተዋል ያለብን ነገር ትናንት ፓትርያልኩን ‹‹ሰይጣን ››አድርጎ ይናገር
የነበረ ኃላ ላይ ግን ‹‹መልአክ ናቸው›› ብሎ ፍጹም ሌላ ሰው እስኪመስሉን ከተቀየረ ነገ ከነገ ወዲያ ይሄ ሰው
ማኀበረ ቅዱሳን ኑፋቄያቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ ሲገልጥባቸው ‹‹ጌታ ከተቀበልን አምስት አመታችን ነው›› እያሉ
እራሳቸውን እንደገለጡ የተሐድሶ መናፍቃን አራማጆች ‹‹ቤተ ክርስቲያንን ለማፈራረስ ሞክሬ አልቻልኩም›› ብሎ ቦታውን ላልታወቀ መናፍቅ ተክቶ
ላለመሔዱ ምን ማስረጃ አለን?
፭. በስብከታቸው እረፍት የሚያሰጡ አለመሆናቸው፡- ወንጌል እረፍት የምታሰጥ
መንፈሳዊት ሕግ ናት፤ በሃይማኖትና በትሕትና ለሚሰማት ሰላምንና ዕረፍት ያገኝ ዘንድ አለው፡፡ ለዚህ ነው ወንጌልን የሰጠን
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹እናንት ሸክማችሁ ከበደ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኃለሁ›› ‹‹እኔ ምሰጣችሁ ሰላም
አለም እንደሚሰጣችሁ ያለ አይደለም ›› ብሎ ቃል ኪዳን የገባልን፡፡ አርዮስ ኑፋቄውን ለማስተማር
ሞክሮ ነበር፡፡ነገር ግን ከጭቅጭቅ በቀር ያመጣው ለውጥ የለም ፤ ዛሬም ወልደ አርዮስ በጋሻው ሙዳየ
ምጽዋትን እንጂ አውደ ምሕረትን የሚቆጣጠር በመጥፋቱ ከጡረተኞቹ ጋር እንደልቡ ቢፏንንበትም ሰላምና ዕረፍት
የምታሰጠውን ወንጌልን ‹‹እሰብካለሁ›› ቢልም በአዋሳ፤በዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ፤ በዲላ……..እንዳየነው ከሁከትና
ከብጥብጥ በቀር ‹‹ትልቅ›› አድርገው የሚያዩትን እንኳ እረፍት የሚያሰጥ ስብከት ማቅረብ አልቻለም፡፡
v መጨረሻቸውስ ይመሳሰል ይሆን???
በመጨረሻ አርዮስ በደገኛው አባት በአቃቤ ሃይማኖት በቅዱስ አትናትዮስ
ተጋድሎ ኑፋቄው መጋለጥ ሲጀምር ‹‹ንስሐ ገብቻለሁ›› እያለ ውስጥ ለውስጥ ኑፋቄውን ማስተማር ቀጠለ፡፡ከዕለታት
በአንድ ቀንም ጓደኞቹ ከመፀዳጃ ቤት ገብቶ ሲቆይባቸው መጥተው ቢመለከቱት በአሰቃቂ ሁኔታ አንጀቱ ተዘርግፎ ፈርሱ እየታየ
በአስከፊ ሁኔታ ሞቶ አግኝተውታል፡፡በጋሻውና ግብረ አበሮቹም በሚያሳዝን ሁኔታ ‹‹ተጸጽቻለሁ›› በማለት በተመሳሳይ የጥፋት
መንገድ እየተጓዙ ይገኛሉ፡፡ በጋሻው እንደ ሽንት ቤት በከረፋው ሕይወትህ ውስጥ ፈርስ ኑፋቄ ፣ ዘረኝነት ፣
ትዕቢት ፣ ፍቅረ ነዋይ ፣ ድንቁርና ለሁሉም ግልፅ ሆኖ ቢታይም ትናንት አባትህ አርዮስን አዋርዶ ቅዱስ አትናትዮስን
አንድም ቤተክርስቲያንን ያከበረ አምላክ ዛሬም አለና ፤ አማናዊውንም ቅጣት ሳያመጣ አይቀርምና እልሁን ትተህ በንስሐ ተመለስ የልጅነት
ምክሬ ነው፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
ይገርማል!!! ወቅቱ የተሃድሶ መቦርቂያ ነው መሰለኝ እዚህ ዋሽንግተን ታላቋን የቅድስት ማርያም ቤ/ክ ተስፋየ መቆያ (የበጋሻው ቀኝ እጅ)እየበጠበጣት ይገኛል። በቅድስቷ በአርሴማ ስም ገንዘብ ካልሰበሰብኩ ቤቷ ይዘጋ ብሎ ተነስቶብናል። እ/ር አባቶቻችንን ያበርታልን።
ReplyDeleteere migerm new tesfaye mekoyam endzhi hone wey gud gen iwnet new?brother
Deleteተስፋዬ መቆያ የሚባለውን አንዲት እህት ስታደንቀው እሰማ ነበር፡፡ በእርግጥ ሰውዬውንም ሆነ ትምህርቱን ሰምቼ አላውቅም፡፡ በስም ሲወራለት ነው የምሰማው፡፡ ይገርማል፡፡
DeleteWe did know about Tesfaye Mekoyia and other 12 years ago, I don't know why the Holy Synod gave them such a loooooooooooooong time ,?????? they must be banned from any church activities and they wish they can join the protestant masters. ?
ReplyDeleteMahibere kidusan EGZIABHERE YETEBEKACH, DINGLE ATILEYACH
ስንት አይነት የመንፈስ መጫወቻ ህዝብ አለ የሄ መቼም የጤና አይደለም
ReplyDeleteለግዚው ነው መጥፍታቸው መች ይቀራል
ReplyDelete"sale lana kedist egzaw mharem yeses crestos" abzetan ensaly borthodox twedo ement lay ymataw mat kalale aydelem slenatwe sl kedest Marym blow yeker belanen enzhen arwsawyan bystgeselen lebona stoache bemelesw wa!! satwe ahon new nesh gebuna tmelesw yengl marym leg zm bel ytwan aymesalach zmetaw mekenyat alw ynatwen asrt ystaten ager ager egezabher ethiopan lmenafikan asalf aystm atlfw nesh gbw!! nesh gebw! ftanew syferedbachu!! satw maltwal leb yalew leb ybale en ytsamazn tnegralh lzbanew arewswyan!! ydengl Maryam yasrat ager leg andw nze!!!!!wa!! wa!! leb ylew leg yebel keledew bk!!
ReplyDeletekale hiwot yasemaln
ReplyDeleteየቤተክርስቲያን ምእመን ትልቁ ችግራችን አንድም ሁሉንም ነገር ለቤተክህነት የመስጠት ነገር አለብን፣ ሌላው አንድ ጥሩ ያልነው ሰባኪ ሲያስተምር እርሱን እየተከተሉ መሯሯጥ እንወዳለን፡፡ ቃሉን ከመቀበል ይልቅ ሰባኪውን የመቀበል ነገር አለብን፣ ልክ ድምጽ ማጉያውን እንደመቀበል ያለ ነገር ነው የሚታይብን፡፡ እስኪ እናስተውል ድምጽ ማጉያ መከተል ማለት ጦአት እንደመከተል እንደሆነ እንኳን ያልተረዳን ብዙ አለን፡፡ ይህ አካሄዳችን ነው በቀላሉ የተኩላውን ባህሪ እንድንወርስ ያደረገን፡፡ ስለዚህ ሁላችንም በራሳችን እራሳችንን እንፈትሽ፤ ወንድማችን ዲ.ዳንኤል እንደመከረን ሰባኪና ማህበርን መከተል ትተን ስለአንድነት እንስራ፡፡ የሰባኪውም የማህበሩም አላማ ሊገባን ይገባል፡፡ ሁሉም ስራቸው ለአንዲት ቤተክርስቲያን እንደሆነ ተረድተን ስራችን ሁሉ ወደ ቤተክርስቲያን አንድነት መሰራት አለበት፡፡ ይህንን ለመስራት ካለፈው ስህተት መማር ነው አንድ አባባል ሰምቻለሁኝ ጠዋት ያደናቀፈህ ድንጋይ ማታ ከደገመህ ድንጋዩ አንተ ነህ የሚለውን አባባል እጁግን ማስተዋል ይፈልጋል፡፡ እናንተ በርቱ እግዚአብሔር ይርዳችሁ፡፡ እንደዚህ አይነት መረጃ ለማግኘትም ችግር ሆኗል፡፡ ምክንያቱም ብዙዎቻችን የኢንተርኔት ተጠቃሚ ላንሆን የምንችልበት ጊዜ አለና በበራሪ ወረቀት የምትሰሩበት መንገድ ቢዘጋጅና ለምእመኑ በመረጃ የተደገፈ ስራ ስንሰጠው ነው የሚቀበለው፡፡ ድህረገፃችሁንም ለማስተዋወቅ በፊስ ቡክ በሌላም ሞክሩ፡፡ ማህበረ ቅዱሳን እያደረጋችሁ ያለው ጥረት በእውነት ደስ የሚልና የሚያበረታታ ነው፡፡ ከዚህ ተምረን ሁላችንም እንበርታ፣ እናንተም በርቱ፡፡ አይዟችሁ፡፡ እውነትን ለመግለጽ መጣር ብዙ ፈተና ቢኖረውም በትእግሰት አሳልፉት፡፡ የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳችሁ፡፡
ReplyDeletelibona yistachew
ReplyDeleteእንደው ይሄ ነገር በጣም የሚገርም ነው ዛሬ ዛሬ ብዙዎቻችን ሰውን መከተል እንጂ ስለእምነታቸው ምንነት ጠንቅቀን የምናውቅ አይመስለንም፥ ነገሩ እንዲህ ነው በዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው በአሁኑ ሰዓት ብዙዎችን ኦርቶዶክሳዊያንን አንገት ያስደፋ እና ለመናፍቃን መሳለቂያ ያደረገንን የደብረ ሰላም ቅድስተ ማሪያም ጉዳይ ነው፤ የዋኃን አሁንም ሃይማኖታችንን እየጠበቅን ነው ቤተክርስቲያናችንን ከቦርድ ነጻ አወጣን በማለት እራሳችንን የምንሸነግል ሰዎች ሆነናል በደብረ ሰላም ቅድስተ ማርያም ቤተክርስቲያን እነ ተስፋዬ መቆያ እና እስቂያስ ማሞ የሚባሉ ቡለት ሰዎች በደንብ በእምነት በዓላማ አንድ ናቸው በዋናነት ትልቅ ተልዕኮ ያላቸው ግለሰቦች አፈ ጮሌዎች ሰዉን ሰባኪያን ነን በማለት የሰዉን ልብ በደንብ በመብላታቸው ዛሬ ትላልቅ የሚባሉ ሰዎች እንኳን የነዚህን መሰሪ ሰዎችን ሥራ ሊረዱ ባለመቻላቸው ዛሬ አብረዋቸው እላይ ታች ሲሉ ይታያሉ እነዚህ ትላልቅ ሰዎች የነገሮችን አመጣት በደብም መመልከት በተገባቸው ነበር ነገር ግን ተስፋዬ መቆያ ባነሳሳው አመጽ እና ሁከት በስነሳው ውስጥ ሰንበት ት/ቤቱ ነው በራሳቸው ሁኔታ እንዲያ ያደረጉት በማለት እራሳቸውን እያታለሉ ነው ያሉት ለምሳሌ ለመጥቀስ ያህል
ReplyDelete1) የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ነው በግልጽ በአውደ ምህረት በመውጣት "ተሃድሶ የሚባል ነገር የለም" በማለት ለምዕመናን ሲናገር የነበረ ሰው ተስፋዬ መቆያ ነው
2) የቅድስ አርሴማ ማኅበር በማለት ገንዘብ በመሰብሰብ ገንዘቡ በቀጥታ የታኦግሎስ እና ቃለ ዓዋዲ የተባሉትን የመናፍቃን ቴሌቪዥን ጣቢያን ሲረዳ የነበረ እንደሆነ ግልጽ መረጃዎች አሉ
3) ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ከተመሰረተች 28 ዓመት ነው ነገር ግን እነዚህ ጥቁር እራሶች ከመጡ ላለፉት 6 ዓመታት ችግር ተፈጥሯል ለምን 22 ዓምት ሰላም ሆነ ነገር ግን ላለፉት 6 ዓመታት ትልቅ ችግር ተፈጠረ??
4) እውነት የቦርድ ችግር ከሆነ በቤተክርስቲያን ያለው ለምን በግልጽ አባላት ተጠርተው በግልጽ ያለውን ጥፋት እና ስህተት አሳይቶ ቦርዱ እንዲወርድ ማድረግ ሲቻል ለምን በአመጽ ወይም በአድማ ለመደረግ ተፈለገ? ምክንያቱ ግልጽ ነው ምዕመናን ይፍረዱ ከተባለ ችግሩን ማሳየት ስለማይችሉ ሰንበት ት/ቤትን አነሳስቶ ከኃላ ሆኖ ሁኔታዎችን እየተቆጣጠረ ያለው ተስፋዬ መቆያ ነው በመቀጠል ህዝቂያስ የሚባለው የተወገዘ ዲያቆን ነው
እዚህ ላይ ስለ ህዝቂያስ ስለሚባለው ሰው በሰበታ ገብርኤል ቤተክስቲያን አገልጋይ የነበረ ዲያቆን ነበረ በቦታው በተፈጠረ ችግር ንስሃ መግባት ስላልቻለ እና ይቅርታ እግዚአብሔርን መጠየቅ ስላልቻለ አባቶችን የሚያንጓጥጥ ግብረ በላ ስለነበረ በወቅቱ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አውግዘው ለይተውት ከቤተክርስቲያን ወጥቷል ነገር ግን አሜሪካ ከልካይ የለም መጋረጃ እየገለጠ እየገባ አገልጋይ ነኝ ማለት ጀመረ
እነዚህ ሰዎች ዋና መገለጫቸው ፈርሃ እግዚአብሔር በጭራሽ የላቸውም፣ ካህናት አባቶችን በጣም ይንቃሉ ይዘረጥጣሉ፣ ይሳደባሉ
ሌላው እነዚህ ሰዎች አፈጮሌዎች በመሆናቸው ዛሬ ዳህጸ ልሳን እንኳ ቢኖርባቸው እና ተሳስተው ስለ ዋናው ዓላማቸው ከተናገሩ ወዲያው ክደው ምናልባት ተሳስቼ ይሆናል እንጂ እኔ እንዴት እንደዚህ እላለው በማለት ሰውን በቶሎ ሰዎችን የመሸንገል ባህሪ አላቸው፤ ስለዚህ እነዚህ ነጣቂ ተኩላዎች በእጅ በእግር ብለው የደብረ ሰላም ቤተክርስቲያንን የዋሃን ምዕመናን ብሎም ትላልቅ የተከበሩ አባቶችን በደነደነ ምላሳቸው አሳምነዋቸው ይህው እነዚህን ሰዎች ተከትለው ይነጉዳሉ መጨረሻው የት እንደሚሆን እጅግ ያስፈራል፣ ቆም ብለን ማየት ካልቻልን ነገ ቤተክርስቲያናችንን የት እንደምናገኛት ለማናችንም መገንዘብ የሚያዳግት አይደለም።
ወገኖቼ በመጨረሻ በደብረ ሰላም ያለውን ትልቁን ችግር እንመልከት እንዴት እነዚህ መናፍቃን ለዚህ ሁሉ ፈተና ዳረጉን
1) የደብረ ሰላም ምዕመናን እግራቸው ነዶ ያጠራቀሙትን ገንዘብ ዛሬ ለዳኛ፣ ለጠበቃ መሰጠቱ በእጅጉ ሊያሳዝነን የሚገባ ነው
2) የደብረ ሰላም ምዕማናን እና አባቶች ላለፉት 28 ዓመታት በፍቅር ሲገለገል ቆይቷል ነገር ግን ዛሬ መናፍቁ የተሃድሶ sleeper ለምድ ለብሶ እንደ እባብ ፈተና ውስጥ ቤተክርስቲያኒቱን ከቶ ዛሬ መለያየት፣ መካሰስ፣ መነቃቀፍ ነግሷል ለምን?
3) ዛሬ በቤተክርስቲያን ምዕመናን ካህናትን እንዳያምኑ እንዲንቁ፣ እንዲሳደቡ፣ እንዲዘልፉ እየተደረገ ያለው ለምን ይሆን? እንዲህ ነው ነገሩ ቀድሞውንም እነዚህ መናፍቃን ከመናፍቃኑ ጋር የተነጋገሩት በምንድነው እኛ ከውስጥ እንገፋለን፣ እናንተ ከውጪ ትቀበሉታላችሁ በሚል ነው ይሄም ምንድነው እነዚህ መናፍቃን በውስጥ የሚገፉት ክፉ ትምህርት በማስተማር አይደለም ብዙዎቻችን የምጠብቀው መናፍቅ ሲባል “ማርያም አታማልድም” ወይም “ቅዱሳን አያስፈልጉንም” የሚለውን የዋናዎቹ መናፍቃን አስተምህሮ ጠብቀን ከሆነ ጠፍተናል ማለት ነው፥ የሚያደርጉት ነገር ምንድነው ቢባል በቤተክርስቲያን ውስጥ ሁሌ አስተማሪ፣ አገልጋይ የመሳሰሉት ናቸው የሚሰሩት ግን በውስጥ አድማ በማስነሳት፣ ህዝብ በህዝብ ላይ በማነሳሳት፣ ምዕመኑን በካህናት ላይ በማስነሳት በአጠቃላይ ህግ የጠፋበት ቦታ ማስደረግ አላማቸው ነው በዚህም ምዕመን እየተማረረ ይጠፋል እነዛ በውጪ በመጠበቅ ኑ እኛ ጋር ኑ ሰላም ነው ችግር የለም በማለት ሰዎችን ምዕመንን ይስባሉ የዛሬዎቹን መናፍቃን ከነ ንስጥሮስ እና አርዮስ የሚለዩት እነ አርዮስ ወልድ ፍጡር ነው በማለት ሲያስተምሩ ከቤተክርስቲያን ተነጥለው ነው የወጡት ትላንት ድምጻቸውን ሲሰማ የነበረ ምዕመን አስተምህሯቸውን ሲሰማ ዓይናችሁን ላፈር ነበር ያለው የዛሬቹ መናፍቃን የትላንቱን ስለሚያቁ ዛሬ ከዛ በደንብ ተምረዋል ምናልባት በመጨረሻ ቢነቃባቸው እና ከቤተክርስቲያን ቢወገዙ እንኳ አላማቸው እንደ አባቶቻቸው ብቻቸውን ከቤተክርስቲያን ላለመውጣት ዛሬ ብዙ ደጀን አዘጋጅተዋል ለምሳሌ በዲሲ ያለውን ችግር ስንመለከት ተስፋዬ መቆያ አስቀድሞ የአርሴማ ማኅበር በማለት አደራጅቷል ተከታይ አለው ስለዚህ ብቻውን አይወጣም ማለት ነው ቲፎዞዎችን ይዞ ነው የሚወጣው ማለት ነው እንግዚህ ምዕመናን አስቡት ምን እየተደረገብን እንዳለ ልብ ልንለው ይገባል፣
እነዚህ ተከትለን የት ልንደርስ እንደምንችል ልብ ልንለው ይገባል አለበለዚያ ተከትለን ገደል እንዳንገባ በእጅጉ ያስፈራናል
እስቲ በሌላ ጊዜ ደግሞ እመለሳለው
ቸር ይግጠመን እንሳለሁ
ከካሊፎርኒያ ተስፋ ሥላሴ ነኝ
EWUNET ADI KEN TIGELETALECHI.EGZIABHER YASTAGISACHEW.YETEGNAN ENINIKA...
ReplyDelete