Saturday, October 31, 2015

መምህር ግርማ የታሰሩት 800ሺህ ብር በማታለል ተጠርጥረው ነው



(አዲስ አድማስ ጥቅምት 20 2008 ዓ.ም)፡- መምህር ግርማ ወንድሙ የታሰሩት እምነትን መነሻ በማድረግ፣ በተፅዕኖ መኖሪያ ቤት በማሸጥና ገንዘብ አታሎ በመውሰድ ወንጀል ተጠርጥረው መሆኑን ፖሊስ ለፍ/ቤት ያስረዳ ሲሆን ተጠርጣሪው ግን አስተባብለዋል፡፡

ባለፈው ረቡዕ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ዘንድ በአጥማቂነት የሚታወቁት መምህር ግርማ ወንድሙ፤ በተጠረጠሩበት ወንጀል ፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልገኛል በማለቱ /ቤቱ 7 ቀን ሰጥቷል፡፡


በተጠርጣሪው ላይ እየተጣራ ያለው የፖሊስ የምርመራ መዝገብ፤ መስከረም 2006 . አቶ በላይነህ ከበደ የተባሉ ግለሰብን ሃይማኖትና እምነትን መነሻ በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ ወሰን ግሮሰሪ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ላይ ከሚገኝ መኖሪያ ቤቱ እስከ ጥር 30 ቀን 2006 . ሸጦ ካልወጡ አስከሬናቸው መውጣቱ የማይቀር መሆኑን በመንገር ግለሰቡ ቦታውን እንዲሸጡ አድርገዋል ይላል፡፡
   
ግለሰቡም ከባለቤታቸው ጋር በመሆን እንደተባሉት ቤቱን 800ሺህ ብር ይሸጣሉ፡፡  ቤቱ በተጠቀሰው ዝቅተኛ ዋጋ እንዲሸጥ ተጠርጣሪው መምህር ግርማ አስተዋጽኦ ነበራቸው ይላል የፖሊስ የምርመራ መዝገብ፡፡ ግለሰቡ ቤታቸውን ከሸጡ በኋላ ተጠርጣሪውበራዕይ ያየሁት ቦታቦሌአለ፤ እሱን ነው መግዛት ያለብህ፣ ቤቱ የተሸጠበትን 800ሺህ ብር አምጣና እንዲበረከትልህ ልፀልይበትብለው ወሰዱት፡፡ የግል ተበዳይ ገንዘባቸውን ለማስመለስ ያደረጉት ጥረት እንዳልሠመረላቸውና ከሀገር ወጥተዋል እንደተባሉ የፖሊስ ምርመራ መዝገብ ያብራራል፡፡

 
 የግል ተበዳይ ጉዳዩ ውሎ ሲያድር ማታለል መሆኑን በመረዳታቸው በመጋቢት 2007 . ወር ገደማ ለፖሊስ ያመለከቱ ሲሆን ፖሊስ ከሄዱበት ሀገር እስኪመለሱ የተበዳዩን ቃልና የምስክሮችን ቃል ሲቀበል መቆየቱን ያትታል፡፡   መምህሩ በበኩላቸው፤ ከሣሽ የተባለውን ግለሰብ ጥቁር ይሁን ቀይ አንድም ቀን አይተውት እንደማያውቁ በመግለጽ ከጀርባዬ የተሴረብኝ ሴራ አለ ሲሉ ለፍ/ቤቱ ተናግረዋል፡፡

 
 ጉዳዩን የያዘው የፖሊስ የምርመራ ቡድን ከትናንት በስቲያ ተጠርጣሪውን በፌደራል መጀመሪያ ደረጃ /ቤት አራዳ ምድብ 1 /ችሎት ያቀረባቸው ሲሆን ግለሰቡ በተጠረጠሩበት የማታለል ወንጀል ቀሪ የምርመራ ስራ ስላለኝ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይሰጠኝ ብሎ /ቤቱን ቢጠይቅም /ቤቱ 7 ቀን ጊዜ በመፍቀድ ጉዳዩን ለጥቅምት 25 ቀጥሯል፡፡ ተጠርጣሪው ፖሊስ የተጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ የተቃወሙና የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው የጠየቁ ቢሆንም ፖሊስ በዋስ ቢለቀቁ መረጃ ያሸሹብኛል በማለቱ /ቤቱ የመምህር ግርማን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ አድርጓል፡፡

1 comment:

  1. ተጠርጥረው ነው የሚለውን አስምሬበታለሁኝ፡፡ የቀረበው ዝርዝር ሪፖርት ግን ምንም የሚያስጠረጥር ነገር የለበትም፡፡ እንዴት ገና ለገና ከዚህ በፊት አንድ ጠንቋይ ይህንን አድርጓልና እሷቸው አንዳንድ የእምነቱ ተከታይም ይሆን የእምነቱ ተቃዋሚ የተለያየ መረጃ የሌለው የሀሰት ወሬ ስለሚወራ ብቻ ፖሊስም ሊሆን ይችላል ብሎ አንድን ሰው ማሰር ማለት የ ዜ ግ ነ ት ክ ብ ር የሚለውን ነገር ፖሊስ የነካ ይመስለኛል፡፡ እሳቸውም ኢትየጰያዊ ናቸው፡፡ የሰው ልጅ ናቸው፡፡ በእምነት በኩል ያለውን ስህተት ብለን ያወጣነውን እንተወውና እንደአንድ ዜጋ ስናሰበው ግን እኔ በራሴ አልተቀበልኩትም፡፡ ምክንያቱም ፖሊስ ያቀረበው ሪፖርት ብዙ ስህተቶችና ለአንድ ሰው ብቻ በመቆም ያደረገው ነገር እንዳለው ያሳብቅበታል፡፡ ስለዚህ ክርስቲያን ነን የምንል ዝም ብለን አህዛብ የቀባጠረውን ወሬ እየያዘን የምናሰብቀው ነገር እግዚአብሔርን እንዳናሳዝን እሰጋለሁኝ፡፡በአህዛብ መንገድ አትሂዱ ነው የተባልነው፡፡ ምክንያቱም ይህ ነገር ሀሰት ሊሆን የሚችልበት ብዙ ነገሮችን ነቅሰን ማውጣት እንችላለን፡፡ሪፖርቱ ብዙ የተደፋፈኑና ሀሰት የሚመስሉ ነገሮችን ስለሚያሳይ ነው፡፡ ለምሳሌ ስልካቸውን ዘግተው ጠፍተው ውጪ ሄደው ምናምን እየተባለ የቀረበው ነገር ያስቃል ሁለት ዓመት ሙሉ ነው የጠፉት ኧረ ለምን ይዋሻል፡፡ በግልጽ ስላሴ ቤተክርስቲያን አገልግሎት እየሰጡ ኧረ ኧረ ኧረ ክርስቲያኖች ነን፡፡ ክርስቲያን ከአህዛብ የሚለየው ሁሉንም መመርመር መቻሉ ነው፡፡ ይህንንማ አህዛብም፣ መናፍቁም፣ የሚያቀነቅኑት ነው፡፡ የቤተክርስቲያናችንን ስም ለማጉደፍ፣ የአባቶቻችንን ተቀባይነት ለመቀነስ የተፈጠረ የመናፍቁም የተሀድሶውም አካሄድ ቢሆንስ ማን ያውቃል? ስለዚህ ይህንን የሚያውቁት ሶስቱ ናቸው አንድ ከሳሽ፣ ሁለት ተከሳሽ፣ ሶስተኛው እግዚአብሔር በቃ፤ ወይ ተከሳሽ ማመን አለበት፣ አለበለዚያ እግዚአብሔር መግለጽ ባለበት መንገድ መግለጽ አለበት፡፡ አለበለዚያ እኛ፣ ባላየነው፣ ባልሰማነው ነገር ተባለ ብለን ብዙ ባንቀባጥር ደስ ይለኛል፡፡ ለሁላችንም ማስተዋል ይስጠን፡፡

    ReplyDelete