Thursday, August 18, 2011

አለመታደል

ስለ ልጆቿ ችግር የሚያለቅስ አባት ያላት ቤተ ክርስቲያን የታደለች ናት። በፈንታው ደግሞ ስለ እርሷ ማልቀስ ሳይሆን የሚያስለቅሷት፣ ስለ እርሷ የሚያዝኑ ሳይሆን የሚያሳዝኗት፣ ልጆቿን በእንባቸውና በትምህርታቸው አጥር መከታ ሆነው ከመጠበቅ ይልቅ ከቅጽሯ የሚያባርሩ ጨካኞች ያሏት ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ሊለቀስላት ይገባል።
ስለ ልጆቻቸውና ስለ ቤተክርስትያን ያለቀሱ አባት
በአክራሪ ሙስሊሞች በተለያዩ የግብጽ አካባቢዎች በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸሙትን ጭፍጨፋዎችና ግድያዎች እንዲሁም ወጣት ክርስቲያን ሴቶችን በግድ እያገቡ ማስለም እና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችን በማሰብ ስለቤተክርስትያ እና ስለልጆቻቸው የሚያለቅሱ አባት


ልጆቻቸውን እና ቤተክርስትያንን  ያስለቀሱ አባት
በአንድ ወቅት አባ ጳውልስ እንዲህ ሲለሉ ተደምጠዋል፡-
ክፍ መሪ ተሰጠን ብላችሁ አታጉረምርሙ።ክፍ መሪ ከሆነም የእናንተ ውጤት ነውThis is what you deserveደግ መሪ ለማግኘት መጀመሪያ ደግ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል‛፡፡ አቡነ ጳውሎስ 

እውነታቸውን ነው እሳቸውን የመሰለ ክፉ መሪ ፤ የልጆቻቸው እምባ የቤተክርስትያናችን በተሀድሶያውያን እና በመናፍቃን መከበብ ምንም ያልመሰላቸው  አባት የተሰጠን ከእኛ ክፋት ቢሆንስ ማን ያውቃል ? ክፉውንም ደጉንም የሚሾም አንድ አምላክ ይወቀው እንጂ፡፡
ከዚያም የሰቆቃው ኤርሚያስ ጸሎት ትዝ አለኝና የመጀመሪያዎቹን አራት ስንኞች እንዲህ እያልኩ አነበነብኩ፤

                        አቤቱ የሆነብንን አስብ፤
                        ተመልከት ስድባችንንም እይ፤                
                        ርስታችን ለእንግድች፤ 
                        ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ።

ስል ሮሮዬን እግዜር ወዳለበት ወደ ሰማይ አሰማሁ።
                                                               በማይገለጥ የተከደነ የለም በሚባለው መጽሃፍ ውስጥ
                                                               አባ ጳዎለሎስና አባ ገ/መዴህን ሲገመገሙ
                                                               (ከዲዊት አዘነ)
2 ቀን ይጠብቁን..........

1 comment:

  1. "EGZIABHER ESE GEHADE YIMETSIE: WE'AMLAKINEHI EYAREMIM ESAT YENEDID KIDMEHU- EGZIABHER BEGEHAD YIMETAL AMLAKACHINIM ZIMM AYLIM BEFITU ESAT YINEDAL"

    ReplyDelete