Tuesday, August 16, 2011

አምላክ : ይማርዎ



አምላክ : ይማርዎ

በንስሐ ፡ አክማ
በትምህርት ፡ ሠይማ
በቅዱሳን ፡ ማማ
በመንበሯ ፡ ሾማ
በክብር ፡ ሸልማ 

ኹሉን ፡ ሳታጓድል
ይዛ ፡ በቅምጥል
ምን ፡ ባጎደለች ፡ ነው ?
ነገሩ ፡ መልክ ፡ ያጣው
ምንድነው ፡ ጥፋቷ ?
ያጓደለው ፡ ቤቷ
እንመርምር ፡ እንጠይቅ
ምን ፡ መኾኑን ፡ እንወቅ
ግራ ፡ ነው ፡ ለሰሚው
መነሻው ፡ መድረሻው
ያከበረን ፡ መናቅ
ከበረከት ፡ መራቅ
ከክብር ፡ መዋረድ
ኤልዛቤልን ፡ መውደድ
በአልባሌ ፡ መንገድ
ዝም ፡ ብሎ ፡ መንጎድ
የሰላም ፡ አይመስልም
የጤናም ፡ አይደለም
ይህን ፡ የተረዳን
ያወቅን ፡ ችግሩን
በአንድነት ፡ ኾነን
እንልዎታለን
ማስተዋል ፡ አድሎ
ዕውቀትን ፡ አክሎ
ቀኙን ፡ አሳይቶ
ከንቅልፍዎ ፡ አንቅቶ
ከተንኮል ፡ አውጥቶ
አምላክ ፡ ይማርዎ
ልቡና ፡ ይስጥዎ


                 ጥቅምት ፡ ፳፬ ፡ ቀን ፡ ፳፻፫ ፡ ዓ.ም. 
‹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ››

No comments:

Post a Comment