Sunday, August 14, 2011

ገንዘቤን ሳትሰጠኝ ትሄዳለህን?


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ዘቁስጥንጥንያ፣ ኤጲፋንዮስ ዘቆጵሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም እኒህ ሦስቱ በአንድነት ሲማሩ አድገዋል:: ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም ኤጲስ ቆጶስነትን በተሾመ ጊዜ ሰይጣን ልቡን በፍቅረ ንዋይ አታለለው /ተዋጋው/ ከዚህም የተነሣ በሚገኝበት አዳራሽ የወርቅ ሰሃን የብር ፃህል ጽዋ አሠርቶ ነበር:: ኤጲፋንዮስ ይህን እየሰማ ሲአዝን:: ከእለታት አንድ ቀን ቦታይቱን እጅ የሚነሣ መስሎ ሊመክረው ቢመጣ በዚሁ አዳራሽ ተገኝለት:: ወንድሜ የቆጵሮስ ሊቃውንት ደጋግ እንደሆኑ ታውቃለህ:: በዚህ አዳራሽ ልገኝላቸው ስጠኝ አለው:: ሰጠው:: እየሰበረ ለነዳያን ይመጸውተው ጀመረ:: ገንዘቤን ስደድልኝ ሲለው ቆየኝ እያለ ሰነበተ:: በሚሄድበት ጊዜ ሄድሁልህ አለው:: ገንዘቤን ሳትሰጠኝ ትሄዳለህን? ብሎ ልብሱን ያዘው:: ዘወር ብሎ እፍ ቢለው ሁለት ዓይኑን ነሣው /አጠፋው/:: ከጫማው ወድቆ ያለቅስ ጀመር:: አንዱን ለዝክረ ነገር ትቶ አንድ ዓይኑን አብርቶለታል:: እርሱም ይህ ምክር ተግሣጽ ሆኖት እስከ ዕለተ ሞቱ ሲመጸውት ኑሯል:: ሲሞት አንድ አላድ እንኳን አልተገኝበትም:: በረከቱ ትድረሰንና ብጹ አብ ቅዱስ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም “ኑባሬ ሃይማኖት” በተሰኘው የነገረ ሃይማኖት መጸሐፉ የታወቀ ሊቅ ነው:: /ከዚህ ምን እንማራለን?/

ምንጭ :‐ የሃይማኖተ አበው ትርጓሜ የብራና ቅጅ ያልታተመ

No comments:

Post a Comment