Tuesday, April 24, 2012

መንግስት ለምን ‹‹ማህበረ ቅዱሳንን›› ጥምድ አድርጎ ያዘው?

ይህ የአንድ ሰው ሀሳብ ነው ፤ የማንም አቋም አይደለም

(አንድ አድርገን ሚያዚያ 17 ፤ 2004 ዓ.ም )፡- መቼስ በባለፈው የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ንግግር ያልተናደደ ቢኖር ማህበረ ቅዱሳንን የማያውቅ ያለበለዚያ በተቃራኒ የቆመ ሰው ብቻ ነው ፤ ማህበሩ ወጥ የሆነ ተጠያቂነትና ግልጽነት ያለው ማህበር ነው ፤ እንደ ጠላት ተደብቆ ስራውን የሚሰራ መንፈሳዊ ተቋም አይደለም ፤ በርካታ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር አባላት ያለው ፤ በተቻለው እና አቅሙ በፈቀደ መጠን ቤተክርስትያንን ለመርዳት ፤ የተዘጉትን ለማስከፈት ፤ የሰባኪ ወንጌል ችግር ያለባቸውን መምህር በመመደብ ፤ ለገዳማትና የተቸገሩ አብያተክርስትያናት ፕሮጀክት በመቅረጽ በቋሚነት የሚረዳ ፤ ምዕመኑ በመንፈሳዊ ህይወቱ ጠንካራ እንዲሆን የቤተክርስትያኒቱን መንፈሳዊ ትምህርት ከማስተማሩም በላይ በርካታ አሁን ዘርዝሬ የማልጨርሳቸውን ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ መንፈሳዊ ተቋም ነው ፤ ከወራት በፊት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በማህበሩ ላይ ያለው ተቃውሞ ባነሳበት ጊዜ የብዙዎች መነጋገሪያ ርዕስ መሆኑ የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው ፤ ይህን የመሰለ አስቸጋሪ ሁኔታም ቢፈጠር ችግሮችን በመነጋገር መፍትሄ በመስጠት በችግር ጊዜ ጥንካሬውን አሳይቷል ፤ መንፈሳዊ ህይወትና ወንጌሉ እንደሚያዘውም በወንድሞች መካከል የተፈጠረውን ቅራኔ ይቅር በማስባባል ያጠፋው ይቅርታ እንዲል ፤ የተበደለውም ይቅርታውን እንዲቀበል አድርጓል ፤ እኛም በሁኔታዎቹ ብናዝንም በስተመጨረሻ ደስ ብሎናል ፤ ፈተና ተቋሙን በሚያናጋ መልኩ ከግለሰብ ሊነሳ ይችላል ፤ ከማህበሩን ከተቃራኒ መንገድ የቆሙ ሰዎች ሊነሳ ይችላል ፤ ከቤተክህነቱም ሊነሳ ይችላል ፤ ከመንግስትም ሊነሳ ይችላል  ፤ እንደ ባለፈው ሳምንት ደግሞ ከጠቅላይ ሚኒስትሩም ሊነሳ ይችላል ፤ ነገር ግን ፈተና በየጊዜው መፈጠሩ ሊያስገርመን አይገባም ፤በዮሐንስ ወንጌል 16፤33 ‹‹በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።›› ተብሎ ተጽፏል ፡፡ ስለዚህ መከራም ይሁን ፈተና በጌታችን በመድሀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናልፈዋለን እንጂ የሚመጣውን ፈተና ፈርተን ወደ ኋላ አንልም ፤ በፊትም ፈተና ነበር ፤ ዛሬም አለ ፤ ነገም የህይወትን መስዋእትነት የሚጠይቅ ፈተና ሊመጣ ይችላል ፤ ግን ሁሉም እንደ አመጣጡ ያልፋል፡፡


መንግስት ለምን ማህበሩን ጠምዶ ያዘው?

ከ97 ዓ.ም በፊት ነገሮች ሁሉ መልካም ይመስሉ ነበር ፤ መንግስት ሌሎች ሲያደርጉ ተመልክቶ ፤ እኔም ለምን ይቅርብኝ በማለት ዲሞክራሲያው ምርጫ አደርጋለሁ ብሎ ተነሳ ፤ ጥሩ የሆነ ሂደት ያለው የፖለቲካ ቅስቀሳ በመላው ሀገሪቱ ተካሄደ ፤ መጨረሻ ግን ሁላችን እንደምናውቀው ውጤቱ መንግስት እንዳልጠበቀው ስለሆነ የምርጫውን አቅጣጫ የሚያስቀይር ስራ ተሰርቶ ፤ ኮሮጆ ተገልብጦ ፤ ብዙ ሰዎች ሞተው ሁሉም ነገር እንዳልሆነ ሆነ ፤ ከዚህ በኋላ መንግስት የሰራው ስራ ቢኖር ለመሸነፌ ምክንያት ምንድነው? ብሎ በመነሳት ከበታችኛው አመራር ጀምሮ እስከ ላይኛው ባለስልጣናት ድረስ ሂስና ግለ ሂስ ፤ ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያቶችን ማውጣት ማውረድ ተያያዙት ፤ በርካቶች ላይ ግልጽ እርምጃ በመውሰድ ከመስመር አስወጧቸው ፤ በርካታ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለ97 ምርጫ መሸነፍ የራሳቸውን ሚና መጫወታቸው በስመጨረሻ ደረስንበት አሉ ፤ ለመያዶች ህጉ በሀገሪቱ ውስጥ የማያሰራቸው በማድረግ ከጨዋታ ውጪ እንዲሆኑ አደረጓቸው ፤ በዚህ ማህበራትን የማክሰም ስራ በርካቶች የተመሰረቱበትን ፍቃድ በግልጽ ፍቃዳቸውን መለሱ ፤ በዚህ ጥናት ወቅት ‹‹ማህበረ ቅዱሳን›› ለመሸነፋችን አንዱ ምክንያት ነው የሚል የውስጥ አቋም ያዙ ፤ ይህን የምነግራችሁ ሂደቱን ስለማውቅ ነው ፤ በምን መስፈርት ሚዛን ላይ ‹‹ማህበረ ቅዱሳንን›› አስቀምጠውት ይህን ሊሉ እንደቻሉ አላውቅም ፤ የህልውና ጉዳይ ስለሆነም የፈለጉትን ቢሉ ተሳስታችኋል ማለት የማይቻልበት ደረጃ ላይ ነበርን ፤ ማህበሩ የተቋቋመበት መንገድ ለማፍረስ ቢፈልጉ ቀላል እንደማይሆን ሌላ ጥያቄ እንደሚያስነሳ ስለተገነዘቡ በውስጥ እና በውጭ አካሄዱን መከታተል ተያያዙት ፤ አንድ ነገር ርግጠኛ ሆኜ መናገር የምችለው ማህበሩ የሚያወጣቸው መጽሄቶች ፤ ጋዜጦች ፤ ሲዲዎች እና የድረ-ገጽ ጽሁፎች ከመንግስት ሰዎች አምልጦ አያውቅም(ተጠንቅቆ መስራ ግድ ነው) ፤ የፈለጉበት ቢሮ ቢገቡ ህትመቶቹን አያጧቸውም ፤ የሚጽፉቸው መንፈሳዊ ጽሁፎች ሁላ የሚታዩበት መነጽር ለየት ያለ ነው ፡፡

ባለፈው ዓመት በአቡነ ሳሙኤል የተጻፈው ‹‹እውን የሀይማኖት መቻቻል አለን? ›› የሚል ባሳተሙት መጽሀፍ እውታውን ስላወጡ መንግስት በፊት ለፊትም ሆነ በቤተክህነቱና በአቡነ ጳውሎስ  በኩል ያሳደረባቸው እና እያሳደረባቸው ያለው ተጽህኖ ማየት ብቻ በቂ ነው ፤ አቡነ ጳውሎስንም እተቀየሟቸው ወደው አይደለም ባይሆን ጸልዩላቸው ፡፡ በተጨማሪ በርካታ ኦርቶዶክሳውያን በጅማ ሲጨፈጨፉ ሁኔታው በሲዲ እንዳይወጣ ክርስትያኑ በአግባቡ እንዳያውቀው ፤ ተደባብሶ እንዲያልፍ መንግስት በሰዎች እና ማህበሩን በመሰሉ ማህበራት ላይ ያሳደረውን ተጽህኖ ማየት ብቻ በቂ ነው ፤ እኛ እኮ ሰው እንግደል አላልንም ፤ ባይሆን የተደረገውን ነገር ለህዝበ ክርስትያኑ ይወቀው ነው የተባለው ፤ በጊዜው የ6ወር ህጻን የእናትበጡት ያልጨረሰ ልጅን ትታ የተሰዋች እናት ነበረች ፤ ከዓመት በኋላ ልጁን አንድ መነኩሴ ጋር አግኝቼው ታሪኩን ነግረውኝ እጁን ስጨብጠው ሰውነቱ ውስጥ አጥንት ያለ አይመስልም ነበር ፤ ስጨብጠው የተሰማኝን ስሜት ለእናንተ በቃላት መግለጽ አልችልም ፤ የእናት ጡት በአግባቡ ስላላገኝ ፤ እናቱም ስለሞተችበት እጅጉን ምግብ እንዳስቸገራቸው በጊዜው ካገኝኋው አባት ማወቅ ቻልኩኝ ፤ በጣም አዘንኩኝ ፤ ግን የመፍትሄ ሰው ባለመሆኔም በራሴም ክፉኛ አዘንኩኝ ፤ በጊዜው ይህን ችግር ህዝቡ እንዳያውቀው መንግስት እንቅፋት ሆኖ ተነሳ ፤ ፖለቲካው ላይ ችግር እንደሚያመጣ ይታወቃል ፤ ነገር ግን እውነት ስለሆነ ‹‹ሰው ማውቅ አለበት የመፍትሄም አካል መሆን አለበት›› የሚል የከረረ የግል አቋም ነበረኝ፡፡ የሞቱትን መመለስ ባይቻል እንኳን ነገ ይህን መሰል አደጋ እንዳይከሰት ማድረግ በተቻለ ነበር ፡፡ 

የ97 ምርጫ ላይ ልክ እንደ አንድ ነጥብ የተያዘበት በጊዜው ማህበሩ 13 ዓመት ሙሉ በርካታ ሰዎች  በእምነት እንዲኖሩ ከሰንበት ትምህርት ቤት አንስቶ እስከ ዩኒቨርሲቲ ተቋማት  ያለው ኔትወርክ ከላይ አንስቶ እስከ ወረዳ ደረጃ ድረስ ሰፊ ግንኙነት መኖሩ መረጃዎችንም በቀላሉ ይወርዳሉ ብለው በማሰባቸው በተለየ አይን እንዲታይ አድርጎታል ፤ መንግስት በ14 ዓመት ውስጥ በሀገሪቱ ላይ ሊሰራ ያልቻለውን ስራ ማህበሩ በጥቂት ጊዜያት መስራት ችሎ መታየቱ ለእነርሱ ጥሩ አጋጣሚ አልነበረም ፤መንግስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች(ቅንጅት ነፍስ ይማር) ‹‹ማህበረ ቅዱሳን›› የዘረጋውን ኔትወርክ ለአላማቸው ማስፈጸሚያ ተጠቅመውበታል የሚል አቋም ነበረው ፤ ይህ ግን የፖለቲከኞቹ  የተሳሳተ ግምት እንጂ እውነታው የመንግስት አቅም ማነስና ህዝብን ያለማድመጥ መሰረታዊ ችግር ነበር  ፤ በጊዜው በየመድረኩ ያጨበጨበ ሁላ ደጋፊ መስሏው ነበር ፤

ምርጫው አልፎ ነገሮች ወደ መስመራቸው ከተመለሱ ከዓመታት በኋላ የመንግስት ባለስልጣን አቶ አቦይ ስብሀት በማን አለብኝነት በነጋድረስ ጋዜጣ እና በተለያዩ መጽሄቶች ላይ ‹‹የኦርቶዶክስ ጳጳሳቱ አይረቡም ›› ‹‹ማህበረ ቅዱሳን የቤተክህበት እዳ ነው›› በማለት በፊት የቋጠሯትን ቂም ግልጽ አድርገው በሚዲያ ተናግረዋል ፤ እኔ እንደ አንድ አማኝ በጊዜው በጣም ተናድጄ ነበር ፤ በመሰረቱ አይደለም አቦይ ስብሀት ጠቅላይ ሚኒስትሩም ቢሆኑ ያለ አግባብ አይደለም አንድን ትልቅ ማህበር ያለመረጃ ይቅርና ግለሰብን የመናገር መብት የላቸውም (ይህ በእኛ ሀገር ደረጃ አይደለም) ፤ ነገር ግን ሙልጭ አድርገው የሺዎችን ማህበር የማይገባውን ስም በመስጠት ሲናገሩ ማንም እረፉ ያላቸው ሰው አልነበረም ፤ እኛም ባለስልጣን ለመቃወም የሚበቃ ወኔ አልነበረንም አሁን የለንም ፤ ይባስ ተብሎ ሰው ዘንድ እንዲደርስ ምዕመኑ ለማህበሩ መልካም አመለካከቱ እንዲቀየር የስትራቴጂ ስራ በመስራት ሰው አንቅሮ እንዲተፋው ያልተሳካ ስራ አከናውነዋል ፤ ግን አልተሳካላቸውም ፤ በዚች አጋጣሚ ‹‹ደጀ-ሰላም›› በጊዜው የጻፈውን ጽሁፍ ሳላደንቅ አላልፍም ፤ አቦይ ስብሀት ማለት የወረደ ብቻ ሳይሆን የዘቀጠ አመለካከት ያላቸው ሰው መሆናቸውን ‹‹የጋዜጠኛው ማስታወሻ›› ጸሀፊ ተስፋዬ ገ/አብ ነግሮናል ፡፡

ሰውየው ጤነኛ ናቸው ብሎ መናገር ይከብዳል ፤ እኔ በበኩሌ አህያ ቢፈሳ አፍንጫ አይያዝም ብዬ አልፌዋለሁኝ ፤ ከአመታት በፊት ኤርትራ ከተገነጠለች በኋላ ኢህአዴግ ግንቦት 20ን ሲያከብር ሰውየው ሁለት ልጆቻቸውን ‹‹ነጻ ኤርትራ›› ‹‹FREE ERITREA›› የሚል ጽሁፍ ጽፈው መስቀል አደባባይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ባሉበት ቲሸርት አስለብሰው መድረክ ላይ ያወጡ ሰው ናቸው ፡፡ ይህ ጤነኝነት ነው ይላሉ ? ይህ ነገር ሀገር መናቅ ነው? ህዝብ መናቅ ነው ? ወይስ ምንድነው ? ስለዚህ ይህን ነገር ያደረገ ሰው ስለ ‹‹ማህበረ ቅዱሳን›› አፉን ቢከፍት ለኔ ምኔም አይደለም ፤ እንዴትስ አድርገን ልናምን እንችላለን ፤ በማህበረሰቡ ዘንድ ተሰሚነት ያለው ሰው ፤ ስብእናው ኢትዮጵያዊነት የተላበሰ ፤ አንቱ ሊባል የሚችል ሰው ቢሆን ኖሮ በርካቶች በተሰናከሉ ነበር ፤ ግን አይደለም ፡፡ ይችን ክፍተት በመጠቀም ተሀድሶያውያኑ የአቦይ ስብሀትን ቃል ለመጽሀፍ አርዕስት አድርገው የዲ/ን ዳንኤል ክብረትን 20 ገጽ ማህበሩ ላይ የጻፈውን ወቀሳ አንድ ላይ በማድረግ መጽሀፍ መጻፋቸውን እናስታውሳለን ፤ የመጽሀፉ ስም ‹‹ማህበረ ቅዱሳን የቤተክህነት እዳ›› የሚል ነበር ፤ ጠላትም አንዳንዴ ጥሩ ነው ምን ያህል እንደተኛን ያመላክተናል ፤ ምን ያህል መስራ እንዳለብንም ትምህርት ይሰጠናል ፤ በጣም የሚገርመው ነገር መጽሀፉን እኔ ለራሴ ‹‹ደሞ ምን አሉ›› በማለት ምን እንደተጻፈ ለማወቅ ገዝቼው ነበር ፤ ከዚያ በኋላ ግን ይህን መጽሀፍ እንደ አቶ በጋሻው ደሳለኝ ሲዲ ቅዳሜ ቅዳሜ ሙሉ ወንጌሎች በር ላይ ሲሸጥ ነበር ፤ በርካታ መናፍቃንና ተሀድሶያውያን መጽሀፉን በእጃቸው ላይ መመልከት ችዬ ነበር ፤ አስቲ አስቡት ሰዎች ምን ያህል ጊዜያቸውን ወስደው ማህበሩን ለማጥፋት ምን ያህል ርቀት እንደሚጓዙ ? ለምንስ መጽሀፉ ሙሉ ወንጌላውያን እና መሰል ተመሳሳይ መናፍቃን ሊገዙትና ሊያነቡት ቻሉ ? የኛ ጉዳይ ለነሱ ምናቸው ነው ? ለኔም የገረመኝ ነገር ነው፡፡ እነርሱ ይህን ካደረጉ እኔም ለምን እንደሚያነቡ ማወቅ አለብኝ የማለት ሀሳብ ውስጤ አደረብኝ ፡፡

ይህን ነገር ለምን እንዳደረጉ ለማወቅ ሰዎች ጋር ቀርቤ እነሱን መስዬ ለማነጋገር ሞክሬ ነበር ፤ እነርሱ እኛን መስለው እንደተጠጉን እኔስ እነርሱን መስዬ አልጠጋቸውም ? ይህን ስራ ስሰራ ያወኩት ሰው እኔም የነርሱ ዘመድ መናፍቅ መስዬው የሚያውቀውን ነገር እንዲህ አለኝ  ፤ ‹‹እነርሱ አያውቁትም እንጂ በመቶዎች የሚቆጠሩ  የማያውቋቸው ሰዎች መሀላቸው አሉ ሲለኝ›› ልቤ ደው ድው እያለ ይመታ ነበር ፤ እነርሱ የተባልነው እኛ ‹‹ኦርቶዶክሳውያን›› ነን ፤ እኛ ዛሬ ላይ ተነስተን ‹‹አሰግድ ሳህሉ›› መናፍቅ ነው ስንል መረጃዎቻችሁን አቅርቡ ይባላል ፤ መረጃችንን ስናቀርብ ሌላ ነገር ይላሉ ፤ እነዚህ ሰዎች ተሀድሶ ናቸው ስንል ሌላ ነገር ይሉናል ፤ እኛ የማናውቃቸው በጣም ብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ መናፍቃን ቤተክርስትያኒቱን ለማፍረስ ከሚገነቧት ጋር አብረው ቆመዋል ፤ እኛ ስለምናውቃቸው ሰዎች ብቻ እንከራከራለን እኛ የማናውቃቸውን እርሱ አንድ አምላክ ስለ ‹‹አንዲት እምነታችን›› እና ስለ ‹‹አንዲት ቤተክርስትያን›› ብሎ ክፉ ስራቸውን ይያዝልን ፡፡ እውነቱን ነው እኛ አናውቃቸውም እንጂ እነርሱ ግን ያውቁናል ፤ እስኪ ስንት ድረ-ገጽ ከፍተው እንደሚሰሩ ተመልከቷቸው ? የኛ ከምንለው እና ከምናነበው ድረ-ገጽ የነርሱ ብሎግ እና ድረ-ገጽ ይበልጣል እኮ ፤ ብዙዎቹ ያልጠነከሩት በነርሱ ስራ ማንን እንመን በማለት ላይ ይገኛል ፤ ፍሬውን ከእንክርዳዱ ምዕመኑ እንዳይለይ የራሳቸውንም ሆነ ቤተክርስትያኒቱን የሚወክሉትን ድረ-ገጾች እውነተኛ ለመባል ሊንክ ፈጥረው አስቀምጠውናል ፤ የእኛን አድራሻ ‹‹አባ ሰላማ›› የሚባለው ገጽ ላይ በማየታችን በጣም ተገርመናል ፤ እኛ ከእነርሱ ጋር አንድ የሚያደርገን ምንም አላማ አንድነት የለንም ፤ እነርሱ ግን በመመሳሰል ስለሚያስወጧቸው ነፍሳት በማሰብ ይህን ሊያደርጉ ችለዋል ፤ ቤተክርስትያኒቱን ትተው ለምን ‹‹ማህበረ ቅዱሳን›› ላይ ብቻ እጃቸውን ይጠቁማሉ ? ‹‹ማህበሩ ከተበተነ ሌላው ገለባ ነው›› በማለት የሚሰሩ ይመስለኛል ፤ ደግሞም እውነት ነው ፤ አሁን ምዕመኑ በማህበሩ ስር በአንድ ላይ ሆኖ ባይቆም ኖሮ ምን ሊከሰት እንደሚችል አስበውት ያውቃሉ ? የህ ነገር ብዙ ያስብላል ስለዚህ ወደ ቀደመ ነገሬ ልመለስ..

የአቦይ ስብሀት አነጋገር ሲገርመን ፤ ባለፈው ሳምንት ደግሞ አቶ መለስ ኦርቶዶክሳዊ  አክራሪ የሚል ትርጉም ያለው ነገር መናገራቸው በጣም አስገርሞናልም ፤ እና ንግግራቸውን ተቃውመን ሰዎች ሰምተው እንዲቃወሙ በር ከፍተናል ፤ ስለዚህ መንግስት ለማህሩ ጥሩ ነገር የለውም ፤ ቢኖረውም ባይኖረውም እና ምንም መስሎ አይታንም ፤ ቤተክርስትያን ላይ የሚደረገውን ጥሩ ያልሆነ የማይጠቅምና የፖለቲካ ትርፍን መሰረት ያደረገን ነገር  ከመቃወም ግን ወደ ኋላ አንልም፡፡

እኛ ‹‹አንድ ሀይማኖት አንዲት ሀገር›› ብለን እናውቃለን?           

እኛ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች   ‹‹አንድ ሀይማኖት አንዲት ሀገር ብለን እናውቃለን?›› አይመስለኝም ፤ ቤተክርስትያንም ‹‹ይህችን ሀገር ክርስትያን ብቻ ይኑርባት›› ብላ አታስተምርም ፤ በዚች  ነገር ሌላ ጥቅም ለማግኝት የማጠጋጋት ስራ የተሰራ ይመስለናል ፤ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፤5 ‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤›› ነው የሚለው የወንጌሉን ቃል  የጥምቀት ወጣቶችም ይህን ነው የለበሱት ፤ መንግስት ህገ መንግስቱን ተጋፋ የሚለው ‹‹አንዲት እምነት›› የሚለው ነገር ነው ፤ ‹‹እንዴት ከ80 በላይ ብሔር ያለባት ኢትዮጵያ እና በርካታ የእምነት ተቋማት ያላት ሀገር ላይ የኦርቶዶክስ  እምነት ተከታዮች ይህን ነገር ያራምዳሉ ››የሚል ሀሳብ ነው ያለው፤ መንግስታችን ስለ ለብሔር ብሄረሰብ ነጻነት የቆመ ስለሆነ ይህ ነገር አይዋጥለትም(አታስቁኝ ልጻፍበት..ቂቂ) ፤ ህገ-መንግስቱ መግቢያ ላይ ‹‹ የግለሰብና የብሔር ብሔረሰብ መሰረታዊ መብቶች መከበራቸው ፤  ኃይማኖቶች ካለአንዳች ልዩነት እንዲራመዱ የማድረግ አስፈላጊነት ጽኑ እምነታችን ነው…›› በማለት ይዘረዝራል   

ይህንም የቲሸርት ጽሁፍ ማህበሩ የሚሰራው መስሎ ይታየዋል ፤ ግን እንደ እኛ እምነት አንዲት ንጽህት እምነት‹‹ኦርቶዶክስ ተዋህዶ›› መሆኗን ከመናገር ወደ ኋላ አንልም ፤ እንደ እኔ እንደ እኔ ይህ አቋማችን ይሆናል ሌሎችን ብስጭት ውስጥ ከቷቸው ጥያቄ እንዲያቀርቡ የሚያደርጓቸው ፤ እና እኛ ምን እናድርግ ፤ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለን የወንጌሉን ቃል አንቀይር ፤ የአምላክን ቃል አናጥፍ ፤ የማይዋጥ እውነት ቢመስላቸውም ይዋጡት ፤ ይህ የጥምቀት በዓል በርካታ ነገሮችን አሳይቶናል ፤ ታቦታቱ በየአካባቢያቸው የጥምቀትን በዓል ያክብሩ በማለት ጃልሜዳ የሚሰበሰበውን ምዕመን የመከፋፈል ስራ ለመስራት ታስቦ ነበር(ካላወቁት) ፤ ይህም ‹‹ለጸጥታ ሲባል›› በሚል ምክንያት ተቀምጦለት ነበር ፤ እንደ ሰው ሀሳብ ሳይሆን እንደ አምላካችን ፍቃድ እስከ አሁን ጃልሜዳ እያከበርን እንገኛለን ፤ ከሁለት ዓመት በፊት በጎንደር ካርኒቫል የሚባል ነገር ከጥምቀት በዓል ጋር አስታከው ገቢ ማሰባሰቢያ በማድረግ የበዓሉን ይዘት ላይ ቀጥተኛ ተጽህኖ ከመፍጠራቸው በላይም ታቦታቱ ከጥር 4 አንስተው ቀስ እያሉ ቢወጡ የሚልም ሀሳብ ላይ ተወያይተው ነበር ፤ በጊዜው ተቃውሞ የበዛበት የጎንደር ባህልና ቱሪዝም ሁኔታው እንዳልተፈጠረ ስብሰባ በማድረግ ኦፊሺያል የሆነ ደብዳቤ ለ‹‹አንድ አድርገን›› ብሎግ ልኳል ፡፡ እኛ ይህን ደብዳቤ  የተመለከትነው የጻፍነው ጽሁፍ በርካቶች ጋር ደርሶ በአካል ሄደው ጥያቄ ማቅረባቸውንና ውጤትም ማምጣቱን ጭምር ነው ፤ የእኛም መነሻ ግባችን ምዕመኑ ለችግሮች መፍትሄ እንዲሆን መረጃዎችን በጊዜ ማቅረብ ነው ፤ ሌላ አንዳች ነገር ከበስተጀርባችን አለመኖሩን በአምላካችን ስም እንምላለን ፤ የጥምቀት ነገር ከተነሳ ስለማያልቅ ስለሆነ ልተወው…



‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤›› የሚለውን የወንጌል ቃል ህገ መንግስቱን ስለሚጋፋ ብቻ እናንተን ደስ እንዲላችሁ መቀየር አንችልም ፤ የጌታችን ቃል የሚታጠፍ አይደለም ፡፡ ይህን ነገር ሲያስረግጥልን ‹‹ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም።›› የማርቆስ ወንጌል 13፤31 ታዲያ እኛን ምን አድርጉ ትሉናላችሁ ? በመጽሀፍ ቅዱስ አትመኑ ማለት አንድ ነገር ነው ፡፡ በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ይህን ነገር የሚያራምዱ ወጣቶች ህገ መንግስቱ ያልገባቸው በትምህርት የሚመለሱ ናቸው›› ብለዋል ፤ እኛ ግን ያልገባዎት እርስዎ ኖት ባዮች ነን ፤ ወጣቶቹ ህገመንግስቱ ባይገባቸው ወንጌሌ ግን ገብቷቸው ታቦታቱን ለማጀብ በረከትም ለማግኝት ‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤›› የሚል ቲሸርት ለብሰው ሊታዩ ችለዋል ፤ ይባስ ብለው ‹‹ይህ አክራሪነት በእንጭጩ ሊቀጭ ይገባዋል ፤ ይህ አመለካከት አፈር መብላት አለበት›› በማለትም አክለዋል ፤ ምኑ ነው አክራሪነት ? እስከ አሁን እኛ ነን ከአፈር ተፈጥረን ወደ አፈር የምንመለስ ሰዎች ነን፤  የአምላካችን ቃል ግን እርስዎ እንደሚያስቡት አይደለም ፤ አመለካከቱም በፍጹም አፈር አይለብስም ፤ ቀድሞ ማን አፈር እንደሚለብስ እናያለን ፤ ቃሉ ከ2000 ዓመት በላይ አሳለፈ ፡፡ አሁንም እርስዎ ያልተዋጠልዎን የወንጌል ቃል ‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤›› ፤ ጌታ ያልነው ‹‹ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፤ አንዲት እምነት ያልናት እኛ የምንገኝባትበ ‹‹ኦርቶዶክስ ተዋህዶ›› ፤ አንዲት ጥምቀት ያልናት ደግሞ ‹‹እኛም እናንተም በ40 በ80 የተጠመቅናት ፤ የስላሴ ልጅነትን ያገኝንባት ጥምቀት›› ናት ….. ሌላ ምንም የምለው የለኝም.. ከተሳሳትኩኝ ለመታረም ዝግጁ ነኝ፡፡



ባለፈው ወር አንድ ሙስሊም ‹‹መጅሊስ አይወክለኝም›› የሚል መልእክት ያለው ጽሁፍ አድርጎ ፖሊስ ይዞ አዲስ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ ነበር ያስገባው ፤ ወዲያው ከ20 የሚበልጡ ወጣቶች አንድ አይነት ተሸርት ለብሰው እኛንም እሰሩን ‹‹መጅሊስ አይወክለኝም›› ሲሏቸው ፖሊሶች የታሰረውን ወጣት ሊፈቱ ችለዋል ፤ ይህ ወጣትም አክራሪ ተብሏል ፤ ይህ ግን ለነገሮች ካለን የተዛባ አመለካከት እንጂ በሌላ አይደለም ፤ ሙስሊም ወንድሞቻችን ሁሉ አክራሪ አይደሉም ፤ የነሱን ጥያቄ ህገ - መንግስቱን መሰረት ተደርጎ ቢመለስላቸው ህዝቡም ባልተነሳሳ ነበር ፤ ለጥያቄዎች በአግባቡ መሰረታዊ የሆነ መልስ መስጠት ሲያቅተው አማኙ ላይ ደስ ያለውን ስም መለጠፍ አግባብ አይደለም ፤

የጥምቀት ወጣቶች በለበሱት ቲሸርት በፓርላማ ላይ እንዴት ‹‹ይህ አክራሪነት በእንጭጩ ካልተቀጨ ብለው ›› አስተያየት ይሰጣሉ ፤ የሚገርመው ነገር ግን ይባስ የእምነቱ ተከታይ ለእምነቱ ያለው አመለካከት እንዲጨምር ያደርገዋል ፤ ይህ ደግሞ ለኛ መልካም ነው ፤ ካለ ልፋት ሀይማኖቴን እንዲል እየገፋችሁት ነው ፤ የሚፈለገውም ይሄ ነው ፤ ይህ ሲገርመን አቡነ ጳውሎስ እና ሌሎች የሀይማኖት አባቶቻችን ቁጭ ብለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲናገሩ ሰምተው ሲያበቁ መውጣት መቻላቸው ነው ፡፡

እኔ ጃንሜዳ  ለበርካታ ጊዜያት በዓል አክብሬአለሁ ፤ አንድም ጊዜ ወጣቶች ከመጽሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ውጪ ስጋዊ ፍላጎታቸውን መሰረት አድርገው ሌላውን የእምነት ተከታይ ለማናደድ ሲባል ጥቅስ ሲጽፉ አላየሁም ፤ እኔ በበኩሌ ያልሆነ ነገር ከስርአተ ቤተክርስትያን ውጪ ብመለከት ማንም ይሁን ማን የመጀመሪያ ተቃዋሚ ነኝ ፤  ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲናገሩ ሁሉንም የሚመለከት ጉዳይ ለማድረግ በመሞከር ከአንዳንድ ሙስሊሞች ጋር የሚያያዘውን ‹‹አክራሪነት›› ወደ እኛ በመግፋት ሚዛናዊ ዘገባ ላቅረብ በማሰብ ይመስለኛል፡፡

ብሎጋችን አሁንም እንደተቆለፈ ነው ፤ ብዙ የመናፍቃን ብሎግ በሚሰራበት ሰዓት የኛ በመዘጋቱ ምንም አይመስለንም ፤ ለዚያውም የምንጽፈው ጽሁፍ የምንልከው መረጃ ለማዘጋት የሚያደርስ ከሆነም መልካም ነው ብለናል ፤ ጠላት ያበረታል ፤ ጠላት የበለጠ እንድንሰራ እንድንጠነክር ያደርጋል ፤በ8ወር እድሜያችን ከ800 ሺህ በላይ ጊዜ ሰዎች ጎብኝተውናል  ፤ ይህ ለኛ ሽልማታችን ነው ፤  እኛ ግን በቀጥታ አንባቢዎቻችን ብሎጉን የሚያነቡበትን የተለያዩ ድረ-ገጾችንና ፌስ ቡክን በመጠቀም መረጃዎችን በሁሉም አቅጣጫ እንደ ውሀ እንዲፈሱ እናደርጋለን ፤ አስፈላጊ ከሆነም ባለን እውቀት የራሳችንን unblock web sites በመስራት መረጃዎችን በተቻለን መጠን ተደራሽ እናደርጋለን ፡፡  

ይህ የአንድ ሰው ጽኁፍ ነው ፤ የማንም  አቋም አይደለም

(ሌላውን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሀሳብ ሌላ ጊዜ ልመለስበት ፤ እስኪ ደግመው የአቶ መለስን ቃል ያድምጡት)

ቸር ሰንብቱ


33 comments:

  1. Akafan akafa malet endih new.....

    ReplyDelete
  2. በጣም ደስ የሚል ሀሳብ ነው፤ሚዛናዊ የሆነ ደስ ብሎኛል፡፡

    ReplyDelete
  3. thanks. i will promise you God is with you.
    let God be the strength to all of us

    ReplyDelete
  4. May God bless u , It is great article , eye opener message, God bless u Andadrgen

    ReplyDelete
  5. በጣም ደስ የሚል ሀሳብ ነው፤ሚዛናዊ የሆነ ደስ ብሎኛል፡፡

    ReplyDelete
  6. A good article but in some places u are speaking for MK. Mk could speak for it self.If this is a personal view, why do u prefer to hide your name? why don't you write like Dn. Ephrem? The phrase "ይህ የአንድ ሰው ጽኁፍ ነው ፤ የማንም አቋም አይደለም" wasn't enough. Isn't this the stand of Andadrigen? Only your views should have been reflected in the article. Your article is an eye opener to conclude that andadirgen belongs to mk.

    ReplyDelete
    Replies
    1. kesemu men alneegna khasbu enje

      Delete
    2. Why do you need his/her name? If you need hisher name, it is 'Andadirgen'. That is all. Yes, s/he stated Mahibre kidusan because Prim Minister Meles talked about Mahibere Kidusan. Andadirgen also wrote his/her feelings about Mahibere Kidusan. What is the importance of knowing his/her name? This is his/her opinion and of course we all share the opinion. If you have objection for any of the points stated in this article, just point-out it. Then we can discuss it.

      To andadirgen, please don't disclose your name, we don't want it as far as your are writing the truth.

      Hailemariam

      Delete
    3. why do u want to know his name ? u will never find him.
      what u need is the info.That is all !! i think u r the one who is assigned by EPDRF to find his name.kkkkkkkkkkkkkkkkkk
      u better search door to door hahahah to find him.
      we will hack gov't webs soon.u will c.


      good job andadergen!

      Delete
  7. beravo ande aderegen ..gen ande neger lengerachu negegerachew lemaheberu agelegelote ymawelewen gize betefe endechemere ..letewahedo yalegnen fekere ..yalewesen enechemere eyadergugne selhone amesgenu legn.....

    ReplyDelete
  8. I still can access this site,,I use ultrasurf to unblock it...anyone can download and use it..

    ReplyDelete
  9. emeberah edmana tsgawen tabezalhe ...long live to ORTHODOX!!!!!

    ReplyDelete
  10. በጣም ደስ የሚል ሀሳብ ነው፤ሚዛናዊ የሆነ ደስ ብሎኛል፡፡

    ReplyDelete
  11. For me the only reason the govt could hate MK is its involvement in politics. It is good for MK to stay away from Politics and carry on its spiritual activity.

    ReplyDelete
    Replies
    1. ከዚህ በላይ ያለውን አስተያየት የጻፍከው/ሽው ሰው ደግነቱ ይሄ የግል አስተያየትህ/ሽ ነው፡፡ ሆኖም ግን ከህሉም በፊት ፖለቲካ ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን ጥያቄ ለራስህ/ሽ ከጠየቅህ/ሽ በኋላ መልሱን በትክክሉ መመለስ ከቻልክ ሌላውንም ማሳመን የምትችል ይመስለኛል፡፡ አለበለዚያ ግን የመንግስት ግልባጭ መሆን ነው የሚተርፈው፡፡

      Delete
    2. ዓይንህ በጨለማ ታወሯልና በመጀመሪያ ብርሀንን ፈልግ ወንድሜ። ከሳጥናኤል አገልጋዮች አንዱ ሳትሆን አትቀርም ወይም ነህ። እ/ር አምላክ የምታስተውል ልቦና ይስጥህ!!

      Delete
  12. Shame on you how do you dare to say... ‹‹ማህበሩ ከተበተነ ሌላው ገለባ ነው›› በማለት የሚሰሩ ይመስለኛል ፤ ደግሞም እውነት ነው....This shows how much you guys think that you are the only son of the church....It is not due to the MK the church have survived thousands of years....the church has millions of believers who are not inferior than the MK members by any standard...

    ReplyDelete
    Replies
    1. ምን እያልክ ነው??????..ጳጳሱ ነው...ቤ.ክያንን እየጠበቀ ያለው...በዘመናችን ቤ.ክያንን ከአውሬዎች እየጠበቃት ያለው MK መሆኑን አትርሳ!!!!!!!!!!!!

      Delete
    2. ከዚህ በላይ ያለው አስተያየት ተገቢ ነው፡፡ እኔም ምንም እንኳን ለረጅም ጊዜ የማህበሩ አባል ብሆንም በዚህ ሃሳብ አልስማማም፡፡ ምክንያቱም የማህበረ ቅዱሳን አባል መሆን የቤተክርስቲያን ልጅ ከመሆን የተገኘ እንጂ የቤተክርስቲያን ልጅነት የማህበረ ቅዱሳን አባል በመሆን የሚገኝ አይደለም እንደአረፍተ ነገሩ፡፡ ይህ የማህበሩ እምነትም ሆነ አቋም አይደለም፡፡ የዚህ ጽሁፍ ጸሃፊም የማህበረ ቅዱሳን አባል እንዳልሆነ በዚህ ማወቅ ይቻላል፡፡ የማህበሩ ስም ያለአግባብ መነሳቱ ያሳዘነው ሰው የጻፈው ይመስለኛል፡፡ ማስተዋሉን ይስጠን!!!

      Delete
    3. can you mention one or two? talking is very easy..

      Delete
    4. Henock it seems that you are in deep love with MK when you say...በዘመናችን ቤ.ክያንን ከአውሬዎች እየጠበቃት ያለው MK መሆኑን አትርሳ...'....God is the only guard of the church.....the church has passed through various temptations over the last thousehdans of years only due to God...while Mk is excited only for less than two decades...dont be fool yourself bro...rely only on God not on human beings...

      Delete
    5. 100% write. wrog mk attitude

      Delete
  13. ortodox hulum endetetafa yefalegalu gen fesum atetafam begeta deme yekorakorache ant ande getahoye hayemanotachenen tabekelen kewset honew selam yeminesuwaten endearam nekelelat argen MGBU

    ReplyDelete
  14. I promise to send your artilce at least to 10 of my friends in living in Addis and other parts of the region by email/Facebook or hard copy. If all of us can do like that, we can make a difference.

    Zed the Sheger

    ReplyDelete
  15. ለወንድሜ' ኤፍሬም:

    ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቃሉ!!!!!!!!!

    በመጀመሪያ ደረጃ ባሕር ማዶ በሞቀ ኑሮ ላይ ሁነህ እዚህ አገር ቤት ባለነው የሁሉም ችግር ገፈት ቀማሾች ብቻ ሳንሆን ጭልጥ አድርገን ጠጪዎች ላይ የስንፍና አንደበትህን ባትከፍት መልካም ይሆን ነበር:: የለም የመጻፍና የመናገር ሱስ አለብኝና ዝም ማለት ፈጽሞ አልችልም ያገሬና የቤተ ክርስቲያኔ ጉዳይ ያገባኛል ያንገበግበኛል ለማለት ከሆነ ግን 'ያልተነካ ግልግል ...ነውና' ዝም ብትልና የሚሆነውን ብትመለከት ወይም እንደገባው እውነተኛ የጌታ ተከታይ ብትጸልይ ይሻልህ ነበር:: ተርፈህ ታተርፋለህና::

    አዎ! በውጭ ሆነው ወይም በዳር ቆመው እርስበርሳችንን ሊያዋጉን የሚፈልጉ የአፍ ጀግኖች ሞልተውናል:: ታሪካችን ይህን በመሰሉ የድል አጥቢያ ባንዳ አርበኞች የተሞላ መሆኑን ያለፈው ተመክሯችን (በጣሊያን ጊዜ ሳይቀር) በሚገባ አስተምሮናልና ለአሁኑዎቹ አንተን መሰል ዳር ቋሚ እሳት ጫሪዎችና ለአንተ ለራስህ ግን ይህ ዓይነቱ አካሄድ አያዋጣችሁም ለአራችንና ለቤተ ክርስቲያናችንም አይጠቅምምና ዝም በሉ ወይም በል የሚል ምክሬን እለግስሃለሁ::

    ከዚህ በተረፈ ማን ምን እየሠራ ነው? ዓላማውስ ምንድነው? ወዘተ ለሚሉት በርካታ ጥያቄዎች መልስ ግን እንኳን አገርን እመራለሁ ለሚል መንግሥት ይቅርና ለእኛ በአገሪቱ ውስጥ የሚሆነውንና እየሆነብን ያለውን ለምናይ ኗሪ ምስክሮች ብቻ ሳይሆን ለእናንተም (በዓላማችሁ ታውራችሁ እንጂ) የተሰወረ አይደለም::

    ስለዚህ እባካህ 'ወንድሜ' ኤፍሬም ከመሰል የግብር ወንድሞችህ ጋር የሚያስተውል ልብ ይኑራችሁና ለአገርና ለቤተክርስቲያን የሚጠቅም አስቡ ተነስታችሁም ፍሬ ያለውና የሚታይ ሥራ ለመሥራት ሞክሩ:: በተጋለጠ የማንነት ሥራችሁ ላይ እንደገና የማይመስልና የማይታመን ነገር በመጻፍ ደግማችሁ ደግማችሁ ሕዝብ ለማታለል አትሞክሩ ወይም ከተቻላችሁ ሌላ የማታለያ ስልት ቀይሱ:: ለእንደዚህ ያለ በሬ ወለድ ነገር ብርቱዎች ናችሁና::

    'እውነት ትመነምናለች እንጂ አትበጠስም' እንዲሉ ስለ ማህበረ ቅዱሳንና ስለተሃድሶ ማንነት ለማዎቅ የሁለታችሁም የሥራ ፍሬ እየገለጣችሁ ስለሆነ ሚዛኑን በዚች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመሆን ወደ ሰማይ ለምናነባ የቤተ ክርስቲያኒቷ ምእመን ተውት:: እንባን የሚያብስ የጌታ ቀን መገለጫው ቀርቧልና::

    'አመጸኛው ወደ ፊት ያምጽ ርኩሱም ወደ ፊት ይርከስ
    ጻድቁም ወደ ፊት ጽድቅ ያድርግ ቅዱሱም ወደ ፊት
    ይቀደስ አለ::' (የዮሐንስ ራእይ 22:11)

    የሞጣው ጊዮርጊስ የቆሎ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ በመላው ያገራችን አድባራትና ገዳማት ውስጥ 'በማህበረ ቅዱሳን' (ዲያቆን ሙሉጌታ ግብራቸውን ተመርኩዞ ያወጣላቸውና ለመጽሐፉ የሰጠው ማሀበረ ሰይጣን የሚለው ስም ይስማማኛል) የፈሰሰውና እየፈሰሰ ያለው የንጹህ ወገኖቻችን ደም አሁንም ሁሉን ቻይ ወደ ሆነው አምላካችን በመጮህ ይጣራልና ወዮ! ወዮ!! ወዮ!!! ለኤፍሬምና ለመሰሎቹ::

    እግዚአብሔር አገራችንና ቤተ ክርስቲያናችንን በመካከላችን ከሚገኙ ተናካሺ ውሾች ይጠብቅ!!!! አሜን::

    ሰላም ለሁላችን ይሁን!!

    በዚህ ጉዳይ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር የዘወትር ሙግት ያለኝ እና የሁሉንም ወገኖቼን እውነተኛ ሰማያዊ ፈውስ የምሻ እህታችሁ

    ReplyDelete
    Replies
    1. የኔ እህት በጽሁፍ ለአንባቢ ግንዛቤ እየሰጡ መታገል ላንቺ ሥራ ፈትነት ነው?! የጦር መሣሪያ መሸከም ነው ላንቺ ትግል ማለት? ሰው በተሰጠው ጸጋ የትም ሆኖ ሊታገል ይችላል እነ በአሉ ግርማን የመሳሰሉ ጸሓፊዎችን ደርግ ከዓይኑ ያራቃቸው ስለ ጻፉ ነው ዛሬም ወያኔ ጋዜጠኞችን የሚያስረው ዝም ብለው ቁጭ ስላሉ አይደለም ጽሁፍ ያነቃል ያበረታል ዝም ብሎ ተቀምጦ የሚሆነውን ማየት ማለት እዛው አንቺን ለመሳሰሉ ለወያኔ ካድሬዎች ካልሆነ እንጂ ህሊና ላለው አያስችልም

      Delete
    2. የኛ ጻድቅ አንቺ ማነሽ ማንነትሽ ገና ከአነጋገርሽ ይታወቃል። ይሄ ከወጭ ሆናችሁ በሞቀ ምናምን የምትይው ነገር ፥ አንቺ የበግ ለምድ ለባሽ ማነን ለማታለል ነው። በናትሽ ለቤተክርስቲያናችን ተቆርቋሪ መሰልሽ። በእርግጥ ይህ አባባል የአስቆሮቱ ይሁዳ ዮሐ. ምዕ.12 ቁ 3-6 እና የመሰሎቹ የሰይጣን ባሪያዎች ምዕምናንን ለማታለል የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው። አንቺ ራስሽን ከፍ ከፍ የምታደርጊ ዳቢሎስ ራስሽን ከገባሽበት ጨለማ/ኑፋቄ/ አውጭ.ገብረ ዳቢሎስ ነሽ.

      Delete
  16. Shame on you. This is only your idea. ማህበሩ ከተበተነ ሌላው ገለባ ነው .... This is not the point made by MK people. MK has its own media, which could handle such issues very wisely. Sometimes silence is the best spiritual solution. God speaks in our silence - said the late Pop Shinoda.
    ‹‹እነርሱ አያውቁትም እንጂ በመቶዎች የሚቆጠሩ የማያውቋቸው ሰዎች መሀላቸው አሉ ሲለኝ›› .... It is true. You are one of them, the cult. The cult who is against some genuine Christians. I am not going to tell you who you are . You are a snake and you are trying to poison the innocent members of MK. Yes, the PM is right he said some members - yes there are some "members" who are working against christianity, against Mk and the Government. Those are what he meant.

    ReplyDelete
  17. ከላይ የጻፍሽው እህት ማንነትሽ ከማን ወገን እንደሆነ ያስታዉቃል በቤተክርስቲያን ስም ለምድ ለብሰሻል ምናልባትም ስራሽን ስለሚያጋልጥብሽ ወይም ስላጋለጠብሽ ለማስተባበል የሞከርሽው ሙከራ ሳይሆን አይቀርም እስካሁን <>ያልሽው
    የምን ደምነው የፈሰሰው አንሺና አንሺን መሰል የማህበሩ አባል ነን ብላቹህ በማህበሩ ስም ያፈሰሳቹህት ደምካለ ብትነግሪኝ ደስ ይለኛል
    እራስሽን ደግሞ ከፍከ ታደርጊያለሽ አንቺ ለሌሎች አልቅሰሽ ምትለምኝ ማን ነሽ አንቺ? በትእቢት የተወጠርሽ? እራሱን ከፍ የሚያደርግ
    ዲያቢሎስና ተከታዮቹ ብቻ ናቸው::

    ReplyDelete
  18. አንድ አድርገን ሠላም ለናንተ፣ ለቤተክርስቲያናችንም ይሁን። እግዚአብሔር አምላክ የቤተክርስቲያንችንን በሮች በሰላም እንዲከፈቱ ያድርግልን። ክርስቶስ ያለውን ማንም ይሁን ማን ሊያስፈራው አይችልም። አምላካችን መዳኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስራችሁን እናንተንም ይባርክ። በርቱ!!!
    ደሳለኝ ከባህርዳር

    ReplyDelete
    Replies
    1. እህታችሁ???????????????find your's mesolochshen fflgi oky!!!!!!!!!!!!!

      Delete
  19. This article provides clear idea in support of the new people
    of blogging, that truly how to do blogging and site-building.
    Also visit my webpage - GFI Norte

    ReplyDelete